Dembecha Zuria Woreda Revenue Office/ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት.

  • Home
  • Ethiopia
  • Dembech'a
  • Dembecha Zuria Woreda Revenue Office/ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት.

Dembecha Zuria Woreda Revenue Office/ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት. Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dembecha Zuria Woreda Revenue Office/ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት., Government Organization, dembecha, Dembech'a.

የመስክ ተግባራት በ8/03/2018 ዓ.ም  እንደቀጠለ ነው ።                 የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኞች እና አመራሩን በማቀናጀት የተሰራው ስምሪት በዛሬው እለት...
17/11/2025

የመስክ ተግባራት በ8/03/2018 ዓ.ም እንደቀጠለ ነው ። የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኞች እና አመራሩን በማቀናጀት የተሰራው ስምሪት በዛሬው እለትም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እና የግብር ስብሠባ ስራ እየተከናወነ ይገኛል። በመሆኑም በእለቱ 71892 ብር መሠብሠብ ተችሏል።

በስምሪት የግንዛፈራ ስራ እና የግብር ስብሰባ ተጀመረ።       በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች  ጽ/ቤት በ6/03/2018 ዓ.ም በተጀመረ ስምሪት ለነጋዴዎች,ለተሽከርካሪ ባለሀብቶች,ለወፍጮ ግ...
15/11/2025

በስምሪት የግንዛፈራ ስራ እና የግብር ስብሰባ ተጀመረ። በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በ6/03/2018 ዓ.ም በተጀመረ ስምሪት ለነጋዴዎች,ለተሽከርካሪ ባለሀብቶች,ለወፍጮ ግብር ከፋዮች ግብር መክፈል ግዴታ ስለመሆኑ በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት ግብር በየ ሩብ አመቱ የሚከፈል ስለመሆኑ እና በሩብ አመት መክፈል ያለው ጠቀሜታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ተከናውኗል። በተጨማሪም የግብር ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ውይይት ከተደረገ በኋል የግብር ስብሰባው ተጠናክሮ ቀጥሎ ውሏል።በመሆኑም በዕለቱ መስክላይ በተሠራ ስራ 39 091 ብር መሠብሠብ ተችሏል። ስምሪቱ ቀጣይነት ያለው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት የተሻለ ስራ የሚያሠራ የመጨረሻ አማራጭ እንደሚሆን በማሠብ ስምሪቱ ወደስራ ማስገባት ተችሏል። በዚህ ስምሪትም የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች በሰፊው የሚሠሩ እንደሚሆን እና የነጋዴዎችን መብት እና ግዴታቸውን አውቀው ህጋዊ ሁነው ስራቸውን መስራትእንዳለባቸው ማሳመን መቻል እንዳለብን ተገልጻል። በዚህ አጋጣሚ ፔጃችንን ለምትከታተሉ ግብር ከፋዬቻችን በሙሉ ግብራችሁን በመክፈል የዜግነት ግዴታችሁን እንድትወጡ ሲል ጽ/ቤቱ ጥብቅ የሆነ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

የስራ ግምገማ እየተካሄደ ነው           የደም/ዙ/ወ/ገቢዎች ጽ/ቤት ከወረዳ አስተዳሪው ከዞን ደጋፊ አመራር እና ከንግድ ጽ/ቤት  ሀላፊና ባለሙያዎች ጋር ተግባራትን እየገመገመ ነው።  ...
12/11/2025

የስራ ግምገማ እየተካሄደ ነው የደም/ዙ/ወ/ገቢዎች ጽ/ቤት ከወረዳ አስተዳሪው ከዞን ደጋፊ አመራር እና ከንግድ ጽ/ቤት ሀላፊና ባለሙያዎች ጋር ተግባራትን እየገመገመ ነው። እስከ 3/3/2018 ዓ.ም ድረስ 18 186 788 ብር የተሠበሠበ መሆኑን የገመገመ ሲሆን አፈጻጸሙ ከእቅዳችን አንጻር ዝቅተኛ መሆኑን የገመገምን ሲሆን በምን አግባብ ከችግር መውጣት አለብን የሚለውን ለማየት ችለናል:: በመሆኑም በተቀናጀ መንገድ ከአጋር አካላት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር መስራት እንዳለብን መግባባት ላይ ደርሠናል። ውጤት ለማምጣት ገቢ ልናገኝ በምንችልበት ዘርፋ መስራት የሚጠበቅ እንደሆነ እንዲሁም ነጋዴዎቻችን ከህገ ወጥ ንግድ ወተው ወደ ህጋዊ መንገድ እንዲገቡ እና ከቅጣት እና ወለድ እንዲድኑ መሥራት አለብን ተብሏል። ስለሆነም ለቀጣይ ነጋዴዎቻችን ከችግር ለማውጣት የቅስቀሳ ስራችንን አጠናክረን መስራት እንዳለብን ተግባብተናል። ለነጋዴዎችም ግብራቸውን ከፍለው ወደ ህጋዊ መንገድ መግባት እንዳለባቸው መልክት ተላልፏል።

በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ንዑስ አንቀጽ 29 መሠረት ከዲጅታል ይዘት ፈጠራ ከሚገኝ ገቢ ግብር እንዲከፈልበት ተደርጓል ሕዳር 2/2018 ዓ.ምበዚሁም መሠረት ከዲጂታል ይዘት...
11/11/2025

በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ንዑስ አንቀጽ 29 መሠረት ከዲጅታል ይዘት ፈጠራ ከሚገኝ ገቢ ግብር እንዲከፈልበት ተደርጓል
ሕዳር 2/2018 ዓ.ም
በዚሁም መሠረት ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ማለት አንድ ግለሰብ፣ ድርጅት የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎቶችን፣ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን፣ የድምጽ ማስተላለፊያ (ፖድካስት) አገልግሎቶችን እና የቀጥታ ስርጭት መድረኮችን ጨምሮ በኦንላይን መድረኮች ላይ ዲጂታል ይዘትን በመፍጠር እና በማሰራጨት የሚያገኘው ማንኛውም የገንዘብ ወይም በአይነት የሚገኝ ገቢ ነው።
ይህም የሚከተሉትን ገቢዎች ያካትታል፦
ሀ) ማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖች፣
ለ) የምርት ስም ስምምነቶች እና ድጋፎች፣
ሐ) የአጋርነት ግብይት እና የምርት ምደባዎች
መ) የደጋፊዎች አስተዋጽኦ፣ የገንዘብ ስጦታዎች ወይም የብዙሃን የገንዘብ ማሰባሰብ
(ክራውድ ፈንዲንግ)፣
ሠ) የአባልነት ክፍያዎች፤
ረ) የዲጂታል ወይም የአካላዊ ሸቀጦች ሽያጭ፣
ሰ) ለማስተዋወቂያ እንቅስቃሴ ምትክ የተገኙ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች እና
ሸ/ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ሌሎች ክፍያዎች፡፡

11/11/2025
በተሻሻለው አዋጅ  1395/2017ሥልጠና ተሠጠ።     ለደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኞች የአሠልጣኞች ሥልጠና በወሠዱ ሠራተኞች  ስልጠና እየተሠጠ ነው። ሥልሠናውን የጽ/ቤታችን ...
04/11/2025

በተሻሻለው አዋጅ 1395/2017ሥልጠና ተሠጠ። ለደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኞች የአሠልጣኞች ሥልጠና በወሠዱ ሠራተኞች ስልጠና እየተሠጠ ነው። ሥልሠናውን የጽ/ቤታችን ሀላፊ ያሥጀመሩት ሲሆን ይህ ሥልጠና ለሠራተኞች ተቀራራቢ የመፈጸም ብቃት እንዲኖራቸው ያሥችላል በማለት ስልጠናውን በይፍ አስጀምረዋል። አሠልጣኞች አያይዘውም ሥልጠናውን በነቃ ተሣትፎ መሠልጠን እና ወደ ሥራ መግባት እንደለብን ገልጸዋል።

ስልጠናው ከስዓት በኋላም እንደቀጠለ ነው።                  ለጠቅላላ ሠራተኛው እየተሠጠ ያለው ስልጠና የቀጠለ ሲሆን  በሥልጠናው ጥሩ የሆነ ግንዛቤ እያገኙ እንደሆነ ሠራተኞች ተናግ...
04/11/2025

ስልጠናው ከስዓት በኋላም እንደቀጠለ ነው። ለጠቅላላ ሠራተኛው እየተሠጠ ያለው ስልጠና የቀጠለ ሲሆን በሥልጠናው ጥሩ የሆነ ግንዛቤ እያገኙ እንደሆነ ሠራተኞች ተናግረዋል።

31/10/2025
በመሆኑም የወረዳችን የደረጃ ሀ ግብር ከፋዬች ከጥቅምት 30/2018 ዓ.ም በፊት  ግብራችሁን  እንድታሣውቁ እየገለጽን  በወቅቱ ባለማሣወቃችሁ ለሚመጣው ቅጣት እና ሌሎች ተጠያቂነቶች ሀላፊነት...
28/10/2025

በመሆኑም የወረዳችን የደረጃ ሀ ግብር ከፋዬች ከጥቅምት 30/2018 ዓ.ም በፊት ግብራችሁን እንድታሣውቁ እየገለጽን በወቅቱ ባለማሣወቃችሁ ለሚመጣው ቅጣት እና ሌሎች ተጠያቂነቶች ሀላፊነት የማንወሥድ መሆኑን እንገልጻለን::ጽ/ቤቱ

Address

Dembecha
Dembech'a

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dembecha Zuria Woreda Revenue Office/ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share