Gozamin Woreda Youth & Sport Office

Gozamin Woreda Youth & Sport Office የስፖርት ህዝባዊነት በጋራ እናረጋግጥ !!

ጎዛምን ይለያል ስል በምክንያት ነው!!!
11/02/2026

ጎዛምን ይለያል ስል በምክንያት ነው!!!

ሰላም ለሀገራችን !!!!!መጋቢት 25/2017 ዓ/ም :9ኛው መላው የምስራቅ ጎጃም ዞን ዘመናዊ የስፖርት ውድድር ዛሬ በደ/ማርቆስ ከተማ በተጀመረበት ዕለት የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሓላ...
04/04/2025

ሰላም ለሀገራችን !!!!!
መጋቢት 25/2017 ዓ/ም :
9ኛው መላው የምስራቅ ጎጃም ዞን ዘመናዊ የስፖርት ውድድር ዛሬ በደ/ማርቆስ ከተማ በተጀመረበት ዕለት የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሓላፊ አቶ ቢሻው ሞላ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ወጣቱ ከስፖርቱ እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ለሀገር ሰላምና አንድነት በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ውድድሩ በቅርቡ በክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አማካይነት ደሴ ላይ ለሚዘጋጀው 9ኛው የአማራ ክልል ዘመናዊ የስፖርት ውድድር የሚሳተፉ ስፖርተኞችን ለመመልመልና የዞኑን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ዓላማ ያደረገ ነው ያሉት አቶ ቢሻው በውድድሩ ከ14 ወረዳዎች የተውጣጡ 450 ስፖርተኞችም እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል።
በመክፈቻው የአትሌቲክስ ውድድር
በ5 000 ሜትር ወንዶች
💐1ኛ መላኩ ክቡር፣
💐2ኛ አባትነህ እንዳላማው፣
💐3ኛ ሲሳይ አስረሳኸኝ ሁሎችም ከጎዛምን ወረዳ ከአ1_ 3 ደረጃ በመያዝ አሸናፊ ሆነዋል።

በ100 ሜትር ወንዶች ውድድር፣
🎒1ኛ ብርሀኑ አባትሁን ከጎዛምን ወረዳ፣
🌷2ኛ ሻምበል ደሳለኝ ከአነደድ ወረዳ፣
🎒3ኛ ገበየሁ አድማስ ከጎዛምን ወረዳ
ደረጃ የያዙ ሲሆን
በተመሳሳይ 100 ሜትር ሴቶች ውድድር
🥀1ኛ የማርውሀ ብርሀኔ ከአዋበል ወረዳ
🥀2ኛ ማስተዋል ላንክረው ከሉማሜ ከተማ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል።
ውድድሩ እንደቀጠለ ነው።

ሰላም ሰላም!በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!      ዛሬ 05/11/15 ዓ.ምየ 2015 ክረምት በጎ ፍቃድ ስራ " የነገር ዛሬ እንትከል "" በሚል መሪ ቃል በጎዛምን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከዞን ...
12/07/2023

ሰላም ሰላም!
በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!
ዛሬ 05/11/15 ዓ.ም
የ 2015 ክረምት በጎ ፍቃድ ስራ
" የነገር ዛሬ እንትከል "" በሚል መሪ ቃል በጎዛምን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከዞን መምሪያ ጋር በመተባበር በጎዛምን ወረዳ አዲስ ጉሊት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሂዷል!!

እኛ እያለን እህቴ/ወንድሜ በትምህርት ቁሳቁስ አይቸገሩም በማለት የወረዳው አመራሮች በግምባር ቀደምነት የበጎነት ተሳትፎዉን ጀምረዋል።✍️አቶ ሙሉሰው ቀሬ:-1000ብር✍️አቶ አለሙ ውበት :-1...
10/07/2023

እኛ እያለን እህቴ/ወንድሜ በትምህርት ቁሳቁስ አይቸገሩም በማለት የወረዳው አመራሮች በግምባር ቀደምነት የበጎነት ተሳትፎዉን ጀምረዋል።

✍️አቶ ሙሉሰው ቀሬ:-1000ብር
✍️አቶ አለሙ ውበት :-1000 ብር
✍️ወ/ቢ ንፁህ አባት:- 1000 ብር
✍️ወ/ሮ አለምነሽ ታምሩ:- 1000 ብር
✍️ወ/ሮ ብዙነሽ አለሙ :- 2 ደርዘን ደብተር
✍️ወ/ሮ ያለምወርቅ ግዛቸው :-1000 ብር
✍️ ወ/ሮ እፁብድንቅ ተሻለ :-500ብር
✍️አቶ ድረስ ካሳ:-1ደርዘን ደብተር
✍️ወ/ሮ በላይነሽ ዋለልኝ:-1ደርዘን ደብተር ቃል ገብተዋል።
እናመሰግናለን
በጎነት ለራስ ነዉ!!!

ሰላም ለሀገራችን ለሁላችን !!!በጎዛምን ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ጽ/ቤት  የ2015ዓ.ም የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ እቅድ የንቅናቄ መድረክ በ29/10/15  ተካሂዷል። በዚህም በክረ...
07/07/2023

ሰላም ለሀገራችን ለሁላችን !!!
በጎዛምን ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ጽ/ቤት የ2015ዓ.ም የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ እቅድ የንቅናቄ መድረክ በ29/10/15 ተካሂዷል። በዚህም በክረምት ወራት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የጋራ መግባባት ተችሎአል።
1ኛ. 26 የአቅመ ደካማ ቤቶች በአዲስ ይሰራሉ!
2ኛ. 52 የአቅመ ደካማ ቤቶች ይጠገናሉ!
3ኛ. በአረንጓዴ አሻራ 7,464,396 ሚሊየን ችግኝ በወጣቶች ይተከላል!
4ኛ. 100 ዩኒት ደም ይለገሳል!
5ኛ. 5034 ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ያገኛሉ!
6ኛ. 10 ትምህርት ቤቶች የመጠገን ይስራ ይሰራል!
7ኛ. ለ2520 ተማሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ ይደረጋል!
8ኛ. በሰብል የጎጃም ገብሬዎችን በማገዝ!
9ኛ. በሌሎችም በርካታ ዘርፎት ወጣቶች በፍላጎታቸው ማሰማራት፡፡

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!

ሰላም ሰላም !!!የጎዛምን ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከጎዛምን ወረዳ እግር ኳስ  እና ቮሊቦል ኮሚቴ  ጋር በመተባበር የ2015 በጀት ዓመት የማጠቃለያ የሰልጣኞችእና   የቀጠና ሊግ ውድ...
02/07/2023

ሰላም ሰላም !!!
የጎዛምን ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከጎዛምን ወረዳ እግር ኳስ እና ቮሊቦል ኮሚቴ ጋር በመተባበር የ2015 በጀት ዓመት የማጠቃለያ የሰልጣኞችእና የቀጠና ሊግ ውድድር ዛሬ በቀን 25/10/15 በደ/ማርቆስ ፖሊስ ኮሌጅ ፍፃሚውን አግኝቷል።
በዚህም የሊግ ውድድር በ3 የስፖርት ዓይነት ማለትም 1.እግር ኳስ ወንዶች
2 .ቮሊቦል ወንዶች
3.ቮሊቦል ሴቶች ሲሆኑ በዚህ ውድድሩም በወንዶች እግር ኳስ አሸናፌዎች
1ኛ ደረጃ የቦቅላ ቀጠና
2ኛ ደረጃ ሊባኖስ ቀጠና
3ኛ ደረጃ ቸርተከል ቀጠና
ቮሊቦል ወንዶች
1ኛ ደረጃ ሊባኖስ ቀጠና
2ኛ ደረጃ የቦቅላ ቀጠና
3ኛ ደረጃ ቸርተከል ቀጠና
ቮሊቦል ሴቶች
1ኛ ደረጃ ቸርተከል ቀጠና
2ኛ ደረጃ ሊባኖስ ቀጠና ሲሆኑ
በዓመቱ በወንዶች እግር ኳስ
1.ኮከብ ተጨዋች
=ወጣት አብርሀም አከቸርተከል ቀጠና
2.ኮከብ ግብ አግቢ
=ወጣት ተፈራ ከየቦቅላ ቀጠና
ዓመታዊ ውድድሩ ተጣናቋል የከርሞ ሰው ይበለን።

ሰላም ለሁላችን!!!የምስራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከባህል ስፖርት ፌዴሪሽን እና ከእጅ ኳስ ፌዴሪሽን ጋር በመተባበር ከሰኔ 10 ጅምሮ ለተከታታይ ቀኖች በደ/ማርቆስ ከተማ   ስ...
10/06/2023

ሰላም ለሁላችን!!!
የምስራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከባህል ስፖርት ፌዴሪሽን እና ከእጅ ኳስ ፌዴሪሽን ጋር በመተባበር ከሰኔ 10 ጅምሮ ለተከታታይ ቀኖች በደ/ማርቆስ ከተማ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን ጨርሶአል:: ስለሆነም:-
1.የባህል ስፖርት ዳኝነት 1ኛ ደረጃ
2. የእጅ ኳስ አሰልጣኝነት 1ኛ ደረጃ ስልጠና ለመውሰድ የምትፈልጉ የጎዛምን ወረዳ ስፖርት ቤተሰብ የሆናችሁ በጎዛምን ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት እስከ ሰኔ 07/10/15 ዓ.ም እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

የምስራቅ ጎጃም የዞን ሊግ እግር ኳስ ውድድር በሞጣ ከተማ በድምቀት ተጀመረ!የምስራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ከምስራቅ ጎጃም ዞን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የተዘጋጀው የዞን ሊግ ...
06/05/2023

የምስራቅ ጎጃም የዞን ሊግ እግር ኳስ ውድድር በሞጣ ከተማ በድምቀት ተጀመረ!

የምስራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ከምስራቅ ጎጃም ዞን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የተዘጋጀው የዞን ሊግ እግር ኳስ ውድድር በሞጣ ከተማ በድምቀት ተጀመረ።

ውድድሩን በይፋ ያስጀመሩት የምስራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ቢሻው ሞላ እንደተናገሩት የዞኑ ስፖርት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቃቃና እየተጠናከረ ሲሆን ዞናችን በሁሉም ስፖርት አይነቶች ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪና አሸናፊ እየሆነ ነው ብለዋል።

ውድድሩ የዞናችንን ስፖርት ለማነቃቃት፣ ጠንካራ እግር ኳስ ክለቦችን ለመፍጠርና በአማራ ክልል የክለቦች ሻምፒዮና የሚሳተፉ ክለቦችንን ለመምረጥ የሚደረግ ነው ያሉት አቶ ቢሻው ሞላ ሲሆን ውድድሩ ለተከታታይ 11 ቀናት በ13 ወረዳዎች መካከል የሚደረግ ሲሆን ከ360 በላይ የስፖርት የልዑካን ቡድን አባላት የሚሳተፉበት ይሆናል ብለዋል።

የምስራቅ ጎጃም ህዝብ ስፖርት ወዳድና ሰላማዊ ህዝብ ነው፤ ውድድሩ በሰላም እንደተጀመረ ሁሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ቡድን መሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ስፖርተኞችና የውቢቷ ሞጣና የአካባቢው ማህበረሰብ የድርሻቸውን እንዲወጡ መምሪያ ኃላፊው አሳስበዋል።

"ሰላም  ለሀገራችን!! ሰላም ለሰላም ወዳድ ህዝባችን!!"በምስራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶችን ስፖርት መምሪያ እና የዞን እግር ኳስ ፌዴረሽን አዘጋጃነት በሞጣ ከተማ አስተናጋጅነት የ2015 በጀት ዓ...
04/05/2023

"ሰላም ለሀገራችን!!
ሰላም ለሰላም ወዳድ ህዝባችን!!"
በምስራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶችን ስፖርት መምሪያ እና የዞን እግር ኳስ ፌዴረሽን አዘጋጃነት በሞጣ ከተማ አስተናጋጅነት
የ2015 በጀት ዓመት እግር ኳስ ሊግ ውድድር ከ27 /ዐ8 /15 ዓ.ም ጀምሮ ይካሂዷል :: በዚህ ውድድር የጎዛምን ወረዳ የእግር ኳስ ሉዑካን ቡድን ይሳተፋል። ሉዑካን ቡድኑ የአቋም መለኪያ ውድድሮችን በማካሂድ የዝግጅት ጊዜውን ጨርሰው ዛሬ 26/08/15 ወደ ሞጣ ተጎዟል።
"መልካም እድል ተመኘን!!"

ሰላም ለሀገራችን ! ሰላም ለህዝባችን !! በጎዛምን  ወረዳ የሚገኝ የቀጠና ቡድኖች መካከል ለ6ኛ ጊዜ የሚካሂደው የቀጠና ሊግ ወድድር በተለያዩ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ዛሬ 13/08 / 1...
21/04/2023

ሰላም ለሀገራችን ! ሰላም ለህዝባችን !!
በጎዛምን ወረዳ የሚገኝ የቀጠና ቡድኖች መካከል ለ6ኛ ጊዜ የሚካሂደው የቀጠና ሊግ ወድድር በተለያዩ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ዛሬ 13/08 / 15 በቸርተከል እና ሊባኖስ ቀጠና መካከል በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች እና በተለያዩ ኩነቶች በድምቀት ጀሮአል ::

07/04/2023
07/04/2023

Address

Debra Markos

Telephone

+251587713035

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gozamin Woreda Youth & Sport Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share