Siyadebr ena wayu cultur& tuorism

Siyadebr ena wayu cultur& tuorism የቱሪዝም ሴክተሩን በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ሚና

ጨለሚት ዋሻ ቅ/ጊዮርጊስ , ሰንከታ ቅ/አርሴማ
23/05/2025

ጨለሚት ዋሻ ቅ/ጊዮርጊስ , ሰንከታ ቅ/አርሴማ

ሃይማኖታዊ የመስቀል በዓል አከባበር ስርዓት1.መስቀሉ የት ነው ያለው? እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ የመሰቀል የደመራ በዓል የተለያዩ ሃይማኖታዊ ፣ባህላዊ ክዋኔዎች የሚከወኑበት...
26/09/2022

ሃይማኖታዊ የመስቀል በዓል አከባበር ስርዓት
1.መስቀሉ የት ነው ያለው?
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ የመሰቀል የደመራ በዓል የተለያዩ ሃይማኖታዊ ፣ባህላዊ ክዋኔዎች የሚከወኑበት እና በኢትዮጵያ ታላቅ ክብር የሚሰጠው በዓል ነው፡፡ ይህ በዓል በ2005 ዓ/ም በ UNSCO የተመዘገበ የዓለም ቅርስ ሆኗል፡፡

ደመራ ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን ጨመረ፣አከማቸ አንድ ላይ አደረገ ማለት ነው፡፡
መስቀል የሚለው "ሰቀለ" ከሚለው የግዕዝ ስርው ቃል የወጣ ሲሆን መሰቀያ ማለት ነው፡፡
2.መስቀሉ እንዴት ጠፋ?
የዚህ በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱ ከአባቶች ባገኘነው መረጃ መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል በተአምራዊነትና በክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የተሰጠው በመሆኑ አይሁድ በቅናት ተነሳስተው የቆሻሻ ጥራጊ እንደደፉበት መስከረም 16 እና 17 ቀን የሚነበበው ስንክሳር ይናገራል፡፡
3.መስቀሉ የት ተቀበረ?
በኢየሩሳሌም ክልል ከሚገኘው ጎልጎታ ከከተማዋ ውጭ ለ300 ዓመታት ያህል አይሁድ በቆሻሻ ጥራጊ መጣያ ቀብረውት ነበር፣
4.መስቀሉ እንዴት ተገኘ?
በ327 ዓ.ም የቆስጠንጢኖስ እናት ንግስት ዕሌኒ ኪራኮስ የተባለ አንድ የታሪክ አዋቂ አይሁዳዊ ሽማግሌ ጠቋሚነት መስቀሉ የተጣለበትን አካባቢ አወቀች፡፡ከዚያን በኋላ ደመራ አስደምራ በእሳት አቀጣጥላ ዕጣን ባስጤሰች ጊዜ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ ተመልሶ መስቀሉ ወደ ተቀበረበት ቦታ አመለከተ፡፡ ንግስት ዕሌኒ በጢሱ ምክንያትነት መስቀሉን ለማውጣት ለ7 ወራት ያህል አስቆፍራ ማለትም መስከረም 17 ቀን አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን እንዲወጣ አድርጋለች፡፡

በዓለ መስቀል እንዴት ተወሰነ?
ቁፋሮው መስከረም 17 ተጀምሮ መጋቢት 10 ቀን የተጠናቀቀ መሆኑን አባቶች ይናገራሉ፡፡
-መጋቢት 10 ቀን ግን ራሱን የቻለ ታሪክ አለው፣ መስቀሉ ለሁለተኛ ጊዜ በፋርሶች ከተማረከበት በንጉሥ ሕርቃል ተመልሶ ወደ ጎልጎታ የገበባበት ቀን ነው፡፡ በስንክሳር መስከረም 16 ቀን በኢየሩሳሌም እና በአካባቢው በንግሥት እሌኒ የተሠሩ አብያተ ክርስቲያናት በመስቀሉ የተባረኩበት ቀን ነው፡፡መስከረም 17 ቀን ደግሞ ቅድስት እሌኒ መስቀሉ በተገኘበት በጎልጎታ ያሠራችው የመስቀሉ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ነው፡፡ ነገር ግን በዐቢይ ጾም በዓል ስለማይከበር የመስቀሉ በዓል ቅዳሴ ቤቱ በተከበረበት ቀን በመስከረም 17 እንዲከበር ሊቃውንት ሥርዓት መሥራታቸውን ስንክሳሩ ይነግረናል፡፡ ስለዚህ የቀድሞ አባቶች ታሪክን ከታሪክ ማገናኘት ልማዳቸው ነውና መስቀሉ መጋቢት 10 ቀን ወደ ጎልጎታ እንዲገባ ያደረጉት ቀድሞ ከተገኘባት ቀን ጋር ለማስተሣሠር ነው ::ዛሬም መስከረም 16 ቀን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በምዕመናኑ ዘንድ ደመራ የሚደመረውም ይህንን ታሪክ አስመልክቶ እንደሆነ ሊቃውንት ይናገራሉ ማለት ነው፡፡
ባህላዊ የመስቀል በዓል አከባበር ስርዓት
የመስቀል የደመራ በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስርዓቱን አስመልክቶ ልዩና ማራኪ በመሆኑ በ2005 ዓ.ም የአለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ ቢሆንም በወረዳችን የመስቀል በዓል አከባበርን እንዳስሳለን፡፡
የመስቀል የደመራ በዓል አከባበር በከተማ
በወረዳችን ርዕሰ መዲና የመስቀል የደመራ በዓል ክንዋኔ መስከረም 16 ቀን ጀምሮ ሲሆን የአካባቢው ወጣቶች የመስቀል የደመራ በዓል የሚከበርበትን ቦታ ቀድመው የማፅዳትና የተለያዩ የዲኮሬሽን ስራዎች በማከናወን ይጀምራሉ፡፡ አመሻሹ ላይ ሁሉም የህ/ሰብ ክፍሎች ወደ ደመራ ቦታ ችቦ በመያዝ ይደመራሉ፣ከዚያም በኋላ የአካባቢው የደብር አገልጋዮችና አባቶች ስርዓቱን በፀሎት ከከፈቱ በኋላ የተለያዩ ያሬዳዊ ዜማዎች ያዜማሉ፣የሰበት ት/ቤት ተማሪዎችም የተለያዩ መዝሙሮችን ይዘምራሉ፣የከተማዋ መሪ መዘጋጃ ቤትና የተለያዩ ኃላፊዎች በመሆን ደመራዉን የመለኮስ ስርዓት ያከናዉናሉ፡፡
የመስቀል የደመራ በዓል አከባበር በገጠር
የደመራ በአል በገጠሩ ማህበረሰብ በ 16 አመሻሹ ላይ የሚጀመር ሲሆን በየአካባቢያቸው ሰብሰብ ብለው የሚያከብሩት በዓል ነው፡፡ ሁሉም የአካባቢው የህ/ሰብ ክፍሎች ባላቸው በወንዶች ልጆች ቁጥር ልክ ኢላማ በመቁረጥ ቀደም ብለው ዒላማውን ወደ ደመራ ቦታ ይወስዳሉ፡፡ከዚያን ሁሉም አባወራዎች በተገኙበት ጉድጓድ ተቆፍሮ ኢላማው ይተከልና ይቆማል፡፡
ከዚያን ሁሉም አባወራዎች በተገኙበት ጉድጓድ ተቆፍሮ ኢላማው ይተከልና ይቆማል፡፡
የተሰበሰበው ማህበረሰብም ደመራ ቦታው ጠላ፣ዳቦ፣አነባበሮ...በመያዝ ይመጣሉ የተሰበሰበው ማህበረሰብብ የተተከለውን ኢላማ በመዞር አንድ የአካባቢው ሆሆ የሚል ችሎታ ያለው የተመረጠ ሽማግሌ
-እዮሐ አበባዬ መስከረም ጠባዬ
-ተው አትኩራ ነፍስ ጎመን ባውጣው ነፍስ በማለት ሶስት ጊዜ ከዞሩ በኋላ ሽማግሌዎቹ የመጣውን ዳቦ እየቆረሱ ከተበላ፣ከተጠጣ በኋላ ሽማግሌዎቹ ይመርቃሉ፡፡የተሰበሰበው ማህበረሰብም ወደ ቤታቸው ተመልሰው ከቤታቸው ችቧቸውን አብርተው
ወደ ደመራው ለመሄድ ይለኩሳሉ፣ችቦ ከቤታቸው መለኮስ ሲጀምሩ ከመውጣታቸው በፊት፡
-የገንፎ ድስት ግባ
የጎመን ድስት ውጣ ብሉው ይሄዳሉ፡፡የአካባቢው ወንዶች ልጆችም ኢላማውን ሲያነዱ አድረው ጠዋት ከብቶቻቸውን ወደ መስክ እየነዱ የመስቀል በአል ያመጣላቸውን ብስራት በመዘከር በደስታና በብሩህ ተስፋ ሲያከብሩ ይስተዋላሉ፡፡

ቅርስ የአንድ ሀገር ህዝብ   የማንነቱ መግለጫ  የሆነ በይዘቱ የአንድ ሃገር ታሪክ ስልጣኔ ባህል  ስረዓቶችንና እድገትን የሚገልፅ    ከአለፈዉ  ትዉልድ እየተወራረሰ ለተተኪዉ ትዉልድ  የሚ...
15/02/2022

ቅርስ የአንድ ሀገር ህዝብ የማንነቱ መግለጫ የሆነ በይዘቱ የአንድ ሃገር ታሪክ ስልጣኔ ባህል ስረዓቶችንና እድገትን የሚገልፅ ከአለፈዉ ትዉልድ እየተወራረሰ ለተተኪዉ ትዉልድ የሚተላለፍ የብዙ ዘመናት የፈጠራ ዉጤት ነዉ፡፡
ኢትዮጵያ በአከባቢያዊ ብሔራዊ ና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚመደቡ እጅግ ብዛት ያላቸዉ ተፈጥሮአዊ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች ባለቤት ናት፡፡ ክልላችንም በርካታና አኩሪ የሆኑ ቅርሶች ከሚገኙባት የሀገራችን ክፍሎች አንዱና ዋናዉ ነዉ ፡፡ ኢትዮጵያዊ በአለም ቅርሶች ካስመዘገበቻቸዉ ቅርሶች መካከል አብዛኞቹ የሚገኙት በክልላችን ዉስጥ ነዉ ፡፡
ቅርሶቹ የተሰሩበት ዘመን በወቅቱ ለነበረዉ የህብረተሰብ ክፍል የተለያየ አገልግሎት እንዲሰጡ ታስቦ የተዘጋጁ ናቸዉ፡፡ ይከዉም ለማህበራዊ ግንኙነት ለንግድ ልዉዉጥ ፣ለመከላከያ፣ለሀይማኖት ለቤት ዉስጥ፣ ለአስተዳደራዊ ለጌጥ፣ ለክብርና ለዝና ማስተረፊያነት ወዘተ አገልግሎት የተሰሩ ናቸዉ፡፡
ይህንን ከፍተኛ ዋጋ ያለዉን በቀላሉ ሊተካ የማይቻል የሀገር ሀብት የሲያደብርና ዋዩ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በወረዳ ዉስጥ የሚገኙ የሚንቀሳቀሱ እና የማይንቀሳቀሱ ቅርሶችን በመመዝገብ ፣ በመቆጣጠር እንዲሁም የጽዳት እና እንክብካቤ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እነዚህ የማንነት መገለጫ የሆኑ ቅርሶችን ማንኛዉም የቅርስ ባለቤት እና ማህበረሰብ ቅርሶችን በመጠበቅ ለተተኪዉ ትዉልድ ማስተላለፍ አለበት እንላለን፡፡

የሲደብርና ዋዩ ወረዳ ከአዲስ አበባ በደ/ብርሃን 177 ኪ/ሜ ሲሆን  በሙከጡሪ ደግሞ 134 ኪ/ሜ ከዞናችን መዲና ደ/ብርሃን 47 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች ፡፡ የወረዳዉ ዋና ከተማ ደነባ ስ...
08/10/2021

የሲደብርና ዋዩ ወረዳ ከአዲስ አበባ በደ/ብርሃን 177 ኪ/ሜ ሲሆን በሙከጡሪ ደግሞ 134 ኪ/ሜ ከዞናችን መዲና ደ/ብርሃን 47 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች ፡፡ የወረዳዉ ዋና ከተማ ደነባ ስትሆን ፤በወረዳዉ አሉ ከሚባሉት ታሪካዊና መንፈሳዊ ቦታዎች ዉስጥ አንዷ የሆነችዉ ሰንከታ ቅድስት አርሴማ ገዳም ናት፡፡ ይህች ገዳም ከወረዳዉ ርዕሰ መዲና እስከ ሲያደብር 12 ኪ.ሜ በመኪና ከተጓዙ በኋላ በእግር በግምት ወደ 13 ኪ/ሜ ቆላማዉን መንገድ በመጓዝ በሰንከታና ዉቅር ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰንከታ ጎጥ በሚባለዉ ቦታ ላይ ገዳሟን ያገኟታል፡፡ ከቦታዉ ከደረሱ በኋላም ቁልቁል ሲመለከቱ የተረገመዉን የበርሲና ወንዝን ይመለከታሉ፡፡ በአመት ዉስጥ የሚከበረዉ በዓሏ ሶስት ጊዜ ሲሆን በርካታ ምዕመናን ወደዚህ ቦታ ሲጓዙ ይታያሉ፡፡
አብይ በዓሏ
-መስከረም 29 ቀን እረፍቷ
-ታህሳስ 6 ቀን ቅዳሴ ቤቷ
-ጥር 21 ቀን ልደቷ
ታላቁና ዋናዉ በአሏ መስከረም 29 ቀን የበዓሏ የእረፍት ቀን በመሆኑ ከተለያዩ የሃገራችን ክፍል ከ15 ሽህ እስከ 20ሽህ ምዕመናን በመሰባሰብ በዓሏን በታላቅ አክብሮትና ድምቀት ባለዉ መልኩ ያከብሯታል፡፡
መስከረም 29 ቀን ሰማዕቷ ቅድሰት አርሴማ በአርማንያ ሀገር በንጉሱ ድርጣድስ ፍርድ አንገቷን የቆረጠበት እና ሰፊ ቃልኪዳን የተቀበለችበት ቀን ነዉ፡፡
በዚህ ዕለት ከእርሷ ጋር በሰማዕትነት የተገደሉ 27 ደናግልም የክብር አክሊል ተቀናጅተዋል፡፡
ሆኖም ቅ/አርሴማ ለፈፀመችዉ የምስክርነት ተጋድሎ የ17 ትዉልድ ምህረት እና የፈዉስ ፀጋ ተሰጥቷታል፡፡በዚህ ዘመን በተለይ በሰንከታ ድንቅ ስራ እየሰራች ነዉ፡፡
በቅድስት አርሴማ ደብርም በዉስጧ የተለያዩ አስገራሚ ቦታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይታዩባታል ፡፡
ከነዚህም ዉስጥ
1 - ድንጋዩ ሲፈረከስ አንደየሰዉ እምንት የተለያዩ የስእልና የምስል አይነቶች ሲገኙ በገዳሙ ዉስጥ የሚኖሩ ታላላቅ አባቶች እንደሚናገሩት ከሆነ ድንጋዩ ሲከፈል የሚገኘዉ ስዕልና ምስል የሚወጣበት አብይ ምክንያት ከክርስቶስ የተሰጣት ቃል ኪዳን ነዉ ይላሉ፡፡ ከድንጋዩ ላይ ከሚወጡት የስእል አይነቶች እንደ ዘንባባ ፤ጽዋ እና የራሷ ስዕል ጭምር ይገኙበታል፡፡ የተገኘውን ስዕልና ምስል ሰውነታቸውን ሲያሻሹት ከተያዙት በሽታ ይፈወሳሉ፡፡ይህንም አንዳንድ ምእመን ቦታዉ ድረስ በመሄድ ከድንጋዩ የሚገኘዉን ስዕልና ምስል ይዘዉ ይሄዳሉ ::
- ፈዋሽነት ያለዉ ጸበሏ ብዙ ተአምራት እያደረገ ለብዙ አይነት በሽታ ፈዉስ እየሰጠ እና ተአምራት እያደረገ መገኘቱ እጅግ አስገራሚ ነዉ፡፡
ጸበሏ ከሚፈዉሳቸዉ በሽታዎች በዋናነት የHIV AIDS፤ የስኳር፤ የመንፈስ ፤የአጋንት እና መሰል በሽታወችን ድህነት ይሰጣል፡፡
3-በዋሻዉ ድንጋይ ላይ ያለዉ የአርሴማ ቅድስት ጡት መገኘቱና ከዚሁ የድንጋይ ጡቷ ላይ ጠብጠብ የሚለዉን ጸበል የጠባ ምእመን ዓለም በቃኝ ብለዉ እንደሚመንኑ በቦታዉ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ይናገራሉ፡፡
‹ለሰባት ዓመት ያክል ተሸሽጋ የጸለየችበት ዋሻ ለብዙ የእምነቱ ተከታዮች ሱባኤ በመግባት ከቅድስት አርሴማ በመንፈስ የሚገናኙበት ከተለያዩ በሽታዎች ፈውስ የሚያገኙበት ቦታ ይገኛል፡፡
4-መካን እናቶች ገድለ መጸሐፏን አዝለዉ ልጅ ለመዉለድ ለተማጸኗት ልጅ ማግኘት መቻላቸዉ ፡፡በአጠቃይ ለክብረ በዓል እና ለሱባኤ ከሚመጡ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸዉ ቱሪስቶች የአካባቢዉ ህ/ሰብ ከፍተኛ ገቢ በማግኘት ኑሮአቸዉን እያሻሻሉ ይገኛሉ፡፡ በቅድስት አርሴማ ደብር ዉስጥ የሚፈጸሙ ድንቅ እና አስገራሚ ተአምራትን በበራሪ ወረቀት ለአንባቢ ማድርስ በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም የገዳሟን ታሪካዊነት የሰማ ወደ ስፍራዉ በማቅናት የዚህ ቦታ ቱሪስት

ሃይማኖታዊ የመስቀል በዓል አከባበር ስርዓት1.መስቀሉ የት ነው ያለው? እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ የመሰቀል የደመራ በዓል የተለያዩ ሃይማኖታዊ ፣ባህላዊ ክዋኔዎች የሚከወኑበት...
22/09/2021

ሃይማኖታዊ የመስቀል በዓል አከባበር ስርዓት
1.መስቀሉ የት ነው ያለው?
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ የመሰቀል የደመራ በዓል የተለያዩ ሃይማኖታዊ ፣ባህላዊ ክዋኔዎች የሚከወኑበት እና በኢትዮጵያ ታላቅ ክብር የሚሰጠው በዓል ነው፡፡ ይህ በዓል በ2005 ዓ/ም በ UNSCO የተመዘገበ የዓለም ቅርስ ሆኗል፡፡
ደመራ ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን ጨመረ፣አከማቸ አንድ ላይ አደረገ ማለት ነው፡፡
መስቀል የሚለው “ሰቀለ” ከሚለው የግዕዝ ስርው ቃል የወጣ ሲሆን መሰቀያ ማለት ነው፡፡
2.መስቀሉ እንዴት ጠፋ?
የዚህ በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱ ከአባቶች ባገኘነው መረጃ መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል በተአምራዊነትና በክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የተሰጠው በመሆኑ አይሁድ በቅናት ተነሳስተው የቆሻሻ ጥራጊ እንደደፉበት መስከረም 16 እና 17 ቀን የሚነበበው ስንክሳር ይናገራል፡፡
3.መስቀሉ የት ተቀበረ?
በኢየሩሳሌም ክልል ከሚገኘው ጎልጎታ ከከተማዋ ውጭ ለ300 ዓመታት ያህል አይሁድ በቆሻሻ ጥራጊ መጣያ ቀብረውት ነበር፣
4.መስቀሉ እንዴት ተገኘ?
በ327 ዓ.ም የቆስጠንጢኖስ እናት ንግስት ዕሌኒ ኪራኮስ የተባለ አንድ የታሪክ አዋቂ አይሁዳዊ ሽማግሌ ጠቋሚነት መስቀሉ የተጣለበትን አካባቢ አወቀች፡፡ከዚያን በኋላ ደመራ አስደምራ በእሳት አቀጣጥላ ዕጣን ባስጤሰች ጊዜ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ ተመልሶ መስቀሉ ወደ ተቀበረበት ቦታ አመለከተ፡፡ ንግስት ዕሌኒ በጢሱ ምክንያትነት መስቀሉን ለማውጣት ለ7 ወራት ያህል አስቆፍራ ማለትም መስከረም 17 ቀን አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን እንዲወጣ አድርጋለች፡፡

5. በዓለ መስቀል እንዴት ተወሰነ?
ቁፋሮው መስከረም 17 ተጀምሮ መጋቢት 10 ቀን የተጠናቀቀ መሆኑን አባቶች ይናገራሉ፡፡
-መጋቢት 10 ቀን ግን ራሱን የቻለ ታሪክ አለው፣ መስቀሉ ለሁለተኛ ጊዜ በፋርሶች ከተማረከበት በንጉሥ ሕርቃል ተመልሶ ወደ ጎልጎታ የገበባበት ቀን ነው፡፡ በስንክሳር መስከረም 16 ቀን በኢየሩሳሌም እና በአካባቢው በንግሥት እሌኒ የተሠሩ አብያተ ክርስቲያናት በመስቀሉ የተባረኩበት ቀን ነው፡፡መስከረም 17 ቀን ደግሞ ቅድስት እሌኒ መስቀሉ በተገኘበት በጎልጎታ ያሠራችው የመስቀሉ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ነው፡፡ ነገር ግን በዐቢይ ጾም በዓል ስለማይከበር የመስቀሉ በዓል ቅዳሴ ቤቱ በተከበረበት ቀን በመስከረም 17 እንዲከበር ሊቃውንት ሥርዓት መሥራታቸውን ስንክሳሩ ይነግረናል፡፡ ስለዚህ የቀድሞ አባቶች ታሪክን ከታሪክ ማገናኘት ልማዳቸው ነውና መስቀሉ መጋቢት 10 ቀን ወደ ጎልጎታ እንዲገባ ያደረጉት ቀድሞ ከተገኘባት ቀን ጋር ለማስተሣሠር ነው ::ዛሬም መስከረም 16 ቀን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በምዕመናኑ ዘንድ ደመራ የሚደመረውም ይህንን ታሪክ አስመልክቶ እንደሆነ ሊቃውንት ይናገራሉ ማለት ነው፡፡

ባህላዊ የመስቀል በዓል አከባበር ስርዓት
የመስቀል የደመራ በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስርዓቱን አስመልክቶ ልዩና ማራኪ በመሆኑ በ2005 ዓ.ም የአለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ ቢሆንም በወረዳችን የመስቀል በዓል አከባበርን እንዳስሳለን፡፡
የመስቀል የደመራ በዓል አከባበር በከተማ
በወረዳችን ርዕሰ መዲና የመስቀል የደመራ በዓል ክንዋኔ መስከረም 16 ቀን ጀምሮ ሲሆን የአካባቢው ወጣቶች የመስቀል የደመራ በዓል የሚከበርበትን ቦታ ቀድመው የማፅዳትና የተለያዩ የዲኮሬሽን ስራዎች በማከናወን ይጀምራሉ፡፡ አመሻሹ ላይ ሁሉም የህ/ሰብ ክፍሎች ወደ ደመራ ቦታ ችቦ በመያዝ ይደመራሉ፣ከዚያም በኋላ የአካባቢው የደብር አገልጋዮችና አባቶች ስርዓቱን በፀሎት ከከፈቱ በኋላ የተለያዩ ያሬዳዊ ዜማዎች ያዜማሉ፣የሰበት ት/ቤት ተማሪዎችም የተለያዩ መዝሙሮችን ይዘምራሉ፣የከተማዋ መሪ መዘጋጃ ቤትና የተለያዩ ኃላፊዎች በመሆን ደመራዉን የመለኮስ ስርዓት ያከናዉናሉ፡፡
የመስቀል የደመራ በዓል አከባበር በገጠር
የደመራ በአል በገጠሩ ማህበረሰብ በ 16 አመሻሹ ላይ የሚጀመር ሲሆን በየአካባቢያቸው ሰብሰብ ብለው የሚያከብሩት በዓል ነው፡፡ ሁሉም የአካባቢው የህ/ሰብ ክፍሎች ባላቸው በወንዶች ልጆች ቁጥር ልክ ኢላማ በመቁረጥ ቀደም ብለው ዒላማውን ወደ ደመራ ቦታ ይወስዳሉ፡፡ከዚያን ሁሉም አባወራዎች በተገኙበት ጉድጓድ ተቆፍሮ ኢላማው ይተከልና ይቆማል፡፡
ከዚያን ሁሉም አባወራዎች በተገኙበት ጉድጓድ ተቆፍሮ ኢላማው ይተከልና ይቆማል፡፡
የተሰበሰበው ማህበረሰብም ደመራ ቦታው ጠላ፣ዳቦ፣አነባበሮ...በመያዝ ይመጣሉ የተሰበሰበው ማህበረሰብብ የተተከለውን ኢላማ በመዞር አንድ የአካባቢው ሆሆ የሚል ችሎታ ያለው የተመረጠ ሽማግሌ
-እዮሐ አበባዬ መስከረም ጠባዬ
-ተው አትኩራ ነፍስ ጎመን ባውጣው ነፍስ በማለት ሶስት ጊዜ ከዞሩ በኋላ ሽማግሌዎቹ የመጣውን ዳቦ እየቆረሱ ከተበላ፣ከተጠጣ በኋላ ሽማግሌዎቹ ይመርቃሉ፡፡የተሰበሰበው ማህበረሰብም ወደ ቤታቸው ተመልሰው ከቤታቸው ችቧቸውን አብርተው ወደ ደመራው ለመሄድ ይለኩሳሉ፣ችቦ ከቤታቸው መለኮስ ሲጀምሩ ከመውጣታቸው በፊት፡
-የገንፎ ድስት ግባ
የጎመን ድስት ውጣ ብሉው ይሄዳሉ፡፡የአካባቢው ወንዶች ልጆችም ኢላማውን ሲያነዱ አድረው ጠዋት ከብቶቻቸውን ወደ መስክ እየነዱ የመስቀል በአል ያመጣላቸውን ብስራት በመዘከር በደስታና በብሩህ ተስፋ ሲያከብሩ ይስተዋላሉ፡፡

ጨለሚት ዋሻ ጊዎርጊስ
24/04/2020

ጨለሚት ዋሻ ጊዎርጊስ

25/03/2015

yekdst arema megegna bota

Address

Deneba

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Siyadebr ena wayu cultur& tuorism posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Siyadebr ena wayu cultur& tuorism:

Share