ሰ/ሸዋ ዞን ኀ/ስ/ማ/ማ/ተ/ጽ/ቤት North Showa Zone cooperative promotion office

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • ሰ/ሸዋ ዞን ኀ/ስ/ማ/ማ/ተ/ጽ/ቤት North Showa Zone cooperative promotion office

ሰ/ሸዋ ዞን ኀ/ስ/ማ/ማ/ተ/ጽ/ቤት North Showa Zone cooperative promotion office ኀ/ስራ ማህበራትን ከማደራጀት ባሻገር
Beyond Organizing ኀ/ስራ ማህበራትን ከማደራጀት ባሻገር

28/05/2026
27/05/2026
23/05/2026
20/05/2026
19/05/2026
የፌደራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌትነት ታደሰ በደብረ ብርሃን ከተማ ተገኝተው የወደራ ዩኒየን የስራ እንቅስቃሴን ተመለከቱ።ግንቦት/10/2018የፌደራል ህብረት ሥራ ኮምሽን ዋና ኮ...
18/05/2026

የፌደራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌትነት ታደሰ በደብረ ብርሃን ከተማ ተገኝተው የወደራ ዩኒየን የስራ እንቅስቃሴን ተመለከቱ።
ግንቦት/10/2018
የፌደራል ህብረት ሥራ ኮምሽን ዋና ኮምሽነር ክቡር አቶ ጌትነት ታደሰ በሰሜን ሸዋ ዞን ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ተገኝተው ሥራዎችን ተመለከቱ፡፡የዩኔኑ አጠቃላይ አወቃቀር ትልቅ እና መሰረቱም ሰፊ እንደሆነ የቀረ ሲሆን የግብአት አቅርቦት፣የምርጥ ዘር ዝግጅት፣የሰብል ግብይት በተለይ ለአደጋ መከላከልና ምላሽ ዩኒየኑ ያዘጋጀውን ተከማችቶ ተመልተዋል እንዲሁም ሌሎችም ሥራዎች ታይተዋል፡፡ኮምሽነሩ የዩኔኑን የሥራ እንቅስቃሴ አይተው በተግዳሮቶቹ ላይ በቀጣይ በመደጋገፍ የተጀመረውን ሪፎርም ተግባራዊ በማድረግ ተቋማዊ የመፈፀም ብቃቱን ለማሳደግ በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡

17/05/2026
11/05/2026

የህግና ሬጉላቶሪ ሪፎርም፡ የጠንካራ ኀብረት ሥራ ማህበራት ምሶሶ እንደመሆኑ፣ ጠንካራ ኀብረት ሥራ ማህበራት ደግሞ በጠንካራ የህግ ማዕቀፍ ላይ የተመሰረቱ ናቸው።

የኢትዮጵያ የኀብረት ሥራ ሪፎርም ከቁጥጥር ተኮርነት ወደ አበረታች እና አሰሪ የህግ ማዕቀፍ ሽግግር እያደረገ ይገኛል።

በሪፎርሙ ተግባራዊ እየተደረጉ ካሉ አጀንዳዎች መካከል የአደረጃጀት፣ የውስጣዊ አመራር፣ የገበያ ተወዳዳሪነት፣ የፋይንስ ተደራሽነት አና የህግ እና ሬጉላቶሪ ሪፎርም ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የሬጉላቶሪ ሪፎርም የሚያተኩርባቸው ዋና ዋና ነጥቦችም፡-
- የህግ ማዕቀፍ፣ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ማዘጋጀት
- ጠንካራ እና ማሰራት የሚችል የቁጥጥር ስርዓት መገንባት፣
- እምነት የሚጣልበት እና ህግ ማስከበር የሚችል በቴክኖሎጂ የተደገፈ የቁጥጥር ስርአት መገንባት
- የአለም አቀፍ የመቆጣጠሪያ ስታንዳርዶች ከሀገር ነባራዊ ሁኔታ ጋር በመቃኘት ስራ ላይ ማዋል
- የኦዲት ሽፋንን ማሳደግ
- የኅብረት ሥራ ማህበረት የብቃትና ምዘና ስርዓት በመዘርጋት የበቁትን ማበረታት፣ ያልበቁትን እንዲጠናከሩ መስራት
- የኅብረት ሥራ ማህበራት በዲጂታል ቴክኖሎጂ መመዝገብ ፣ መሠረዝ ፣ መቆጣጠር የሬጉላቶሪ ቁልፍ ስራዎች ናቸው።

እነዚህ የህግ ማእቀፎች በአግባቡ በስራ ላይ ሲውሉም፦

- የኀብረት ሥራ የአሰራር ነፃነትን እና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን

- የገበያ ተወዳዳሪነትንና የእሴት ሰንሰለት ትስስርን

- የፋይናንስ ተደራሽነትን

- ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትንና የአባላት ጥበቃን ያጠናክራል።

በቅርቡም የኅብረት ሥራ ማሻሻያ አዋጅ የሚፀድቅ ሲሆን፣ አዋጁ ፀድቆ ወደስራ ሲገባም፣ ህጋዊ ማዕቀፍን በማሻሻል የቁጥጥር ስርዓትን ማጠናከር ከማስቻሉ ባለፈ የኀብረት ሥራ ማህበራት ዕምቅ አቅም ጎልቶ እንዲታይ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ይሆናል።

የዘመነ የኅብረት ሥራ ቁጥጥር ለዘመኑ ኅብረት ሥራ ማህበራት ወሳኝ ከመሆኑም ባሻገር፣ ሪፎርሙ ማህበራትን ከድጎማ ምርት አከፋፋይነት ወደ ኢንቨስትመንት የሚደረግ ሽግግር መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

በተጨማሪም የኅብረት ሥራን ፅንሰ ሃሳብ ከማኅበር ተኮር አገልግሎት ወደ ስራ ፈጣሪነት ማሻገር በእጅጉ አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም ማኅበራት እና ባለድርሻ አካላት ይህን ትልቅ ሃገራዊ ተልእኮ ለማሳካት ሰፊ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

Address

Debre Birhan

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰ/ሸዋ ዞን ኀ/ስ/ማ/ማ/ተ/ጽ/ቤት North Showa Zone cooperative promotion office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ሰ/ሸዋ ዞን ኀ/ስ/ማ/ማ/ተ/ጽ/ቤት North Showa Zone cooperative promotion office:

Share