27/08/2026
ዛሬ በከተማችን ደብረ ብርሃን ሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት መምሪያየመንግስት ተቋማት የለውጥ አመራር አደረጃጀትና አሰራር ማሻሻል አፈፃፀም በከተማችን ካሉት አጠቃላይ መምሪያዎች ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የላቀ ዉጤት በማስመዝገብ #1ኛ በመዉጣታችን የዋንጫና ሰርተፍኬት የእዉቅና ሽልማት ተስጥቶናል።
አጠቃላይ የመምሪያችን ሰራተኞች ይህ ዉጤት እንዲመጣ የእናንት የአገልግሎት አስጣጥ እና የታታሪነት ጉልህ ሚና በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ።
ነገም አግልግሎታችንን በማዘመን ለአልሚ ባለሀብቶቻችን ፈጣንና ቀልጣፋ ግሎጋሎት በመስጠት ከተማችንን አሁን ካለችበት የኢንዱስትሪ ማዕከልነቷን ወደተሻለ አሸጋግረን የከተማችንን ወጣቶች ስራ እድል ተጠቃሚነት ከፍ አድርገን እንድንሰራ የሚያነሳሳ እዉቅና ነዉ።