12/07/2023
"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"
በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የወጣቶች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈፃሚ አቶ ድርሻዬ ደበበ ተገኝተው የደም ልገሳ ፕሮግራም አስጀምረዋል ።
የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ድርሻዬ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት አንዱ የሆነው የደም ልገሳ ተግባር ቀደም ብሎ በክፍለ ከተማችን ቀበሌዎች የተጀመረ ሲሆን በዛሬው እለትም በክፍለ ከተማ ደረጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።
ደም እጦት ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች እንደሚገኙ ገልፀው ነገር ግን የብዙዎችን ህይወት መታደግ ምንችለው ደግሞ ደም በመለገስ ነው ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።
ደም መለገስ በገንዘብ የማይተመን የሰውን ልጅ ህይወት የማትረፍ ትልቅ ስራ ነው ብለዋል።
በዛሬው እለትም ደም ለመለገስ የተሰባሰቡትን ደም ለጋሾች በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስም አመስግነዋል፡፡
አያይዘው በዛሬው እለት ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ ደም በመሆኑና በዚህም ተገኝቼ ደም መለገስ በመቻሌ ደስተኛ ነኝ ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ድርሻዬ ገልፀዋል ።
አስተያየታቸውን የሰጡ ደም ለጋሾች በገንዘብ የማይተመነውን የሰውን ልጅ ህይወት ለማትረፍ የሚያስችለውን ደም በተደጋጋሚ እየሰጡ እንደሆነና የደስታ ስሜት ከመፍጠር ውጪ የሚፈጥርባቸው የጤና ችግር እንደሌለና ሁሉም ደም መስጠት የሚችል ደም በመስጠት በደም እጦት ምክንያት የሚሰቃዩና ህይወታቸው አደጋ ላይ የወደቀ ወገኖችን ህይወት በመታደግ ረገድ ተሳትፎ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት - ደብረ ብርሃን