16/03/2026
ዳቃ ቂርቆስ ንጉስ ይትባረክ የተሸነፉበት(የሞቱበት) አፄ ይኩኖአምላክ ድል ያደረጉበት ቦታ ነው፡፡
• በታች ጋይንት ወረዳ የሚገኝ የጦር አውድማ ቦታወች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከአርብ ገብያ አንሰታ ጊወርጊስ በሚያስሄደው መንገድ ከወረዳው ዋና ከተማ አርብ ገበያ በ13 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል ።በመኪና ከ20-30 ደቂቃ በእግር ለሚጓዙ ደግሞ ከ 1:30-2:00 ገደማ ይወስዳል። ብዙ ነገስታቶችን ያፈራረቀው ይህ ቦታ በክረምትም ሆነ በበጋ ለጎብኚዎች ምቹ ነው።
• ዳቃ ማላት በግዕዝ ወጋ ፤መታ፤ጎሰመ ማላት ነዉ፡፡
• ዳቃ ቂርቆስ በአፄ ኢዛና ዘመነ መንግስት እንደተመሠረተ የሚነገርለት ቤተክርስቲያን ፅላቱ ከእየሩሳሌም በንግስት ሳባ ልጅ በምንትልክ( በአፄ ሚኒሊክ አንደኛ ) አክሱም ፂወንን ሲያመጣ አብሮ የመጣ እንደሆነ ይነገርለታል ።
• በዚች ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ከውጭ ወደ ቅጥር ጊቢው ሲገቡ በቀኝ በኩል ከተራራው ማዶ ላይ የፈራረሰ ጥንታዊ ከተማ ይታያል። ይህ ከተማ ዘበላ ከተማ በመባል ይጠራል ። ዘበላ ከተማ በንግስት ዘበላ በራሷ ስም የሚጠራ እንደሆን ታሪክ ያወሳል ።ይህ ከተማ ሰፊ ከተማ ሲሆን በአካባቢው የሚገኙ ገበሬዎች እርሻ በምናርስበት ሰአት አልፎ አልፎ የሰው ቅሪት አካል እናገኛለን ይላሉ።
• ዳቃ ቂርቆስ አበው እንደሚሉት ለ 2 ጊዜ ታድሷል። የመጀመርያው እድሳት በአፄ ይኩኖአምላክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በ1964-65 ዓ.ም ነው።
• የዛጉዌ ፍፃሜ የመጣው የድል ናኦድ ዘር እና ትክክለኛ ወራሽ መሆኑን በቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም ሆነ በቅዱስ ኢያሱ ሞአ መሪነት ራሱን ንጉስ ብሎ ያወጀው ይኩኖ አምላክ የመጨረሻውን የዛግዌ ንጉስን በማሳደድ ሲገድል ነበር ፡፡
• በዳቃ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የመጨረሻው የዛግዌ ስርዕዎ መንግስት እንደሆነ የሚነገርለት አፄ ይትባረክ የተፋለሙበት የተሸነፉበት(የሞቱበት) ከሰሎሞን ስርዎ መንግስት የሚመደበው አፄ ይኩኖአምላክ ድል ያደረጉበት ቦታ ነው። በዚህም የተነሳ አፄ ይኩኖአምላክ አፄ ይትባረክን በጦር "ደቃ" ሲል ዳቃ የሚለውን እንዳገኘ ይነገርለታል።
• በዚህ ድንቅ ቤተክርስቲያን ውስጥ የአፄ ይትባረክ፤ የርሳቸው ጳጳስ ክርስቶስ ደውሎ እና የኤዾስ ቆዾሱ ሀውልቶች ፊትና ኋላ ቁመው ይገኛሉ።
በስፍራው በወቅቱ አፄ ይኩኖ አምላክ ከጎጃም ጭነው እንዳመጡት የሚታመነው አፍር ይገኛል ።
የአበምኔቱ መካነ መቃብር ይገኛሉ። ሁሉንም መካነ መቃብሮች አሸናፊው ንጉስ አፄ ይኩኖአምላክ እንዳሰራቸው ይነገራል ።
ይምጡና ይጎብኙ፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ