ደብረ ወርቅ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Debre work city prosperity party office

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Werk'
  • ደብረ ወርቅ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Debre work city prosperity party office

ደብረ ወርቅ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Debre work city prosperity party office prosperity for all

ትናንት፣ ዛሬና ነገ....በሀገራችን ውስጥ በሚዛን ሊያዝ የሚገባው ነገር በትናንት፣  በዛሬና በነገ መካከል ያለው ምልከታ ነው፡፡ ትናንትን ፈፅሞ የመቀደስም ሆነ ትናንትን ፈፅሞ የማርከስ ጉዞ...
27/05/2026

ትናንት፣ ዛሬና ነገ....

በሀገራችን ውስጥ በሚዛን ሊያዝ የሚገባው ነገር በትናንት፣ በዛሬና በነገ መካከል ያለው ምልከታ ነው፡፡ ትናንትን ፈፅሞ የመቀደስም ሆነ ትናንትን ፈፅሞ የማርከስ ጉዞ ሀገርን ያለ ወረት ያስቀራል።

ዛሬንና ነገን ማቃለልም ሆነ ዛሬና ነገን የሁሉም ነገር መጀመሪያ ማድረግ ሀገርን ያለ መነሻ ያስቀራል፡፡ ብልፅግና ትናንት ከዛሬና ከነገ ጋር በሚዛን የሚታይበትን መርሕ ይከተላል፡፡

• ከትናንቱ መልካሙን መውሰድ፤ እንከኑን ማረም
• ዛሬን፣ በትናንት መሠረት ላይ ገንብቶ በሚገባ መጠቀም
• ለነገ ተግባብቶ ወረት ማቆየት

ትናንትን ከዛሬና ነገ ጋር በሚዛን ለማየት እንዲቻል፣ የትናንት ቁርሾዎችን የምናክምባቸው፣በትናንትጉዞ ላይ የምንግባባባቸው ፤ ነገን በጋራ የምንተልምባቸው መንገዶችን መከተል አለብን ብሎ ያምናል፡፡

እነዚህም፡-
👉በሰከነ ምክክር አዲስ ቃል ኪዳን ማሠር ፤

ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት፣ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ፓርቲያችን በቀዳሚነት አስቀምጧል፡፡ለዘመናት በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳይ እንኳን ያላግባቡን ጉዳዮች በሀገራዊ ምክክር ምላሽ እንዲያገኙ ቁርጠኛ አቋምም አለው። ፓርቲያችን ብሔራዊ መግባባት ለሀገረ መንግሥቱ ግንባታ የማዕዘን ድንጋይ እንደሆነ ያምናል።

የፖለቲካ ማኅበረሰቡ የትናንት ቅራኔዎችን በመግባባትና በዕውቅና፣ በዕርቅና በሽግግር ፍትሕ መፍታት እንዳለበት እናምናለን፡፡ ስለዚህም በስክነትና በዕውቀት፣ ሀገራዊ ምክክሩ እንዲሠምር ሕዝባችንና የፖለቲካ ልሂቃን አዎንታዊ ሀገራዊ ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አናቀርባለን።

በዚህ የጸና እምነታችንና መሻታችን የተነሣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋም ሂደት እንደ ፓርቲና እንደ መንግሥት የሚጠበቅብንን አድርገናል፡፡

የሕዝብ ተሳትፎን በማረጋገጥ፣ ለኮሚሽኑ ሥራ አስፈላጊ የሆኑትን የፋይናንስ፣ የሎጀስቲክስና የመረጃ አቅርቦቶችን ያለተዐቅቦ በማሟላት፣ እንዲሁም ነጻነቱን በማክበር ባለፈው ምርጫ ዘመን ቃል የገባንውን በተግባር ፈፅመናል።

በቀጣይ አምስት ዓመታትም፡-

በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መሪነት በሂደት የሚደረስባቸው ውሳኔዎችና ምክረ ሐሳቦች ይኖራሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

እነዚህን ውሳኔዎችና ምክረ ሐሳቦች ወስደን ለሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች፣ ለፖለቲካ ሥርዓት ማሻሻያዎች፣ ለሰብአዊ መብቶች ማሻሻያዎች እና ለቀደሙ በደሎች የመፍትሔ መንገዶች አድርገን እንደ ፓርቲና መንግሥት ለመፈጸምና ለማስፈጸም እንሠራለን።

👉በሽግግር ፍትሕ መሥመር፤ ቁርሾን መሻር ፤

በኢትዮጵያ ለዘመናት የኖሩ በደሎች፣ ቁርሾዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሉ፡፡ እነዚህን በተመለከተ ፈውስ የሚሰጥ ፍትሕን እና ይቅርታን ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትሕ እንደሚያስፈልገን ፓርቲያችን ያምናል። ይህንን መሠረት በማድረግም ባለፉት ዓመታት ሕጋዊና ተቋማዊ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡

በቀጣይ ዓመታትም፡-

ለተፈጸሙ በደሎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በሽግግር ፍትሕ ማዕቀፍ የወንጀል ምርመራና ክስ፣ እውነትን የማፈላለግ እና ይፋ የማውጣት ተግባር፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት፣ ግለሰባዊ እና ማኅበረሰባዊ ዕርቅ ለማስፈን እንሠራለን፡፡

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ሕጋዊና ባህላዊ መንገዶችን እንጠቀማለን፤ ማካካሻና ተቋማዊ ማሻሻያን ይተገበራል።በዚህም ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደ ሀገር እንዲተገበር እንሠራለን።

የብሔራዊ መግባባት፣ የዕርቅና የፍትሕ ሂደት እንዲሠምር የሀገራትን ተሞክሮ ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አስማምተን እንጠቀማለን። እንዲሁም ባሕላዊ የግጭት አፈታትና የዕርቀ ሰላም ሥርዓቶችን እንደየአካባቢው እንተገብራለን፡፡ ይህንንም በማድረግ ሀገራዊ አንድነታችንን እና ብሔራዊ መግባባታችንን እናጠናክራለን፡፡

የሽግግር ፍትሕ ሂደት ከተፅዕኖ እና ከፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲከናወን እናደርጋለን፡፡ ተአማኒነቱን እና ቅቡልነቱን ለማረጋገጥ፣ ሐቅ አፈላላጊ ኮሚሽን፣ ልዩ ዐቃቤ ሕግና ልዩ ችሎት ይቋቋምለታል፡፡

በእነዚህ ተቋማት በሚመራ ምርመራና ዳኝነት አማካኝነት እንዲከናወን በማድረግ፣ የሽግግር ፍትሕ ያስቀመጣቸውን ብሔራዊ ግቦች እንዲመታ እናደርጋለን።

👉የተሐድሶ ፕሮግራም ፤

በተለያዩ አካባቢዎች ነፍጥ አንግተው ጫካ የገቡ አካላት ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ ፓርቲያችን ሲሠራ ቆይቷል፡፡ በዚህ መንገድም በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።

እነዚህ ታጣቂዎች በተሐድሶ ፕሮግራም ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ ይገባናል፡፡ ታጣቂ ቡድኖች እንዲበተኑ፤ ታጣቂዎች ትጥቅ እንዲያወርዱ እና ወደ ሰላማዊው መንገድ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ የቦታ፣ የገንዘብ፣ የቴክኒክ እና የሥነ ልቦና ዝግጅት ይፈልጋል፡፡

ለዚህ ታላቅ ተግባር የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ የበጀትና የቁሳቁስ ዝግጅት በማከናወን የተሐድሶን ፕሮግራም በተሟላ መልኩ ለማከናወንና የጸና ሰላምን ለመመሥረት ፓርቲያችን ይሠራል፡፡



#ኢትዮጵያንወደተምሳሌትሀገር
#ብልፅግናፓርቲንይምረጡ

26/05/2026

በደብረ ወርቅ ከተማ የተካሄደ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ የህዝብ ማዕበል፣

ለደብረ ወርቅ የምርጫ ክልል ብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ዞናዊ የማጠቃለያ የምርጫ ቅስቀሳ በምስል።  #ምልክታችን _የስንዴ ነዶ_ነው!! !!
26/05/2026

ለደብረ ወርቅ የምርጫ ክልል ብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ዞናዊ የማጠቃለያ የምርጫ ቅስቀሳ በምስል።

#ምልክታችን _የስንዴ ነዶ_ነው!!
!!

በደብረ ወርቅ ከተማ አስተዳደር እና በእናርጅ እናውጋ ወረዳ አስተዳደር የጋራ ትብብር የደብረ ወርቅ የምርጫ ክልል ብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እና ዞናዊ የማጠቃለያ የምር...
26/05/2026

በደብረ ወርቅ ከተማ አስተዳደር እና በእናርጅ እናውጋ ወረዳ አስተዳደር የጋራ ትብብር የደብረ ወርቅ የምርጫ ክልል ብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እና ዞናዊ የማጠቃለያ የምርጫ ቅስቀሳ በደብረ ወርቅ ከተማ ተካሄደ።
********
በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ወርቅ ከተማ አስተዳደር እና በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የጋራ አዘጋጅነት "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሃገር !" በሚል መሪ መልዕክት ለ7ኛው ሃገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን የዕጩዎች ትውውቅ፣ የምርጫ ምልክት የማስተዋወቅ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በደብረ ወርቅ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በሰልፉ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለምናደርገው ጉዞ ብልፅግናን መምረጥ የብሩህ ተስፋና ዋስትና ነው፤ ብልፅግናን በመምረጥ በሀገራችን የተጀመሩ ትልልቅ የልማት ስራዎችን እናስቀጥላለን ፣ብልፅግናን በመምረጥ ሀገራችንን ከፍ እናደርጋለን ፤ብልፅግና ፓርቲን መምረጥ ተምሳሌተ ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው!፤ብልፅግናን መምረጥ በዓለም መድረክ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን መገንባት ነው!፤ብልፅግና ፓርቲ ከዕዳ ወደ ምንዳ የተሻገረ ኢኮኖሚ እየገነባ፥ ፀጋን ወደ ሀብት የሚቀይር ፓርቲ ነው!፤ብልፅግና ፓርቲ ለዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚሰራ ፓርቲ ነው ‎የሚሉ እና ሌሎችንም መፈክሮችን በመያዝ የድጋፍ ሰልፉ በመካሄድ ላይ ነው።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ፓርቲው ባለፉት ዓመታት በሰላም፣በልማትና በዴሞክራሲ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በማንሳት ለተወዳዳሪዎቹ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

በድጋፍ ሰልፉ የዞን እና የክልል አመራሮች እንዲሁም የወረዳናየከተማ ጠቅላላ አመራሮች መላ ህዝቡ ታድመውበታል።
#ምልክታችን _የስንዴ ነዶ_ነው!!
!!

በእናርጅ እናውጋ ወረዳ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በ5ት/ቤቶች መሰጠት ተጀመረ።*********በምስራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በ5ት/...
25/05/2026

በእናርጅ እናውጋ ወረዳ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በ5ት/ቤቶች መሰጠት ተጀመረ።
*********
በምስራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በ5ት/ቤቶች መሰጠት ተጀምሯል።

25/05/2026

#በደብረ ወርቅ ከተማ ሲካሄድ በቆየው የምስራቅ ጎጃም ዞን የወረዳዎች የእግር ኳስ ሻምፒዮና አማኑኤል ከነማ የእግርኳስ ቡድን የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።

24/05/2026
24/05/2026
24/05/2026

Address

Debre Werk'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደብረ ወርቅ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Debre work city prosperity party office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ደብረ ወርቅ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Debre work city prosperity party office:

Share