ቡልጋ ከተማ አስተዳደር Bulga city Administration

ቡልጋ ከተማ አስተዳደር  Bulga city Administration በዚህ ፔጅ ስለ ቡልጋ ከተማ አስተዳደር መረጃወችን የምንለዋወጥ ይሆናል

05/04/2026
18/03/2026
09/03/2026
01/03/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
አቶ መካሻ አለማየሁ
እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

አድዋ በአፍሪካ ሰማይ ላይ ያንዣበበውን የቅኝ ግዛት ደመና ለመግለጥ በኢትዮጵያ ላይ የወጣ ጸሀይ ነው ።
የአድዋ ድል ለኢትዮጵያው ከጦርነት ድል በላይ ነው። የኢትዮጵያዊያን አንድነት፣ ብልህነትና የአይበገሬነት ታላቅ መንፈስ የከተበው የታሪክ ምዕራፍ ነው።

ዳግማዊ አፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ ለአንድ ዓላማ የማሰለፍ ጥበብን አስተምረውናል።

ልዩነትን ወደ ጎን በመተው ለጋራ ጠላት በአንድነት መቆም ምን ያህል ኃይል እንዳለው የታየበት ድል ነው።

አድዋ የጦር ሜዳ ላይ ድል ብቻ ሳይሆን በብልሃት የታገሉበት የዲፕሎማሲ ድልም ጭምር ነው።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷን ያስከበረችበት ድንቅ ታሪክ ነው።
በነጻ ሳይሆን ሀገር እንቁ ልጆቹ ገብራ በአጥንትና በደም የተሻገርነው የታሪክ ምእራፍ ነው።
ከገበሬው እስከ ጦር መሪው፣ ከሴት እስከ ወንድ ሁሉም ለነፃነቱና ለክብሩ ሲል ሕይወቱን የገበረበት፣ "ሀገር ካለች ነው እኔም ያለሁት" የሚለውን እውነት ለዓለም ያሳየንበት ክስተት ነው።
ዛሬም ከአድዋ የምንማረው ትልቁ ቁምነገር አንድነት ኃይል መሆኑን ነው። የታሪክ ባለአደራዎች ነንና ክብራችንን እንጠብቅ።
ለታላቅ አላማ በአንድነት በጽናት እንቁም !!

መልካም በዓል !!

01/03/2026

እንኳን ለ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!

የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያን አንድነት ማሳያ፤ የአይበገሬነት ማረጋገጫ ማሕተም ነው። ዓድዋ ከኢትዮጵያውያን አልፎ ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነጻነት ምልክት ነው። በትውልድ ቅብሎሽ ሒደት ጸንቶ የሚኖር ዘላለማዊ ክብርና ኩራትም ነው።

በጀግኖች አርበኛ አባቶቻችን ተጋድሎ የሀገራችን ብሔራዊ ክብር የተረጋገጠበት፤ ለመላው ጥቁር ህዝቦችም የነፃነት ችቦ የተለኮሰበት ታላቅ ድል ነው፡፡

የአያት ቅድመ አያቶቻችን የጀግንነት ታሪክ የሚዘከርበት የዓድዋ ድል የቅኝ ግዛት አስተሳሰብን በመስበር ለሰው ልጆች ሁሉ ሰብአዊ ክብር፣ ፍትህና እኩልነትን አብስሯል። ኢትዮጵያም የአርበኞች ሀገር መሆኗን በዓለም አደባባይ በተግባር አስመስክሯል።

የዓድዋ ድል የተገኘው በጽናት እና በሀገር ፍቅር ስሜት በተከፈለ ብርቱ መስዋዕትነት ነው፤ በአንድነት እና በጽናት ከቆምን ማንኛውንም ፈተና ማሸነፍ እንደሚቻል ዓድዋ ያስረዳናል።

ኢትዮጵያዊያን ዘመናዊ መሣሪያ ከታጠቀ የቅኝ ገዢ ኀይል ጋር ተፋልመው ድል በማድረግ ዘመን አይሽሬ ታሪክ ያኖሩት የሀገራቸውን ክብር አስቀድመው በአንድነትና በትበብር ጸንተው በመቆማቸው ነው።

የዛሬው ትውልዶች የታላቁ የዓድዋ ድል ባለአደራ ነን። ከአባቶቻችን የወረስነውን ጽናት ተላብሰን ሉአላዊነቷ የተከበረ፤ ድህነትን ታሪክ ያደረገች፤ የበለጸገች ሀገር በመገንባት ለትውልድ የማስረከብ አደራ አለብን።

የዓድዋ ድል መሠረቱ ከፍ ባለ የስነልቦና ልዕልና ለጋራ ዓላማ በጋራ መሠለፍ በመቻል የተመዘገበ ድል ነው። በዘመኑ በሕብረት ቆመን በማሸነፍ አድል አድራጊነታችን ለዓለም አሳይተናል። ዛሬም የትናንት ታሪካችንን ጠብቀን ሌላ አዲስ ታሪክ ለማስመዝገብ በጋራ መሥራት ይገባናል።

የዚህ ዘመን ትውልድ የአርበኝነት የትግል ምዕራፍ በአንድነቷ የጸናች፣ ብሔራዊ ጥቅሟ የተረጋገጠና ከድህነት የተላቀቀች ተምሳሌታዊ ሀገር መገንባት ሊሆን ይገባል፡፡

ዛሬ በላብና በጥረታችን የምናሸንፈው የድህነት ታሪክ ነገ ለትውልድ በኩራት የምናስረክበው የጋራ ክብር ነው።

ስለሆነም በዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል የጀግኖች አባቶቻችን አኩሪ ገድል ስንዘክር ከልዩነት ይልቅ አንድነትን፣ ከግጭት ይልቅ ሰላምን፤ ከጥፋት ይልቅ ልማትና እድገትን በሚያጠናክሩ ስራዎች ላይ በማተኮር ሊሆን ይገባል።

ክብር ለጀግኖች አርበኞቻችን!

ለመላ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መልካም የድል በዓል!

01/03/2026

እንኳን ለ130 ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

አቶ መካሻ አለማየሁ
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

አድዋ በአፍሪካ ሰማይ ላይ ያንዣበበውን የቅኝ ግዛት ደመና ለመግለጥ በኢትዮጵያ ላይ የወጣ ጸሀይ ነው ።
የአድዋ ድል ለኢትዮጵያው ከጦርነት ድል በላይ ነው። የኢትዮጵያዊያን አንድነት፣ ብልህነትና የአይበገሬነት ታላቅ መንፈስ የከተበው የታሪክ ምዕራፍ ነው።

ዳግማዊ አፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ ለአንድ ዓላማ የማሰለፍ ጥበብን አስተምረውናል።

ልዩነትን ወደ ጎን በመተው ለጋራ ጠላት በአንድነት መቆም ምን ያህል ኃይል እንዳለው የታየበት ድል ነው።

አድዋ የጦር ሜዳ ላይ ድል ብቻ ሳይሆን በብልሃት የታገሉበት የዲፕሎማሲ ድልም ጭምር ነው።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷን ያስከበረችበት ድንቅ ታሪክ ነው።
በነጻ ሳይሆን ሀገር እንቁ ልጆቹ ገብራ በአጥንትና በደም የተሻገርነው የታሪክ ምእራፍ ነው።
ከገበሬው እስከ ጦር መሪው፣ ከሴት እስከ ወንድ ሁሉም ለነፃነቱና ለክብሩ ሲል ሕይወቱን የገበረበት፣ "ሀገር ካለች ነው እኔም ያለሁት" የሚለውን እውነት ለዓለም ያሳየንበት ክስተት ነው።
ዛሬም ከአድዋ የምንማረው ትልቁ ቁምነገር አንድነት ኃይል መሆኑን ነው። የታሪክ ባለአደራዎች ነንና ክብራችንን እንጠብቅ።
ለታላቅ አላማ በአንድነት በጽናት እንቁም !!

መልካም በዓል !!

Address

BULGA
Debre Birhan

Telephone

+251909090909

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቡልጋ ከተማ አስተዳደር Bulga city Administration posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share