Dejen Woreda Culture and Tourism Office

Dejen Woreda Culture and Tourism Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dejen Woreda Culture and Tourism Office, Government Building, Dejen.

08/09/2026
የቅዱስ ሩፋኤል ክብረ በዓል በዓባይ ወንዝ በድምቀት ተከበረ፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል ክብረ በዓል በዛሬው ዕለት ማለትም  ጳጉሜ 3 ቀን 2018ዓ.ም በአባይ ወንዝ በቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ ድልድይ...
08/09/2026

የቅዱስ ሩፋኤል ክብረ በዓል በዓባይ ወንዝ በድምቀት ተከበረ፡፡
የቅዱስ ሩፋኤል ክብረ በዓል በዛሬው ዕለት ማለትም ጳጉሜ 3 ቀን 2018ዓ.ም በአባይ ወንዝ በቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ ድልድይ ላይ በድምቀት ተከበረ፡፡ በዕለቱም ልዩልዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶችና ባህላዊ ክዋኔዎች የቀረቡ ሲሆን ከአማራ ክልል እና ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የማህበረሰብ ክፍሎች በዓሉን በድምቀት አክብረዋል፡፡

የእንግጫ መደላደያ /ነቀላ/ በዓል "ባህላችን ድልድያችን ፤አንድነታችን መዳረሻችን" በሚል መሪ ቃል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በየትኖራ ቀበ...
04/09/2026

የእንግጫ መደላደያ /ነቀላ/ በዓል "ባህላችን ድልድያችን ፤አንድነታችን መዳረሻችን" በሚል መሪ ቃል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በየትኖራ ቀበሌ በመስክ ነሀሴ 29/2018 ዓ.ም በድምቀት ተከበረ። በበዓሉ ላይም የወረዳ መንግስት ሰራተኞች፣ የጽ/ቤት ሃላፊዎች፣የዓባይ ዳር የሙዚቃና ቴአትር ክበብ አባላትና የአካባቢው ማህበረሰብ ታድመዋል።

የእንግጫ መደላደያ /ነቀላ/ በዓል "ባህላችን ድልድያችን ፤አንድነታችን መዳረሻችን" በሚል መሪ ቃል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በፓናል ውይይ...
04/09/2026

የእንግጫ መደላደያ /ነቀላ/ በዓል "ባህላችን ድልድያችን ፤አንድነታችን መዳረሻችን" በሚል መሪ ቃል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በፓናል ውይይት ነሀሴ 28/2018 ዓ.ም ተከበረ። በበዓሉ ላይ የወረዳው መንግስት ሰራተኞችና የጽ/ቤት ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ በገልገሌ ቀበሌ በመርሃ ኢየሱስ አቡነ ተክለሀይማኖት ገዳም የአቡነ ተክለሀይማኖት የእረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በ24/12/2018ዓ.ም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስ...
04/09/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ በገልገሌ ቀበሌ በመርሃ ኢየሱስ አቡነ ተክለሀይማኖት ገዳም የአቡነ ተክለሀይማኖት የእረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በ24/12/2018ዓ.ም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በድምቀት ተከበረ፡፡በእለቱም የካህናት ወረብና በሰባኪያን ስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን፣በምዕመናንም ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ክዋኔዎች ቀርበዋል፡፡ በወጣቶችም ሆታና ባህላዊ ጭፈራዎች ደምቆ በዓሉ በሰላም ተከብሯል፡፡

ጥንታዊው የገማጤ ዋሻ ቤተ ክርስቲያንና መካነ መቃብር የገመጤ ዋሻ ቤተ ክርስቲያን ከደጀን ከተማ በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በግምት በ18 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምንጅ ይብዛ ቀበሌ ይገኛል፡፡ የቤ...
25/05/2026

ጥንታዊው የገማጤ ዋሻ ቤተ ክርስቲያንና መካነ መቃብር
የገመጤ ዋሻ ቤተ ክርስቲያን ከደጀን ከተማ በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በግምት በ18 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምንጅ ይብዛ ቀበሌ ይገኛል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ፍርስራሹ ከገማጤ ገደል መሃል ላይ የሚገኝ ሲሆን በ5ኛው መ/ክ/ዘመን በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን በቤተክርስቲያንነትና መኗሪያነት ያገለግል እንደነበር የአካባቢው የእድሜ ባለጸጎች ይናገራሉ፡፡ ለአካባቢው ህብረተሰብ የመቃብር ቦታ እንደነበርም በአሁኑ ወቅት ከቤተክርስቲያኑ ፍርስራሽ ዙሪያውን ያሉ ያልፈራረሱ መቃብሮችና አጽሙ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ የዋሻ ቤተክርስቲያኑ ከፊሉ የተፈጥሮ ዋሻ ሲሆን የውጨኛው ክፍል፣ መግቢያ በሮችና የውስጥ ክፍሎች ግን የጥንታዊት ኢትዮጵያን የኪነ ህንጻ ጥበብን ተከትለው የተሰሩ ናቸው፡፡ የዋሻ ቤተክርስቲያኑ ሶስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነዚህም ቅኔ ማህሌት፤ ቅድስትና ቅድስተ ቅዱሳን ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ክፍሎች ብዙም ያልፈራረሱ ሲሆን ሶስተኛው ክፍል ግን በውል አይታወቅም፡፡ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩት አገዎች እንደሰሩት የሚነገረው ይህ የዋሻ ቤተ ክርስቲያን በዮዲት ጉዲት ዘመን በርካታ ቤተክርስቲያናትና ንዋያተ ቅድሳት ሲቃጠሉ ብራቴ የሚባል አገው ታቦተ ማሪያምን ይዞ ጭራ ገደል ወደሚባል በረሃ በመሸሽ ከዘረፋና መቃጠል እንዳዳነው የአካባቢው አባቶች ይናገራሉ፡፡ በዚህ ዋሻ አካባቢ ሌላው አስገራሚ ነገር የመካነ መቃብሩ የአቀባበር ስርዓት ነው፡፡ ይህም በዋሻ ቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያውን ቀጥ ያለውን ገደል በመፈልፈል አስከሬኑን ይከቱታል፡፡ ሌላ ሰው በሚሞትበት ጊዜ በፊት ከተቀበረው አስከሬን በላይ /ሁለቱ አሰከሬን እንዳይነካካ በማድረግ/ ይቀበራል፡፡ እንዲህ እንዲህ አያለ እስከ 8 መቃብር ወደ ላይ የተደራረበ ቀብር በማስረጃነት አግኝተናል፡፡ ይህ የዋሻቤተ ክርስቲያን እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ስርዓተ ቅዳሴ ይደረግበት እንደነበርና በ1976 ዓ.ም የአሁኗ ምንጅ ማርያም ቤተከርስቲያን ከዋሻው በግምት በ1 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንደተሰራች በአካባቢው የሚኖሩ አባቶች ይናገራሉ፡፡ በዚሁ አካባቢ ከገማጤ ዋሻ በ2 ኪ.ሜ ርቀት ዥሬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሽመላም ዋሻ ይገኛል፡፡ ይህ ዋሻ ለአካባቢው ህብረተሰብ በመኗሪያነትና በተጨማሪም የአሁኑ ቅዱስ ሚካዔል ቤተክርስቲያን ከመሰራቱ በፊት በቤተ ክርስቲያንነት ያገለግል እንደነበር የአካባቢው የእድሜ ባለጸጎች ይናገራሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ ፍርስራሽም በአሁኑ ወቅት በማስረጃነት ይገኛል፡፡

በደጀን ወረዳ የክበቦች የበጋ ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር በቀን 09/09/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በ5 ቡድኖች ...
18/05/2026

በደጀን ወረዳ የክበቦች የበጋ ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር በቀን 09/09/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በ5 ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የበጋ ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር ግንቦት 9/2018 ዓ.ም ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ የፍጻሜ ጨዋታውም በጢቅ ታዳጊ የእግር ኳስ ቡድን እና በቦረቦር ቀበሌ የእግር ኳስ ቡድን መካከል ተካሂዶ በመደበኛ ደቂቃው በ2 ነጥብ አቻ ውጤት በመጠናቀቁ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምት የቦረቦር ቀበሌ የእግር ኳስ ቡድን የጢቅ አቻውን በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡ በውድድሩ ማጠቃለያ ለአሸናፊ ቡድኑ የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ ለዳኞችና ለተሳታፊ ቡድኖችም የምስጋናና የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲሆን ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም የምስጋናና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ለኮከብ ተጫዋቾች፣ለምስጉን ዳኞችና ለኮከብ ግብ አስቆጣሪዎች ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች በመባል የጢቅ ታዳጊ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቹ ተዋቸው ማዘንጊያው ሲመረጥ የቦረቦር ቀበሌ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የሆነው ሀብታሙ ደጓለ በ8 ግብ ኮኮብ ግብ አስቆጣሪ በመሆን አጠናቋል፡፡

የዓባይ ሸለቆ የተፈጥሮ ገጽታ በደጀን ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ከተመዘገቡት የመስህብ ሃብቶች ውስጥ የዓባይ ሸለቆ አንዱ ነው፡፡ የዓባይ ሸለቆ በጣም የሚስብና ማራኪ የተፈጥሮ ገጽታ ያለው...
19/03/2026

የዓባይ ሸለቆ የተፈጥሮ ገጽታ
በደጀን ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ከተመዘገቡት የመስህብ ሃብቶች ውስጥ የዓባይ ሸለቆ አንዱ ነው፡፡ የዓባይ ሸለቆ በጣም የሚስብና ማራኪ የተፈጥሮ ገጽታ ያለው ሲሆን በውስጡም እምቅ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የመስህብ ሃብቶችን የያዘ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል
ድልአርድ ዋሻ
የአገው ካብ
ጥንታዊው የመርኃ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን
ገማጤ ዋሻ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎች ያልተጠኑና ወደፊት ሰፊ ጥናት የሚጠይቁ ሃብቶችን የያዘ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ረጅም ዓመታት ያስቆጠሩ የእንስሳትና ዕጽዋት ቅሪት አካላት መገኛም እንደሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጅ ተመራማሪዎች በ2004ዓ.ም እና በ2005 ዓ.ም ባደረጉት ጥናት ገልጸዋል፡፡ በ2015 ዓ.ም በአባይ ሸለቆ በሚገኙ የአዕዋፍ ዝርያዎች ዙሪያ ጥናት ያደረገው ኤለፋንት ቱር በሸለቆው ውስጥ 155 የአዕዋፍ ዝርያዎች መኖራቸውን አረጋግጧል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 14ቱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ብርቅየ የአዕዋፍ ዝርያዎች መሆናቸውን ጥናቱ ለይቷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ዲላና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የጂኦሎጅ፣ ጂኦግራፊ፣ ኧርዝ ሳንስና ሌሎች ተማሪዎች ለጥናት ወደ ዓባይ ሸለቆ ይመጣሉ፡፡ በተጨማሪም ሸለቆው የበርካታ የከበሩ ማዕድናት መገኛም ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ኦፓል፣ ድንጋይ ከሰል ፣እምነ በረድ፣ ቀይ አሸዋ፣ ጥቁር አሸዋ፣ ጀስፐር፣ ጀሶ ፣ነጭ እጣን ፣ሴራሚክና ሌሎችም ሲኖሩ በአጠቃላይ ሸለቆው ወደፊት ትልቅ የጥናትና ምርምር ማዕከል ሊሆንና ለአካባቢው ህብረተሰብ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

130ኛው የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረበምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ 130ኛው የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡የአድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በመራር ...
10/03/2026

130ኛው የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ
በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ 130ኛው የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡የአድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በመራር የትግል መስዋዕትነት ያስመዘገቡትና ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ተምሣሌት የሆነ የድል ሐውልት ነው። ይህ የድል በዓል ዘንድሮ ለ130ኛ ጊዜ “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ!!!” "Glorious Past, Radiant Horizon" በሚል መሪ ቃል በቀን 23/06/2018ዓ.ም በድምቀት ተከበረ።በፕሮግራሙም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን በዓሉን አስመልክቶ ልዩ ልዩ መልክቶች ተላልፈዋል የፓናል ውይይትም ተካሂዷል፡፡ አባይ ዳር የሙዚቃና ትያትር ቡድን አባላት የተለያዩ ዝግጅቶችን አቅርበዋል።በአሉን አስመልክቶም ስነ ጹሁፍ ቀርቧል፡፡
ክብር ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ታላቅ ታሪክ ለአወረሱን አባቶቻችን!!!

Address

Dejen

Telephone

+251587760784

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dejen Woreda Culture and Tourism Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share