06/05/2026
#ታዳሽ ኃይል !
በሀገራችን ፈጣን ኢኮኖሚ ዕድገት እና በሕዝብ የአኗኗር ዘየ መቀየር የተነሣ የኃይል ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል፡፡ ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ዐቅምን ለማሳደግ ፓርቲያችን በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡ ባለፉት ዓመታት የተጀመሩትን የሕዳሴ ግድብን አጠናቀን የኮይሻ ግድብን በከፍተኛ ፍጥነት ለማጠናቀቅ ፓርቲያችን እየሠራ ይገኛል፡፡
ባለፉት ዓመታት የተጀመሩ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ ቃል ገብተን ነበር፡፡ ከዚህ ውስጥ ከለውጡ በፊት በፕሮጀክት አመራር እና በሌሎች ተያያዥ ችግሮች ምክንያት ከፍተኛ እክል ገጥሞት ቆሞ የነበረውን የሕዳሴ ግድባችንን በውጤታማነት አጠናቀናል። በሠራናቸው ውጤታማ ሥራዎች ፕሮጀክቱ በጳጉሜን 2017 ተገባዶ በይፋ ተመርቋል።
በጊቤ-3 እና ኮይሻ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ፈተና ነበረባቸው፡፡ ችግሮቻቸውን ፈተን ጊቤ ሦስት ተጠናቆ ወደ ሙሉ ሥራ ገብቷል። የኮይሻ ፕሮጀክት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 72.5 በመቶ ደርሷል። በተጨማሪም ከነፋስ ኃይል የሚያመነጩት የአይሻ እና አሰላ ፕሮጀክቶች በጥሩ አፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አይሻ 85.9 በመቶ፣ አሰላ ደግሞ 93.4 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደርሰዋል።
በአጠቃላይ ከታዳሽ ኃይል ኤሌክትሪክ የማመንጨት ዐቅማችን በ2012 ከነበረው 4,478 ሜጋ ዋት፣ በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 9,704.1 ሜ.ዋ ደርሷል። 21.1 ሺህ ኪ.ሜ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መሥመሮችን ዘርግተናል፡፡ በ2014 በጀት ዓመት 4.3 ሚልዮን ተጠቃሚዎች ከብሔራዊ ግሪድ ይጠቀሙ ነበር፡፡ በ2017 በጀት ዓመት ይህን ቁጥር ወደ 5.2 ሚልዮን ለማሳደግ ተችሏል።
የኃይል አቅርቦት መሠረተ ልማት፣ ኃይልን ከማመንጨት ያለፈ ሥራ ይፈልጋል፡፡ የማሠራጫ፣ የማስተላለፊያና የሰብ ስቴሽን መሠረተ ልማቶችን ጎን ለጎን ማከናወንን ይጠይቃል፡፡ ከዚህ አንጻር የተሠራው መሠረተ ልማት በቂ ያልሆነና የፍትሐዊነት ጥያቄ የሚነሣበት ነበር። በዚህም የተለያዩ አካባቢዎች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች የኃይል ተጠቃሚነት ሳይረጋገጥ ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል።
ፓርቲያችን ይህንን የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ለመመለስ የኃይል ማስተላላፊያ፣ የማሠራጫ እና የሰብስቴሽን ማስፋፊያ ፕሮግራሞችን ቀርጾ ተግባራዊ አድርጓል። እነዚህ መሠረተ ልማቶች፣ በተወሰነ ደረጃ የኅብረተሰባችን የኃይል አቅርቦት ጥያቄ እንዲመለስ ለማድረግ አስችለዋል።
ፓርቲያችን ኢትዮጵያ ያላትን የታዳሽ ኃይል ዕምቅ ዐቅም ጥቅም ላይ በማዋል በአፍሪካ ደረጃ አረንጓዴ ልማትን ለማረጋገጥ እየሠራ ነው። በተለይ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ ባደረግነው ርብርብ ተጨማሪ ኃይል አግኝተናል፡፡ ከዚህም ከሀገር ባለፈ ለቀጣናው ሀገራት ወደ ውጭ መላክ ችለናል፡፡ በዚህ መሠረት በ2017 የበጀት ዓመት 335.7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ችለናል።
በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከኤሌክትሪክ ኤክስፖርት 246 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
- Facebook
https://www.facebook.com/dmprosperity
- Twitter https://x.com/DMCityPP03/status/1944331259439644898?t=bw56-VDAVeL9g5k3Y1a_fg&s=19
- You tube
https://www.youtube.com/