ደብረብርሃን ከተማ እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • ደብረብርሃን ከተማ እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

ደብረብርሃን ከተማ እምዬ ምኒልክ  ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የደ/ብርሃን ከተማ በአፄ ዘርያእቆብ ዘመነ መንግስት በ1446 ዓ.ም የተቆረቆረች ጥንታዊ ከተማ ነች፡፡

30/01/2024
በእምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ በአደንዛዥ ዕፅ አስጠቃሚ ግለሰቦች ቤት ድንገተኛ ፍተሻ ተደረገ።በክፍለ ከተማው የፀጥታ ሃይሉ ስምሪት በመውሰድ ድንገተኛ ፍተሻ የተደረገ ሲሆን በዚህም  89 የሺሻ...
30/06/2023

በእምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ በአደንዛዥ ዕፅ አስጠቃሚ ግለሰቦች ቤት ድንገተኛ ፍተሻ ተደረገ።

በክፍለ ከተማው የፀጥታ ሃይሉ ስምሪት በመውሰድ ድንገተኛ ፍተሻ የተደረገ ሲሆን በዚህም 89 የሺሻ እቃ ፣ 172 ሙሬ ፣ 60 የሺሻ እቃ ገመድ ፣ 80 የሺሻ ዕቃ ማቀፊያ ብረት ፣ 14 የሺሻ እቃ ቋሚ ብረት ፣ 5 ሙአሰል መያዙ ተገልጿል ።

ወጣቶች በተለያየ ሁኔታ በማስጨሻ ቤቶች ለትውልድ ኪሳራ በሆነ መንገድ አደንዛዥ እፅ በመጠቀም ላይ ያሉ 21 ሰዎችን አራት አስጫሾችን ጨምሮ በህግ ጥላ ስር ውለዋል፤

ሀያ ሁለት ( 22 ) የተለያየ መጠን ያላቸው የማስጠቀሚያ ቤቶች በድንገተኛ ተፈትሸዋል

ይህ ተግባር በቀጣይም ወጣቶችን የመታደግ ትልቅ የኀላፊነት ስራ መሆኑን በመገንዘብ ህብረተሰቡ በሚሰጠው መረጃ መነሻነት እና እፁ የሚያስከትለውን ውድመት በማሰብ የትኩረት አቅጣጫ ሆኖ ይሰራበታልም ተብሏል።

አመራሩ  ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታት ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ ።ደብረ ብረሀን :-ሰኔ 19/2015ዓ.ም (ደብኮ)አመ...
26/06/2023

አመራሩ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታት ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ ።
ደብረ ብረሀን :-ሰኔ 19/2015ዓ.ም (ደብኮ)አመራሩ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታት ተቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ ።

በደብረብርሃን ከተማ መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ በሚል መሪ ሃሳብ ከከተማ እስከ ቀበሌ ላሉ የፓርቲ አመራሮች ሲሰጥ የሰነበተው ስልጠና ተጠናቀቀ።

የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጌታቸው እንደገለጹት አመራሩ በመልካም ስነምግባር ህብረተሰቡን በቅንነት ማገልገል እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የከተማው ሠላም በዘላቂነት ተጠብቆ እንዲዘልቅ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን ሆኖ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የማዳበሪያ አቅርቦት፣የኑሮ ውድነት፣የሥራ አጥነት ችግር እንዲፈታ በየደረጃው እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ካሳሁን እምቢአለ መድረኩን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት ስርቆትን በጽናት ታግሎ በማስተካከል እና የአመራር አንድነት በማጠናከር ለህዝብና ለመንግስት የሚጠቅም ተጨባጭ ስራ መፈጸም እንደሚጠበቅ አሳውቀዋል፡፡
በተለይም አመራሩ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታት ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡አመራር በተግባር ሰርቶ ውጤት ማምጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
አሁን እንደ ሀገር ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመፍታት ለሀገረ መንግስት ግንባታ የምክክር ኮሚሽኑ ስራ ፋይዳው የጎላ መሆኑን አንስተው ለተግባራዊነቱ ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አመልክተዋል፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ ከ57 ሺህ በላይ ወጣቶችን በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማሳተፍ መታቀዱ ተገለጸበጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ -2 በሚል መሪ መልዕክት የደብረ ብርሃን ከተማ ወጣትና ስፖር...
23/06/2023

በደብረ ብርሃን ከተማ ከ57 ሺህ በላይ ወጣቶችን በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማሳተፍ መታቀዱ ተገለጸ

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ -2 በሚል መሪ መልዕክት የደብረ ብርሃን ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ የ2015ዓ.ም የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ይገኛል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ቶማስ መኮንን የእንኳን ደህና መጣችሁ የመከፈቻ ንግግር አድርገዋል።

በ2014ዓ.ም በክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት በክልሉ ከሚገኙ ከተሞች 1ኛ መውጣቱን አንስተዋል።በዚህ ዓመትም በተመሳሳይ የላቀ አፈፃጸም ለማስመዝገብ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
በመጪው ክረምት በደብረብርሃን ከተማ 57 ሺህ 540 ወጣቶችን በማሳተፍ 57 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ሃብት ከወጪ ማዳን እንደሚቻል ተገልጿል።

በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳዳር ትጥቅ ይዘው ህውከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው ግለሰቦች በተኩስ ልውውጥ ከነ ጦርመሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ። በከተማ አስተዳደሩ በእቴጌ ...
23/06/2023

በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳዳር ትጥቅ ይዘው ህውከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው ግለሰቦች በተኩስ ልውውጥ ከነ ጦርመሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በከተማ አስተዳደሩ በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ሳሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቦሰና ምንጭ በሚባል አካባቢ ቁጥራቸዉ በርከት ያሉ ሰዎች በጦር መሳሪያ የተደገፈ ህውከትና ብጥብጥ ለመፍጠር እየተዘጋጁ መሆኑ መረጃው ለጸጥታ ሀይሉ ይደርሳል።
ጉዳዩን በመረጃ ያጠናከረው የጸጥታ ሀይሉ ሰኔ 14 ለ15/2015 ዓ/ም ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ድንገተኛ የተቀናጀ ስምሪት ተደርጎ ከሰዓታት ከባድ የተኩስ ምልልስ በኋላ የጥፋት ግለሰቦች ከነ መሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በአካባቢው የከፋ ጉዳት እንዳይፈጠር የፀጥታ ሀይሉ እጅግ በከፍተኛ ጥንቃቄ በወታደራዊ ጥበብ ያለምንም ኪሳራ ያለ መስዕዋትነት ድል ማድረግ ችሏል።

በኦፕሬሽኑ 26 ግለሰቦች ከነ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን አራት እስናይፐር ከ1261 ጥይት ጋር፣አንድ ድሽቃ ከ490 ጥይት ጋር፣5 ክላሽ ከሰባት ካርታና 530 ጥይት ጋር፣ 2 ብሬን፣ 3 የእጅ ቦንብ፣ ሁለት የቱርክ ሽጉጥ ከመሰል ስምንት ጥይት ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።

መረጃው የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ነዉ

የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚዛናዊና ፈጣን  መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ ።ደብረ ብረሀን :- ሰኔ 13/2015ዓ.ም (ደብኮ)የኮሙንኬሽን ባለሙያዎች ሚዛናዊ...
20/06/2023

የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚዛናዊና ፈጣን መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ ።
ደብረ ብረሀን :- ሰኔ 13/2015ዓ.ም (ደብኮ)የኮሙንኬሽን ባለሙያዎች ሚዛናዊና ፈጣን መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ ።
የደብረ ብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ለኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በዜና አዘገጃጀት እና አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ ።
ስልጠናው የዜና ዕቅድ፣ይዘት አመራረጥ፣አጭር ዜና አዘገጃጀት እና አጠቃቀም ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በንድፈ ሀሳብ ተተንትኖ፤ በተግባር ልምምድ ተደግፎ ተሰጥቷል፡፡
ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከስልጠናው መጠቀማቸውንና ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው ክፍተታቸውን የሞላ፣ለቀጣይ ስራ አቅም የሚገነባ መሆኑን አንስተዋል፡፡ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስቦ ስላዘጋጀው አመስግነው ቀጣይነት እንዲኖረውም ጠይቀዋል፡፡
የደብረብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ ብዙነህ ስልጠናውን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት እስካሁን የነበሩ ክፍተቶችን አርሞ ጥንካሬዎችን አጎልብቶ ተቀናጅቶ መስራት ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በቀጣይ የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ትክክለኛ፣ሚዛናዊና ፈጣን መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በእምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ " ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን " በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ጋር ኮንፈረንስ ተካሄደ።" ፈተናዎችን ወ...
01/06/2023

በእምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ " ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን " በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ጋር ኮንፈረንስ ተካሄደ።

" ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን " በሚል መሪ ቃል ከክልል ጀምሮ በየደረጃው እየተካሄደ የሚገኘው በክልሉ ውስጥ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመው ኮንፈረስ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ጋር የጀመረ ሲሆን በመድረኩም የህዝብ አንድነት በሚያመጡ እና በመሰረታዊነት በሚነሱ የአማራ ክልል ጥያቄዎችን ከታሪካዊ ዳራው ጀምሮ በየዘመኑ እስከተፈጠሩት ሃሰተኛ ትርክት ምክንያት የመጣብንን ምስቅልቅል ለመቀየር በሚቻልበት አግባብ ኮንፈረንሱ ተካሂዷል ።

በክልላችን በተሳሳተ ትርክት ፣ በወሰን ማንነት እና በሰላም እጦት ምክንያት ያሉ ጥያቄዎችን በሂደት ለመመለስ እንደ ህዝብ በአንድነት መቆም ዋነኛ ተግባር መሆኑን ለማስገንዘብ እና በተለይ በመንግሥት ተቋማት ላይ በሃላፊነት ህዝብን በማገልገል አካባቢያዊ ጥያቄዎችን በራስ አቅም መመለስ እንደሚገባም ተነስቷል ።

የእምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ህንፃ ሹም ተጠሪ ፅ/ቤት የአዲሱ ማህበር  በተለምዶው 633ቱ ማህበር እጣ ወጥቶላቸው ቦታ ለተረከቡ የማህበር አባላት የግንባታ ፈቃድ የመስጠት አገልግሎት በይፋ መ...
01/06/2023

የእምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ህንፃ ሹም ተጠሪ ፅ/ቤት የአዲሱ ማህበር በተለምዶው 633ቱ ማህበር እጣ ወጥቶላቸው ቦታ ለተረከቡ የማህበር አባላት የግንባታ ፈቃድ የመስጠት አገልግሎት በይፋ መጀመሩን አበሰረ።

የክፍለ ከተማው ህንፃ ሹም ተጠሪ ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ጥሩወርቅ ሙላቱ እንደገለፁት በክፍለ ከተማችን ዘወትር ማክሰኞ እና ሀሙስ ደንበኞች ወደ ተቋሙ ሲመጡ ማሟላት ያለባቸውን በማሟላት እንዲቀርቡ አሳስበው አዲስ የማህበር ፕላን ፣ የግንባታ ፈቃድ ለማግኘት ፣ የኘላን ስምምነት የሚጠይቁ ማህበራት ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ አውቀው እንዲያሟሉ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል ።

የኘላን ስምምነት መረጃ ከከተማና መሰረተ ልማት የተሞላ ቅፅ እና የይዞታ ማረጋገጫ ኮፒ ሆኖ ማህተም ያለው ፣የሊዝ ውለታ ኦርጅናል ለህንፃ ሹም ግልባጭ የተደረገውን ፣ የማህበር እውቅና የተሰጠበት ደብዳቤ ከእነ አባላት ዝርዝር የያዘ ኮፒ ፣ የማህበሩ ሊቀ መንበር/ፀሐፊ ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ሰው፣ የአባላት ስም ዝርዝር እና ስልክ ቁጥር ፣ ወፍራም ክላሴር አንድ እና የኘላን ስምምነት ቅፃቅፅ ኮፒ ፣ የአገልግሎት ክፍያ 300 ብር ናቸው ፣ መታወቂያ ይዞ መቅረብ እንዳለበት አሳስቦ በክፍለ ከተማችን በሚሰጡ የአገልግሎት ሁነቶች ሁሉ በተገቢው እንደሚፈፅሙ ሃላፊዋ ገልፀዋል ።

‹‹የኢትዮጵያ መዳኛ ትርክት አብሮነት፣ወንድማማችነትና በጋራ ሀገርን የመገንባት ትርክት ነው፡፡ ››  አቶ ግዛቸው ሙሉነህ***የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ የሚገኙ የዞንና የከተማ አስ...
22/05/2023

‹‹የኢትዮጵያ መዳኛ ትርክት አብሮነት፣ወንድማማችነትና በጋራ ሀገርን የመገንባት ትርክት ነው፡፡ ›› አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
***
የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ የሚገኙ የዞንና የከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ወቅታዊ ክልላዊ ሁኔታዎችን መሰረት ያደረገ ውይይት በባህር ዳር ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በውይይቱ የተገኙት የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ቀውስ የአመራር መናጋትን ይፈጥራል፤ በዚህ ምክንያት የመልካም አስተዳር ችግሮችን የሚያባብስ እና የአካባቢን ሠላም የሚያደፈርስ በመሆኑ ለዚህ የሚመጥን የሚዲያና የተግባቦት ሥራ በሁሉም አካባቢዎች በአግባቡ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡

አሁን ላይ በአገራችንም ሆነ በክልሉ ብዙ አይነት የትርክት መዛነፍ እንዳለ ያነሱት ቢሮ ኃላፊው ሀገርን ሊያድን የሚችለውን ትርክት ማጽናት ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡

‹‹የኢትዮጵያ መዳኛ ትርክት አብሮነት፣ወንድማማችነትና በጋራ ሀገርን የመገንባት፣ኢኮኖሚን የማሳደግ ትርክት ነው›› ያሉት አቶ ግዛቸው ከዚህ ውጪ ያሉ ትርክቶች ሀገርን የሚያፈርሱና ለጠላት አጋልጠው የሚሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት አድርጎ የተግባቦት ሥራ አለመስራት በኮሙኒኬሽን መዋቅሩ የሚታይ የተግባቦት ዝንፈት መሆኑን የገለጹት ቢሮ ኃፊው የአብሮነት እሳቤዎችን በሚያጎሉ ክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

ለህዝቡ መድረስ የሚገባውን ወቅታዊ መረጃ ተግባቦትን በሚያጠናክር መልኩ ሁሉንም የመገናኛ አማራጮች በመጠቀም የኮሙኒኬሽን መዋቅሩ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡


አማራ ክልል ኮሙኒኬሽን

ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት ወረዳ የምትገኝ ታላቅ ደብር ናት። ተድባበ ...
08/05/2023

ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም

ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት ወረዳ የምትገኝ ታላቅ ደብር ናት።

ተድባበ ማርያም ከደሴ በ225 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከአማራ ሳይንት ርዕሰ ከተማ አጅባር በ25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

ደብሯ ዙሪያዋ ገደል ሆኖ በግራና ቀኝ በጉንዳና ገዳማይ ጅረቶች እንዲሁም በሽሎ ወንዝ ታጅባ የምትገኝ ውብ የታሪክ አምባ ነች፡፡ አምባው ለመውጣት 12 በሮች አሉት፡፡ ፊት በር፣ ቦካ፣ ገተም፣ ሞገራ ግራኝ፣ ታሪኳ፣ የዘንጌ፣ አሳስት፣ አጎና፣ አምጣ ፈረሴን፣ አህያ መደብለያና የጌለት ናቸው፡፡ አምባው ላይ በዮሐንስ ራዕይ ላይ የ7ቱ ቤተ-ክርስቲያን አምሳያ 7 ቤተ ክርስቲያኖች አሉ፡፡

በኢትዮጵያ መስዋዕተ ኦሪት ከተሰዋባቸው አራት ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አክሱም ጽዮን፣ ተድባበ ማሪያም፣ መርጦ ለማሪያምና ጣና ቂርቆስ መካከል አንዷ ናት፡፡ በአመሰራረት ቅደም ተከል ከአክሱም ጽዮን ቀጥላ ሁለተኛዋ ጥንታዊና ብቸኛ ባለታሪክ ደብር ናት፡፡

ደብሯ ከክርስቶስ ልደት በፊት የተመሰረተች በመሆኗ ከ3 ሺህ ዓመታት በላይ ዕድሜ አስቆጥራለች፡፡ የተሰራችውም በቀዳማዊ ዳዊት የወንድም ልጅ አሚናዳብ አማካኝነት በ982ዓ.ዓ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ቤተ-ክርስቲያኗ 9 ጊዜ ፈርሶ ተሰርቷል፡፡ ብዙ ጊዜም ተጠግኗል፡፡

የአፄ ገላውዲዮስ አጽም ያረፈው በዚህ ደብር እንቁላል ግንብ በሚባለው ነው፡፡ በደብሯ በርካታ ቅርሶች ያሉ ሲሆን ንዋየ ቅድሳት፣ የብራና መጽሃፍት ገድሎች፣ ስዕሎች፣ የነገስታት ዘውዶች፣ ወንበርና አልባሳት፣ የነገስታት አጽም፣ የጥንት ነገስታት የጦር መሳሪያ ወዘተ ይገኛሉ፡፡ በድንጋይ ግድግዳና በቆርቆሮ ክዳን የተሰራ ነው፡፡

ዓመታዊ ክብረ በዓሏ አጼ ገላውዲዮስ ታቦተ ልደቷን ከእየሩሳሌም አስመጥተው ወደ ቤተ-ክርስቲያኑ ያስገቡበትን ቀን መነሻ በማድረግ ግንቦት 1 ቀን በልደታ እንዲሁም ግንቦት 2 ቀን ይከበራል፡፡

ዘገባው፦ የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው።

ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል።  ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም  ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባሕል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳ...
27/04/2023

ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል።

ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባሕል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው።

ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው።

ነፍስህ በሰላም ትረፍ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የደብረ ብረሀን ኮሙንኬሽን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ፀጥታ ለማስጠበቅ ጥሎት የነበረውን ገደብ በከፊል ማንሳቱን አስታወቀ፡፡ሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም (ደብኮ) የደብረ ብረሀን ከ...
24/04/2023

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ፀጥታ ለማስጠበቅ ጥሎት የነበረውን ገደብ በከፊል ማንሳቱን አስታወቀ፡፡

ሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም (ደብኮ) የደብረ ብረሀን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማ አስተዳደሩን ሰላም ለማረጋገጥና የህግ የበላይነት ለማስከበር አስቀምጧቸው የነበሩ ክልከላዎች በከፊል ማንሳቱን አስታውቋል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ከሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን የታወጁ ክልከላዎችን በማስፈፀም ከተማዋ ወደቀድሞ ሰላሟ እንድትመለስ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሃይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ለሁሉም የከተማው የፀጥታ መዋቅር አባላት እና ለከተማው ነዋሪዎች በሙሉ ምስጋና በማቅረብ የተጣሉ ክልከላዎችን በከፊል ከዛሬ ጀምሮ መነሳታቸውን አስታውቋል፡፡

የቀጠሉ ክልከላዎች

1. በከተማ አስተዳደሩ ከተፈቀደለት የፀጥታ አካል ውጪ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል ነው፡፡
2. የሰራዊቱን ሚሊተሪ አልባሳት ከሰራዊቱ አባላት ውጪ ለብሶ መንቀሳቀስ ክልክል ነው
3. ያለ ከተማ አስተዳደሩ ፈቃድ በተለያዩ አካባዎች በቡድን መሰባሰብ ለከተማው የሠላም ችግር መንስኤ ስለሚሆን ፍፁም ተከለከለ ነው፡፡

ከተማዋም በአሁኑ ሰዓት የቀደመ ሰላሟ ተመልሶ በፍፁም መረጋጋት ውስጥ ያለች እና ሁሉም የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ የሚገኙ በመሆኑ ሰላም ወዳዱ የደብረ ብርሃን ህዝብም አሁን ያለውን ሰላም እንዲያስቅጥል እና ማንኛውንም የተለየና አዲስ እንግዳ የሆነ ነገር ሲያጋጥም እንደተለመደው ለፀጥታ ተቋማት ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክት ተላልፏል፡፡

Address

Debre Birhan
1000

Telephone

+251911776619

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደብረብርሃን ከተማ እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ደብረብርሃን ከተማ እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት:

Share