የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት, Government Organization, Ethiopia, Amhara rigion, East Gojjam zone, Debre Mark'os.

ለዘንድሮ ተፈተኝ ተማሪዎች መልካም የፈተና ጊዜ!!! መልካም ውጤት እንመኛለን።
14/05/2016

ለዘንድሮ ተፈተኝ ተማሪዎች መልካም የፈተና ጊዜ!!! መልካም ውጤት እንመኛለን።

13/05/2016
13/05/2016

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) የዋጋ ግምታቸው 908 ሺህ 640 ብር የሆነ የተለያዩ መድሃኒቶች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሞያሌ ላይ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የሞያሌ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጀ አቶ ጫንያለ...

13/05/2016

New WHO recommendations will speed detection and improve treatment of multidrug resistant tuberculosis (MDR-TB) through use of a new rapid diagnostic test and a shorter, cheaper treatment regimen. The novel diagnostic test, called MTBDRsl, is a DNA-based test that identifies genetic mutations in MDR...

13/05/2016

ከሳንባና ከእንቅልፍ ጋር ተያያዥ በሽታዎች ህክምና የሚሰጥ ሆስፒታል ተመረቀ

ከሳንባና ከእንቅልፍ ጋር ተያያዥ ለሆኑ በሽታዎች በአገር ውስጥ ህክምና የሚሰጥ ሆስፒታል ተመረቀ።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዘዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በ300 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባውና ''ሀሌሉያ አጠቃላይ ሆስፒታል'' በሚል የተሰየመውን ተቋም ዛሬ መርቀውታል።

ሆስፒታሉ በአገር ውስጥ በማይሰጡ አዳዲስ ህመሞች ላይ በተለይም የሳንባ፣ የኩላሊት፣ጉበት፣ ከእንቅልፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸውና የልብ ህመሞችን አዳዲስ ህክምናዎችን መስጠት እንደሚያስችል በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

በመሆኑም ባለሃብቶች በጤናው ኢንቨስትመንት ላይ መዋዕለ ነዋያቸውን ቢያፈሱ ትርፋማ ከመሆናቸውም በላይ፤ በየጊዜው ዜጎች የተሻለ ህክምና አገልግሎት ፍለጋ ወደ ውጭ የሚደረገውን እንግልትና የሃብት ብክነትን ማስቀረት እንደሚቻልም አስታውቀዋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተ ብርሃን አድማሱ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በበሽታ መከላከል ላይ ውጤታማ ስራዎች ቢሰሩም፤ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ የሚፈለገውን ያህል ውጤታማ መሆን ሳይቻል መቆየቱን ተናግረዋል።

በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተደራሽነትና ጥራት ላይ ትኩረት ተደርጓል ያሉት ሚኒስትሩ እንደዚህ ዓይነት ሆስፒታሎች በተለይም ለጽኑ ህመም ህክምናዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል።

"የጤና ፖሊሲያችን በቅድመ በሽታ መከላከል ላይ ያተኮረ ቢሆንም፤ ከፍተኛ ዕውቀትና ቴክኖሎጂ በሚጠይቁ ህክምናዎች ላይ ለሚሰማሩ የግል ባለሃብቶች መንግስት የተለያዩ ማበረታቻዎችን በማድረግ ላይ ነው።"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ እንዳሉት ሆስፒታሉ የመዲናዋን ነዋሪዎች የጤና ሽፋን ተደራሽነት እንደሚያሳድገው ገልጸዋል።

በመዲናዋ ከ30 በላይ ሆስፒታሎች ያሉ ቢሆንም፤አሁንም ተጨማሪ የልዩ በሽታዎች የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንደሚያስፈልጉና አስተዳደሩ በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።

የአገሪቱና የአፍሪካና ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫዋ ከተማ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆስፒታሎች እንደሚያስፈልጓት የገለጹት ከንቲባ ድሪባ፣ መንግስት ብቁና ጤናማ የሆኑ ዜጎች እንዲፈጠሩ የጀመረውን ጥረት እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።

የሀሌሉያ አጠቃላይ ሆስፒታል ባለቤት ፕሮፌሰር ጌታቸው አደራይ እንደገለጹት ሆስፒታሉ ከ45 በላይ በሽታዎች ህክምና መስጠት እንደሚችልና 118 የመኝታ ክፍሎች እንዳሉት ገልጸዋል።

ሆስፒታሉ በቀን እስከ 400 አገልግሎት ፈላጊዎችን የማስተናገድ አቅም አለው።ለ500 ዜጎችም የስራ ዕድል ፈጥሯል።

ሆስፒታሉ በቀጣይ የኩላሊት ንቅለ ተከላና ቀዶ ጥገና፣ የመንገደኞች ክትባት፣ የቆዳ ውበት ቀዶ ጥገናና የጸጉር ንቅለ ተከላ ህክምና አገልግሎት እንደሚጀምርም ተገልጿል።

ምንጭ ኢዜአ/አዲስ አበባ ሚያዚያ 29/2008

12/05/2016

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህንዳውያኑ የ72 እና 79 አመት ጥንዶች በ46 አመት የትዳር ዘመናቸው የመጀመሪያውን ጤናማ ልጃቸውን አግኝተዋል፡፡ ...

09/05/2016
የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ የመጨረሻው ምዕራፍ የህዝብ ንቅናቄ  መድረክ የአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ!       ♣♣♣♣♣♣♣♣♣የአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የክልል፣የዞን፣ ...
08/05/2016

የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ የመጨረሻው ምዕራፍ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ የአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ!
♣♣♣♣♣♣♣♣♣
የአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የክልል፣የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የኮሚኒኬሽና ሚዲያ አመራሮች እና የልዩ ልዩ አደረጃጀት መሪዎች በተገኙበት ሚያዚያ 29 ቀን 2008 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ የመጨረሻው ምዕራፍ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ። የኤች.አይ.ቪ /ኤድስ ወረርሽኝ በዓለም ከተከሰተበት እ.ኤ.አ 1982 ጀምሮ በሽታውን ለመከላከል በርካታ ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን አበረታች ውጤትም ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ በ2007 ዓ.ም የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ከ39 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኤች.አይ.ቪ ምክንያት ህይወታቸውን ሲያጡ በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን 36.9 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ውስጥ ሲገኝ ከእነዚህ ውስጥ ከ71% በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች የሚኖሩ ናቸው። በሀገራችን በ2008 ዓ.ም ጥምር የኤች.አይ.ቪ /ኤድስ ትምበያ 748,933 ሰዎች ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ሲሆን በክልላችን ደግሞ 187,173 ሰዎች እንዳሉ ይገመታል።
በአሁኑ ሰዓት በአገር አቀፍ ደረጃ የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ስርጭት መጠን 1.2% ሲሆን በክልላችን ደግሞ 1.3% እንደ ሆነ ጥናቶች ያመላክታሉ። ወረርሽኙ በአገር አቀፍም ሆነ በክልላችን የመቀነስ አዝማሚያን የሚያሳይ ቢሆንም ስርጭቱ ከቦታ ቦታ፣በማህበረሰብና በፆታ ደረጃ እየጨመረ እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወረርሽኙ የጠፋ እሰኪመስል ከከፍተኛ እስከ ታችኛው እርከን ድረስ በሚገኘው አመራር እና በማህበረሰቡ ከፍተኛ የሆነ መዘናጋትና መቀዛቀዝ እንዲሁም የትኩረት ማነስ ችግር እንዳለ በመድረኩ በሰፊው ተገልፃል። በመሆኑም እንዲህ ዓይነቱ መዘናጋት በፍጥነት ታርሞ በየደረጃው ያለው አመራር እና ማህበረሰቡ እጅ እና ጓንት ሆኖ በሙሉ አቅሙ በክልሉ ሁሉን አቀፍ ስራዎችን ካልሰራ በስተቀር ክልላችንም ሆነ የክልሉን ማህበረሰብ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል ስጋት እንዳለ በማስረጃና ካለንበት ነባራዊ ሁኔታዎች አንፃር በመድረኩ ተሳታፊዎች ሰፊ ትንታኔ ቀርቧል። በዋነኛነት በት/ት ተቋማት በተለይ በከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ፣ በሺሻና ጫት ቤቶች፣ ዳንኪራ ቤቶች እና በልማት ኮሪደሮች አካባቢ በትኩረት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የግንዛቤ ፈጠራ ስራና የቁጥጥር ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ #የአብክመ #ጤና #ጥበቃ #ቢሮ አሳስቧል። ሌላው ቢሮው የመጨረሻው ምዕራፍ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ህዝባዊ ንቅናቄ አስፈላጊነት በተመለከተ አላማ ያደረጋቸው ጉዳዮች፡-
1ኛ. የኤች.አይ.ቪ ስርጭት መጠን ተመልሶ ሊያገረሽ በሚችል ደረጃ መሆኑ፣
2ኛ. ከልማት እንቅስቃሴዎች ጋር ተያይዞ የተጋላጭነት ክስተቶች መኖር፣
3ኛ. ትኩረት የሚሹ የህ/ሰብ ክፍሎችን በፍጥነት ለመድረስ በየደረጃው የሚገኘውን አመራርና ማህ/ሰብ ቅንጅት የሚጠይቅ መሆኑ፣
4ኛ. ኤድስን የመግታት አገራዊ ራዕያችንን እውን ማድረግ ወደ ሚያስችለን ምዕራፍ ለመሸጋገር በስትራቴጂክ ዕቅዱ የተቀመጡ ግቦችን መድረስ ወሳኝ መሆኑ፣
5ኛ. የፀረ-ኤች.አይ.ቪ ዘርፈ ብዙ ምላሽ በየደረጃው መቀዛቀዝና በሚፈለገው መጠን ያለማከናወን እና በተቋማት አመራሮች በባለቤትነት ወስዶ ከመምራት አንፃር የሚታዬ ክፍተቶች መኖር፣
6ኛ. በአመራር ደረጃ በተወሰኑ ሴክተሮች የፀረ-ኤች.አይ.ቪ /ኤድስ ፕሮግራምን እንደ መደበኛ ስራ ከማቀድ ይልቅ የተነጠለ ዕቅድ እና የጤናው ሴክተር ብቻ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ መታየቱ፣
7ኛ. ሴክተሮች ለፀረ-ኤች.አይ.ቪ /ኤድስ ፕሮግራም 2% አለመመደብ፣ የመደቡትም ቢሆን በአግባቡ ፕሮግራሙን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አለመስጠት፣
8ኛ. ስራውን በተደራቢነት ለአንድ ባለሙያ መስጠት፣ የተመደበው ሰራተኛም በአፈፃፀም የማይገመገምበት፣ በውጤት የማይለካበት በመሆኑ ትኩረት የተነፈገው በመሆኑ ምክንያት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ማዘጋጀት አስፈልጓል ይላል ለመድረኩ ተሳታፊዎች የተበተነው በራሪ ወረቀት። በአጠቃላይ በሀገራችን በተደረገው እልህ አስጨራሽ ጥረት በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የመከላከል ስራ የመጣው ለውጥ አበረታች ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ዝምታው ከበረታ የኤች.አይ.ቪ ውረርሽኝ ግርሻ መምጣቱ አይቀርም፤ ስለዚህ እንደ ሀገራችን አቆጣጠር በ2023 ዓ.ም ከኤድስ ነፃ የሆነ ትውልድ ( ) የመፍጠር ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የመጨረሻው ምዕራፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የህዝብ ንቅናቄ ማካሄድ አግባብነት ያለው ሲሆን የመጨረሻው የተባለበት ሀገራችን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ወረርሽኝን እና ሞት የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ የሚሰራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በማቋቋም ጭምር መጠነ ሰፊ የዘርፈ ብዙ ምላሽ አገለግሎት ስትሰጥ የቆየች ሲሆን በወቅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱን ለማቋቋም ምክንያት የነበረውን ወረርሽኝ መቀልበስ የተቻለ በመሆኑና ችግሩ የጤና ችግር በመሆኑ የጤናው ሴክተር በባለቤትነት በመያዝ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የማሀበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤውን እና የፀረ- ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ህክምና (ክሊኒካል) አገልግሎቶችን በማቀናጀት የዘርፈ ብዙ ምላሽ አገለግሎቱን አጠናክሮ መምራት በማስፈለጉ ቀደም ሲል በማስተባበሪያ ጽ/ቤትነት ያገለግል የነበረውን ተቋም ወደ ጤና ጥበቃ ማዋሃድ አስፈላጊ በመሆኑ አደረጃጀቱ በአዲስ መልክ ተስተካክሎ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዘርፈ ብዙ ምላሽ አገልግሎት በሚል መደራጀቱን የአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ በእለቱ ለነበሩ ተሳታፊዎች የገለፀ ሲሆን መላ ህ/ሰቡ፣ የእምነት ተቋማት በየቤተ እምነታቸው፣ በየደረጃው ያሉ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች በጎ አድራጎት ማህበራት፣ በየአካባቢው እና በየደረጃው የሚገኙ የኤድስ ም/ቤቶችና የቦርድ አደረጃጀቶች፣ የወጣትና ሴት አደረጃጀቶች የከፍተኛ ት/ት ተቋማት አመራሮችና ተማሪዎች፣ሁሉም የመንግስት ሴክተር መ/ቤቶች እና
የየአካባቢው የኮሚኒኬሽንና ሚኒሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች እንደ የአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ የችግሩን አሳሳቢነት ከልብ ዋጋ በመስጠት መላ ህዝቡን የማንቃትና ግንዛቤ የማስጨበጥ የንቅናቄ መድረክ ማዘጋጀት እና በየአካባቢው ከሚገኘው ነዋሪ ማህበረሰብ ጋር መገባባት እንደሚገባ በክልል ደረጃ በተዘጋጀው መድረክ የጋራ መግባባት የተደረሰበት ሲሆን በተለይ በንቅናቄው ወቅት #ሶስት ጉዳዮችን ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ በመድረኩ ለማስገንዘብ ተሞክሯል #የመጀመሪያው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ህ/ሰብን የማንቃት፣የማስተማርና የማስገንዘብ ስራ በትኩረት መስራት፣ #ሁለተኛው የተቋማት ሜንስትሪሚንግና ዕቅድ በተመለከተ ከይስሙላ ወጥቶ ከልብ ተግባራዊ መድረግ እና #ሶስተኛው ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ለሚገኝ ወገኖች ሁሉን አቀፍ የድጋፍና ክብካቤ ስራ አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ተገልጿል። በመጨረሻም የጤናው ሴክተር አሁን ያለበትን የኤች.አይ.ቪ መመርመሪያ ኪት እጥረት በመፍታት ትኩረት የሚሹ ተጋላጭ የህ/ሰብ ክፍሎችን ቢያንስ 90% በመድረስ መመርመር፣ ተመርምረው የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው መኖሩ የተረጋገጠ የህ/ሰብ ክፍሎቹን ቢያንስ 90% የሚሆኑትን የፀረ-ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ህክምና እንዲጀምሩ ማስቻል እና የፀረ- ኤች አይቪ/ኤድስ ህክምና እየተከታተሉ ያሉ ወገኖችን የመድሀኒት አዎሳሰድና ክትትል በማሻሻል ቢያንስ 90% የሚሆኑትን በደማቸው ውስጥ ያለውን የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መጠን ያለም ጤና ድርጅት ያስቀመጠውን የመጠን ስታንዳርድ ላይ ማድረስና በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክንያት የሚሞቱ ወገኖችን ቁጥር መቀነስ እና ሌላው ከእናት ወደ ልጅ በፅንስ ወቅት፣ በወሊድ ጊዜና በጡት ማጥባት ወቅት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የመተላለፊያ መንገዶችን 100% የመከላከል ስራው ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ቢሮው ለተሳታፊዎች በማሳሰብ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።
✍✍✍✍✍✍✍✍

06/05/2016
06/05/2016

Address

Ethiopia, Amhara Rigion, East Gojjam Zone
Debre Mark'os

Telephone

0587714019/0838

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share