Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ

Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ Deputy Prime Minister of Ethiopia 🇪🇹

03/06/2026
የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዐት የሚረጋገጠው በጥራት፣ በዓይነት እና በብዛት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በራስ ዕውቀት፣ በራስ ክህሎት እና በራስ ቴክኖሎጂ ማምረት ስንችል ነው፡፡መንግሥትም በ...
03/06/2026

የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዐት የሚረጋገጠው በጥራት፣ በዓይነት እና በብዛት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በራስ ዕውቀት፣ በራስ ክህሎት እና በራስ ቴክኖሎጂ ማምረት ስንችል ነው፡፡

መንግሥትም በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የታለመውን ዘላቂ ዕድገት እና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ፖሊሲዎችን አሻሽሏል፡፡ አሠራሮችን ዘርግቷል፡፡ ማበረታቻዎችን አድርጓል።

የዚህ ሪፎርም አካል የሆነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄም ፍሬው በግልጽ እየታየ ነው።

ኢትዮጵያውያን በታሪካችን አዲስ የድልና የከፍታ ምዕራፍ ፅፈናል!ሕዝባችን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በነቂስ በመትመም፣ ጠንካራና ሉዓላዊ ሀገረ ...
02/06/2026

ኢትዮጵያውያን በታሪካችን አዲስ የድልና የከፍታ ምዕራፍ ፅፈናል!

ሕዝባችን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በነቂስ በመትመም፣ ጠንካራና ሉዓላዊ ሀገረ መንግሥት ሊመሠረት የሚችለው በሕዝብ ነጻ ፍላጎትና በምርጫ ብቻ መሆኑን በተግባር አረጋግጧል።

ከዚህ ታሪካዊ ሂደት የምንማረው ታላቅ እውነት አለ፤ በሀገራችን የፖለቲካ ስልጣን ከሕዝብ ነጻ ድምፅ ውጪ በየትኛውም ሌላ አማራጭ፣ በኃይልም ሆነ በጣልቃ ገብነት ሊመጣ እንደማይችልና እንደማይፈቀድ።

ኢትዮጵያውያን የትኛውንም ልዩነት በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚችሉ የሰለጠነ ዴሞክራሲ አራማጆች መሆናቸውን ለዓለም አስመስክረዋል።

እያንዳንዱ ዜጋ በብርድ፣ በቀትር ፀሐይ፣ በጨለማና ረጅም ሰዓታትን ተሰልፎ በመጠበቅ ሳይታክት በምርጫ ጣቢያ ተገኝቶ ድምፅ የሰጠው የሀገሪቱን የወደፊት እጣ ፈንታ የመወሰን አቅም እንዳለው በጥልቅ ተረድቶ ነው።

ለዚህ ታሪካዊ ስኬት መገኘት ባለፉት ዓመታት የጀመርናቸው ተቋማዊ ሪፎርሞች ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። በተለይም በገለልተኝነትና በጥንካሬ የተገነቡ የዴሞክራሲ ተቋማት በሕዝባችን ዘንድ የፈጠሩት ከፍተኛ ቅቡልነትና እምነት ለዛሬው ስልጡን ሂደት ዋነኛ መሰረት ሆኗል።

በመጨረሻም ማረጋገጥ የምፈልገው፣ የዚህ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ምንም ይሁን ምን ኢትዮጵያ አሸንፋለች! የኢትዮጵያን መፍረስና መበታተን ሲመኙ የነበሩ፣ በምርጫው ሰበብ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሌሊትና ቀን ያሴሩ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ፍላጎትና እኩይ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።

የሀገራችንን አንድነትና ህልውና አስከብራችሁ፣ በነጻነት ድምፃችሁን ለሰጣችሁ ለመላው የሀገራችን ሕዝቦች የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

02/06/2026

የሀገር ግንባታ ሂደትን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር እና የሕዝብ አደራን ለመጠበቅ ብቸኛው መንገድ በርትቶ መሥራት ነው።

ዛሬ ጠዋት መርቀን አገልግሎት ያስጀመርነው ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም የተሠራው የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም በመንግሥታችን ከዛሬ የተሻገረ ራዕይ፣ ዕቅድና በዜጎቻችን ትጋት እየተመራ ለስኬት የበቃ ህያው ዐሻራችን ነው።

02/06/2026
01/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

01/06/2026

የላቀ የዜግነት ቁርጠኝነት ተምሳሌት!

በሰሜን ሽዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ፣ አባያ ቀበሌ (ሳክላ ምርጫ ጣቢያ) እጅግ ልብ የሚነካ እና ታላቅ የዜግነት ኃላፊነት የታየበት ክሥተት ተመዝግቧል።

ልጃቸው በሞት የተለየባቸው ቤተሰቦች፣ አስከሬን በቤት አስቀምጠው 7 የቤተሰቡ አባላት በማለዳ ወደ ምርጫ ጣቢያ አምርተዋል። በቦታው የነበረው ማኅበረሰብም ለኀዘናቸው ጥልቅ ክብር በመስጠት፤ ሰልፍ ሳይጠብቁ ቅድሚያ ሰጥተዋቸው ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ወደ ልቅሶ ቤታቸው ተመልሰዋል።

ይህ ተግባር ሕዝባችን በምርጫው ሂደት ላይ ያለውን ጽኑ እምነት እና ለሀገሩ ያለውን የላቀ ክብር በተግባር ያረጋገጠበት ህያው ምስክር ነው።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው! ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ ሀገረ መንግሥታቸውን ሊያጸኑ ከቤት ሲወጡ ፀሐይ አልቀደመቻቸውም። እንኳን ወደ ምርጫ ጣቢያ ወደ አድዋም ዘምተናል ብለው ተመሙ። እነሆ ታሪ...
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ ሀገረ መንግሥታቸውን ሊያጸኑ ከቤት ሲወጡ ፀሐይ አልቀደመቻቸውም። እንኳን ወደ ምርጫ ጣቢያ ወደ አድዋም ዘምተናል ብለው ተመሙ። እነሆ ታሪክን ሊሠሩና ታሪክን ሊጽፉ ድምፃቸውን እየሰጡ ነው!

እኔም እንደ አንድ ዜጋ በዚህ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በባሕር ዳር ከተማ የምርጫ ክልል በመገኘት ድምጼን ሰጥቻለሁ።

ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓታችን ምሦሶ፣ የሕዝባችን ድምፅ ደግሞ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚመራ መንግሥትን መመሥረቻ ነው። ዛሬ የምንሰጠው እያንዳንዱ ድምጽ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ብልጽግና የሚኖረው አስተዋጽዖ የላቀ ነው።

መላው የሀገራችን ሕዝብ በነቂስ በመውጣት በድምፁ የነገ ዕጣ ፈንታውን እየወሰነ፣ የሀገሩን የዴሞክራሲ ፍኖት ለዓለም በማሳየት ተአምር እየሠራ ይገኛል።

ይህ የዴሞክራሲ ጉዟችን ማጽኛ የሆነው ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጋ እስከ ምሽት ድረስ ድምፁን እንዲሰጥና ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ አቀርባለሁ!

27/05/2026

Address

Debra Markos

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ:

Share