South Gonder Zone Civil Service Department

South Gonder Zone Civil Service Department Government organization

A good place to trade your     🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
20/09/2024

A good place to trade your 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

የደቡብ ጎንደር ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶችን የሪፎርም አፈጻጸም በጠቅላላ አመራር ኮሚቴ አስገመገመ.....በግምገማ መድረኩ ላይ የዞን ዋና አስ...
18/01/2023

የደቡብ ጎንደር ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶችን የሪፎርም አፈጻጸም በጠቅላላ አመራር ኮሚቴ አስገመገመ.....
በግምገማ መድረኩ ላይ የዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የዞን መምሪያ አመራሮች፣ የወረዳ አስተዳደሮች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባወች፣ የሁሉም ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ሃላፊወችና የዞን ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊወች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመድረኩ የተቋማት የሪፎርም አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፣የዞኑ ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊና የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሃላፊ መድረኩን በጋራ እየመሩ የተገመገመ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ የተቀመጡ የጥንካሬ እና የድክመት ዝንባሌወች ላይ ጥልቅ ግምገማ በማድረግ የጋራ መግባባት የተደርሶ የቀጣይ አቅጣጫ ተሰጥቶ ተጠናቋል

የደቡብ ጎንደር ዞን ጠቅላላ አመራር ኮሚቴ የዞን ተቋማት የሪፎርም አፈጻጸም ግምገማ በማደርግ ላይ
18/01/2023

የደቡብ ጎንደር ዞን ጠቅላላ አመራር ኮሚቴ የዞን ተቋማት የሪፎርም አፈጻጸም ግምገማ በማደርግ ላይ

"ሁሉም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ ተወስኗል" በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የትምህርት ሚኒስቴርን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና ...
24/05/2022

"ሁሉም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ ተወስኗል" በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የትምህርት ሚኒስቴርን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎችን በመልቀቅ ውዥንብር እየፈጠሩ ያሉ የማህበራዊ ገፆችን እያየን ነው።

ስለሆነም ተማሪዎች የሚሰራጩት መረጃዎች የተሳሳቱ እና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን አውቃችሁ ትኩረታችሁን ትምህርታችሁ ላይ ብቻ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰቡ ይህንን በመረዳት ከተሳሳቱ መረጃዎች ራሳችሁን በማራቅ ሌሎች እንዳይሳሳቱ የማድረግ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪ እያቀረብን የትምህርት ሚኒስቴር ትክከለኛ የመረጃ ማሳረጫዎች የሚከተሉት መሆናቸውን እናሳውቃለን።
ከእነዚህ ውጭ ባሉ አድራሻዎች እኛን የሚመለከቱ አሳሳች መረጃዎች ስታገኙ እንድትጠቁሙንም በአክብሮት እንጠይቃለን።

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

ምዕራብ ዕዝ የጠላትን ኃይል ድባቅ መምታት የሚችል የሜካናይዝድ ኃይል መገንባቱን ገለፀምዕራብ ዕዝ የጠላትን ኃይል ድባቅ መምታት የሚችል የሜካናይዝድ ኃይል መገንባቱን ገለፀ።በምዕራብ ዕዝ የሜ...
24/05/2022

ምዕራብ ዕዝ የጠላትን ኃይል ድባቅ መምታት የሚችል የሜካናይዝድ ኃይል መገንባቱን ገለፀ

ምዕራብ ዕዝ የጠላትን ኃይል ድባቅ መምታት የሚችል የሜካናይዝድ ኃይል መገንባቱን ገለፀ።
በምዕራብ ዕዝ የሜካናይዝድ ክፍል አስተባባሪ ኮሎኔል ታደሰ ተበጀ እንደገለፁት÷ የተኩስ አመራሩ እና የምድብተኛ ኃይሉ ያለፈውን የጦርነት ጊዜያት መነሻ ያደረገ በቂ ዝግጅት አድርጓል፡፡

በሁሉም የሜካናይዝድ ኃይል ወታደራዊ ስልጠናዎች ተካሂደዋል ያሉት ኮሎኔል ታደሰ÷ የሜካናይዝድ ክፍሎች የሚሰጣቸውን ግዳጅ ተቀብለው የጠላትን ኃይል ድባቅ ለመምታት የላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

ሰራዊቱ ካካሄዳቸው ውጊያዎች በርካታ ልምዶችን በመውሰድ በሁኔታዎች መሃል በየጊዜው የሜካናይዝድ ኃይሉን የማድረግ አቅም ማሳደግ መቻሉንም ነው የገለጹት፡፡

የሜካናይዝድ ክፍሎች ለእግረኛ ክፍለ ጦሮች የተኩስ ድጋፍ ለመስጠት እና የጠላትን ኢላማዎች በአስተማማኝ ሁኔታ ለማውደም ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁች ናቸው ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

23/05/2022
የክልሉ መንግሥት እየወሰደ  ባለው የሕግ የበላይነት ማረጋገጥ ተግባር ሕዝቡ እያሳየ ያለውን ድጋፍ  አጠናክሮ  እንዲቀጥል የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡ የአማራ ክልል ሰ...
23/05/2022

የክልሉ መንግሥት እየወሰደ ባለው የሕግ የበላይነት ማረጋገጥ ተግባር ሕዝቡ እያሳየ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡

የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በሰጡት መግለጫ የክልሉን ሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት ዋስትና ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት የሚታዩ ሕገወጥ ድርጊቶችን የመከላከል፣ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ እና የሕዝብን ደኅንነት የማስጠበቅ ሚናውን እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡

ጠላት ለዳግም ወረራ እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት ከውስጥ እና ከውጭ የጠላትን ተልዕኮ ወስደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ወቅት ከማረሚያ ቤት ያመለጡ እና በተለያዩ ሕገወጥ ድርጊቶች የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን መንግሥት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ነው ኀላፊው ያነሱት፡፡

በተወሰደው የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ ከ4 ሺህ 500 በላይ ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር እንደዋሉም ኀላፊው አስታውቀዋል፡፡

ከዚኽ ውሥጥ ደግሞ፡-

•210 በነፍስ ግድያ ተጠርጥረው ተከሰው የምርመራ ሂደቱ ለሕልውና ዘመቻው ቅድሚያ በመስጠት ሳይታይ የቆየ፤

•ከ40 በላይ ተጠርጣሪዎች ደግሞ በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ወቅት እና በተለያዩ ምክንያቶች ከማረሚያ ቤት ያመለጡ፤

•39 ተጠርጣሪዎች በግድያ እና በልዩ ልዩ ወንጀሎች ተከሰው በሌሉበት ተፈርዶባቸው የነበሩ፤

•917 ከውስጥ እና ከውጭ ተልዕኮ ሲቀበሉ የነበሩ ጸጉረ ልውጦች ሲኾኑ የመጡበት ዓላማ እየተጣራ እንደሚገኝም ኀላፊው አብራርተዋል፡፡

•ከ1 ሺህ 780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ፣ በልዩ ልዩ ወንጀል በመሳተፍ ጭምር የተጠረጠሩ፣ በጸጥታ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ አባላትም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተጠቅሷል፡፡

•የክልሉ ሰላም እጦት እንዲባባስ፣ ከክልሉ ውስጥ እና ከክልሉ ውጭ ተልዕኮ ተቀብለው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሠሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም ተይዘዋል ብለዋል፡፡

ኀላፊው በመግለጫቸው እንዳነሱት የተለያዩ ወንጀሎችን እየሠሩ በእውነተኛው ፋኖ ስም የሚነግዱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከእውነተኛ ፋኖ ጋር በማስተሳሰር ሥም የሚያጠለሹ ግለሰቦች እና ቡድኖች ተቀባይነት የላቸለውም፡፡

ትክክለኛ ለሀገር የቆመውን ፋኖ በማደራጀት እና በማሰልጠን በመንግሥት አደረጃጀት ስር ኾኖ ለክልሉ አንድ አቅም እንዲኾን ይደረጋል ብለዋል፡፡

የተጀመረውን የጦር መሳሪያ ምዝገባ በተመለከተ ኀላፊው በክልሉ ነዋሪው ያለውን የጦር መሳሪያ ሕጋዊ አድርጎ የሀገሩን ሰላም እንዲጠብቅ መንግሥት የጦር መሳሪያ ምዝገባ ፈቅዶ እየሠራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ምዝገባው እስከ 17/09/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድም ኀላፊው ገልጸዋል፡፡ ምዝገባው እንደተጠናቀቀም የትጥቅ አያያዝ እና አጠቃቀም ሕግን አስመልክቶ ሥልጠና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

ኀላፊው የክልሉ መንግሥት እየወሰደ ላለው የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ ሕዝቡ እያሳየ ላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

አኹንም ሕገወጥነትን ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ ሕዝቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው የአሚኮ ነው

30/12/2020
15/12/2020

ታህሳስ 05/2013ዓ.ም

03/12/2020
19/11/2020

Address

Debre Tabor

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251584410239

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Gonder Zone Civil Service Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South Gonder Zone Civil Service Department:

Share