ድምሩ ከበደ ወንድምአገኝ

ድምሩ ከበደ ወንድምአገኝ VERY HONESTLY UTILITY.

26/03/2026

📌 በልዩ ሁኔታ በመንግስት ስም የገቡ ቆጣሪዎች ለሌላ አካል ለማስተላለፍ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች⚡️

👉 ማመልከቻ /ቅጽ መሙላት፣
👉 የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/ የፋይዳ፣ ብሔራዊ መታወቂያ/ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ፣
👉አንድ የወቅቱ ጉርድ 3X4 የሆነ ፎቶ ግራፍ፣
👉መንግስታዊ ቢሮ ስልጣን በተሰጠው አካል የስም ዝውውር እንዲደረግ የተፈቀደ ደብዳቤ፣
👉በቀድሞ ደንበኛ ስም እዳ አለመኖሩ የተረጋገጠበት ሰነድ
👉 አንድ የውል ቴምብር

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

19/01/2026
08/10/2025

የኢነርጂ አጠቃቀም፣ ቆጣሪና ተያያዥ ዕቃዎች አጠቃቀም መመሪያ ምን ይላል?

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥራት ያለው እና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር አዳዲስ የአሠራር ሥርዓቶችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ የአገልግሎት አሰጣጡን የሚያስተጓጉሉ እኩይ ተግባራት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ትልቅ ተግዳሮት ሆኖበታል፡፡ ተቋሙ እነዚህን እኩይ ተግባራት ለመከላከል የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች ያሉት የኢነርጂ አጠቃቀም፣ ቆጣሪና ተያያዥ ዕቃዎች ምርመራ መመርያ በሥራ ላይ አውሏል፡፡
#በመመሪያው መሰረት:- ➡️ የኃይል ሥርቆት መፈጸሙ የተረጋገጠ አንድ ደንበኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቱ በጊዜያዊነት ከምሰሶ ወይም ከአቅርቦት መነሻ ላይ እንዲቋረጥበት ይደረጋል፣

➡️የተቋሙ የሕግ አገልግሎት ክስ ይመሰርታል፣ ፖሊስ/አቃቤ ህግ የምርመራ ሂደቱን ማጠናቀቁን በጹሁፍ እስኪያሳዉቅ እንዲሁም ደንበኛዉ የሚጠበቅበትን ክፍያ እስኪፈፅም እና መተማመኛ የዉል ሰነድ ላይ እስኪፈርም ድረስ በስርቆት ምክንያት የተቋረጠው ኃይል ተቋርጦ የሚቆይ ይሆናል፡፡

➡️የኃይል ስርቆት የፈፀመ ደንበኛ ከሌሎች ክፍያ በተጨማሪ ዉል በመተላለፉ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚጣልበት በመመሪያው ተደንግጓል፡፡

➡️ የመኖሪያ ቤት ደንበኛ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት ፈፅሞ ሲገኝ 20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልበታል፤ የጠቅላላ ታሪፍ ተጠቃሚ 500 ሺህ ብር፣ የዝቀተኛ ኢንደስትሪ ታሪፍ ተጠቃሚ 750 ሺህ ብር፣ የመካከለኛ ኢንደስትሪ ታሪፍ ተጠቃሚ 1 ሚሊየን ብር ይቀጣል፡፡

➡️በተያያዘም ከኃይል ስርቆት ድርጊታቸው ያልታረሙና ለሁለተኛ ጊዜ የኃይል ስርቆት ሲፈፅሙ የተገኙ ደንበኞች መጀመሪያ የከፈሉትን ቅጣት እጥፍ እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

➡️ በተጨማሪ በኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት ለሁለተኛ ጊዜ ተሳትፎ የነበራቸው የዝቅተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ታሪፍ ደንበኞች 2 ሚሊየን ብር፣ የጠቅላላ ታሪፍ ደንበኞች 1 ሚሊየን ብር ተቀማጭ (Security Deposit) ለተቋሙ ማስያዝ እንዳለባቸው መመሪያው ይገልፃል፡፡

➡️ተቀማጭ ያስያዙ ደንበኞች ለተከታታይ ሁለት ዓመታት የተቋሙን ደንብና መመሪያ አክብረው በትክክለኛ መንገድ ኃይል መጠቀማቸው ሲረጋገጥ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

➡️ ከተቋሙ ሠራተኞች ውጪ ማንኛውም ግለሰብ የኃይል ስርቆት በሚፈፅም አካል ላይ ጥቆማ ካቀረበ የቅጣቱ 25 በመቶ ክፍያ የሚከፈለው ይሆናል፡፡

የኃይል ስርቆት መፈፀሙን የጠቆመ አካል ማንነት ሚስጥራዊነት የተጠበቀ ሲሆን ስማርት ቆጣሪዎችን በተመለከተ ከሲስተም በቂ መረጃ ማግኘት ስለሚቻል የጥቆማ ማበረታቻ አይከፈልበትም፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

28/06/2025
15/05/2025

አዲስ ቆጣሪ ለማግኘት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ሲመጡ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎችን ያሟሉ
*******************
ተቋማችን አዲስ ቆጣሪ የሚፈልጉ ደንበኞችን በቀላሉ መገልገል እንዲችሉ በቅርቡ አዲስ መመሪያ አውጥቶ ስራ ላይ አውሏል፡፡ እርሶም አዲስ ቆጣሪ ለማግኘት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ሲመጡ ቀጣይ የተገለፁትን ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲያሟሉ እንጠይቃለን፡፡

የነጠላ ፌዝ ቆጣሪ /Single Phase Meter/ ለማግኘት፡-

• የአመልካቹ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ፣
• አንድ ጉርድ ፎቶ /3 በ 4 የሆነ/፣
• የኪራይ ቤት ከሆነ ከባለቤቱ የተሰጠ የስምምነት ደብዳቤ፣
• ለኃይል ማሻሻያ ወይም ለተጨማሪ ቆጣሪ ከሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የመጨረሻ ክፍያ ደረሰኝ፣
• ጥያቄው ለሽርክና ማህበር ከሆነ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሽርክና ማረጋገጫ ሰነድ ኮፒ፤

• የኃይል ጥያቄው በመንግስት ለሚተዳደሩ ቤቶችና ቦታዎች ከሆነ፡-

 የኃይል ጥያቂውን ያቀረበው ቤቱን በመንግስት ስም የተዋዋለ ተከራይ ከሆነ በሚመለከተው የመንግስት አካል ፍቀድ ማግኘት እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ሲያቀርብ አገልግሎቱ የሚፈቀድለት ሲሆን፤ ማንኛውም ኃላፊነት ቤቱን የሚያስተዳድረው የመንግስት አካል ይሆናል፡፡
 የመንግስት /የቀበሌ ቤት/ ተከራይ የኪራይ ውል አያይዞ ሲያቀርብ አገልግሎቱን በተከራዩ ስም ሊያገኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን ሙሉ ኃላፊነት የተከራዩ ይሆናል፡፡

• የኃይል ጥያቄው ኃላፊነቱ ለተወሰነ የግል ድርጅት ከሆነ ከላይ በተራ ቁጥር የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ ሆኖ የድርጅቱ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የድርጅቱን ዋና ስራ አስኪያጅ ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያ፣

• ኢንስፔክሽን /ማስገመቻ ለነጠላ ፌዝ 90 ብር ይከፈላል፡፡

የሶስት ፌዝ ቆጣሪ /Three Phase Meter/ ለማግኘት፡-

• የኃይል ጥያቄው ከ14 ኪሎ ዋት እና በላይ ከሆነ ከላይ ለነጠላ ፌዝ አገልግሎት ከተጠቀሱት ማስረጃዎች በተጨማሪ በኤሌክትሪክ ነክ ሥራዎች ፈቃድ ባለው ተቋራጭ የተሰራ የኤሌክትሪክ ዲዛይን ፕላን ማቅረብ ይጠበቃል፣

• አገልግልቱን ለመስጠት ለሚከናወኑ የኢንስፔክሽን እና የማስገመቻ ክፍያዎች (በየጊዜው የሚደረገው የዋጋ ክለሳ እንደተጠበቀ ሆኖ፣

 ለባለ ሶስት ፌዝ ቆጣሪ 300 ብር፣
 ከ24 ኪሎ ዋት እስከ 120 ኪሎ ዋት 500 ብር፣
 ከ121 ኪሎ ዋት እስከ 1 ሜጋ ዋት 5000 ብር፣
 ከ 1 ሜጋ ዋት በላይ 10 ሺህ ብር ብር የሚከፈል ይሆናል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም አዲስ ቆጣሪ የሚፈልግ ደንበኛ ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች ብቻ አገልግሎቱን የምሰጥ ሲሆን፤ ከዚህ ውጪ በአቋራጭ ቆጣሪ እናስገባለን ከሚሉ ደላሎችና ግለሰቦች እንዲሁም ከሌሎች ብልሹ አሰራሮች ራሳችሁን እንድትጠብቁ በዚህ አጋጣሚ እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et

25/02/2025
19/02/2025

ሪጅኑ አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት እየሠራ ነው
*******************
የደብረ-ብርሃን ሪጅን አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ የኃይል መቆራረጥ ችግር የሚታይባቸዉ መስመሮችን በመለየት የመልሶ ግንባታ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የደብረ-ብርሃን ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ ገለጹ፡፡

ሀገረ ማርያም 33 ኬ.ቪ፣ እነዋሪ 33 ኬ.ቪ፣ አጣዬ 15 ኬ.ቪ እና አረርቲ 33 ኬ.ቪ መስመሮች የኃይል መቆራረጥ የሚስተዋልባቸው ከፍተኛ መስመሮች መሆናቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ የእንዋሪ 33 ኬ.ቪ መስመር 42 ሳታላይቶችን እና የእንዋሪ ከተማ መጋቢ መስመር በሸክላ ሲኒ የተዘረጋ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ሪጅኑ ባከናወነው መስመር ፍተሻ ስራ ከደብረብርሃን እስከ እንዋሪ የተዘረጋው 67 ኪ.ሜ መስመር፤ ከደነባ-አንጭቆረር 12.5 ኪ.ሜ እንዲሁም ከደነባ - ሲያ ደብር 16 ኪ.ሜ በአጠቃላይ 95.5 ኪ.ሜ መስመር ላይ ያሉት 6000 የሸክላ ሲኒዎች ሙሉ በሙሉ የማያገለግሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሪጅኑና ማዕከላቱ በጋራ ባከናወኑት ሥራ ከደብረ ብርሃን እስከ እንዋሪ አና ከደነባ እስከ አንጭቆረር የተዘረጉ 3 ሺህ 300 ሸክላ ሲኒዎችን ወደ ፕላስቲክ ሲኒ የመቀየር ስራ እንዲሁም የረገቡ መስመሮችን የመወጠር ስራ መከናወኑን አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም ዳይሬክተሩ በ2017 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ሪጅኑ በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን የመለየት እና የቅድመ ጥገና ሥራዎችን በስፋት ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በግማሽ ዓመቱ 1365.4 ኪ.ሜ መካከለኛ መስመር ላይ ያሉ ችግሮችን የመለየት ሥራ በማከናወን 251.5 ኪ.ሜ የቅድመ ጥገና እና 1785 ቁጥር ያለው አስቸኳይ ጥገና ስራ መሠራቱን ገልጸዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

19/02/2025

በቂ የትራንስፎርመር አቅርቦት ያለ በመሆኑ አዲስ ኃይል ጠያቂ ደንበኞች ከተቋሙ መውሰድ ይችላሉ
*******************
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቂ የትራንስፎርመር አቅርቦት ያለ በመሆኑ ደንበኞች ከተቋሙ በመውሰድ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ የተቋሙ ኢንጂነሪንግ ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ደርቤ ገለፁ፡፡

ኃይል ለማቅረብ የሚያስፈልገው የትራንስፎርመር ግብዓት በተቋሙ ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ደንበኞች ማቅረብ እንደማይጠበቅባቸው የጠቀሱት ዳይሬክተሩ በአንፃሩ የሚፈለገው ግብዓት በተቋሙ አለመኖሩ ሲረጋገጥ ደንበኞች እንዲያቀርቡ እየተደረገ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ሲደረግ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

በተለይ ከአሁን በፊት የትራንስፎርመር አቅርቦት ችግር ስለነበር ደንበኞች በራሳቸው ትራንስፎርመር እንዲያቀርቡ ፍቃድ ተሰጥቷቸው በተቋሙ ፍተሻ ከተደረገ በኋላ የጠየቁት ኃይል ባቀረቡት ትራንስፎርመር እንዲገናኝላቸው ይደረግ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ይህ አሠራር ደንበኞች እንዲጉላሉ እና ላላስፈላጊ ወጪ እንዲዳረጉ ከማድረጉም ባሻገር አንዳንድ የትራንስፎርመር አምራቾች የጥራት ችግር ሲገኝባቸው በግል ጥራት የሌለው ትራንስፎርመር ለደንበኞች በመሸጥ ዙሮ ወደ ተቋሙ መሰረተ ልማት እንዲገባ በማድረጋቸው ለሃይል መቆራረጥ መንስኤ እየሆነ በመምጣቱ ለጊዜው ደንበኞች ከአምራቾች መግዛት እንዲያቆሙ መደረጉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ተቋሙ በአገር ውስጥ ካሉና በስታንዳርዱ መሠረት ማምረት ከሚችሉ አምራቾች ጋር ውል በመያዝ ትራንስፎርመሮችን እየተረከበ እንደሆነ ተናግረው በሌላ በኩል አምርቼ ተቋሙ ሳይገዛኝ ቀረ ወይም ለመግዛት ፍቃደኛ አይደለም የሚል አምራች ካለ ጥያቄውን በግልፅ ማቅረብ ይቻላል ብለዋል፡፡

ተቋሙ ከአብዛኞቹ የሃገር ውስጥ የትራንስፎርመር አምራቾች ጋር በቅርበት እየሠራና እያበረታታ መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አምራቾች ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ዳይሬክተሩ ለአገልግሎት አሰጣጡ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ከሃገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ሃገር አምራቾች እንደሚገዛና በሃገር ውስጥ የማይመረቱ ትራንስፎርመሮችን ከውጪ የሚያስገባ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ተቋሙ የሃገር ውስጥ አምራቾችን ላለማበረታታ ከሃገር ውስጥ አምራቾች የትራንስፎርመር ግዥ አልፈፅምም እንዳለ ተደርጎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ተቋማት የቀረበው መረጃ ስህተት መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Address

Debre Birhan

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ድምሩ ከበደ ወንድምአገኝ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ድምሩ ከበደ ወንድምአገኝ:

Share