Ethiopia Tekedem/ኢትዮጵያ ትቅደም/

Ethiopia Tekedem/ኢትዮጵያ ትቅደም/ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopia Tekedem/ኢትዮጵያ ትቅደም/, Political organisation, menaheriya, Dangila.

31/01/2026
30/01/2026
30/01/2026
30/01/2026
30/01/2026
30/01/2026
30/01/2026

ለማስታወስ .....

የፌስታል ዘመን አበቃ — እገዳው ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል::

አዲስ አበባ — ከነገ ጥር 23 ቀን ጀምሮ የፕላስቲክ ከረጢት (ፌስታል) መያዝ፣ መጠቀምም ሆነ ማከማቸት በፍጹም የተከለከለ መሆኑ ተረጋግጧል ከ6 ወር በፊት ህጉ መፅደቁ ይታወቃል ።

ባለሥልጡንም የ6 ወሩ የመሸጋገሪያ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ነገ ጥር 23 2018 ወደ ሙሉ እርምጃ እንደሚገባ ይጠበቃል።

በአዲሱ አዋጅ መሠረት፣
በፌስታል አጠቃቀም ላይ የተጣሉት ቅጣቶች የሚከተሉት ናቸው፡

* ለተጠቃሚዎች ፌስታል ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው ከ5,000 እስከ 10,000 ብር የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል።

* የፕላስቲክ ከረጢት ማምረት ወደ አገር ማስገባት ወይም ለገበያ ማቅረብ ከ50,000 እስከ 100,000 ብር ቅጣት ያስቀጣል።

ልዩ ማሳሰቢያ፦ ድርጊቱ የተፈጸመው በድርጅት ደረጃ ከሆነ፣ የገንዘብ ቅጣቱ በሦስት እጥፍ እንደሚባዛ ተገልጿል።

ከአላስፈላጊ የገንዘብ ቅጣትና እስራት ለመዳን፣ ከነገ ጀምሮ አማራጭ የጨርቅ ወይም የወረቀት ከረጢቶችን እንዲጠቀሙ እንመክራለን።

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

30/01/2026
30/01/2026

ግብረ_ገባዊ ትውልድ
🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ግብረ ገባዊ ትውልድ ማለት በሥነ-ምግባር፣ በእውቀት እና በማህበራዊ እሴቶች የታነፀ፣ ለራሱና ለሀገሩ የሚጠቅም ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ነው።

ይህ ትውልድ በትምህርት ቤት፣ በቤተሰብና በማህበረሰብ ተፅዕኖ በመልካም ባህሪ፣ በመቻቻል፣ በመከባበርና ተጠያቂነትን በመረዳት የሚመራ ትውልድ ነው።

የግብረ_ገባዊ ትውልድ ዋና ዋና መገለጫዎች፡
🍃🍃🍃🍃🍃
👉በሥነ-ምግባር መታነፅ፡ ውስጣዊ ማንነትን በግብረ-ገብ በማፅዳት በአስተሳሰብና በባህሪ መልካም መሆን።

👉ኃላፊነትና ተጠያቂነት፡ በሥራና በዕለት ተዕለት ሕይወት ማድረግ የሚገባውንና የማይገባውን ለይቶ ማወቅ።

👉ማህበራዊ እሴቶች፡ ጓደኛን ማክበር፣ ሕሙማንንና አካል ጉዳተኞችን መንከባከብ፣ እንዲሁም የአቻ ግፊትን በአዎንታዊ መንገድ መወጣት።

👉ሰብአዊነት፡ ሌሎችን ማክበር፣ ማገዝ እና በአክብሮት መያዝ።

✍️ግብረ ገባዊ ትውልድ ለማፍራት የሚደረጉ ጥረቶች፡

_በተቋማትና በትምህርት ቤቶች ውስጥ የግብረ ገብ ትምህርትን መስጠት።

_በቤተሰብ አስተዳደግና በማህበረሰባዊ እሴቶች ማሳደግ።

_የውስጣዊ ማንነትን (ባህሪ፣ እውቀት፣ እምነት) ማፅዳትና መገንባት።

_ግብረ ገብነት የሰውን ልጅ ከተግባር እስከ ባህሪ፣ ከአኗኗር እስከ ስራ የሚመራበት መሰረት ነው።

ትዉልድን በሥነ ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

30/01/2026

ለመሪዎች ጉባኤ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል - አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቅርቡ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ።

ሚኒስትር ዴኤታው ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ እንግዶችን ከመቀበል ጀምሮ የትራንስፖርት፣ የሆቴል ዝግጅትና የደህንነት ስራዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በጉባኤው በዲፕሎማሲ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በሌሎችም መስኮች ለመወያየት ትኩረት ሊደረግባቸው በታቀዱ ዋና ዋና አጀንዳዎች ዙሪያ ከህብረቱና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በሰፊው እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ትልልቅ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ከተለያዩ ሀገራት የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ እንዲሁም በኮሪደር ልማትና በሌሎች መስኮች የልምድ ልውውጦችን ለማድረግ በተጠናከረ መልኩ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን የአፍሪካ-ጣሊያን ጉባኤ እንግዶችን ተቀብሎ በተሟላ ሁኔታ ለማስተናገድ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የህብረቱ መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን በአህጉራዊ መድረኮች ያላትን ሚና ለማጠናከርና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥርም አስረድተዋል።

ለዚህም የሀገራችንን ትልቅነት፣ ክብርና አኗኗር ማስተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፥ ለጉባኤው ስኬት የሁሉም አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ መልእክት አስተላልፈዋል።

በቅድስት ዘውዱ

👉ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች የፋና ዲጂታል አድራሻዎችን ከአስተያየት መስጫ ሳጥን ያግኙ

Address

Menaheriya
Dangila

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Tekedem/ኢትዮጵያ ትቅደም/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share