ጊዎን አምሐራ የትግል አርማ

ጊዎን አምሐራ  የትግል አርማ አንድ አምሐራ ለሁሉም አምሐራ!
ትግላችን ለነፃነታችን!

  በአያት አ.ማ በሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በኃላፊነት ሲሰራ የነበረው እና የ5 ልጆች አባት የሆነው አቶ   ጥር 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ፈረንሳይ ለጋሲዮን ል...
02/02/2024


በአያት አ.ማ በሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በኃላፊነት ሲሰራ የነበረው እና የ5 ልጆች አባት የሆነው አቶ ጥር 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ፈረንሳይ ለጋሲዮን ልዩ ስሙ ወይብላ ፀበል አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እንደወጣ አልተመለሰም፡፡
ቤተሰቦቹ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፖሊስ ጣቢያ ያመለከቱ ሲሆን በሆስፒታሎች እና ሌሎች ቦታዎች ቢያፈላልጉትም ሊገኝ አልቻለም።
ተፈላጊው በእለቱ ጥቁር ሰማያዊ ጃኬት እና ሰማያዊ ጂንስ ሱሪ የለበሰ ሲሆን በምስሉ ላይ የሚታየውን ተፈላጊ ያየ ወይንም ያለበትን የሚያውቅ ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች ደውሎ እንዲጠቁመን በፈጣሪ ስም አንማፀናለን፡፡

0913503238 ወይንም 0913091983 (ባለቤቱ ወ/ሮ ስሜነሽ አያሌው)

ባለቤቱ እና ልጆቹ !!!

02/02/2024

አምሐራ!

07/09/2023

ብርሀኑ ጁላ ቪዲዮ አሳዩኝ እስኪ አለ አሳየነው። ሌላ ምን ማየት ትፈልጋለህ በሉልኝ?

በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁሉም ነገር ወደነበረበት እንመልሰዋለን አሉን ወራቶች ተቆጠሩ። በቃ እርማችሁን አውጡ ብአዴን ላይመለስ ተቀብሯል።
እውነት የማካበድ ወይም የሌላ አይደለም።

እንደ አማራ ስነልቦናው ጠንካራ የሆነ ሕዝብ በምድር ላይ የለም። የብዙ አገር ወጣቶችን አይቻለሁ፣የአማራ ወጣት ከቅድመ አያቶቹ የወረሰው የተለየ ነገር አለ። እውነት ነው,,,,በብዙዎች መሀል ውስጥ ባንዳ አለ።

ባንዳ የሚሆኑት ደግሞ የእውቀት፣የግንዛቤ ችግር ያለባቸው እና ሰርተው ሆዳቸውን መሙላት የማይችሉ ሰነፍ ስለሆኑ ስንፍናቸውን ለመደበቀ Easy Money ለማግኘት ሲሉ ህሊናቸውን የሚሸጡ ናቸው። አልያም ደግሞ Identity crisis ያለባቸው ልክ እንደ ጋኔል ክብረት አይነት ሰዎች። አሁን ጋኔል ክብረት ዘሩ የት እንደሆነ አይታወቅም።

አርበኛ ከፍያለው ጌቱ

04/09/2023

ሰበር! ሰበር! ሰበር!
ደጋዳሞት!
አንድ ጀኔራል ተሸኝቷል
ባለ ከዘራው ተማርኳል!
ፋኖ ድል ማድረጉን ቀጥሏል
ሙሉ መከላከያ ተበትኗል

ወጥር አምሐራ!

31/08/2023

#
******
ከአማራ ህዝባዊ ግንባር የተላለፈ ጥሪ..‼️‼️

ፋኖ😂💪
👉 1፦ በመከላከያ ስም የተላከው ወራሪ ቡድን የኦነግ ሀይል በገባባቸው ቦታዎች አካባቢወች ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ይገኛል ።
ነገርግን ሰራዊታችን ማንኛውም ከኦነግ ሰራዊት ውጪ ማለትም ከሶማሌ፣ ከአፋር ፣ከጋንቤላ ፣ከደቡብ ፣ከቤንሻንጉል ክልሎች የተማረኩና የቆሰሉ ምርኮኞች ተገቢውን እንክብካቤ እየተደረገላቸው ወደ እየመጡበት እንዲመለሱ እያደረገ ነው ።
👉 2፦ የሸኔ ገዳይ ቡድን ምርኮ ግን አብይ አህመድ በመከላከያ ስም ወደ አማራ ክልል ያስገባውን ወራሪ ቡድን እስካላስወጣ ድረስ ምርኮኞቹ አይለቀቁም። እንዳስፈላጊነቱም ከዚህም የከፋ እርምጃ እንደምንወስድ ማሳሰብ እንፈልጋለን ።
👉 3:- ለኦሮሞ ህዝብ የምናስተላልፈው ጥሪ ይኸው ፋሽስት ና አምባገነኑ አብይ አህመድ ለራሱ ስልጣን ማስጠበቂያ ሲል ምስኪን የኦሮሞ ወጣቶችን እየማገደ በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ይህንን አውቆ ልጆቹን ከአጉል እልቂት እንዲታደጋቸው ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

ፋኖ ይችላል 😂💪
ወደ አዱ ገነት እየመጣ ነው😂💪💪

27/08/2023

ሰበር ደብረ ማርቆስ!
የበላይ ትውልድ ላይመለስ ተነስቷል ውጊያው እንደቀጠለ ነው! አብዛኛው የከተማዋ ክፍል በፋኖ ቁጥጥር ሆናለች
አድማ በታኝ የሚባል የአማራ ካድሬ በህዝቡ ላይ እየተኮሰ ነው
ቤተሰብ ያላቸው ደውሎ ይንገራቸው የኦነግ ሰራዊት መሸነፉን አምኖ ከባድ መሳሪያ ወደ መኗሪያ ሰፈሮች እየተኮሰ ነው

የበላይ ትንፋሽ! ቀጥቅጠው!

25/08/2023

ሰበር ዜና! ደብረ ማርቆስ! ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው!

22/08/2023

ጎጃም!

ከደጀን እስከ አምበር የማርቆስ መስመር ተዘግቷል ከባድ ውጥረት ውስጥ ይገኛል፡፡ ጀምር በለው ለብልበው አምሐራዬ!

13/08/2023

ሰበር ዜና!

በፍኖተ ሰላም ንፁሀንን በድሮን ያስጨፈጨፈው የአብይ ተላላኪ ካድሬ አስተኳሽ ተሸኝቷል!
ወጥር አምሐራዬ በየጎሬው የተወሸቁ ካድሬዎች መፅዳት አለባቸው፡፡

  ባህርዳር ከተማ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል።አባይ ድልድይ ሻሁር እየወሰዱ የነበሩ ሦስት ወጣቶችን ተኩሰው ገደሉ። አባይ ወንዝም እንደ እንጨት እያግተለተለ ወስዷቸዋል።  አንድ ከመራዊ የመጣ አባት ...
12/08/2023

ባህርዳር ከተማ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል።አባይ ድልድይ ሻሁር እየወሰዱ የነበሩ ሦስት ወጣቶችን ተኩሰው ገደሉ። አባይ ወንዝም እንደ እንጨት እያግተለተለ ወስዷቸዋል። አንድ ከመራዊ የመጣ አባት ቀበሌ 14 ላይ የ4 ዓመት ህፃን ልጁ ተገድሎ አባትዬው አቅፎ "ልጄን፥ ልጄን" እያለ እያለቀሰ ሲዞር ውሏል። አባይ ማዶ ሰማዕታት ፊት ለፊት አንዲት መጫትን በእንጨት አልጋ ይዘው የሚሄዱ ሰዎች በአደባባይ ተረሽነዋል። ተሸካሚዎች አራቱ፣ መጫቷንና ገና ከተወለደ አንድ ቀን የማይሞላውን ጨቅላ ተገድለዋል። እዛው አባይ ማዶ አየር ጤና አካባቢ ሁለት ወጣቶችን ድንጋይ አንሱ በማለት ደረታቸው በጥይት ተመትቶ ተገድለዋል። ቀበሌ 3 ሊስትሮ ይሰራ የነበረ ሙስሊም ሰውየ ለአራት ልጆቹ ደረቅ እንጀራ ፍለጋ ላስቲክ ይዞ እንደወጣ ገድለውታል።

የተባበሩት ስጦታ ሥጋ ቤት አካባቢ አንድ ሰውየ ይገደላል። ልጅ ያዘለች ሚስቱ እየጮኸች ስትሄድ እሷንም ገደሏት። ህፃን ልጃቸው እየሮጠ ሲመጣ እሱንም ደገሙት። አስክሬኑ ሲነሳ የታዘለው ህፃን እስትንፋሱ አለ። አልሞተም። በተመሳሳይ በተለምዶ ዲፖ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ አባት የህፃን ልጁን ይዞ ሲሄድ ህፃኑንና አባትዬውን ተኩሰው ገድለዋቸዋል።
ወጣቶች ለማንሳት እየሮጡ ሲሄዱ ተኩሰውባቸው ሬሳው ሳይነሳ ውሏል።

የሆራይዞን ትምህርት ቤት ባለቤት የሆነውን የ26 ዓመት ልጁን ልደታ ሰፈር ከቤት ገብተው እረሽነውታል። እዛው ልደታ ሰፈር የቤት ለቤት እረሸና ተፈጽሟል። አንድ ሰውየን ከውጭ አንበርክከው ከውስጥ ያለችውን ሚስቱን ደፍረዋታል። ቤት ለቤት በሚያደርጉት ፍተሻ ከአንገት ሀብል እየበጠሱ፣ ሞባይልና ላብቶፖ እየቀሙ ወስደዋል። ምንም የማያውቁ የቆሎ ተማሪዎች ተገድለዋል። ባጠቃላይ ከትጥቁ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ከ700 በላይ ንፁሐን ተጨፍጭፈዋል። ልደታ ማርያም ከ54 በላይ፣ አቡነ ሐራ ቤተክርስቲያን ከ46 በላይ፣ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከ36 በላይ ሰዎች ያሉበት የጅምላ መቃብር ተፈጽሟል።

እርምጃ ተወስዶባቸው በደም የተበከሉና ዝንጥልጥላቸው የወጣ አስክሬኖች በመስቀለኛ መንገዶች ላይ፣ በዋና አውራ ጎጃናዎች ላይ፣ እቤቶች አጠገብ ላይ ተጥለው የሬሳ ኤግዚቪሽን ታይቷል። የህዝቡን ስነልቦና ለመጉዳት ሬሳ ሳይነሳ ሦስትና አራት ቀን ቆይቷል። ባጠቃላይ
በባህርዳር የተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ እና እጅግ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት (grave violation of human rights) ለዐማራ ከልክ በላይ ያላቸውን ጥላቻ ያሳዩበት ነው። አሁንም ግድያው አልቆመም። ሰዎች እየተገደሉ የትም እየተጣሉ ናቸው። በየጥሻው፣ በየበቆሎው ተገድሎ የተጣለ ሬሳ እየተገኘ ነው። ባህርዳር የሚታየው ነጠላውን ዘቅዝቆ ለቅሶ ለመድረስ የሚመርመሰመስ ሰው ነው። አንድ ሰው በቀን ቢያንስ በእግሩ ከአራት እና ከአምስት በላይ ለቅሶ ቤት ይደርሳል። በየቦታው ሀዘን ነው። በየቦታው መከፋት ነው።

አሁንም ከሰኞ ጀምረን ቤት ለቤት ፍተሻ እናደርጋለን እያሉ ናቸው። አሁንም ንፁሐን ይገደላሉ። ንብረት ይዘረፋል። ሴቶች ይደፈራሉ። "በለው" ነው። "ተኩሰበት" ነው። አንድ ወታደር ርችት እንደመተኮስ ያህል ጥይት ተኩሶ ንፁሐንን ያጋድማል። ተጠያቂ የለም፤ ጠያቂም የለም።

እንዲህ ያሉ ግፎች እንዳይዘገቡ ኔትወርክ ተዝግቷል። ይህን የምንጽፈው በሞት ቀለበት ውስጥ ሆነን ነው። ከህዝባችን የሚበልጥ የለም በሚል ነው። መረጃውን በቲዊተር፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክና በምታገኙት አጋጣሚ እንድታሰራጩ እጠይቃለሁ።

ታደለ ጥበቡ

ዋሽንግተን ፖስት ፋኖን አሸባሪ የሚያስብለው በፋኖ የተፈፀመ ድርጊት አለማገኘቱን ዘገበ። ዋሽንግተን ፖስት ወርለድ ኒውስ፣ ጆርዳን ጋዜጣ የህንዱ ቻካር ታየምስ በተመሳሳይ ሰአት ስለፋኖ ይዘውት...
11/08/2023

ዋሽንግተን ፖስት ፋኖን አሸባሪ የሚያስብለው በፋኖ የተፈፀመ ድርጊት አለማገኘቱን ዘገበ። ዋሽንግተን ፖስት ወርለድ ኒውስ፣ ጆርዳን ጋዜጣ የህንዱ ቻካር ታየምስ በተመሳሳይ ሰአት ስለፋኖ ይዘውት ባወጡት ዘገባ ላይ ታጣቂዎቹ በውጊያ ስምሪት ላይ ሆነው በነሱ የተደፈረ እንስት፣ የተዘረፈ ሀብት በግፍ የተገደለ ንፁሀን፣ በሙርኮ ላይ ያለ ወታደር እራሱ እንዳላገኙ ነው የዘገቡት።

በተለይ ጆርዳን ጋዜጣ ይዞት በወጣው ሀተታው ፋኖ በሽምቅ ተዋጊነት ራሱን ያጎለበት ባለው ህዝባዊ ወገንተኝነት ነው ብሏል።

ዋሽንግተን ፖስት በበኩሉ ፋኖ አደገኛ የማጥቃት አቅም እንዳለው ዘግቦ ቡድኑ በሰሞውኑን ያደረገው ውጊያ የአቅም መፈታተሽን ለማወቅና ያለበትን የመሳሪያ ችግር ለመሟላት እንጅ የጨበጣ ውጊያ አለማድረጉን ነው የዘገው። ጋዜጣው አክሎም መንግስት ፋኖን ደመሰስኩ ቡልም በመንግስት የተገደለ የፋኖው ቁጥር ለድምሰሳ አይበቃም ብሏል። በተቃራኒው ፋኖ የገደላቸውና የማረካቸውን የመንግስት ሀይሎች ብዙ መሆናቸውን ነው የዘገበው።

ብልፅግና ግን ይችን ሀቅ ክዶ ተበተነ ይለናል። የአለማቀፍ መርማሪ ጋዜጠኛች ግን እንዲህ እራቁቱን ያስቀሩታል። ይህ አንዱ የሰሞውኑን የዘመቻ ውጤት ነው።

ሱሌማን አብደላ

የድል ዜና…! "…የፋሽስቱ አፓርታይድ የአረመኔው የዳንኤል ክብረት እና የአቢይ አሕመድ ጃውሳ ብሎ የዘር ማጥፍያ ታፔላ የለጠፈበትን የዐማራ ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ዛሬ ወደ ብቸና ገብቶ ጠዋት ላይ ...
10/08/2023

የድል ዜና…!

"…የፋሽስቱ አፓርታይድ የአረመኔው የዳንኤል ክብረት እና የአቢይ አሕመድ ጃውሳ ብሎ የዘር ማጥፍያ ታፔላ የለጠፈበትን የዐማራ ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ዛሬ ወደ ብቸና ገብቶ ጠዋት ላይ ከተማ መደብደብ የጀመረው ፈሪ ሽንታም ቦቁባቃ የጆላ ኦሮሙማ ጦር በብቸና ከተማ 10 ንጹሐን በቤታቸው እንዳሉ የተገደሉ ሲሆን የበላይ ዘለቀ ልጆች የሶማ በረሃ አናብስቶቹ በቆረጣ ገብተው እንዳይሆን አድርገው አበለሻሽተውት ከምረውት በታትነውታል።

"…መከላከያው ከዋና ማዘዣው እንዴት በፋኖ በገበሬ ጦር ትፈታላችሁ በማለት ተጨማሪ ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ጦር መጥቶለት ሬሳና ቁስለኞቹን ይዞ ወደ ደብረወርቅ ጉዞ ጀምረው የነበረ ቢሆንም ደብረወርቅም እንዲሁ ትንታጉ የዐማራ ፋኖ እሳት ልሶ ነው የጠበቃቸው። አሁን በዚህ ሰዓት የጉባዬ በርሀ ላይ ገጥመው ይሸካሸኩ ጀምረዋል። ብቸናም ተመልሶ በፋኖ እጅ ገብቷል።

"…በሌላ ዜና ዛሬ በተደረገው ውጊያ የእነማይ እና የሸበል በረንታ ፋኖዎች ጥምረት ፈጥረቅ በጥቂት ፋኖ መስዋእትነት ከ2ሺ በላይ የኦነግ መከላከያ ዱቄት በማድረግ ከጥቅም ውጪ አድርገዋል። ኔትወርክ ሲከፈት ጉድ ለማየት ተዘጋጁ። በጎጃም ዛሬ ውሎው ይህን ይመስላል። ለዘመናት በዐማራ ላይ እንደመርግ የተጫነው ብአዴን በዐማራ ክልል ያውም በጎጃም ግብአተ መሬቱ ተጠናቋል።

"…ቶማስ ጃጀው፣ ጌትነት አልማው፣ ስዩም ተሾመ፣ ዳንኤል ክብረት ዐማራን መሳደብ ማቆማቸው ፌር አይደለም። ለዐማራ የእነዚህ ሰዎች ስድብ ልክ እንደ አበራታች ዕጽ ነው። ማን ክፉ ነው የመከረብን በማርያም። ቲሽ… 😂😂

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለዐማራ ሕዝብ…!

ከዘመድሁን

Address

Debre Mark'os
ABRIHAM

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጊዎን አምሐራ የትግል አርማ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share