08/09/2026
አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አምስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች!
በትግራይ ክልል አበርገለ የጭላ ወረዳ በሚገኘው የጭላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከስምረት ጤና ጣቢያ የመጣች አንዲት እናት አምስት ህፃናትን በሰላም መገላገሏን የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች አስታወቁ።
በወቅቱ እናቲቱን ያወለዱት አዋልድ ነርስ ገብረዮሐንስ ደስታ እንደገለጹት፡ እናቲቱ በማህፀኗ አምስት ህፃናትን የያዘች የነበረች ሲሆን፣ አራቱ ህፃናት ሙሉ እድገታቸውን ጨርሰው በጤና ተወልደዋል።
አምስተኛው ህፃን በሁለተኛው የእድገት ደረጃ (በአምስተኛው ወር አካባቢ) እድገቱ የቆመ ቢሆንም፣ እናቲቱ አራቱን ሙሉ ጤነኛ ህፃናት እና አንዱን እድገቱን ያላጠናቀቀውን ህፃን ጨምሮ በድምሩ አምስት ህፃናትን በሰላም ተገላግላለች።
ስለ እናቲቱ የተገለጹ አስደናቂ እውነታዎች፡እናቲቱ በቤተሰቧ የመንታ ዘር ያላት ከመሆኑም በላይ፣ እሷ ራሷ የመንታ ልጅ ነች! ይህ የመጀመሪያ ልጅ መውለዷ (በኩር) እንደሆነ ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት እናቲቱ ከባድ የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባት የሆስፒታሉ ባለሙያዎች አክለው ገልጸዋል።
በአሁኑ ሰዓት የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙት እናትና ህፃናት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።
ለበለጠ መረጃ:-
Telegram:- https://t.me/DBCSH2
page:- https://www.facebook.com/DBCSH
Tiktok:- https://tiktok.com/
(መረጃው፡- የአበርገለ የጭላ ወረዳ የመረጃና ህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ነው)