Amara supreme Court debre birhan division /የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረብርሀን ምድብ

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • Amara supreme Court debre birhan division /የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረብርሀን ምድብ

Amara supreme Court debre birhan division /የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረብርሀን ምድብ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amara supreme Court debre birhan division /የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረብርሀን ምድብ, near getva hotel, Debre Birhan.

ለቀረበበት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማስተባበያ እንዲሆነው  ከሳሽ የሆነ ወገን አስቀድሞ በክሱ ካቀረበው ማስረጃ በተጨማሪ ማቅረብ እንደሚችል።ምክንያቱም ፨ ከሳሽ የሆነ ወገን አስቀድሞ የሚመ...
25/03/2026

ለቀረበበት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማስተባበያ እንዲሆነው ከሳሽ የሆነ ወገን አስቀድሞ በክሱ ካቀረበው ማስረጃ በተጨማሪ ማቅረብ እንደሚችል።
ምክንያቱም ፨ ከሳሽ የሆነ ወገን አስቀድሞ የሚመጣውን መቃወሚያ አውቆ በክሱ ጊዜ ማስረጃ ማያያዝ ነበረበት ማለት አይቻልም።

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ።​ጋብቻ ሳይኖር እንደ ባልና ሚስት በሚኖሩ ሰዎች መሀከል ንብረትን አስመልክቶ የሚደረጉ ስምምነቶች በፍርድ ቤት እንዲፀድቁ ግዴታ የለም።
15/02/2026

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ።
​ጋብቻ ሳይኖር እንደ ባልና ሚስት በሚኖሩ ሰዎች መሀከል ንብረትን አስመልክቶ የሚደረጉ ስምምነቶች በፍርድ ቤት እንዲፀድቁ ግዴታ የለም።

አንድ ሰዉ መብቱን የሚነካ ዉሳኔ የተፈጸመ እንደሆነ አዲስ ክስ በማቅረብ መብቱን ማስከበር የሚችለዉ፣ ከአቅም በላይ ወይም በቂ በሆነ ምክንያት ዉሳኔዉ ከመፈጸሙ በፊት መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ስ...
03/02/2026

አንድ ሰዉ መብቱን የሚነካ ዉሳኔ የተፈጸመ እንደሆነ አዲስ ክስ በማቅረብ መብቱን ማስከበር የሚችለዉ፣ ከአቅም በላይ ወይም በቂ በሆነ ምክንያት ዉሳኔዉ ከመፈጸሙ በፊት መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ስለመኖሩ ማወቅ ባለመቻሉ ወይም በተመሳሳይ ምክንያት መቃወሚያ ማቅረብ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔበውጭ አገር የተሰጠ ወይም የተሰረዘ የውክልና ሰነድ በኢትዮጵያ ህጋዊ የሚሆነው አገር ውስጥ ገብቶ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ  ሲመዘገብ ብቻ ነው።
06/01/2026

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ
በውጭ አገር የተሰጠ ወይም የተሰረዘ የውክልና ሰነድ በኢትዮጵያ ህጋዊ የሚሆነው አገር ውስጥ ገብቶ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ሲመዘገብ ብቻ ነው።

የውንብድና ወንጀል የፈፀመ ሰው የዘረፈው ንብረት የብዙ ሰዎች ንብረት ቢሆንም ንብረቶቹ የብዙ ሰዎች መሆናቸውን እያወቀ መዝረፉ በአቃቢ ሕግ ማስረጃ ካልተረጋገጠ በወንጅል ሕግ አንቀጽ 60(ሐ)...
04/01/2026

የውንብድና ወንጀል የፈፀመ ሰው የዘረፈው ንብረት የብዙ ሰዎች ንብረት ቢሆንም ንብረቶቹ የብዙ ሰዎች መሆናቸውን እያወቀ መዝረፉ በአቃቢ ሕግ ማስረጃ ካልተረጋገጠ በወንጅል ሕግ አንቀጽ 60(ሐ) መሰረት በተደራራቢ ወንጀል ጥፋተኛ ሊባል አይችልም።

23/12/2025

በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ መብትን የሚሰጥ ስጦታ በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ አሠራር ዐይነት ካልተደረገ ፈራሽ ነው።የፍ/ሕ/ቁ 2443

የማታለል ድርጊቱ ተፈጽሞብኛል የሚለው ሰው አብሮ የወንጀሉ ፍሬ ተጠቃሚ ለመሆን የተስማማ ከሆነ የማታለል ተግባር ተፈጽሞብኛል ለማለት አይችልም፡፡
23/12/2025

የማታለል ድርጊቱ ተፈጽሞብኛል የሚለው ሰው አብሮ የወንጀሉ ፍሬ ተጠቃሚ ለመሆን የተስማማ ከሆነ የማታለል ተግባር ተፈጽሞብኛል ለማለት አይችልም፡፡

ውል እንዲፈርስ የሚወሰን ከሆነ ተዋዋዮች ከውለታቸው በፊት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ መወሰን የፍርድ ቤት ሃላፊነት እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 182(2) ላይ በተደነገገው አግባብ ዳኝነት ...
22/12/2025

ውል እንዲፈርስ የሚወሰን ከሆነ ተዋዋዮች ከውለታቸው በፊት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ መወሰን የፍርድ ቤት ሃላፊነት እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 182(2) ላይ በተደነገገው አግባብ ዳኝነት ሊጠየቅበት ይገባ ነበር በማለት ማለፍ ተገቢነት የለውም፡፡

የወንጀል ምስክር ጥበቃን በተመለከተ የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ።
18/12/2025

የወንጀል ምስክር ጥበቃን በተመለከተ የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ።

14/12/2025

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር መዝገብ ቁጥር።
239453 ቅጽ 27 አውራሹ ሲሞት ለአቅመ አዳም ያልደረሰ ልጅ 18 አመት ከሞላው ጀምሮ እስከ 10 አመት ድረስ ውርሱን መጠየቅ ይችላል።

57114
52407 ቅጽ 11
120841 ቅጽ 20 እነዚህ ውሳኔዎች ደግሞ አውራሹ ሲሞት ለአቅመ አዳም ያልደረሰ ልጅ 18 አመት ከሞላው ጀምሮ እስከ 15 አመት ድረስ ውርሱን መጠየቅ ይችላል በሚል የተወሰኑ ናቸው።

ልዩነት ይኖራቸው ይሆን?

የመንግስት አስተዳደር ተቋማት ገንዘብ እንዲታገድ የሚሰጥ ትእዛዝ በጥንቃቄ ተመርምሮ መሆን አለበት።ከፍርድ በፊት ለክርክሩ መነሻ ያልሆነዉን ንብረት(ገንዘብ)  በማስከበር የሚሰጥ ትእዛዝ (የፍ...
14/12/2025

የመንግስት አስተዳደር ተቋማት ገንዘብ እንዲታገድ የሚሰጥ ትእዛዝ በጥንቃቄ ተመርምሮ መሆን አለበት።

ከፍርድ በፊት ለክርክሩ መነሻ ያልሆነዉን ንብረት(ገንዘብ)
በማስከበር የሚሰጥ ትእዛዝ (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 153/5 ) በዋናዉ ጉዳይ ላይ ዉሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ተጠብቆ ይግባኝ የሚባልበት ነዉ ወይም እንደጊዜያዊ ትዕዛዝ(interlocutory decision/order) የሚቆጠር አይደለም። እግዱን ለሰጠው ፍርድ ቤት አቤቱታው ቀርቦ ተቀባይነት ካላገኘ ይግባኝ ሊባልበት ይችላል።

ከአቅም በላይ ችግር ( ) ምክንያት ውሉን ያልፈፀመ ተዋዋይ ከግዴታው ነፃ የሚሆነው በውሉ አግባብ ባለመፈፀሙ የደረሰውን የጉዳት ኪሳራ ክፍያውን እንጂ   #ዋናውን የውል ግዴታ መፈጸም አለበት...
04/11/2025

ከአቅም በላይ ችግር ( ) ምክንያት ውሉን ያልፈፀመ ተዋዋይ ከግዴታው ነፃ የሚሆነው በውሉ አግባብ ባለመፈፀሙ የደረሰውን የጉዳት ኪሳራ ክፍያውን እንጂ #ዋናውን የውል ግዴታ መፈጸም አለበት።

Address

Near Getva Hotel
Debre Birhan

Telephone

+251116811977

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amara supreme Court debre birhan division /የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረብርሀን ምድብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share