Machakel woreda industry and investment office

Machakel woreda industry and investment office ኑ ማቻከለን አብረን እናልማ

በማቻክል ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስደው ከተሰማሩት ውስጥ በዘበበብ ታዳጊ ከተማ በንብ ማነብና ደን ልማት ፕሮጀክት የተሰማራው ባለሃብት የአቶ ታዴ ቀለ...
05/06/2023

በማቻክል ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስደው ከተሰማሩት ውስጥ በዘበበብ ታዳጊ ከተማ በንብ ማነብና ደን ልማት ፕሮጀክት የተሰማራው ባለሃብት የአቶ ታዴ ቀለሙ ግንባታን አፈጻጸም ሂደት የሚያሳይ

25/05/2023
16/05/2023
16/05/2023

የአማራ ክልል ወደ ከፍታ የሚያደርገውን ጉዞ በህዝቦቹ ብርታት አጠናክሮ ቀጥሏል፤ማንም የራሱን የፖለቲካ አጀንዳ ከክልሉም ሆነ ከሕዝብ ሊያስበልጥ አይችልም፡፡

የትኛውም ሃይል ከአማራ ኢትዮጵያዊነት ከፍታ ሊያወርደን አይደለም ትልቁን ምስላችንን እንዲያደበዝዝ አንፈቅድለትም፤ምክንያቱም አማራ ከምንም ይልቃል፡፡ በክልላዊ አንድነት ጥላ ስር ተሰብስበን ለሃገራዊ ለውጥ የምንተጋበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡

ለዘመናት በተካሄደ ትግል በልጆቿ በተገነባች ኢትዮጵያ ውስጥ በዴሞክራሲና በነፃነት እየኖሩ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እገዛ ከማድረግ እና የብልጽግና ጉዟችንን ከማፋጠን ይልቅ በጽንፈኝነት ፈረስ ጋልቦ የራስን የስልጣን ጥም ለማርካት ከውስጥም ከውጭም በባዕዳን ነዋይ ተደልለው በገዛ ሀገራቸው የጸረ-አንድነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ተመልክተናል፡፡

ሆኖም ግን ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በማጎልበት ለእንደዚህ አይነቱ የጸረ አንድነት እንቅስቃሴ ምላሽ የሚሆን ህዝብን ያማከለ ስራ እየተሰራ ነው፡፡ ክልሉን በለውጥ ሃዲድ ውስጥ ማሻገር የሚቻለው የክልሉን ህዝብ አንድነት ማጎልበት እና ትስስሩን ማጠናከር ሲቻል ነው፡፡

ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በፈተና ውስጥ አልፎ ነገን ለድል የሚበቃ የአሸናፊነት ተምሳሌት የሚሆን እና ሰፊ የህዝብ መሰረት ያለው ልማታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ሲቻል መሆኑን ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ እውነት ነው፡፡ የአማራ ክልልን ወደ ከፍታ የማሸጋገር ሂደቱ በሁሉም የክልሉ ህዝብ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ትውልዱ ዕውነትን ይዞ ህዝብን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሻገር ታሪካዊ አደራ የተጣለበት ጊዜ ላይ ይገኛል፡፡ አንድነትን፣ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን፣የእርስ በእርስ መተሳሰብን በጥቅሉ የቆዩ እሴቶቻችንን ለመመለስ እየተሰራ ሲሆን እነዚህን ወደ ኋላ ለመመለስ ከሚጥሩ ሃይሎች ጋር ፊት ለፊት መታገል ያስፈልጋል፡፡

ያለ ፈተና ድል አይገኝም፣ያለ ውድድር አሸናፊነት የለምና ባለፉት የለውጥ ዓመታት እንደ ክልልም ሆነ እንደ አገር በርካታ ተግዳሮቶች ቢገጥሙንም ከህዝባችን ጋር በመሆን ከገጠመን የመፈራረስ አደጋ እንድንወጣና ህልውናችን እንዲቀጥል ታሪክ የማይረሳው ስራ ተሰርቷል፤ምንም እንኳ ውስጣዊ ቀሪ ፈተናዎችን መወጣት የግድ ቢሆንም፡፡

•~•~•


°~~~~°
"ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"

ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
Facebook ፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100064441132268
Telegram ፦https://t.me/+-lkHrR7G6gFmNWVk
ትዊተር ፦https://twitter.com/GojjamZone?t=LLH7s_4hUhLuxPw6AsDlNg&s=35

Youtube:https://youtube.com/channel/UCT7iBR5_KZKOZG2nO71AXgg

✍️✍️በቀን 03/7/15 ዓ/ም በዝበበብ ከተማ የማህበረሰብ ውይይት ተደረገ✍️✍️የማቻክል ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመን ጽ/ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ከዝበበብ ታዳጊ ከተማ እና...
13/03/2023

✍️✍️በቀን 03/7/15 ዓ/ም በዝበበብ ከተማ የማህበረሰብ ውይይት ተደረገ✍️✍️

የማቻክል ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመን ጽ/ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ከዝበበብ ታዳጊ ከተማ እና ከአማሪ የወበሽ ቀበሌ መሀበረሰብ ጋር በእለቱ የጋራ ወይይት ተደርጓል።

1ኛ.ለሚመጡ ባለሀብቶች አካባቢያችን እንዲያለሙ እንዴት ቀና ሆነን እናስተናግዳለን እና የጋራ የደንበር መሬት ላይ እንዴት እንፍታ የሚልና
2ኛ.በመዓድን ዘረፍ ወጣቶችን እንዴት እናሰማራ በሚል እና መሰል ተግባሮች ሲሆን
✍️ውይይቱ ከአካባቢው መሀበረሰብ ጋር የተደረገ ሲሆን በጋራ ከማን ምን ይጠበቃልና አካሄዳቸውን ጠብቀው የሚሰሩ ስራወችን መሀበረሰቡ በማንሳት የጋራ በማድረግ የተሻለ መግባባትን የሚያመጣ ውይይት ተደርጓል።

💗በቀን 27/6/15 ለኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታ ማህበረሰቡ ፈቀደ💗በዚህ እለት በዝበበብ ታዳጊ ከተማ የ2 የዱቄት ፋብሪካወች መትከያ የሚሆን መሬትን ከማህበረሰቡ የዝች ከተማ መሀበረሰብ የለ ...
12/03/2023

💗በቀን 27/6/15 ለኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታ ማህበረሰቡ ፈቀደ💗

በዚህ እለት በዝበበብ ታዳጊ ከተማ የ2 የዱቄት ፋብሪካወች መትከያ የሚሆን መሬትን ከማህበረሰቡ የዝች ከተማ መሀበረሰብ የለ ኢንቨስትመንት የከተማ ለውጥ አይመጣም ለልጆቻችን የስራ እድል መፍጠርያ ይሆናል የተለያዩ የደረጃ ለውጦችን የምናይበትና የተሻሉ ባለሀብቶችን ወደቀበሌያችን የምንስበው የመጡትን ባለሀብቶችን ስንቀበል ነው ሲል በመወያየት ፈቃድ ሰጥቷል ።

 # #ማቻክል በ 40 ሚልዮን ብር በጀት  የተገነባውን የነዳጅ ማድያ አስመረቀች።************************************************ በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረ...
17/01/2023

# #ማቻክል በ 40 ሚልዮን ብር በጀት የተገነባውን የነዳጅ ማድያ አስመረቀች።
************************************************ በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ ገዘም ታዳጊ ከተማ በአቶ አሰፋ ዘሪሁን በተባለው ባለ ሃብት የተገነባው የነዳጅ ማድያ የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪ በአቶ መንበሩ ዘውዴ ፣የሚመለከታቸው የዞን አመራሮች፣የወረዳ እና የከተማ ወረዳ አመራሮች በተገኙበት በድምቀት ተመረቋል።
በነዳጅ ማድያው የምረቃ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ዘውዴ በ አሰፋ ዘርሁን የተገነባው የነዳጅ ማድያ በወረዳው ወስጥ ባለው የማድያ እጥረት ምክንያት የሚፈጠረውን የነዳጅ አቅርቦት ችግር የሚፈታ መሆኑን በመግለጽ ማድያው የራሱ የሆነ የከርሰ-ምድር ውሃ፣የተሽከርካሪ ማቆምያ እንዲሁም የአስተዳድር ቢሮዎችን ያካተተ ግንባታ እንዳለው የተናገሩት አስተዳዳሪው ማንኛውም ባለሃብት ለልማት ወደ ወረዳው ቢመጣ ያለምንም ቢሮክራሲ የሚያስተናግድ መሆኑን ተናግረዋል።

ሌላው በምረቃ ፕሮግራሙ በክብር እንግድነት የተገኙት የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መንበሩ ዘውዴ ትርፍ አምራች የሆነውን ዞን በሁሉም ተግባር ቀዳሚ ለማድረግ በተለያዮ ዘርፎች መሰማራት ከሚፈልጉ ባለ ሃብቶችን ጋር በቅርበት እየንደሚራ በመግለጽ በማቻክል ወረዳ በአሰፋ የተገነባው የነዳጅ ማድያ በማድያዎች ቁጥር ማነስ ምክንያት የሚፈጠረውን የነዳጅ አቅርቦት እና ወረፋ ችግርን ለመቅርፍ ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

Address

Machakel Woreda Debere Markos Amhara Region Of Ethiopia
Debra Markos

Telephone

+251904595202

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Machakel woreda industry and investment office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Machakel woreda industry and investment office:

Share