ሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ/North Shoa Zone Health Department

ሰሜን ሸዋ  ዞን ጤና መምሪያ/North Shoa Zone Health Department ለማንኛውም ችግር የማይበገር የጤና ተቋም ለመገንባት ተግተን እንሰራለን።

ተቀራራቢ የዲግሪ ፕሮግራሞች
18/08/2025

ተቀራራቢ የዲግሪ ፕሮግራሞች

09/08/2025
20/12/2022
በአብክመ ጤና ቢሮ ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ እና በደ/ብርሃን ሪጅዎ ፖሊታን ጤና መምሪያ ትብብር የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን ዉጤታማ ለማድሰግ ከዛሬጥቅምት 28 ጀምርሮ እስከ ጥቅምት...
07/11/2022

በአብክመ ጤና ቢሮ ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ እና በደ/ብርሃን ሪጅዎ ፖሊታን ጤና መምሪያ ትብብር የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን ዉጤታማ ለማድሰግ ከዛሬጥቅምት 28 ጀምርሮ እስከ ጥቅምት 29/2015 ዓ ም የሚቆይ በደ/ብርሃን ከተማ የምክክር እና የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው፤
በንቅናቄ መድረኩ የሚመለከታቸው የአብክመ ጤና ቢሮ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የሰ/ሸዋ ዞን እና የደ/ብርሃን ሪጅዎ ፖሊታን ከፍተኛ አመራሮች እና በለሙያዎች፣ በዞኑ ያሉ ጠቅላላ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣በዞኑ ሥር ባሉ የሁሉም ወረዴ አስተዳዳሪዎች፣ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣የጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የየጤና ተቋማቶች ኃላፊዎች በጥቅሉ ከ1300 ሰዎች በላይ የተሳተፉበት መድረክ ነወ።
በመድረኩ መጀመሪያ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ገስጥ ጥላሁን እንደተናገሩት በምክክር መድረኩ ትኩረት የሚደረግባቸው
1.የትራንስፎርሜሽን አጀንዳ የመፈጸም አቅም ማጎልበት
2.በጤና ኤክስቴንሽኖች በኩል የሚታዩ የመልካም አስተዳደር የመፍታት ጉዳይ
3.እንዚህን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ለመፈጸም ከባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል የሚሉና
4.በዞኑ ካሉ ጠቅላላ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ጤና ኤክስቴንሽኖች የሽልማትና እዉቅና የመስጠት ፕሮግራሞች እነደተካተቱ ገልጸዋል፤
በመቀጠልም የሰ/ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ክላል ሳህለማርያም የተቀዛቀዘውን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ወደነበረበት ከፍታ ለማድረስ እና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ሁሉም የየድርሻውን እንዲወጣ ያሳሰቡ ሲሆን የአብክመ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ መልእክት ሲያስተላልፉ የጤናው ሴክተር ሰው የምንፈጥርበት ተቋም ሲሆን የራሱን ጤና በቤቱ የሚያመርት ህብረተሰብ መፍጠር የሚቻለው እንደሆነና ከጥራትና ከተደራሽነት አኳያ የምንሰራቸው ሥራዎች ዘመን ተሻጋሪ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበው ለመወያያ የሚሆን ፕረዘንቴሽን በአብክመ ጤና ቢሮ ጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም አስተባባሪ አቶ ወንድሙ ገበየሁ የቀረበ ሲሆን የምክክር መድረኩ ሞቅ ደመቅ ባለ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ጥቅምት 28//2015 ዓ.ም

ደ/ብርሃን

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና ቁጥጥር ኬዝ ቲም (PHEM) ከአብክመ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለወባ ሰርቬላንስ ኦፊሰሮች ስልጠና ሰጠ፡፡የሰሜን ...
06/11/2022

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና ቁጥጥር ኬዝ ቲም (PHEM) ከአብክመ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለወባ ሰርቬላንስ ኦፊሰሮች ስልጠና ሰጠ፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና ቁጥጥር ኬዝ ቲም (PHEM) ከአብክመ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የወባ በሽታ አሰሳና ቅኝት (Malaria Surveillance) ሥራ እንዲሰሩ በኮንትራት ለተቀጠሩ ከ70 በላይ ለሚሆኑ ለወባ ሰርቬላንስ ኦፊሰሮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ጤና ባለሙያዎች ከጥቅምት 25/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በሸዋሮቢት ከተማ በወባ በሽታ መከላከልልና ቁጥጥር ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በመስጠት ላይገኛል፤
የዞኑጤና መምሪያ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና ቁጥጥር ኬዝ ቲም (PHEM) አስተባበሪ አቶ በላይሁን ከበደ በስልጠናው መጀመሪያ ላይ እንደተናገሩት በዞኑ ስር የወባ ስርጭት የሚበዛባቸው በርካታ ወረዳዎች ሲኖሩ የ Malaria Elimination Program ለማሳካት በነዚህ ወባማ ወረዳዎች ላይ የወባ በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ሥራዎችን አጠናክረን መስራት እንደሚገባ እንዲሁም በኮንትራት የተቀጠሩት ሰልጣኞች ከስልጠናው በኋላ በዞኑ ሥር ባሉ የተለያዩ ወረዳዎች ለ3 ተከታታይ ወራት ተመድበው የሚሰሩ ሲሆን የአሰሳና ቅኝት ሥራውን በሚሰሩበት ወቅት ህብረተሰቡን ስለወባ በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ሥራዎች እንደ የአካባቢ የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ቁጥጥር፣አጎበር አጠቃቀምና ሌሎች የወባ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ሥራዎች ላይ ማስተማር እንዳለባቸው አሳስበዋል፤ ስልጠናውም ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች አሰልጣኝነት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ጥቅምት 27/2015 ዓ.ም
ሸዋሮቢት

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ቲቢ ክፍል ከMSH USAID-Eliminate TB Project ጋር በመተባበር  የማህበረሰብ አቀፍ ቲቢን አስመልክቶ ለጤና ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ፤የሰሜን ሸዋ...
30/09/2022

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ቲቢ ክፍል ከMSH USAID-Eliminate TB Project ጋር በመተባበር የማህበረሰብ አቀፍ ቲቢን አስመልክቶ ለጤና ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ፤
የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ቲቢ ክፍል ከMSH USAID-Eliminate TB Project ጋር በመተባበር የማህበረሰብ አቀፍ ቲቢን አስመልክቶ ከ2 ወረዳዎች(አንጾኪያ ገምዛና ኤፍራታና ግድም) በስራቸው ካሉ ጤና ተቋማት (ወረዳ ጤና ጽ/ቤቶች፣ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች) ለተዉጣጡ ከ40 በላይ ለሚሆኑ ጤና ባለሙያዎች በዛሬው እለት መስከረም 20/2015ዓ.ም በሸዋሮቢት ከተማ ኦረንቴሽን በመሰጠት ላይ ነው፤
በኦረንቴሽኑ መክፈቻ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ጸዳለ ሰሙንጉስ እንደተናገሩት የቲቢ በሽታ በዞናችን በተለይም በእነዚህ ወረዳዎች ከፍተኛ ሲሆን የቲቢ እና ቲቢ መሰል ምልክት ያለባቸውን እየለዩ ለምርመራ ወደ አቅራቢያወ ጤና ተቋም ከመላክ አንጻር እስከ አሁን እየሰራን ያለወ በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የቲቢ በሽታ ሰርጭት እየበዛ መሆኑን ገልጸዉ ቲቢ እና ቲቢ መሰል ምልክት ያለባቸውን ሰዎች የመለየት ሥራውን ከመቸውም በበለጠ አጠናክረንና አቀናጅተን በመሥራት የቲቢ ህክምና ሽፋን(TB Treatment Coverage) በማሳደግ የበሽታውን ስርጭት መቀነስ እንዳለብን አሳስበዋል።
የMSH USAID-Eliminate TB Project የሰሜን ሸዋ ዞን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኤሊያስ ቀለም የማሕበረሰብ አቀፍ ቲቢ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈለገበትን ሲገልጹ በየቤቱ በሽታውን ሳያዉቁት ቀርተው ወደህክምና ያልሄዱትን እና እየተሰቃዩ ያሉትንና በሽታውንም እያሰራጩ ያሉትን በመድረስ ወደ ህክምና ተቋም እየመጡ እንዲመረመሩና ህክምናውን እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ አጠናክረን ለመስራትና በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የበሽታውን ሥርጭት መቀነስ በማስፈለጉ እንደሆነ ጠቁመዉ ይህን ሥራ ከነዚህ ወረዳዎች ተሞክሮና ልምድ በመዉሰድ ወደ ሌሎች ወረዳዎች ለማስፋት እንደ ታሰበም ገልጸዋል።
በመቀጠልም ቴክኒካል ስልጠናው የፕሮጀክቱ የማሕበረሰብ አቀፍ ቲቢ መከላከልና መቆጣጠር አድቫይዘር በሆኑት ሲ/ር ወጋየሁ ጌታቸው እና የዞኑ ጤና መምሪያ የቲቢ ሊፕረሲና ቲቢ ኤች አይ ቪ ኦፊሰር በሆኑት ሲ/ር ተናኘወርቅ ጥላሁን አማካይነት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ 🥀የ2014 በጀት ዓመት መደበኛ የጤና ተግባራትና የማህበረሰብ ጤና መድን አፈጻጸም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ትዉዉቅ 🥀በህልዉና ዘመቻዉ የላቀ አስተዋ...
04/08/2022

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ
🥀የ2014 በጀት ዓመት መደበኛ የጤና ተግባራትና የማህበረሰብ
ጤና መድን አፈጻጸም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ትዉዉቅ
🥀በህልዉና ዘመቻዉ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና
ፕሮግራም በሚል በ27/11/2014 ዓ.ም የጀመረዉን በዛሬዉ ዕለትም
ከዞኑ አስተዳደር ጋር በመሆን በሞቀና በደመቀ ሁኔታ አጠናክሮ ቀጥሏል።
ሐምሌ 28/11/2014 ዓ.ም

ደብሰብርሃን

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ 🥀የ2014 በጀት ዓመት መደበኛ የጤና ተግባራትና የማህበረሰብ ጤና መድን አፈጻጸም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ትዉዉቅ 🥀በህልዉና ዘመቻዉ የላቀ አስተዋ...
03/08/2022

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ
🥀የ2014 በጀት ዓመት መደበኛ የጤና ተግባራትና የማህበረሰብ
ጤና መድን አፈጻጸም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ትዉዉቅ
🥀በህልዉና ዘመቻዉ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና ፕሮግራም
በዛሬው ዕለት ሐምሌ 27/2014 ዓ ም በደ/ብርሃን ከተማ መካሄዱን ጀምሯል።

Address

North Shoa Zone Conpound
Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ/North Shoa Zone Health Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share