Guna Mountain Community Conservation Area Officeየጉና ተራራ የማህ/ሰብ ጥብቅ ስፍራ ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Tabor
  • Guna Mountain Community Conservation Area Officeየጉና ተራራ የማህ/ሰብ ጥብቅ ስፍራ ጽ/ቤት

Guna Mountain Community Conservation Area Officeየጉና ተራራ የማህ/ሰብ ጥብቅ ስፍራ ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Guna Mountain Community Conservation Area Officeየጉና ተራራ የማህ/ሰብ ጥብቅ ስፍራ ጽ/ቤት, Government Organization, Debre Tabor.

አስኔ (አውራ አምባ ቱር) እናመሰግናለን!!!👏👏👏
30/11/2024

አስኔ (አውራ አምባ ቱር) እናመሰግናለን!!!👏👏👏

Check out Asne 🕘’s video.

East African water tower-Guna Mountain!!!
14/03/2023

East African water tower-Guna Mountain!!!

25/03/2022

የምኒልክ ድኩላ የገደለው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡

በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ደሎ መና ወረዳ አንድ የምኒልክ ድኩላ የገደለው ግለሰብ በአንድ አመት ከስድስት ወራት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡
በደሎ መና ወረዳ ኗሪ የሆነው ተከሳሽ መሀመድ ኢብራሂም የምኒልክ ድኩላ በመግደል ወንጀል በአቃቢ ህግ ክስ ተመስርቶበት ዛሬ መጋቢት 15/2014 ዓ.ም በደሎ መና ወረዳ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ጥፋተኛ መሆኑ በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን አስተላልፏል፡፡

18/03/2022

የማህበረሰብ ደን ይዞታን ለግል ጥቅም ያዋሉግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።

ተከሳሾች፡-1/አቶ መንግስቱ ጌቴ
2/አቶ ይበልጣል አበዋ
3/አቶ አዳነ ላቀ
4/አቶ ሙሉአለም ወለላው
5/አቶ ደሴ ጤናአለም
6/አቶ አየለ ቢያዝን
7/አቶ በድሉ ጅጋር
8/አቶ አበባው ተደሰ የተባሉት የአነደድ ወረዳ ሻፎ ጉዳልማ ቀበሌ ነዋሪዎች ነሐሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሲሆን በሻፎ ጉዳልማ ቀበሌ የሚገኘውን የሻፎ ጉዳልማ ማህበረሰብ የሆነውን ደን በመጨፍጨፍ በቁመት 30 ሜትር በወርድ 200 ሜትር አርሰው ስንዴ በመዝራታቸው የአነደድ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት በደረሰው ጥቆማ መሰረት ምርመራ በማጣራት የምርመራ መዝገቡን ለወረዳው ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት ልኳል፡፡
የአነደድ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤትም የፖሊስን የምርመራ መዝገብ መርምሮ ግለሶቦቹ በተጠረጠሩበት የወንጀል ህግ አንቀፅ 686(2) መሰረት በአነደድ ወረዳ ፍ/ቤት ክስ በመመስረት ሲከራከር የቆየ ሲሆን የወረዳው ፍ/ቤትም በቀን 08/07/2014 ዓ/ም በአስቻለው ችሎት ከ1ኛ እስከ 7ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾች በ1 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ 8ኛ ተከሳሽ ደግም 1 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወሳኔ ሰጥታል በማለት የአነደድ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡
የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ

18/03/2022
Serengeti National Park, Tanzania
21/10/2021

Serengeti National Park, Tanzania

05/03/2021

በኢትዮጵያ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው አምስት የዱር እንስሳት ዝርያዎች የትኞቹ ናቸው?
-------------------------------------------------------------------------------------------
ኢትዮጵያ በዱር እንስሳት ሀብት ስብጥር ስሟ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የምትነሳ አገር ናት። በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በሚገኙ የዱር እንስሳቶች፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ አራተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ አገር መሆኗን የዱር እንስሳት ባለሙያው አቶ ጨመረ ዘውዴ ያስረዳሉ።
የዚህ ስብጥር ምክንያት ያሉትንም ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ ሲያስረዱ የአገሪቱ የመሬት አቀማመጥ፣ አዋሳኝ አገራት፣ ከደጋ እና ቆላ መካከል የምትገኝ አገር መሆኗ የዱር እንስሳት ስብጥር በርከት ብሎ የሚገኝባት እንዳደረጋት ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም ቀጭኔን ኢትዮጵያ ውስጥ ማየት ቀላል የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ፈተና ሆኗል። ቀይ ቀበሮዎች በሰሜንና በባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርኮች፣ በሰሜን ወሎ አቡነ ዮሴፍ ተራራ ላይ እና በመንዝ ገሳ አካባቢ ይገኝ ነበረ ቢሆንም አሁን ግን ቁጥሩ ተመናምኖ የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው እንስሳት መካከል ስሙ ሰፍሮ ይገኛል።
ኢትዮጵያን በዓለም ላይ ስሟን ሊያስጠራ የሚችል የዱር እንስሳት ሀብት ቢኖርም የአብዛኞቹ ይዞታ ግን ከጊዜ ወደጊዜ እየተመናመነ መምጣቱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ።
የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለሙያ እና አማካሪ የሆኑት ዶ/ር መኮንን በኢትዮጵያ የዱር እንስሳቱ የመኖሪያ አካባቢያቸው በትክክል ባለመጠበቁ እና በመረበሹ የመራባት ዕድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱም ለመጥፋት የተጋለጡ እንዳሉ ያስረዳሉ።
ሙሉውን ለማንበብ፦https://bbc.in/3kP2YXi

🌻🌻🌻መልካም አዲስ አመት!🌻🌻🌻****የጉና ተራራ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ ጽ/ቤት ለመላው ኢትዮጵያዊያን አዲሱ አመት የፍቅር፣ የሠላም እና የመተሳሰብ ዘመን ይሆን ዘንድ ይመኛል።🌻🌻🌻🌻🌻እንኳ...
11/09/2020

🌻🌻🌻መልካም አዲስ አመት!🌻🌻🌻
****
የጉና ተራራ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ ጽ/ቤት ለመላው ኢትዮጵያዊያን አዲሱ አመት የፍቅር፣ የሠላም እና የመተሳሰብ ዘመን ይሆን ዘንድ ይመኛል።
🌻🌻🌻🌻🌻እንኳን አደረሳችሁ!🌻🌻🌻

Address

Debre Tabor

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guna Mountain Community Conservation Area Officeየጉና ተራራ የማህ/ሰብ ጥብቅ ስፍራ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share