ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ

ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ, Government Organization, Dessi.

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላምና የጤና በዓል እንድሆን እንመኛለንደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ
26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላምና የጤና በዓል እንድሆን እንመኛለን

ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ

18/05/2026
14/05/2026
ቃሉ ወረዳ በዲጂታል ጤና ዘርፍ የሀገር አቀፍ ሞዴልነቱን አረጋገጠ!​እንኳን ደስ አላችሁ፤ ደስ ያለን!ግንቦት 04/2018 ዓ/ም (ቃሉ ኮሙኒኬሽን)​የቃሉ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ታሪክ ሰርቷ...
12/05/2026

ቃሉ ወረዳ በዲጂታል ጤና ዘርፍ የሀገር አቀፍ ሞዴልነቱን አረጋገጠ!

​እንኳን ደስ አላችሁ፤ ደስ ያለን!

ግንቦት 04/2018 ዓ/ም (ቃሉ ኮሙኒኬሽን)

​የቃሉ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ታሪክ ሰርቷል!

"በጤና መረጃ እና በዲጂታል ጤና ፈጠራዎች ላይ ዘላቂ ኢንቨስትመንት በማድረግ የጤና ትሩፋትን ማፋጠን" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በተካሄደው 5ኛው ሀገር አቀፍ የጤና መረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንት፣ ወረዳችን በታላቅ ክብር ተሸልሟል።

​ይህ ሽልማት የቃሉ ወረዳን ስም በኢትዮጵያ የጤና መረጃ አብዮት (Information Revolution) አውድማ ላይ በወርቅ ቀለም የጻፈ ደማቅ ድል ነው!

​ከክብርት ሚኒስትሯ እጅ የተገኘው የላቀ እውቅና
የቃሉ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ጋሻው እንደገለጹት፤ ወረዳችን በመረጃ አብዮት ትግበራ እንደ ሀገር ሞዴል ተብለው ከተመረጡ ጥቂት (11) ወረዳዎች መካከል አንዱ በመሆን ተሸላሚ ሆኗል።

ኃላፊው ሽልማቱን ከክብርት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እጅ የተቀበሉ ሲሆን፣ ሽልማቱም ​የላቀ የክብር ክሪስታል ዋንጫ፣ ​የምስክር ወረቀት እና ​ለቀጣይ ስራ ማጠናከሪያ የሚሆን የላፕቶፕ ኮምፒውተር ሽልማትን ያካተተ ነው።

ይህ ድል በዘፈቀደ የመጣ ሳይሆን፣ በወረዳው ለመረጃ አብዮትና ለዲጂታይዜሽን የተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ውጤት ነው። ከወረዳ አስተዳደሩ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ ያለው የጤና አመራር፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች በቅንጅት የሰሩት የክትትልና ድጋፍ ስራ ፍሬ ነው።

ይህ እውቅና የቃሉን ሕዝብና የዘርፉን ተዋናዮች እጅግ የሚያኮራ ብቻ ሳይሆን፣ ወረዳችን በሁሉም ዘርፎች ሞዴል ሆኖ እንዲቀጥል ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ የሞራል ስንቅና መነሳሳትን የሚፈጥር ነው።

​"ወረዳችንን በሁሉም ዘርፍ ሞዴል ለማድረግ አቅደን እየሰራን ነው" ያሉት አቶ ዳንኤል፤ ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ የጤናው ዘርፍ ጀግኖች በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

​ድሉ የጋራችን ነው!
እንኳን ደስ አላችሁ!

የወባ በሽታን ለመከላከል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የአማራ ሳይንት ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ገለፀ።አጅባር፦ ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም (የአማራ ሳይንት ወረዳ ኮሙኒኬሽን)በ...
05/05/2026

የወባ በሽታን ለመከላከል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የአማራ ሳይንት ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ገለፀ።

አጅባር፦ ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም (የአማራ ሳይንት ወረዳ ኮሙኒኬሽን)

በወረዳው ለወባ በሽታ ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑ ቀበሌዎች የሚከሰተውን የወባ በሽታ ለመከላከል የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን የአማራ ሳይንት ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ከተማው ቸሩ ገልፀዋል።

አሁን ላይ እየዘነበ የሚገኘው የበልግ ዝናብ ለወባ በሽታ መስፋፋት ምቹ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ችግሩን ቀድሞ ለመከላከል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ለወባ መራቢያ ምቹ የሆኑ ውሃማና ረግራጋማ አካባቢዎችን የማፋሰስና የማዳፈን፣ የግንዛቤ ፈጠራ እንድሁም የወባ ምርመራ እየተከናዎኑ ከሚገኙ ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ።

የወባ በሽታን ለመከላከል የአካባቢ ቁጥጥር ስራ አስፈላጊ በመሆኑ በሚከናዎኑ ተግባራት ላይ ህብረተሰቡ ይበልጥ ተሳታፊ መሆን እንዳለበት ጽ/ቤቱ መልዕክቱን አስተላልፏል።

እስካሁን 2 ሺህ 276 የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በወባ በሽታ የተጠቁ ስለመሆናቸው ተገልጿል። ለነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎችም የህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል።

በወረዳው በሚገኙ የጤና ተቋማት ለበሽታው አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ግብዓቶች እየቀረቡ መሆኑንና በወባ በሽታ የሚጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊውን ህክምና እያገኙ እንደሆነ አቶ ከተማው አስረድተዋል።

የማህበረሰቡን የጤና ተደራሽነት ለማስፋትና ለማጠናከር የማህበረሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ።መ/ሰላም፣ ሚያዝያ 26/2018ዓ፣ም(ቦረና ኮሙዩኒኬሽን) በደቡብ ወሎዞን የቦረና ወረዳ ...
04/05/2026

የማህበረሰቡን የጤና ተደራሽነት ለማስፋትና ለማጠናከር የማህበረሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ።

መ/ሰላም፣ ሚያዝያ 26/2018ዓ፣ም(ቦረና ኮሙዩኒኬሽን) በደቡብ ወሎዞን የቦረና ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በጤና አገልግሎት ፓኬጆች፣የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትና የ1ለ10 አደረጃጀቶች ያተኮረ ስልጠና ለሴቶች የልማት ህብረትና ለጎጥ ጤና መሪዎች ሰጥቷል።

በስልጠናው በማህበረሰቡ ውስጥ የሚሰሩ የጤና አገልግሎቶችን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ የተገለጸ ው።

ስልጠናውም ይህንኑ የጤና አገልግሎት ተደረሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ በጤና ተቋማት ከመስጠት ባለፈ የህብረተሰቡን የነቃ ተሳትፎና ግንዛቤ ለማጠናከር ያለመ ነውም ተብሏል።

በቀጣይም የሴቶች የልማት ህብረት አረጃጀቶችና የጤጎጥ ጤና መሪዎች በማህበረሰቡ የጤና ተደራሽነት ላይ በተግባር ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባልም ነው የተባለው።
********************

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በተመረጡ ወረዳዎችና ጤና ተቋማት የ WASH FIT ስልጠና መሰጠቱ ተገለፀ፡፡ ደቡብ ወሎ ዞን  መምሪያሚያዚያ 24/2018...
02/05/2026

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በተመረጡ ወረዳዎችና ጤና ተቋማት የ WASH FIT ስልጠና መሰጠቱ ተገለፀ፡፡

ደቡብ ወሎ ዞን መምሪያ
ሚያዚያ 24/2018ዓ.ም
ደሴ

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ አብዱ መሃመድ በስልጠናው ማጠቃለያ ወቅት እንደተናገሩት ስልጠናው የጤና ተቋማት ፅዱ፣ ለአገልግሎት ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የጤና አገልግሎትን ለመስጠት ጉልህ አስተዋፆ የሚያበረክት መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ እንደ ሀገር እየተተገበረ የሚገኘው ፅዱ ኢትዮጵያን የመፍጠር ፕሮጄክት ለዚህ ስራ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ ሰልጣኞች ከስልጠና መልስ ጤና ተቋማቶቻቸውን ፅዱ፣ ለአገልግሎት ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ወደ ተግባር መግባት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

ስልጠናው ከ 11 ወረዳዎች እና 16 ጤና ጣቢያዎች ለተውጣጡ የጤና ጣቢያ ሃላፊዎች ፣ፋይናንስ ባለሞያዎች፣ የተመላላሽ ህክምና እና ላብራቶሪ ባለሞያዎች፣ የፋርማሲና እናቶች ጤና ባለሞያዎች ለ 3 ተከታታይ ቀናት የተሰጠ ሲሆን የተመረጡት ጤና ተቋማት እስካሁን በሌሎች መሰል ፕሮጄክቶች ያልታቀፉ መሆናቸው ተመላክተቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የህክምና ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ዘላቂነትና የአገልግሎት ጥራትን የሚያሻሽሉ በርካታ ስራዎችና ስኬቶች የተመዘገቡበት ጊዜ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ። ደቡብ...
29/04/2026

በበጀት ዓመቱ የህክምና ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ዘላቂነትና የአገልግሎት ጥራትን የሚያሻሽሉ በርካታ ስራዎችና ስኬቶች የተመዘገቡበት ጊዜ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።

ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ
ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም
ኮ/ቻ

ጤና መምሪያው የ 9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሃላፊዎችና ምክትል ሃላፊዎች ፣ የሆስፒታል ስራ አስኪያጆች እንድሁም የዞን ጤና መምሪያ ባለሞያወች በተገኙበት በዛሬው እለት በኮምቦልቻ ከተማ አካሂዷል።

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ጌታቸው በለጠ በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የጤና አገልግሎት በየትኛውም ጊዜ ቢሆን ሊቋረጥ የማይችል መሆኑን ገልፀው ወረዳዎች ወቅታዊ ችግሮችን በመቋቋም የጤና አገልግሎት ጥራት በማሻሻል ረገድ በርካታ ተግባራት መከናዎችን ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው ጨምረው እንደገለፁት አሁን ላይ ግምገማውን ማካሄድ መቻሉ በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ይበልጥ መሻሻል ያለባቸውን ፕሮግራሞች በመለየት ወደ ተግባር በመግባት በጀት ዓመቱን በስኬት ለመቋጨት እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ አብዱ መሀመድ በበኩላቸው የጤና ተግባራቱ አፈፃፀም ከወረዳ ወረዳ የተለያዬ መሆኑን ጠቁመው ይህን ልዩነት የማጥበብ እና ሁሉም ወረዳዎች የተሻለ እንድፈፅሙ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል። ከዚህ አንፃር መሪዎች ትልቁን ሚና እንዳላቸው የገለፁት ም/መምሪያ ሀላፊው በቀሪ ወራት የርብርብ ማዕከላት ልናደርግባቸው የሚገቡ ተግባራትን ለይቶ የአጭር ጊዜ የማስፈፀሚያ ስልቶችን በመጠቀም ጭምር የተሻለ መፈፀም እንደሚገባ አሳስበዋል።

በጤናው ዘርፍ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ የበለጠ ለማሻሻልና ተደራሽ ለማድረግ የጎጥ የጤና መሪዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ ።ደሴ :-ሚያዝያ 19/2018 ዓ ም ( ደሴ ዙሪያ ወረዳ መንግስ...
27/04/2026

በጤናው ዘርፍ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ የበለጠ ለማሻሻልና ተደራሽ ለማድረግ የጎጥ የጤና መሪዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ ።

ደሴ :-ሚያዝያ 19/2018 ዓ ም ( ደሴ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን )

በደቡብ ወሎ ዞን በደሴ ዙሪያ ወረዳ በጤናው ዘርፍ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ የበለጠ ለማሻሻል ፣ ፍትሃዊነትና ተደራሽ እንድሆን የጎጥ የጤና መሪዎች (Community Leaders) ወይም የአካባቢው ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ያላቸው ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል ።

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥበቃ ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንድሪስ ሁሴን እንዳስረዱት በወረዳው ውስጥ ማህበረሰባዊ ትስስሩ ጠንካራ እንዲሆንና የጤና ፖሊሲዎች መሬት እንዲረግጡ የጎጥ ጤና መሪዎች በጤናው ዘርፍ የሚያበረክቷቸው አስተዋጽኦዎች :- ግንኙነትን ማቀላጠፍ (Bridging the Gap)
በጤና ባለሙያዎችና በማህበረሰቡ መካከል እንደ ድልድይ ያገለግላሉ። ህዝቡ የጤና ባለሙያዎችን እንዲያምንና የህክምና ምክሮችን እንዲቀበል በማድረግ ረገድ ግንባር ቀደም ናቸው።

የግንዛቤ ማስጨበጥ እና ቅስቀሳ
የተለያዩ የጤና መልዕክቶች ለህዝቡ እንዲደርሱ ያደርጋሉ ። ለምሳሌ ያክል :-
የክትባት ዘመቻዎች :- ወላጆች ልጆቻቸውን ለክትባት እንዲያወጡ በማነቃቃት።
የንፅህና አጠባበቅ :- በአካባቢ ንፅህና እና በሽንት ቤት አጠቃቀም ላይ አርአያ በመሆን።
ተላላፊ በሽታዎች፡ እንደ ኮቪድ-19 ፣ ወባ ያሉ በሽታዎችንና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶችን ለመምራት ወሳኝነት አላቸው ።

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን መዋጋት
በማህበረሰቡ ውስጥ ስር የሰደዱና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ልማዶችን (ለምሳሌ፡ ያለ ዕድሜ ጋብቻ፣ የሴት ልጅ ግርዛት) ለማስቀረት የጎጥ መሪዎች የሚሰጡት ትምህርትና የሚያወጡት የአካባቢ ደንብ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ወሳኝነት አለው ።

የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማሳደግ
እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ ማበረታታት :- በቤት ውስጥ የሚደረግ ምጥ የሚያስከትለውን አደጋ በማስረዳት እናቶች ወደ ጤና ጣቢያ እንዲሄዱ ይገፋፋሉ።
የአምቡላንስ አገልግሎት:-ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥም ወይም ምጥ ሲመጣ ማህበረሰቡን በማስተባበር የትራንስፖርት ችግር እንዲቀረፍ ያደርጋሉ።

መረጃን መሰብሰብና ማደራጀት
በየጎጡ የሚከሰቱ አዳዲስ የበሽታ ምልክቶችን ወይም የጤና እክሎችን ለጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በፍጥነት በማሳወቅ ወረርሽኝ እንዳይከሰት ይከላከላሉ ሲሉ ሰፋ አድርገው አስረድተዋል ።

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሃመድ አረጋ በበኩላቸው ሲያጠቃልሉ የጎጥ የጤና መሪዎች የጤና ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ለማሻሻልና ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝነት ያላቸው ሲሆን ፤ የጎጥ የጤና መሪዎች ለህዝቡ "ጆሮ እና አንደበት" ናቸው ብለዋል ።

ኃላፊው አያይዘውም የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙ ስኬታማ እንዲሆን የነሱ ተሳትፎና ቁርጠኝነት መሰረታዊ ተግባር ነው ፤
በአካባቢዎ ያሉ የጎጥ የጤና መሪዎች ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት :-
በመተጋገዝ ላይ የተመሰረተ ሲሆን የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ብቻቸውን መድረስ የማይችሉባቸውን ቦታዎች ለመድረስ የጎጥ የጤና መሪዎችን "ቁልፍ" አድርገው በመጠቀም የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ወሳኝነት አላቸው ሲሉ ገልፀዋል

በቃሉ ወረዳ 06 ጮሪሳ ቀበሌ በስነ-ተዋልዶ የተቀናጀ ጤና አገልግሎት ላይ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።​ሚያዝያ 18/2018 ዓ/ም (ቃሉ ኮሙኒኬሽን)​በደቡ...
27/04/2026

በቃሉ ወረዳ 06 ጮሪሳ ቀበሌ በስነ-ተዋልዶ የተቀናጀ ጤና አገልግሎት ላይ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

​ሚያዝያ 18/2018 ዓ/ም (ቃሉ ኮሙኒኬሽን)

​በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ 06 ጮሪሳ ቀበሌ የማህበረሰቡን የስነ-ተዋልዶ የተቀናጀ የጤና አገልግሎት ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ ወሳኝ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።

​በ06 ጮሪሳ ቀበሌ በኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር አዘጋጅነት የተካሄደው ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ከ UNFPA በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ SRH ፕሮጀክት አማካኝነት የተከናወነ ሲሆን፤ በስልጠናው ላይ የቀበሌ አመራሮች፣ የጎጥ የጤና መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የእድር መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና በጎ ፈቃደኞች በንቃት ተሳትፈዋል።

​በስልጠና መድረኩ እናቶች በእርግዝና ወቅት ሊያደርጓቸው ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች፣ ስለ ስነ-ተዋልዶ ጤና፣ ስለ ህፃናት የ1000 ቀናት አመጋገብና ክትባት፣ እንዲሁም ከተላላፊና ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ራስን የመጠበቅ ስልቶች ላይ ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

​በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ አሰልጣኞችና የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ለቀጣይ ስራ መነሻ የሚሆኑ ወሳኝ መልዕክቶችንም አስቀምጠዋል።

የ SRH ፕሮጀክት አስተባባሪ ​አቶ ሙሉአለም አይሸሽም ፕሮጀክቱ በስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸው፣ በዕለቱ የተገኘው ግንዛቤ በየደረጃው ወርዶ ወደ ተግባር መቀየር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። አስተባባሪው አክለውም ፕሮጀክቱ ከግንዛቤ ማስጨበጥ ባለፈ በተግባር እናቶችን ለመርዳት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በሃርቡ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ መጥተው ለሚወልዱ እናቶች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ አስፈላጊ የሆኑ የቁሳቁስ ድጋፎችን ፕሮጀክቱ ማሟላቱን ገልጸዋል። "ግባችን እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ ማበረታታትና በወሊድ ምክንያት የሚመጣን ሞትና እንግልት ማስቀረት ነው" ያሉት አቶ ሙሉአለም፣ በቀጣይም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሰል የድጋፍና የክትትል ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የሀርቡ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ​ዳይሬክተርና አሰልጣኝ አቶ ዳንኤል ብርሃኑ በማህበረሰብ ጤና አጠባበቅ ዙሪያ በሰጡት ሰፊ ማብራሪያና ማጠቃለያ አንዲት እናት ልክ እርግዝና መኖሩን ካወቀችበት ቀን ጀምሮ በጤና ተቋም የክትትል አገልግሎት ማግኘት እንዳለባትና ይህም እናቶች በእርግዝና ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ጤናማ ልጅ ለመውለድ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ከስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት አኳያ ማህበረሰቡ በተለይም ወጣቶችና ጥንዶች ስለ ስነ-ተዋልዶ ጤና ግንዛቤ ኖሯቸው ራሳቸውን ካልተፈለገ እርግዝናና በግብረ-ስጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎች እንዲጠብቁና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን መጠቀም የእናትየዋን ጤና ለማገገም እንዲሁም ለልጁ በቂ እንክብካቤ ለመስጠት የሚኖረውን ፋይዳም በዝርዝር አብራርተዋል።

በህፃናት ጤና ላይ በተለይ "የመጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት" (ከፅንሰት ጀምሮ እስከ 2 አመት) ለልጁ የአእምሮና የአካል እድገት ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸው በዚህ ወቅት ​ልጁ በተገቢው ሁኔታ ክትባቶችን ማግኘት እንዳለበት፤​እናቶች የተመጣጠነ ምግብ እንዲመገቡና ለልጆቻቸውም እንዲያቀርቡ እና ​የተሟላ የጡት ወተት አገልግሎት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

Address

Dessi

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share