የደቡብ ጎንደር ዞን ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

የደቡብ ጎንደር ዞን ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን S/G VERA

04/12/2025

ትውልድን በስነ- ምግባር ፣ ተቋምን በአሰራር
የ2018 ዓ.ም የፀረ-ሙስና ቀን መሪ ቃል

የሰዴ ሙጃ ወረዳ አሰ/ፅ/ቤትየሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባን በገጠርና በከተማ እንዴት መስራት እንዳለብን ከወረዳው አብይ ኮሚቴ ጋር የጋራ ውይይት ተደርኋል።በውይይቱም በወቅታዊ ችግሩ ምክንያት በማ...
04/12/2025

የሰዴ ሙጃ ወረዳ አሰ/ፅ/ቤት
የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባን በገጠርና በከተማ እንዴት መስራት እንዳለብን ከወረዳው አብይ ኮሚቴ ጋር የጋራ ውይይት ተደርኋል።በውይይቱም በወቅታዊ ችግሩ ምክንያት በማድረግ ምዝገባው የተዳከመበት ሁኔታ መኖሩን በመገምገም ጤና ኤክስቴንሽንና ስራ አስኪያጅ ተናበው በትኩረት በመስራት የላቀ ውጤት ማምጣት እንዳለብን ተወያይተናል

ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር የሲብልና ቤተሰብ ቡድን ለቀበሌ አድማጭ ቡድኖችና ባለሙያዎች በወኩም ፅንሰ ሃሳብና ጠቀሜታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።በደቡብ  ጎንደር  ዞን መካነ  ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር...
04/12/2025

ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር የሲብልና ቤተሰብ ቡድን ለቀበሌ አድማጭ ቡድኖችና ባለሙያዎች በወኩም ፅንሰ ሃሳብና ጠቀሜታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

በደቡብ ጎንደር ዞን መካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን ለቀበሌ አድማጭ ቡድኖችና ባለሙያዎች በወኩም ፅንሰ ሃሳብና ጠቀሜታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

የስልጠናውን ሰነድ በመካነ ኢየሱስ ከተማ የሲቪልና ምዝገባ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ገብሬ ወርቁ ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

በተሠጠው ስልጠና ሰፊ ግንዛቤ ያገኙ መሆኑንና በስራ ላይ የሚገጥሙንን ክፍተቶችን ያረመላቸው መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

በስልጠናው የመካነ ኢየሱስ ከተማ አሰተዳደር ተወካይ ከንቲባና የከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሞገስ አለነ እደገለፁት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሃገራዊ መረጃ በመሆኑ ስልጠነውን በትኩረት በመያዝ መረጃው በትክክልና ወቅቱን ጠብቆ መመዝገብ አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

በስልጠናው የመካነ ኢየሱስከተማ አስተዳደር ተወካይ ከንቲባና ከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሞገሰ አለነ መካነ ኢየሱስ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን መሪ አቶ ገበሬ ወርቁና የኩነት ባለሙያዎች ፥ የቀበሌ ባለሙያዎችና አድማጭ ቡድኖችና አጋር አካላት ተገኝተዋል ።

"መረጃ ለሃገራዊ ፍይዳ"

ህዳር 23 2018 ዓ ም
መካነ ኢየሱስ ኮምንኬሽን

27/11/2025
"የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ  ስርዓት ለዜጎች ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መረጋገጥ ወሳኝ ነዉ !" የፋርጣ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ እና ተወካይ ዋና አስተዳዳሪ  አቶ ሲሳይ ተስ...
26/11/2025

"የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓት ለዜጎች ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መረጋገጥ ወሳኝ ነዉ !" የፋርጣ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ እና ተወካይ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ተስፋ

‎የፋርጣ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ቡድን ከአጋር አካላት ጋር የዉይይት መድረክ አካሄደ።

‎የፋርጣ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስማረ ግዛቸዉ በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደገለፁት የሲቪል ማህበረሰብ ምዝገባ ከ2008 ዓመተ ምህረት አንስቶ በሀገር አቀፍ ደረጃና በክልል አቀፍ ደረጃ የሲቪል ማህበረሰብ ወይም ኩነት ምዝገባ በአለም አቀፍ ደረጃ 10 ኩነቶች አሉ። ስለዚህ በአግባቡና በስታንዳርዱ መሠረት መመዝገብ፣ መረጃ መያዝና ማስቀመጥ ተገቢ ነዉ ብለዋል።

‎በመሆኑም የኩነት ሰዎች ላይ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ቀረቢታ አለዉ። ስለዚህ የሲቪል እና የቤተሰብ ማህበረሰብ ምዝገባ ልደት፣ መት፣ ጋብቻና ፍች ለፍትህ ስርአቱ ወሳኝ ናቸዉ ብለዋል።

‎የፋርጣ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ቡድን የመረጃ ቅበላ ባለሙያ የሆኑት አቶ ገበየ አዘዘ የ4ወር እቅድ አፈፃፀም በዝርዝር አቅርበዉ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበታል።

‎የፋርጣ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ቡድን መሪ አቶ ሙሉጌታ ግርማ በአዋጅ ቁጥር 1370/2018 ደነብ ቁጥር 229/2018 መመረያ አቅርበዉ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበታል። በተጨማሪም የ4ወር ጠቅላላ ዕቅድ 1ሺ 262 ታቅዶ እቅድ ክንዉኑ 877 አፈፃፀም 69.4% መሠራቱን ገልፀዋል። በቀጣይ የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ በወቅቱ በማስመዝገብ ሁሉም ሰዉ የሚታወቅበት ኢትዮጵያን እንገንባ ብለዋል።

‎የፋርጣ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስማረ ግዛቸዉ በማጠቃለያዉ እንደገለፁት ለአንድ ሀገር ፍትሀዊ አገልግሎት ለመስጠት እና ዘላቂ ልማት እንድታስመዘግብ እንደ ልደት፣ ሞት፣ ጋብቻና ፍቺ ያሉ የሲቪል እና የቢተሰብ ምዝገባ መመዝገብ አስፈላጊነዉ ብለዋል።

‎የፋርጣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድምነዉ ላቀዉ እንደገለፁት በጤና ተቋማት የሚከሰቱ ልደትና ጋብቻ ኩነቶች በወቅቱ በማሳወቂያ ሰነድ እንዲመዘገቡ በተዋረድ ያሉ የጤና ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

‎አቶ ወንድምነዉ አክለዉም ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ተፈፃሚ እየሆኑ የሚገኙ እንደ ልደት፣ ጋብቻና ፍቺ፣ ሞት ኩነቶችን የመረጃ አያያዝ ስርዓት በማካተት የበለፀገች ኢትዮጵያን እዉን ለማድረግ በየደረጃዉ በትኩረት መሠራት አለበት ብለዋል።

‎የፋርጣ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ እና ተወካይ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ተስፋ እንደገለፁት የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ በቀረበዉ ሰነድ ላይ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ለሀገርም ሆነ ለግለሰቦች ያለዉ ፋይዳ የጎላ በመሆኑ ማህበረሰቡ ጠቀሚታዉን በመገንዘብ ባህልን ማዳበር አለበት ብለዋል።

‎አቶ ሲሳይ አክለዉም የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ስርአትን በማዘመን ቀልጣፋና ዉጤታማ አገልግሎት ለወረዳዉ ማህበረሰብ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።

‎የዉይይቱ ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት ዉይይት መሰጠቱ ለስራ ዉጤታመነት ወስኝ መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይ ወደ ተግባር በመግባት ጥራት ያለዉ ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል

‎በዉይይቱም ላይ የሲቪል እና ቤተሰብ ሞዝገባ ቡድን አብይ ኮሚቴ፣ ቴክኒክ ኮሚቴ፣ የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ አዋላጅ ነርሶች፣ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የቀበሌ ስራ አስኪያጆች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ አካላት ተገኝተዋል።



ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሠላም🕊

ምንጭ፦ የፋርጣ ወረዳ የመንግስት ኮሙዮኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት"

ህዳር 16/2018 ዓ.ም

የመቀጠዋ ወረዳ  ፍትህ ጽ/ቤት በቀን 8 /3/2018ዓ/ም"የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባን "አስመልክቶ ከወረዳዉ የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ አብይ ኮሜቴ ጋር  በሚመለከቱት ጉዳዮች ዉይይት ተደ...
21/11/2025

የመቀጠዋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በቀን 8 /3/2018ዓ/ም"የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባን "አስመልክቶ ከወረዳዉ የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ አብይ ኮሜቴ ጋር በሚመለከቱት ጉዳዮች ዉይይት ተደርጓል፦
👉 ትምህርት ጽ/ቤት በወረዳው መደበኛ ትምህርት በመጀመሩ አባላት ያለዉ ቡድን በመፍጠር የተቀናጀ የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ስራን እንዴት መስራት እንዳለበት
👉ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በጤና ጣቢያወች የሚወለዱ ህጻናትን በሚመለከት በባለሞያወች ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ በተቀናጀ እና በአግባቡ መመዝገባቸውን ክትትል ማድረግ እንዳለበት
👉የወረዳዉ ስራ አስኪያጅች ከጤና ኤክስቴሽን ባለሞያወች ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸዉ
👉አስተዳደር ጽ/ቤት የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ ጽ/ቤት በአዋጁ 1370/2017 አንቀጽ 5 በዝርዝር የተገለጹትን ተግባራት መከናወናቸውን ክትትል ማድረግ እንደለበት
👉በ 2018 በጀት ዓመት በወረዳዉ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም በመጠቀም ሁሉን አቀፍ የተደራጀና አሳታፊ የሆነ የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ማድረግን
👉ልደትን፣ሞትን፣ ፍችን ጋብቻን እና የመሳሰሉትን የወሳኝ ኩነት ጉዳዮች ማን፣ የት፣ መቸ እንዴት በክብር መዝገብ ማስመዝገብ እንዳለብን አዋጁን 1370/2017 መሰረት በማድረግ ሰፋ ባለ መንገድ ዉይይት ማድረግ
👉 የወረዳዉ የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ አብይ ኮሜቴ ሊሰሩ የሚገባቸዉን ስራወችን አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱን አጠናቋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን  የፋርጣ   ወረዳ    ሲቪል  ናቤተሰብ ምዝገባ የስራ  ቡድን በቀን 11/03/2018 ለቀበሌ-ስራ  አሲኪጆች  እና  አጠቃላይ  ለተቋም  ባለሙያዎች በደንበ ቁጥር 137...
21/11/2025

የደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ሲቪል ናቤተሰብ ምዝገባ የስራ ቡድን በቀን 11/03/2018 ለቀበሌ-ስራ አሲኪጆች እና አጠቃላይ ለተቋም ባለሙያዎች በደንበ ቁጥር 1370/2017 እና ሌሎች ስራወችን በሚመለከት የተሰጠ ስልጠና።

የደቡብ ጎንደር ዞን/አስ/ ሲ/ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን የአብክመ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አዲስ በአወረደዉ የቴክኒክ ኮሚቴ አደረጃጀትና እቅድ የዞኑ ኮሜቴ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት ዞ...
07/11/2025

የደቡብ ጎንደር ዞን/አስ/ ሲ/ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን የአብክመ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አዲስ በአወረደዉ የቴክኒክ ኮሚቴ አደረጃጀትና እቅድ የዞኑ ኮሜቴ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት ዞናዊ የሆነ እቅድ ማቀድና በእቅዱም ላይ ውይይት ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ ከክልል የተላከውን መነሻ እቅድ መሰረት በማድረግ ዞናዊ እቅድ በማዘጋጀት ከትምህርት መምሪያ ፣ ከጤና መምሪያና ከሴቶች ህፃናትና ሀረጋዊ መምሪያ ለተመረጡ አዲስና ነባር የኮሚቴ አባላት በ27/2/2018 ዓ/ም የዞኑየሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባቡድን መሪ በአቶ ማሩ ያለዉ የእቅዱ ላይ ኦረንቴሽን ተሰጥቷል ፡፡
በቀረበዉ እቅድ ላይ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል፣፣አባላቱም እቅዱ ወደ ወረዳ እንዲወርድና እውቅና እንዲፈጠርበት የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባውን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ከ2017 የበጀት አመት አፈፃፀም በተሻለ መልኩ የ2018 ምዝገባ የተሳካ ይሆናል በሚል አስተያየቶችን በመስጠት ለእቅዱ ተፈፃሚነት የሁሉም መመሪያዎች ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ፡፡ ሁላችንም የኮሚቴ አባላት በተዋረድ ያሉ ጽ/ቤቶችን በማስተባበር ኃላፊነታችን እንወጣለን የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥቷል፡፡

28/09/2025
27/09/2025

Address

Debre Tabor

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደቡብ ጎንደር ዞን ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share