Siadebirna wayu woreda health office

Siadebirna wayu woreda health office swho

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅቤት ባለሙያዎች ለኮሮና ተጠርጣሪ የተዘጋጀዉን የለይቶ ማቆያ በዚህ መልኩ ሲያዘጋጁ ዉለዋሌ
17/06/2020

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅቤት ባለሙያዎች ለኮሮና ተጠርጣሪ የተዘጋጀዉን የለይቶ ማቆያ በዚህ መልኩ ሲያዘጋጁ ዉለዋሌ

16/06/2020

ዴክሳሜታሰን መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት እንደሚታደግ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአነስተኛ ዋጋ በስፋት የሚገኘው “ዴክሳሜታሰን” የተባለው መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት ለመታደግ እንደሚረዳ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁ።

እንደተመራማሪዎቹ ገለፃ በመድሃኒቱ በአነስተኛ ዶዝ በሚሰጠው የስቴሮይድ ህክምና የኮሮና ቫይረስን በመዋጋት ሂደት ከፍተኛ ውጤት የሚያመጣ ነው።

መድሃኒቱ በተለይም በመተንፈሻ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) እና ኦክሲጅን ድጋፍ የሚተነፍሱትን ታማሚዎች የመሞት እድልን የሚቀንስ መሆኑንም አስታውቀዋል።

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለፃ መድሃኒቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በብሪታኒያ እንደገባ ጥቅም ላይ መዋል ቢጀምር እስከ 5 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን ህይወት መታደግ ይቻል ነበረ።

“ዴክሳሜታሰን” የተባለው መድሃኒት ዋጋም አነስተኛ በመሆኑ በተለይም ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን ለያዙ በዝትቀኛ የገቢ ደረጃ ላይ ላሉ ሀገራት ጠቃሚ መሆኑንም አስታውቅዋል።

በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 20 ሰዎች ውስጥ 19 በቶሎ የሚያገግሙ መሆኑን ያስታወቁት ተመራማሪዎቹ፥ በፀና ታመው ሆስፒታል ከሚገቡት መካከል ውስጥ ግን የተወሰኑት እንደ ቬንትሌተር እና ኦክሲጅን አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያዎች ያስፈልጋቸዋል ይላሉ።

ታዲያ “ዴክሳሜታሰን” የተባለው መድሃኒትም በአጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያዎች ለሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች ነው ጥቅም ላይ የሚውለውም ብለዋል።

በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ቡድን በመድሃኒቱ ላይ በተደረገው ጥናትም በሆስፒታል ውስጥ ለሚገኙ 2 ሺህ ሰዎች “ዴክሳሜታሰን” እንዲሰጥ በማድረግ መድሃኒቱን ካልወሰዱት 4 ሺህ ሰዎች ጋር በማነፃፀር ተመልክቷል።

በዚህም በመተንፈሻ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) ድጋፍ ላይ ባሉ ታማሚዎችላይ የሚከሰት ሞትን ከ40 እስከ 28 በመቶ ቀንሷል ያሉ ሲሆን፥ በኦክሲጅን ታግዘው በሚተነፍሱ ታማሚዎች ላይ የሚከሰትን ሞትን ደግሞ ከ25 እስከ 20 በመቶ መቀነሱን አስታውቅዋል።

የጥናት ቡድኑ መሪ ፕሮፌሰር ፒተር ሆርቢ ፥ እስካሁን ከተደረጉ ሙከራዎች በኮሮና ቫይረስ የሚከሰት ሞትን በመቀነስ ረገድ “ዴክሳሜታሰን” መድሃኒት የመጀመሪያው መሆኑን እና በኮቪድ 19 ላይ በሚደረገው ምርምርም ትልቅ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።

በጥናቱ ላይ የተሳተፉት ፐሮፌሰር ማርቲን ላንድረይ በበኩላቸው፥ መድሃኒቱ በዓለም ዙሪያ የሚገኝ መሆኑ እና ዋጋውን አነስተኛ መሆኑ በፅኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት በመታደግ ረገድ ከፍተኛ ጥቅም አለው ብለዋል።

ሆስፒታሎች በኮቪድ 19 በጽኑ ለተመሙ ታካሚዎቻቸው መድሃኒቱን እንዲሰጡ እናበረታታለን ያሉት ፐሮፌሰር ማርቲን ላንድረይ፥ ሆኖም ግን መድሃኒቱ በጽኑ ለታመሙት ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ ሰዎች በራሳቸው ፍቃድ ገዝተው ሊጠቀሙት አይገባም ሲሉም አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ



የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

11/06/2020
10/06/2020
24/04/2020
የሲ/ዋ/ወ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ኮሮናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ለማሻሻል ወደ ወረዳው የሚገቡትን  ሰዎች የሙቀት መለካት በቀን 16/08/2012 ዓ.ም ጀምሯል፡፡
24/04/2020

የሲ/ዋ/ወ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ኮሮናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ለማሻሻል ወደ ወረዳው የሚገቡትን ሰዎች የሙቀት መለካት በቀን 16/08/2012 ዓ.ም ጀምሯል፡፡

21/03/2020

Support my page please 🙏🙏😊
Thank God for the gift of life💯💯

Address

Deneba

Telephone

+251921139550

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Siadebirna wayu woreda health office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Siadebirna wayu woreda health office:

Share