14/03/2026
የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነዉ!
በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በቀንና በሌሊት ፈረቃ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
ፕሮጀክቱ በ153 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ግንባታውን በሚመጣው ሚያዝያ ወር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው።
ፕሮጀክቱ የህዝቡን የቆየ ጥያቄ ከመመለሱ ባለፈ፣ ለአካባቢው ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ይኖረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያከናወናቸው ካሉ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው ይህ ማረፊያ፣ የከተማዋን የንግድና የቱሪዝም እንቅስቃሴ ያነቃቃል ተብሎ ይጠበቃል።