ደብረብርሃን ከተማ ጠባሴ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • ደብረብርሃን ከተማ ጠባሴ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

ደብረብርሃን ከተማ ጠባሴ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን  ጽ/ቤት የደ/ብርሃን ከተማ በአፄ ዘርያእቆብ ዘመነ መንግስት በ1446 ዓ.ም የተቆረቆረች ጥንታዊ ከተማ ነች፡፡

የጠባሴ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲስ አበባ የሚኖሩ ተወላጆችን በማስተባበር ግምቱ 124,900 ብር በላይ የሚገመት የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ። በጠባሴ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የንሮ ደረጃ ለ...
01/01/2024

የጠባሴ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲስ አበባ የሚኖሩ ተወላጆችን በማስተባበር ግምቱ 124,900 ብር በላይ የሚገመት የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።

በጠባሴ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የንሮ ደረጃ ለሚገኙ 70 ለሚሆኑ ወገኖቻችን ግምቱ ከ124,900 ብር የሚገመት ለምግብነት የሚውል የአይነት ድጋፍ ተደርጓል።

በድጋፉ ወቅት የጠባሴ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መርሻ ማሞ የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ውብሸት መንግስቴ የጎል ኢትዮጵያ አስተባባሪዎች እንዲሁም የክፍለ ለተማ እና የቀበሌ አመራሮች ተገኝተውበታል።

ድጋፉን ከተለያዩ መልካም አሳቢ ወገኖች ማሰባሰብ እንደቻሉ የገለጹት አቶ ውብሸት መንግስቴ ድጋፉ በቂ ነው ባይባልም በዓሉን ምክንያት በማድረግ ወገኖቻችንን ለማሰብ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።

ስለተደረገው ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን ያቀረቡት የጠባሴ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መርሻ ማሞ ድጋፉ ዝቅተኛ የንሮ ደረጃ ያላቸውን ወገኖች ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ ከመንፈስ እርካታ ባሻገር ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን የሚያጎለብት አንድነትን የሚያጠናክር ድጋፍ እንደሆነ ገልጸዋል።

የደብረ ብርሀን ከተማ ተጨማሪ ውበት ገርበኤራ ሰው ሰራሽ የመስኖ ግድብ ጠባሴ ክፍለ ከተማ አንጎለላ ቀበሌ ይምጡ ይጎብኙ  !!!
27/06/2023

የደብረ ብርሀን ከተማ ተጨማሪ ውበት ገርበኤራ ሰው ሰራሽ የመስኖ ግድብ ጠባሴ ክፍለ ከተማ አንጎለላ ቀበሌ ይምጡ ይጎብኙ !!!

አመራሩ  ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታት ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ ።ደብረ ብረሀን :-ሰኔ 19/2015ዓ.ም (ደብኮ)አመ...
26/06/2023

አመራሩ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታት ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ ።
ደብረ ብረሀን :-ሰኔ 19/2015ዓ.ም (ደብኮ)አመራሩ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታት ተቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ ።

በደብረብርሃን ከተማ መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ በሚል መሪ ሃሳብ ከከተማ እስከ ቀበሌ ላሉ የፓርቲ አመራሮች ሲሰጥ የሰነበተው ስልጠና ተጠናቀቀ።

የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጌታቸው እንደገለጹት አመራሩ በመልካም ስነምግባር ህብረተሰቡን በቅንነት ማገልገል እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የከተማው ሠላም በዘላቂነት ተጠብቆ እንዲዘልቅ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን ሆኖ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የማዳበሪያ አቅርቦት፣የኑሮ ውድነት፣የሥራ አጥነት ችግር እንዲፈታ በየደረጃው እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ካሳሁን እምቢአለ መድረኩን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት ስርቆትን በጽናት ታግሎ በማስተካከል እና የአመራር አንድነት በማጠናከር ለህዝብና ለመንግስት የሚጠቅም ተጨባጭ ስራ መፈጸም እንደሚጠበቅ አሳውቀዋል፡፡
በተለይም አመራሩ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታት ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡አመራር በተግባር ሰርቶ ውጤት ማምጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
አሁን እንደ ሀገር ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመፍታት ለሀገረ መንግስት ግንባታ የምክክር ኮሚሽኑ ስራ ፋይዳው የጎላ መሆኑን አንስተው ለተግባራዊነቱ ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አመልክተዋል፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ ከ57 ሺህ በላይ ወጣቶችን በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማሳተፍ መታቀዱ ተገለጸበጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ -2 በሚል መሪ መልዕክት የደብረ ብርሃን ከተማ ወጣትና ስፖር...
23/06/2023

በደብረ ብርሃን ከተማ ከ57 ሺህ በላይ ወጣቶችን በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማሳተፍ መታቀዱ ተገለጸ

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ -2 በሚል መሪ መልዕክት የደብረ ብርሃን ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ የ2015ዓ.ም የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ይገኛል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ቶማስ መኮንን የእንኳን ደህና መጣችሁ የመከፈቻ ንግግር አድርገዋል።

በ2014ዓ.ም በክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት በክልሉ ከሚገኙ ከተሞች 1ኛ መውጣቱን አንስተዋል።በዚህ ዓመትም በተመሳሳይ የላቀ አፈፃጸም ለማስመዝገብ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
በመጪው ክረምት በደብረብርሃን ከተማ 57 ሺህ 540 ወጣቶችን በማሳተፍ 57 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ሃብት ከወጪ ማዳን እንደሚቻል ተገልጿል።

በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳዳር ትጥቅ ይዘው ህውከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው ግለሰቦች በተኩስ ልውውጥ ከነ ጦርመሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ። በከተማ አስተዳደሩ በእቴጌ ...
23/06/2023

በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳዳር ትጥቅ ይዘው ህውከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው ግለሰቦች በተኩስ ልውውጥ ከነ ጦርመሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በከተማ አስተዳደሩ በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ሳሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቦሰና ምንጭ በሚባል አካባቢ ቁጥራቸዉ በርከት ያሉ ሰዎች በጦር መሳሪያ የተደገፈ ህውከትና ብጥብጥ ለመፍጠር እየተዘጋጁ መሆኑ መረጃው ለጸጥታ ሀይሉ ይደርሳል።
ጉዳዩን በመረጃ ያጠናከረው የጸጥታ ሀይሉ ሰኔ 14 ለ15/2015 ዓ/ም ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ድንገተኛ የተቀናጀ ስምሪት ተደርጎ ከሰዓታት ከባድ የተኩስ ምልልስ በኋላ የጥፋት ግለሰቦች ከነ መሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በአካባቢው የከፋ ጉዳት እንዳይፈጠር የፀጥታ ሀይሉ እጅግ በከፍተኛ ጥንቃቄ በወታደራዊ ጥበብ ያለምንም ኪሳራ ያለ መስዕዋትነት ድል ማድረግ ችሏል።

በኦፕሬሽኑ 26 ግለሰቦች ከነ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን አራት እስናይፐር ከ1261 ጥይት ጋር፣አንድ ድሽቃ ከ490 ጥይት ጋር፣5 ክላሽ ከሰባት ካርታና 530 ጥይት ጋር፣ 2 ብሬን፣ 3 የእጅ ቦንብ፣ ሁለት የቱርክ ሽጉጥ ከመሰል ስምንት ጥይት ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።

መረጃው የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ነዉ

የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚዛናዊና ፈጣን  መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ ።ደብረ ብረሀን :- ሰኔ 13/2015ዓ.ም (ደብኮ)የኮሙንኬሽን ባለሙያዎች ሚዛናዊ...
20/06/2023

የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚዛናዊና ፈጣን መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ ።
ደብረ ብረሀን :- ሰኔ 13/2015ዓ.ም (ደብኮ)የኮሙንኬሽን ባለሙያዎች ሚዛናዊና ፈጣን መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ ።
የደብረ ብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ለኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በዜና አዘገጃጀት እና አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ ።
ስልጠናው የዜና ዕቅድ፣ይዘት አመራረጥ፣አጭር ዜና አዘገጃጀት እና አጠቃቀም ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በንድፈ ሀሳብ ተተንትኖ፤ በተግባር ልምምድ ተደግፎ ተሰጥቷል፡፡
ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከስልጠናው መጠቀማቸውንና ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው ክፍተታቸውን የሞላ፣ለቀጣይ ስራ አቅም የሚገነባ መሆኑን አንስተዋል፡፡ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስቦ ስላዘጋጀው አመስግነው ቀጣይነት እንዲኖረውም ጠይቀዋል፡፡
የደብረብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ ብዙነህ ስልጠናውን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት እስካሁን የነበሩ ክፍተቶችን አርሞ ጥንካሬዎችን አጎልብቶ ተቀናጅቶ መስራት ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በቀጣይ የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ትክክለኛ፣ሚዛናዊና ፈጣን መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

" ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችን እናሻግራለን !!” በሚል መሪ ቃል በጠባሴ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሴክተር መ/ቤት መሠረታዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ጠቅላላ የመንግስት...
01/06/2023

" ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችን እናሻግራለን !!” በሚል መሪ ቃል በጠባሴ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሴክተር መ/ቤት መሠረታዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ጠቅላላ የመንግስት ሰራተኞች የሚሳተፉበት የብልፅግና ፓርቲ ኮንፈረንስ መከናወን ጀመረ።

"ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችን እናሻግራለን !!” በሚል መሪ ቃል በጠባሴ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሴክተር መሠረታዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ጠቅላላ የመንግስት ሰራተኞች የሚሳተፉበት የብልፅግና ፓርቲ ኮንፈረንስ መከናወን ጀመረ።

በኮንፈረንሱ የጠባሴ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መርሻ ማሞ የጠባሴ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው የሺጥላ የጠባሴ ክፍለ ከተማ ም/ስራ አስፈጻሚ እና የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደምሰው ታደሰ የጠባሴ ክፍለ ከተማ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢደር ይማም የስራ ኃላፊዎች የሴክተር መስሪያ ቤት የመሰረታዊ ድርጅት አባላት እና የመንግስት ሰራተኞች ተገኝተውበታል።

በኮንፈረንሱ የሚጠብቁ አላማ እና ግቦችን በማስገንዘብ መድረኩን የከፈቱት የጠባሴ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መርሻ ማሞ
የተጀመረውን ለውጥ የማጠናከርና የማፅናት ሂደትን በጥልቀት በመገምገም ለውጡ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች በማጽናት እና የሚታዩ ድክመቶችን ማረም የሚያስችል ውስጣዊ አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም የአማራ ክልል ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ የትግል ስልት በመከተል የሚፈቱበትን የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ በጋራ በመምከር በማድረግ የጋራ መግባባት ለመያዝ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓት የውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ እየቀረበ ሲሆን በቀረበው መነሻ ጽሁፍ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይትና በችግሮቻችን ላይ በመግባባት ውስጣዊ አንድነትን የሚያጸና ማደማደሚያ ሀሳብ ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል።

DBPP

‹‹የኢትዮጵያ መዳኛ ትርክት አብሮነት፣ወንድማማችነትና በጋራ ሀገርን የመገንባት ትርክት ነው፡፡ ››  አቶ ግዛቸው ሙሉነህ***የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ የሚገኙ የዞንና የከተማ አስ...
22/05/2023

‹‹የኢትዮጵያ መዳኛ ትርክት አብሮነት፣ወንድማማችነትና በጋራ ሀገርን የመገንባት ትርክት ነው፡፡ ›› አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
***
የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ የሚገኙ የዞንና የከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ወቅታዊ ክልላዊ ሁኔታዎችን መሰረት ያደረገ ውይይት በባህር ዳር ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በውይይቱ የተገኙት የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ቀውስ የአመራር መናጋትን ይፈጥራል፤ በዚህ ምክንያት የመልካም አስተዳር ችግሮችን የሚያባብስ እና የአካባቢን ሠላም የሚያደፈርስ በመሆኑ ለዚህ የሚመጥን የሚዲያና የተግባቦት ሥራ በሁሉም አካባቢዎች በአግባቡ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡

አሁን ላይ በአገራችንም ሆነ በክልሉ ብዙ አይነት የትርክት መዛነፍ እንዳለ ያነሱት ቢሮ ኃላፊው ሀገርን ሊያድን የሚችለውን ትርክት ማጽናት ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡

‹‹የኢትዮጵያ መዳኛ ትርክት አብሮነት፣ወንድማማችነትና በጋራ ሀገርን የመገንባት፣ኢኮኖሚን የማሳደግ ትርክት ነው›› ያሉት አቶ ግዛቸው ከዚህ ውጪ ያሉ ትርክቶች ሀገርን የሚያፈርሱና ለጠላት አጋልጠው የሚሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት አድርጎ የተግባቦት ሥራ አለመስራት በኮሙኒኬሽን መዋቅሩ የሚታይ የተግባቦት ዝንፈት መሆኑን የገለጹት ቢሮ ኃፊው የአብሮነት እሳቤዎችን በሚያጎሉ ክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

ለህዝቡ መድረስ የሚገባውን ወቅታዊ መረጃ ተግባቦትን በሚያጠናክር መልኩ ሁሉንም የመገናኛ አማራጮች በመጠቀም የኮሙኒኬሽን መዋቅሩ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡


አማራ ክልል ኮሙኒኬሽን

ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት ወረዳ የምትገኝ ታላቅ ደብር ናት። ተድባበ ...
08/05/2023

ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም

ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት ወረዳ የምትገኝ ታላቅ ደብር ናት።

ተድባበ ማርያም ከደሴ በ225 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከአማራ ሳይንት ርዕሰ ከተማ አጅባር በ25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

ደብሯ ዙሪያዋ ገደል ሆኖ በግራና ቀኝ በጉንዳና ገዳማይ ጅረቶች እንዲሁም በሽሎ ወንዝ ታጅባ የምትገኝ ውብ የታሪክ አምባ ነች፡፡ አምባው ለመውጣት 12 በሮች አሉት፡፡ ፊት በር፣ ቦካ፣ ገተም፣ ሞገራ ግራኝ፣ ታሪኳ፣ የዘንጌ፣ አሳስት፣ አጎና፣ አምጣ ፈረሴን፣ አህያ መደብለያና የጌለት ናቸው፡፡ አምባው ላይ በዮሐንስ ራዕይ ላይ የ7ቱ ቤተ-ክርስቲያን አምሳያ 7 ቤተ ክርስቲያኖች አሉ፡፡

በኢትዮጵያ መስዋዕተ ኦሪት ከተሰዋባቸው አራት ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አክሱም ጽዮን፣ ተድባበ ማሪያም፣ መርጦ ለማሪያምና ጣና ቂርቆስ መካከል አንዷ ናት፡፡ በአመሰራረት ቅደም ተከል ከአክሱም ጽዮን ቀጥላ ሁለተኛዋ ጥንታዊና ብቸኛ ባለታሪክ ደብር ናት፡፡

ደብሯ ከክርስቶስ ልደት በፊት የተመሰረተች በመሆኗ ከ3 ሺህ ዓመታት በላይ ዕድሜ አስቆጥራለች፡፡ የተሰራችውም በቀዳማዊ ዳዊት የወንድም ልጅ አሚናዳብ አማካኝነት በ982ዓ.ዓ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ቤተ-ክርስቲያኗ 9 ጊዜ ፈርሶ ተሰርቷል፡፡ ብዙ ጊዜም ተጠግኗል፡፡

የአፄ ገላውዲዮስ አጽም ያረፈው በዚህ ደብር እንቁላል ግንብ በሚባለው ነው፡፡ በደብሯ በርካታ ቅርሶች ያሉ ሲሆን ንዋየ ቅድሳት፣ የብራና መጽሃፍት ገድሎች፣ ስዕሎች፣ የነገስታት ዘውዶች፣ ወንበርና አልባሳት፣ የነገስታት አጽም፣ የጥንት ነገስታት የጦር መሳሪያ ወዘተ ይገኛሉ፡፡ በድንጋይ ግድግዳና በቆርቆሮ ክዳን የተሰራ ነው፡፡

ዓመታዊ ክብረ በዓሏ አጼ ገላውዲዮስ ታቦተ ልደቷን ከእየሩሳሌም አስመጥተው ወደ ቤተ-ክርስቲያኑ ያስገቡበትን ቀን መነሻ በማድረግ ግንቦት 1 ቀን በልደታ እንዲሁም ግንቦት 2 ቀን ይከበራል፡፡

ዘገባው፦ የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው።

ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል።  ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም  ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባሕል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳ...
27/04/2023

ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል።

ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባሕል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው።

ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው።

ነፍስህ በሰላም ትረፍ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የደብረ ብረሀን ኮሙንኬሽን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ፀጥታ ለማስጠበቅ ጥሎት የነበረውን ገደብ በከፊል ማንሳቱን አስታወቀ፡፡ሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም (ደብኮ) የደብረ ብረሀን ከ...
24/04/2023

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ፀጥታ ለማስጠበቅ ጥሎት የነበረውን ገደብ በከፊል ማንሳቱን አስታወቀ፡፡

ሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም (ደብኮ) የደብረ ብረሀን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማ አስተዳደሩን ሰላም ለማረጋገጥና የህግ የበላይነት ለማስከበር አስቀምጧቸው የነበሩ ክልከላዎች በከፊል ማንሳቱን አስታውቋል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ከሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን የታወጁ ክልከላዎችን በማስፈፀም ከተማዋ ወደቀድሞ ሰላሟ እንድትመለስ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሃይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ለሁሉም የከተማው የፀጥታ መዋቅር አባላት እና ለከተማው ነዋሪዎች በሙሉ ምስጋና በማቅረብ የተጣሉ ክልከላዎችን በከፊል ከዛሬ ጀምሮ መነሳታቸውን አስታውቋል፡፡

የቀጠሉ ክልከላዎች

1. በከተማ አስተዳደሩ ከተፈቀደለት የፀጥታ አካል ውጪ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል ነው፡፡
2. የሰራዊቱን ሚሊተሪ አልባሳት ከሰራዊቱ አባላት ውጪ ለብሶ መንቀሳቀስ ክልክል ነው
3. ያለ ከተማ አስተዳደሩ ፈቃድ በተለያዩ አካባዎች በቡድን መሰባሰብ ለከተማው የሠላም ችግር መንስኤ ስለሚሆን ፍፁም ተከለከለ ነው፡፡

ከተማዋም በአሁኑ ሰዓት የቀደመ ሰላሟ ተመልሶ በፍፁም መረጋጋት ውስጥ ያለች እና ሁሉም የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ የሚገኙ በመሆኑ ሰላም ወዳዱ የደብረ ብርሃን ህዝብም አሁን ያለውን ሰላም እንዲያስቅጥል እና ማንኛውንም የተለየና አዲስ እንግዳ የሆነ ነገር ሲያጋጥም እንደተለመደው ለፀጥታ ተቋማት ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክት ተላልፏል፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ቀደመ ሰላሟ በመመልስ መደበኛ እንቅስቃሴዋን ጀምረች፡፡ሚያዚያ 04/2015 ዓ.ም (ደብኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ቀደመ ሰላሟ በመመልስ መደበኛ እንቅስቃሴዋን ጀ...
12/04/2023

የደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ቀደመ ሰላሟ በመመልስ መደበኛ እንቅስቃሴዋን ጀምረች፡፡

ሚያዚያ 04/2015 ዓ.ም (ደብኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ቀደመ ሰላሟ በመመልስ መደበኛ እንቅስቃሴዋን ጀመረች፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አሁን ወዳለችበት ሰላም እንድትመለስ አስተዋፅኦ ያበረከታችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ሁሉም የከተማችን የፀጥታ መዋቅር አባላት እና የከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ የከተማ አስተዳደሩ ትልቅ ምስጋና አቅርቧል ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ የምትገኙ የንግድ ተቋማት፣ ባንኮች፣ ሆቴሎች፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የከተማ ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች አሁን የደብረ ብርሃን ከተማ ሰላም በፊት ወደ ነበረበት የተመለሰ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ተግባራችሁ እንድትመለሱ እናሳስባለን፡፡

የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሰራተኞች በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራችሁ ገብታችሁ የተለመደ የህዝብ አገልግሎት እንድትሰጡ እናሳስባለን፡፡

በተመሳሳይ ትምህርት ቤቶች ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገቡ የሚመለከታችሁ የትምህርት ተቋማት አመራሮች ኃላፊነት ወስዳችሁ የመማር ማስተማር ስራ እንድትጀምሩ እንገልፃለን፡፡

በከተማችን አሁን የሀገር መከላከያ ሰራዊት የገባ ስለሆነና ከመደበኛው የፀጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት የከተማዋን ሰላም ለማረጋገጥ በጋራ እየሰራ ስለሆነ ፀጥታ ለማስከበር በሚደረገው ሂደት ሁሉም አካል ለዚህ ተባባሪ እንዲሆን እናሳስባለን፡፡

የከተማዋ ወጣቶችም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በተሳሳተ መረጃ ከመፈረጅ ወጥታችሁ ከሰራዊቱ እና ከከተማው የፀጥታ መዋቅር ጋር በጋራ እና በትብብር እንድትሰሩ እያሳሰብን ሆን ብሎ አፍራሽ ተልእኮን ይዞ የሚሰራ አካል ካለ ግን የከተማ አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አሁንም ያሉ ችግሮችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ በውይይት በአገር ሽማግሌዎች በሀይማኖት አባቶች የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል እና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በልዩ ሁኔታ በከተማችን ለምትገኙ ተፈናቃዮች የመጣዉ ሰላም ወደ ነበረበት እስከሚመለስ እና የከተማ አስተዳደሩ የፀጥታ ምክር ቤት ያወጣው የሰአት እላፊ ገደብ ያልተነሳ መሆኑን አውቃችሁ በካምፓችሁ ብቻ እንድትቀመጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

በከተማችን የምትገኙ እና ከአጎራባች ወረዳዎች የመጣችሁ ወጣቶች አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከመክፈል ተቆጥባችሁ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከከተማው የፀጥታ መዋቅር ጎን እንድትሰለፋ ጥሪ እናስተላለፋለን ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ያወጣቸው ክልከላዎች ላልተወሰነ ጊዜ የሚቀጥሉ ሲሆን እነዚህን ክልከላዎች ተላልፎ በሚገኝ አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር
ሚያዚያ 04/2015 ዓ.ም

Address

Debre Birhan
1000

Telephone

+251911776619

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደብረብርሃን ከተማ ጠባሴ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ደብረብርሃን ከተማ ጠባሴ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት:

Share