የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ /North shoa zone revenues department/

የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ /North shoa zone revenues department/ this page is information site of north shoa revenues department activities.

ነሀሴ 28/2018 ዓ.ምየአንደኝነት ደረጃውን አስጠብቆ ቀጥሏልየሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በሁሉን አቀፍ ተግባራት በክልል ደረጃ ተመዝኖ እንደ አምናና ካቻምናው ሁሉ...
03/09/2026

ነሀሴ 28/2018 ዓ.ም
የአንደኝነት ደረጃውን አስጠብቆ ቀጥሏል
የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በሁሉን አቀፍ ተግባራት በክልል ደረጃ ተመዝኖ እንደ አምናና ካቻምናው ሁሉ ከክልሉ ዚኖች የ1ኛነትን ደረጃ አግኝቷል፡፡
ይህ ውጤት እንዲመጣ ከዞን እስከ ወረዳ ና ከተማ ያለው የገቢ ተቋሙ ባለሙያና አመራር ባደረገው ያላሰለሰ ጥረትና ወጥቶ ወርዶ በመስራት የመጣ ውጤት ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን የዞን የወረዳና የከተማ አመራር ትልቅ ድርሻ ነበራቸው እንዲሁም አጋርና ባለድርሻ አካላት የንግዱ ማህበረሰብ ለገቢ አሰባሰቡ ከፍተኛ አስተዋዕፃ አድረገዋል፡፡
በ2019 በጀት ዓመት ልንሰበስበው የያዝነውን 9.7 ቢሊዮን ብር እቅድ በተሸለ መነሳሳት መፈፀም የሚያስችለንጥሩ መነሻሆነ ሽልማትና እውቅናአግኝተናልሁሉንም እናመሰግናለን፡፡
ዘገባው ፡-የሰመን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የግብር ትምህርትና ኮሙንኬሽን ዋና የስራ ሂደት ነው

03/09/2026
ግብር በግፊትና በጫና ሣይሆን በመግባባትና በመተማመን ነው የሚሰበሰበው ተባለ፣ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም የዞን፣ የወረዳና ከተማ ጠቅላላ የገቢ ተቋም አመራርና ባለሙያ እንዲሁም የወረዳ፣ ከተማና...
21/08/2026

ግብር በግፊትና በጫና ሣይሆን በመግባባትና በመተማመን ነው የሚሰበሰበው ተባለ፣
ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም የዞን፣ የወረዳና ከተማ ጠቅላላ የገቢ ተቋም አመራርና ባለሙያ እንዲሁም የወረዳ፣ ከተማና የዞን አመራሮች በተገኙበት የ2019 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ትውውቅና የተደረሰበት አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ፡፡ ወ/ሮ ቀለም ተስፋዬ የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ ከባለፈው አመት 4.9 ቢሊዬን ብር ጭማሪ የተደረገበት 9.7 ቢሊዮን ብር ዕቅድ ለዞኑ ተሰጥቷል ይህንንም ለወረዳና ከተማ ክፍፍል ተደርጓል፡፡ የእቅዱ መነሻ ታሣቢዎች የ2018 ዓ.ም የቀን ገቢ ግምት ጥናት፣ የብር የመግዛት አቅም መጋሸብን፣ የእርሻ ግብር በአዲስ አዋጅ የተሻሻለ በመሆኑ፤ የከተማ አገልግሎት ገቢ የተሻሻለ ደንብ መውጣቱ፣ ሃገራዊ የደመወዝ ጭማሪ በ2018 የስራ ግብሩ ያልተሰበሰበ በመሆኑ፤ አዲስ ነጋዴዎች መጠናታቸው እና አመራሩ የገቢ ስራን በትኩረት እየሰራ በመሆኑ ዞኑ 9.7 ቢሊዬን ብር መሰብሰብ እንዳለበት ታቅዷል፡፡ ይህ እቅድ ዓላማው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡ እቅድንም ሁሉም ወረዳና ከተማ ለሚመለከታቸው ሁሉ እንድታስተዋውቁ፣ እንዲሁም ከነጋዴዎች ጋር ትልልቅ መድረክ በመፍጠር በጥናቱ ዙሪያ በመተማመን ወደ ግብር ማስከፈሉ በመግባት ለህብረተሰቡ ልማት የሚውል ሀብት እንሰብስብ፣ የታቀደውን እቅድ ተከትሎ እስከአሁን የደረጃ “ለ” እና የኪራይ ገቢ አሰባሰብ ያለው አፈፃፀም፡- የተጠኑ ነጋዴዎች 29,732፣ በሲስተም ተመዝግበዋል 28,307፣ ተወስኖ የከፈሉ ቢል የተሰጣቸው29,560፣ እስከአሁን ግብር የከፈሉ 12,369 ናቸው፣ በዚህ ገቢ አሰባሰብ አሣግርትና ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የተሻሉ ናቸው፡፡ ዝቅተኛ አፈፃፀም ላይ ያሉ ዓለም ከተማ፣ መንዝ ቀያ፣ ባሶና ወራና፣ እነዋሪ ይጠቀሣሉ ሲሉ መምሪያ ኃላፊዋ አሣውቀዋል፡፡ ወረዳና ከተሞች ያላቸውን ተሞክሮ በማቅረብና የገጠማቸውን ችግር የተወሰኑ ወረዳና ከተሞች አቅርበው በማጠቃለያው አቶ እያሱ አምባዬ የክልል የገቢ ባለሙያ በተነሱ ሃሣቦች ላይ ሲያስገነዝቡ በበጀት አመቱ የያዝነው የተለጠጠ የገቢ እቅድ ስለሆነ ለእቅዱ መሣካት የተጠናውን የቀን ገቢ ጥናት ተቀብሎ መሰብሰብ እንጂ በቅሬታ ሰበብ መቀነስ ተገቢም ትክክልም አይደለም የቀረበ ቅሬታ ሁሉ ትክክል ነው ማለት ይደለም ከአመለካከት ጋር የመጣ የህዝበኝነት ችግር እንዳለ ያመለክታል በተግባባችሁት ልክ ወደ ተግባር ግቡ ሲሉ የክልሉ ባለሙያ አስገንዝበዋል፡፡ በመጨረሻም አቶ አይነኩሉ አበበ የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሲገልፁ ግብር በግፊትና በጫና ሣይሆን በመግባባትና በመተማመን ነው የሚሰበሰበው የቀረበን ቅሬታ ፍትሃዊነትን ጠብቀን አሣማኝ የሆኑ የውስን ነጋዴ ሊቀነስ ይችላል እንጅ የቀረበውን በሙሉ መናድ ተገቢ አይደለም፡፡ የአመራር ስራ ከግብር ከፋዩ ጋር በእቅድ ላይ በመወያየት የተጠናው ጥናት በመግባባትና መተማመንን በመፍጠር ማስከፈልና ውጤት ማምጣት ነው ብለዋል አቶ አይነኩሉ
ዘገባው የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የግብር ትምህርትና ኮሙንኬሽ ዋና የስራ ሂደት

13/08/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ 2019 በጀት ዓመት በ22 ወረዳዎች ፤ በ9 ከተማ አስተዳድሮች እና በዞን መሰበሰበው የመደበኛና የከተማ አገልግሎት ገቢ እቅድ ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ ተገልፆል በዚሁ መሰረት በየደረጃው ያለ የገቢተቋሙ ባለሙያና አመራር፤ አጋር አካላት፤ በየደረጃው ያለ አመራር፤ ግብረ ከፋዮች እና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ግብር በፍትሀዊነትና በወቅቱ እንዲሰበሰብና ለአካባቢ ልማት እንዲውል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
1 ሸዋሮቢት -መደበኛ ገቢ 420,929,448 ከ/አገልግሎት 358,105,403 ድምር 779,034,851
2 መ/ ሜዳ-መደበኛ ገቢ 140,631,039 ከ/አገልግሎት 83,881,242 ድምር 224,512,281
3 ዓለምከተማ- መደበኛ ገቢ 139,477,860 ከ/አገልግሎት 112,397,320 ድምር 251,875,180
4. አጣዬ-መደበኛ ገቢ 111,127,244 ከ/አገልግሎት 117,002,985 ድምር 228,130,229
5. አረርቲ-መደበኛ 459,459,202 ከ/አገልግሎት 97,273,850 ድምር 556,733,052
6.እነዋሪ-መደበኛ 100,795,668 ከ/አገልግሎት 100,795,668 ድምር 178,624,527
7. ሞላሌ-መደበኛ 80,551,270 ከ/አገልግሎት 54,273,645 ድምር 134,824,915
8. ደብረሲና-መደበኛ 110,136,689 ከ/አገልግሎት 85,588,888 ድምር 195,725,577
9. ቡልጋ-መደበኛ 1,009,918,116 ከ/አገልግሎት 140,958,199 ድምር 1,150,876,315
10. ሀገረማሪያም-መደበኛ 167,297,802
11. አንጎለላ ጠራ -መደበኛ 304,476,831
12.ምንጃር ሸንኮራ- መደበኛ 324,384,499
13.ባሶና ወራና- መደበኛ 158,084,380
14. ጣርማበር- መደበኛ 196,335,879
15.ኤፍራታናግድም - መደበኛ 248,608,516
16. ሚዳ ወረሞ- መደበኛ 222,224,950
17.መርሃቤቴ- መደበኛ 221,427,894
18. ሞረትናጅሩ- መደበኛ 156,932,986
19. መንዝ ጌራ- መደበኛ 256,298,105
20.መንዝ ማማ-መደበኛ-183,775,586
21.አንኮበር - መደበኛ 177,652,339
22. ሞጃና ወደራ-መደበኛ 238,907,440
23. ሲያደብርና ዋዩ-መደበኛ 288,881,063
24. ቀወት- መደበኛ 224,806,094
25. አንፆኪያ-- መደበኛ 190,037,806
26.እንሳሮ --መደበኛ 1,500,139,157
27. አሳግርት--መደበኛ 130,887,048
28. በረኸት--መደበኛ 125,834,148
29. ግሼ---መደበኛ 124,985,533
30. መንዝ ቀያ--መደበኛ 134,478,432
31. መንዝ ላሎ--መደበኛ 100,610,718
32. ዞን----- መደበኛ 314,214,615
እንደ ዞን ጠቅላላ ድምር 9,691,618,748
የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የግብር ትምህርትና ኮሙንኬሽ ዋና የስራ ሂደት
ነሀሴ 07/2018 ዓ.ም

31/07/2026

የተሸሻለው የቴምብር ቀረጥ አዋጅ ቁጥር 307/2018
አዋጁን ማሻሻል ያስፈለገበት ዋና ዋና ምክንያቶች
 በሰነዶች ላይ የተጣለው የቴምብር ቀረጥ የኪነጥበብ ዕድገትንና የካፒታል ንብረት ዝውውርን ለማገዝ በሚያስችል አኳሃን እንዲሻሻል ማድረግ አሰፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት፤
 በስራ ላይ ያለው የቴምብር ቀረጥ አዋጅ ቁጥር 31 /1991 የተቀመጠው የቴምብር ቀረጥ ማስከፈያ መጣኔ ከ27 ዓመት በላይ ያስቆጠረና በሰነዶች ላይ የሚሰበሰበው የቴምብር ቀረጥ ክፍያ ዝቅተኛ በመሆኑ ከተገልጋዮች የመክፈል አቅም ጋር የተመጣጠነ አድርጎ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
 ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ በቴብር ቀረጥ አዋጅ አስመልክቶ ማሻሻያ የተደረገባቸው አዋጆች ለአፈጻጸም እንዲያመች በዚህ ማሻሻያ አዋጅ አጠቃሎ ማውጣት በማስፈለጉ፣
 በተሻሻለው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕገ መንግስት አንቀፅ 49(3) እና 11) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
የማሻሻው አላማዎች
የቴምብር ቀረጥ አዋጅ ማሻሻያ የሚከተሉት አራት አላማዎች ያሉት ነው፡-
1) የታክስ መሰረትን ማስፋት፤
2) ከሰነዱ ተጠቃሚዎች የመክፈል አቅም ጋር ማጣጣም፣
3) በአንዳንድ የሰነድ ክፍያዎች ላይ የሴቶችንና የህጻናትንና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣
4) የታክስ ስርአቱ ላይ የሚታዩ የፍሃዊነት ችግሮችን መቅረፍ፤ አጭር ርዕስ
• ይህ አዋጅ “ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቴምብር ቀረጥ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 307/2018 “ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
ትርጓሜ
 የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ :-
 “ግልግል” ማለት ስለግልግል፣ ስለእርቅ፣ ስለስምምነት ወይም ስለሌላ ተመሣሣይ ጉዳይ በሁለት ተዋዋይ ወገኖች በተደረገ ስምምነት መሠረት በፍርድ ቤት ሣይሆን በገላጋዬች አልቆ በጽሁፍ የተሰጠ ውሣኔ ነው።
 “ማገቻ” ማለት የተወሰነ ነገር በተፈፀሙ ወይም ባለመፈፀሙ ምክንያት የሚቀር ሆኖ አንድ ሰው ለሌላው ገንዘብ ለመክፈል ግዴታ የሚገባበት ማናቸውም ሰነድ ወይም በምስክር የተረጋገጠ ሆኖ ነገር ግን በትዕዛዝም ሆነ ለአምጪው የማይከፈልበት አንድ ሰው ለሌላው ገንዘብ ለመክፈል ግዴታ የሚገባበትን ማናቸውንም ሰነድ ይጨምራል።
 የህብረት ስምምነት” ማለት በአንድ ወይም ከአንድ በላይ የሠራተኞች ማህበራት ወኪሎች እና በአንድ ወይም ከአንድ በሚበልጡ አሰሪዎች ወይም የአሰሪ ማህበራት ወኪሎች ወይም አሰሪዎችን በሚወክሉ ተጠሪዎች መካከል ስለ ሰራ ውኔታዎች የሚደረግ በጽሁፍ የሰፈረ ስምምነት ነው።
 “የሥራ ውል” ማለት ማንኛውም ሰው ደመወዝ እየተከፈለው በአሰሪ መሪነት በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ወይም የተወሰነ ስራ ለአሪው ለመስራት ሲስማማ በሁለቱ መካከል የሚሰሩት ውል ነው።
 “ሰነድ” ማለት ማናቸውንመ መብት ወይም ግዴታ የተመሰረተበት፣ የተመዘገበበት፣ የተላለፈበት ወይም የተጠቀሰው ግድጊት ተፈጽሟል የተባለበት ማናቸውም የጽሁፍ መረጃ ነው።
 “ቢሮ” ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገንዘብ ቢሮ ነው።
 “ገቢዎች ቢሮ” ማለት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎችቢሮ ሲሆን በየደረጃ ያሉትን የገቢ ተቋማትን ይጨምራል።
 “ማረጋገጫ” ማለት የህዝብ ጉዳዬችን ለማረጋገጥ ስልጣን ባለው ሰው በሰነዶች ላይ የሚሰጥ ምስክርነት ነው።
 “አካል ጉዳተኛ” ማለት በፌደራል በአዋጅ ቁጥር 568/2000 አንቀጽ ፪ (፩) መሠረት የደረሰበትን የአካል፣ የአዕምሮ ወይም የስሜት ህዋሳት ጉዳት ተከትሎ በሚመጣ የኢኮኖሚያዊ፣ የማኅበራዊ ወይም የባህላዊ መድሎ ሳቢያ በሥራ ስምሪት የእኩል እድል ተጠቃሚ ያልሆነ ሰው ነው።
 “ ሰነድ ማስፈጸም” ማለት መስራት፣ ማውጣት በሰነዱ የተመለከተውን ማስፈጸም ወይም ሰነዱን ማዛወር ነው።
 “የመያዣ ሠነድ” ማለት ተበዳሪው ወይም ዋሱ ለአበዳሪው በሙሉ ወይም በከፊል ንብረቱን በመያዣነት የሚሰጥበት የሰነድ ነው።
 “ስታርትፕ” ማለት ምንም የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ታሪክ ሳይኖረው ወይም የተወሰነ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ታሪክ ብቻ ኖሮት ኢኖቬሽንን ተግባራዊ የሚደርግ፣ የቴክኖሎጂ ወይም በቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ተመንዳጊእና የገበያ መዋቅር የሚለውጥ ምርትን፣ አገልግሎትን ወይም ሒደትን በማስተዋወቅ በመፍጠር፣ በማበልጸግ፣ ሽግግርና ማላመድ በማድረግ ወይም በምልስ ምሕንድስና አማካኝነት ኢኮኖሚያዊ ዕሴትን በመፍጠር ላይ የተሰማራ ቡድን ወይም ሰው ነው፡፡
 “መተዳደሪያ ደንብ” ማለት አንድን ድርጅት ለማቋቋም የተዘጋጀ ደንብ ወይም የመመስረቻ ጽሁፍ ነው።
 “ሰው” ማለት ማናቸውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ቢሆንም ባይሆንም ማናቸውም ድርጅት ነው።
የቴምብር ቀረጦች የሚከፈልባቸው ሰነዶች
 የሚከተሉት ሰነዶች የቴምብር ቀረጥ ይከፈልባቸዋል።
 የማንኛውንም ንግድ ማህበር፣ የህብረት ስራ ማህበር ወይም የማንኛውንም ዓይነት
ማህበር መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ፣
 ግልግል
 ማገቻ
 የዕቃ ማከማቻ ማረጋገጫ ሰነድ፣
 ውል፣ ስምምነትና የእነዚህ መገለጫ፣
 የመያዣ ሰነዶች፣

 የሕብረት ስምምነት፣
 የሥራ /ቅጥር/ ውል፣
 የኪራይ፣ የተከራይ አከራይና መሰል መብት የማስተላለፊያ ሰነዶች ጭምር ፣
 ማረጋገጫ ፣
 የውክልና ሥልጣን፣
 የንብረት ባለቤትነትን ማስመዝገቢያ ሰነድ፣
የቴምብር ቀረጥ አከፋፈል ልክ
 በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ መከፈል የሚገባው የቀረጥ መጠን በሠንጠረዥ ውስጥ እንደተዘረዘረው ይሆናል።
 አንድ ሰነድ ለ2ኛ ጊዜ ተፈጻሚ ሲሆን ሊከፈል የሚገባው የቀረጥ መጠን በዚሁ ሠንጠረዥ ውስጥ የተመለከተው ነው።

30/07/2026

በሰሜን ሸዋ ዞን ስር ላላችሁ የደረጃ “ለ” እና የቤት ኪራይ ግብር ከፋዮች በሙሉ፣
በሰሜን ሸዋ ዞን ስር ያላችሁ የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች፣ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች፣ የወፍጮ አገልግሎት ሰጪዎች፣ በጥብቅና ስራ የተሰማራችሁና የቤት አከራዮች አመታዊ ግብር በሐምሌ ወር መክፈል እንዳለባችሁ የግብር አዋጁ ይደነግጋል፡፡
የዞኑ ገቢዎች መምሪያ 33,493 የደረጃ “ለ” እና 5,526 አከራዮች ለሚሆኑ ግብር ከፋዮች በሁሉም ወረዳና ከተማ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባችሁን ግብር ያለእንግልትና ወረፋ ጥበቃ በሲስተም እቤታችሁ ሆናችሁ እንድትከፍሉ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላችኋል፡፡
በሐምሌ ወር ግብርና ታክሣችሁን ለመክፈል በየአካባቢያችሁ ባሉ የገቢ ተቋማት የሚላክላችሁን ውሣኔ በመቀበል የደረጃ “ለ” ነጋዴዎች፣ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች፣ የወፍጮ አገልግሎት ሰጪዎች በጥብቅና የተሰማራችሁና የቤት አከራዮች ከሐምሌ 15 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በሁሉም ወረዳና ከተሞች ግብር የሚሰበሰብ ሲሆን በዞኑ ስር የምትገኙ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባችሁን ግብር በመክፈል ሃገራዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

" ግብሬን ደስ ብሎኝ እከፍላለሁ "
የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ

30/07/2026
23/07/2026
የዘመኑን ቴክኒዮሎጂ ተጠቅመን በሲስተም ግብር በመሰብሰባችን ብልሹ አሰራርን መከላከል አስችሎናል ተባለ ፡- የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በቀን 16/11/2018 ዓ.ም. ባደረገው የጠቅላላ...
23/07/2026

የዘመኑን ቴክኒዮሎጂ ተጠቅመን በሲስተም ግብር በመሰብሰባችን ብልሹ አሰራርን መከላከል አስችሎናል ተባለ ፡-
የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በቀን 16/11/2018 ዓ.ም. ባደረገው የጠቅላላ ሠራተኛ ስብሰባ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል፡፡
አፈጻጸሙን ያቀረቡት አቶ ደምሴ አርአያ የመምሪያው የዕቅድ ክትትል አስተባባሪ ሲሆኑ በበጀት አመቱ ዕቅዱን የጋራ በማድረግ ከአጋር አካላት ከአመራሩና ከፈጻሚ አካላት ጋር በመግባባት ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ ተለይተው የነበሩ 12 የሚሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ መፍታት ችለናል፡፡ በክልሉ እና በየወረዳና ከተማ አቅም ባላቸው አሰልጣኞች የባለሙያና የአመራሩን አቅም መገንባት የተቻለበት አመት ነው እንዲሁም ግብር ከፋዩ ግብር በዛብኝ ብሎ ያቀረበባቸውን ቅሬታና ይግባኝ በወቅቱ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የግብር ከፋዩን የህግ ተገዥነት ለማሣደግ ተከታታይ ትምህርትና ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ በዚህም ለውጥ መጥቶ ያለቅጣት ግብራቸውን የከፈሉ 95.1% ያህሉ ሆነዋል፡፡ በሌላ በኩል ሐሰተኛ ደረሰኝ 261 ያህል ደረሰኞች ተገኝተው የእርምት ሥራ ተሰርቷል፡፡ ለህብረተሰቡ መረጃ ለመስጠት ቴሌግራምና ፌስቡክን በመጠቀም ወረዳና ከተሞች የሰሩት ሥራ አበረታች ነው፡፡ በሂሣብ መዝገብ ምርመራ 117.7 ሚሊየን ብር በልዩነት የተገኘ ሲሆን የገቢ አሰባሰቡን ከፍ ያደረጉት የቫት አሰባሰብ ፡ የግብይት መረጃ አጠቃቀም ፣ ውዝፍ ግብር ማስከፈልና ንግድ ትርፍ መሰብሰብ ፣ የግል ድርጅት የሥራ ግብርን የማስከፈል ሥራችን የተሳካ በመሆኑ አፈጻጸሙ 94% የሆነ ግብርና ታክስ ሰብስበናል ፡፡ በዚህም ወረዳና ከተሞችን እንደአፈፃፀማቸው በሁሉም የሂደት ስራዎች ተመዝነው በደረጃ አስቀምጠናል በማለት አቶ ደምሴ አርአያ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ተሣታፊዎች ጥያቄና ተጨማሪ ሀሳቦችን አንስተው የመምሪያው ኃላፊዋ ወ/ሮ ቀለም ተስፋዬ ሲያጠቃልሉ በሁሉም የስራ ሂደቶች ጠንካራ ተሣትፎና በባለሙያዎች ታታሪነት የተሻለ ገቢ መሰብሰብ ችለናል እንዲሁም ወረዳና ከተሞችን በዙም ውይይት ተከታታይ ግምገማና ደጋፍ ማድረጋችን ለውጤቱ አስተዋፅኦ አበረክቷል በሌላ በኩል 23 ሺህ የሚሆኑ ግብር ከፋዮች በአዲሱ ቴክኔዎሎጂ በሲስተም ማስከፈል በመቻላችን ብልሹ አሰራርን መከላከል ችለናል ለመጣው ውጤት ባለድርሻ አካላትና በየደረጃው ያለው የፖለቲካ አመራር ንቁ ተሣትፎ በማድረግ 5.1 ቢለየን ብር ገቢ እንድንሰበስብ እድል ፈጥሮአልና ሲሉ መምሪያ ኃላፊዋ አስረድተዋል፡፡
ዘገባው፡- የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የግብር ትምህርትና ኮሙዩንኬሽን ዋና የሥራ ሂደት

Address

Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ /North shoa zone revenues department/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share