Asagirt Industry and investment office

Asagirt Industry and investment office የአሳግርት ወረዳ ኢንዱስትሪ ና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት
Asagirt woreda industry and investment office

12/09/2026
03/09/2026
21/08/2026
በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ የ"ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት" ዞናዊ  መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡በርካታ የፌዴራል፣የክልል፣የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች አንዲሁም የዞኑ አልሚ...
08/02/2026

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ የ"ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት" ዞናዊ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
በርካታ የፌዴራል፣የክልል፣የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች አንዲሁም የዞኑ አልሚ ባለሃብቶች በተገኙበት መድረክ፦

የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ ባስተላለፋት መልዕክት አምራች ኢንዱስትሪውን ለማነቃቃት በተሠራው ሥራ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል በማለት ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ዋና ዋና የማነቆ ችግሮችን የመፍታት ሥራ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን አመላክተዋል። አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች ወደ ክልሉ እንዲመጡ እና በስፋት እንዲያመርቱ ምቹ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መኾኑንም ገልጸዋል።

የክልሉን የኢኮኖሚ መዋቅር ታሳቢ ያደረጉ የሪፎርም ሥራዎች መከናወናቸውንም አቶ እንድሪስ አክለው ገልጸዋል። በዚሁ መሰረት "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ከመጀመሩ በፊት የነበረው 46 ነጥብ 2 በመቶ የማምረት አቅም አሁን ላይ ወደ 62 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ብለዋል።

ይህ የ16 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት በክልሉ የኢንዱስትሪ ልማት ላይ ትልቅ መነቃቃት መፈጠሩን ማሳያ መኾኑ ተጠቁሟል።

ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 35 አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ በመግባት ውጤታማ ተግባራትን ማከናወናቸውን አሳውቀዋል። ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት የተያዘው ግብ ስኬታማ እየኾነ መምጣቱንም አስረድተዋል።

ክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት ጸጋ በመጠቀም ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ድርሻ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

«ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት»በሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ «ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት» በሚል መሪ ሀሳብ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።ጥር 23/2018 ዓ.ም       (አሳ/ወ/...
31/01/2026

«ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት»

በሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ «ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት» በሚል መሪ ሀሳብ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።
ጥር 23/2018 ዓ.ም
(አሳ/ወ/ኢንዱ/ኢንቨ/ጽ/ቤት)

በንቅናቄ መድረኩ የአሳግርት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አላዩ ብሬ ፣የወረዳው ም/አስተዳዳሪና ሰላምና ጸጥታ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ባህሩ እሸቱ፣ በወረዳው የሚገኙ ባለሀብቶች፣ የፋይናንስ ተቋማትና የሚመለከታቸው የተቋማት አመራሮች፣ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተውበታል።

በመድረኩም የአሳግርት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አላዩ ብሬ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት “ኢትዮጵያ-ታምርት፤ እኛም እንሸምት” በሚል የተዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ በአካባቢያችን ያሉ የኢንቨስትመንት ጸጋዎችን ለይተን ወረዳችንን ለማልማትና ወደ ተሻለ ደረጃ ለመሸጋገር ቁርጠኝነትን የምንሰንቅበት ነው ብለዋል።

በወረዳችን ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ አዲስ ባለሐብቶች ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉና በዘርፉ የተሰተዋሉ ማናቆዎችን መንግስትና ባለሐብቶች በጋራ እንዲፈቱ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።

በመቀጠልም ለውይይት የተዘጋጀው ሰነድ በአሳግርት ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መረተ ገላግሌ የቀረበ ሲሆን በሳል ውይይት ተደርጎበት ተጠናቋል።

22/09/2025

Address

Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Asagirt Industry and investment office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share