ANRS North Shoa Zone Administration የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር

ANRS North Shoa Zone Administration      የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር North Shoa Zone Administration የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መካሻ አለማየሁ በሾላ ገበያ ምርጫ ክልል በቡልጋ ምርጫ ጣቢያ ድምፃቸውን ሰጡ።
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መካሻ አለማየሁ በሾላ ገበያ ምርጫ ክልል በቡልጋ ምርጫ ጣቢያ ድምፃቸውን ሰጡ።

 ጥልቅ የሀዘን መግለጫየእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ 10 አለቃ ተ/አረጋይ ጌታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ።10 አለቀ ተ/አረጋይ ጌታቸው ባለትዳር ...
27/05/2026


ጥልቅ የሀዘን መግለጫ

የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ 10 አለቃ ተ/አረጋይ ጌታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ።

10 አለቀ ተ/አረጋይ ጌታቸው ባለትዳር እና የአንድ ሴትና የአራት ወንድ አባት ነበሩ ።

10 አለቃ ተ/አረጋይ በ1990--1993 በኢትዮ-ኤርትራ ዘምተው ለሀገር መፅዋት የከፈሉና በቦርድ የተሰናበቱ፣ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2016 ዓ/ም በደብረብርሃን ከተማ ህዝባዊ ሚሊሻነት ህዝብን ያገለገሉ ናቸው።

በ2013-2014 ዓ/ም ሀገር ችግር ውስጥ በገጠማት ወቅት በሰሜኑ ጦርነት ከ4 ጊዜ በላይ የሰላም አስከባሪና ሚሊሻን ይዘው በጀግንነት ተዋግተዋል።

ከ25/01/2016 ዓ/ም የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ሰላም አስከባሪ ባለሙያ ሆኖ ያገለገለ።
ከ05/10/2016ዓ/ም የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የሚሊሻ ጽ/ቤት ፀጥታ ስምሪት ቡድን መሪ ሆኖ የሰራ።

ከ16/11/2017ዓ/ም አስከ ህይወታቸው እስከ አለፈበት ሰዓት ድረስ የህዝብን አደራ ተወጥተዋል ።

እንደ አንድ የህዝብ አደራ እንደተቀበለ አመራር እና እንደ ተወላጅ ከተማዋ የሚገባትን እድገትና ማዕረግ እንድታገኝ እንዲሁም ነዋሪዎቿ ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ በከፍተኛ ቁጭት እየሰሩ የሚገኙ ወጣት አመራር ነበሩ ።

10 አለቃ ተ/አረጋይ ጌታቸው ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን ፤ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ከልብ እንመኛለን።

በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6 ስዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የስርአተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።
ዘገባው የእቴጌ ጣይቱ ክፍለከተማ ነው

🌙✨ እንኳን ለ1447 ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ✨🌙=============//===============       አቶ ግዛቸው ነገሠ የሰሜን ሸዋ ዞን ጽ/ቤት ኃ...
26/05/2026

🌙✨ እንኳን ለ1447 ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ✨🌙
=============//===============

አቶ ግዛቸው ነገሠ የሰሜን ሸዋ ዞን ጽ/ቤት ኃላፊ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የ1447 ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የሰላም፣ የደስታ እና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን ከልብ የመነጨ መልካም ምኞታቸውኖ ገልፀዋል።

ኢድ ሙባረክ! 🌙✨

የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ ሰዓዳ ኢብራሂም የ1447 ኛውን አረፋ በዓል አስመልክቶ መልእክት አስተላልፈዋል።ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ  እ...
26/05/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ ሰዓዳ ኢብራሂም የ1447 ኛውን አረፋ በዓል አስመልክቶ መልእክት አስተላልፈዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ ታላቁ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!አደረሰን!!🌙

የአረፋ በዓል መነሻ ታሪክ ከነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) እና ከልጃቸው ነቢዩ እስማዔል ፍጹም የፈጣሪ ታዛዥነት ገድል ጋር የተቆራኘ ነው። ይህ በዓል ማህበራዊ ፍቅርና አንድነት በተግባር የሚታይበት፣በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሐጅ ተጓዦች በዓረፋ ተራራ ላይ ያለምንም የዘር፣ የቋንቋ እና የሀብት ልዩነት በነጭ የ“ኢህራም” ልብስ ደምቀው የሰው ልጅ በፈጣሪ ፊት እኩል መሆኑን የሚያረጋግጡበት ታላቅ ቀን ነው።

በተጨማሪም በበዓሉ የሚታረደው የኡድሒያ መስዋዕት ለምስኪኖች፣ ለዘመድ/ጎረቤት እና ለቤተሰብ በሶስት እኩል ቦታ ተከፍሎ በመሰጠት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከራስ ወዳድነት ወጥቶ ለሌሎች የሚያስብበት የፍቅርና የአብሮነት መገለጫ ነው።
በድምቀት የሚከበረውን ይህንን በዓል ስናከብር ምስኪኖችን በማሰብ፣ ያለንን ለሌላቸው በማካፈልና አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን ይገባል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የአንድነትና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ።
በድጋሜ መልካም የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል! እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!! ሲሉ ወይዘሮ ሰዓዳ የመልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ የ 1447 ኛዉ የአረፋ በዓል አስመልክቶ መልእክት አስተላልፈዋል።ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወንድም እና እህቶቼ...
26/05/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ የ 1447 ኛዉ የአረፋ በዓል አስመልክቶ መልእክት አስተላልፈዋል።

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወንድም እና እህቶቼ እንኳን ለ1447ኛዉ አመተ ሂጅራ የኢድአል አድሀ አረፋ በአል እንኳን አደረሳችሁ::

ኢድ አል-አድሀ የትዕግሥት፣ የመስዋዕትነት፣የመተሳሰብ እሴቶችን የምናስታውስበት የክብር በዓል ነው።

ይህ በዓል በሁላችንም ልብ ውስጥ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን እና በጎ ፈቃድን የምናሳይበትና ያየንበት የእዝነትና የምህረት በአል ነው።

ኢድ ሙባረክ!
መልካም ባዓል ሲሉ አቶ ኤልያስ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን አስተላልፈዋል

🌙 እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ! 🌙ይህ ታላቅ የእምነት፣ የመስዋዕትነት፣ የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል በሁላችን ልብ ውስጥ ሰላም፣ አንድነት፣ ይ...
26/05/2026

🌙 እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ! 🌙

ይህ ታላቅ የእምነት፣ የመስዋዕትነት፣ የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል በሁላችን ልብ ውስጥ ሰላም፣ አንድነት፣ ይቅርታና ቸርነትን ያጠናክርልን።
በዚህ የኢድ በዓል ቤታችሁ በደስታ፣ ህይወታችሁ በበረከት፣ ሀገራችንም በሰላምና በፍቅር እንድትሞላ እመኛለሁ።
አቶ መካሻ አለማየሁ የሰሜን ሸዋ ዞን
ዋናአስተዳዳሪ

🕌 ኢድ ሙባረክ!
🌙 መልካም የኢድ አልድሃ በዓል!

"የባህር በር ጥያቄ የቅንጦት አይደለም፤ የታሪክና የህልውና ጥያቄያችን እንጂ!" ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ​ብልፅግና ፓርቲ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌትነት እናሸጋግራለን" በሚል መሪ ...
26/05/2026

"የባህር በር ጥያቄ የቅንጦት አይደለም፤ የታሪክና የህልውና ጥያቄያችን እንጂ!" ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ

​ብልፅግና ፓርቲ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌትነት እናሸጋግራለን" በሚል መሪ ቃል በባሕር ዳር ከተማ ደማቅ የድጋፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር አካሂዷል።

​በመርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፤ ብልፅግና ፓርቲ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የጀመራቸውን የልማትና የሪፎርም ስራዎች ይበልጥ ለማጠናከርና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

​ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም፣ የአንድ ሀገር እድገትና የሕዝብ ብልፅግና ሙሉ ሊሆን የሚችለው የሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም ሲከበር መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም መሠረት፣ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ወቅቱ የሚጠይቀው አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ መንግስት ይህንን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ፣ በጋራ የማልማት መርህ እና በዲፕሎማሲያዊ ድርድር ምላሽ እንዲያገኝ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

​የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የቅንጦት ወይም የፖለቲካ ፍላጎት ሳይሆን፣ የሕዝቡ የህልውና፣ የኢኮኖሚ ነፃነት እና ታሪካዊ ጥያቄ መሆኑን ያነሱት ርእሰ መስተዳደሩ፤ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበርና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ፓርቲያቸው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

​በመጨረሻም፣ "ያጋጠሙንን ፈተናዎች በጽናት በመሻገር የተጀመሩ የሪፎርም እና የልማት ስራዎችን በላቀ ፍጥነት በማስቀጠል፣ የሕዝባችንን የብልፅግና ጉዞ እውን ለማድረግ ፓርቲያችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በትጋት እየሰራ ይገኛል" በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

በድጋፍ ሰልፉ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኀላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

‎ብልፅግናን ይምረጡ!
‎ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብረሃን ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ።ኢትዮጲያን ወደተምሳሌት ሀገር!!
26/05/2026

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብረሃን ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ።
ኢትዮጲያን ወደተምሳሌት ሀገር!!

26/05/2026

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ሲካሄድ፦

ከሲያደብርና ዋዩ ወረዳ አስተዳደር የተሰጠ የሀዘን መግለጫበሲያደብርና ዋዩ ወረዳ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ  ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ የኋሉ በልሁ በድንገተኛ ሕይወታቸው ማለፉን ስንሰ...
24/05/2026

ከሲያደብርና ዋዩ ወረዳ አስተዳደር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ የኋሉ በልሁ በድንገተኛ ሕይወታቸው ማለፉን ስንሰማ የተሰማን ኃዘን እጅግ ጥልቅና መራራ ነው።

አቶ የኋሉ በልሁ በሥራ ዘመናቸው የወረዳችንን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር፣ የሕዝባችንን ደኅንነት ለመጠበቅና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሌሊት ከቀን በቁርጠኝነትና በታማኝነት ያገለገሉ ታታሪ መሪ ነበሩ።

በሥራቸው ባሳዩት መልካም ሥነ-ምግባር፣ ለሕዝብ ባላቸው ተቆርቋሪነትና በውስብስብ ሁኔታዎች ውስጥ በነበራቸው የማስተማርና የማስታረቅ ብቃት በሥራ ባልደረቦቻቸውና በወረዳው ማኅበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ፍቅርና አክብሮት ያተረፉ ውድ የሕዝብ ልጅ ነበሩ።

ይህ ድንገተኛና አሰቃቂ ክስተት የወረዳችንን አስተዳደር ብቻ ሳይሆን መላውን የአካባቢያችንን ማኅበረሰብ ከፍተኛ ሐዘን ላይ ጥሏል። እርሳቸው በትጋት የገነቡትና የታገሉለት የሰላም ስምሪት ምንጊዜም በታሪክ ሲታወስ ይኖራል።

በዚህ አስቸጋሪና መራራ የሐዘን ወቅት ለባለቤታቸው፣ ለልጆቻቸው፣ ለቅርብ ቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ሕዝብ መጽናናትንና ብርታትን ይስጥልን።

የአቶ የኋሉ በልሁ መልካም ሥራና ታሪክ ሁሌም በልባችን ሕያው ሆኖ ይኖራል!

ፈጣሪ ነፍስህን በገነት ያኑርልን!
መረጃው፦ የሲያደብርና ዋዩ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው

Address

Debre Birhan

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS North Shoa Zone Administration የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share