ወራቤ ማረሚያ ተቋም Worabe Prison Institution

ወራቤ ማረሚያ ተቋም Worabe Prison Institution የህግ ታራሚዎችን አርሞና አንፆ አምራች ዜጋ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረግ ነዉ

የፍትህ ዘርፍና የዳኝነት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሄደ!ወራቤ፣ ህዳር 21/2017 የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበትና የስልጤ ዞን ምክር ቤት ...
30/11/2024

የፍትህ ዘርፍና የዳኝነት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሄደ!

ወራቤ፣ ህዳር 21/2017

የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበትና የስልጤ ዞን ምክር ቤት ከዞኑ የፍትህና የዳኝነት አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የስልጤ ዞን የፍትህ ዘርፍና የዳኝነት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻልን ዓላማው ያደረገ የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ ተካሄዷል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ የዞኑን ፍትህ ዘርፍ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ በስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ በረከት ከድር ሲቀርብ በሌላም በኩል በዞን ደረጃ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የተዘጋጀ የውይይት ሰነድ በስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት በአቶ ነስሮ አለሙ ቀርቦ ምክክር ተደርጓል፡፡

በቀረቡ ሰነዶች በዞን ደረጃ ከፍትህና ከዳኝነት ተግባራት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮች እንዲሁም ሊሻሻሉና ሊፈቱ የሚገቡ ጉዳዮች በስፋት ተነስተው በየደረጃው ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የጋራ መግባባት ተፈጥሯል፡፡

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ በረከት ከድር በፍትህና በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ጉድለቶችን ማረምና አገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል የሁሉንም እገዛ የሚጠይቅ ሂደታዊ ተግባር መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመምሪያው በኩል ነባር ችግሮችን ለመፍታትና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የፍትህ ተቋማትን በማስተባበርና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ተከታታይ ስራዎች እንደሚሰሩ አቶ በረከት ገልጸዋል፡፡

የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት አቶ ነስሮ ዓለሙ በበኩላቸው በፍትህና የዳኝነት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በየደረጃው ያሉ የፍትህ፣ የፍርድ ቤትና የፖሊስ ተቋማት ቅንጅታቸውን በማጠናከር ተጨባጩን እየገመገሙ ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ቅንጅታዊ አሰራርን ከማጎልበት ባለፈ የማህበረሰብ ተሳትፎን ማጠናከርና የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችንም በተገቢው መጠቀም እንደሚያስፈልግ አቶ ነስሮ መክረዋል፡፡

በህላዊ ዳኝነት ላይ የሚስተዋሉ ጉድለቶችን በመፍታትና ተቀራርቦ በመስራት በየ ጊዜው መልካቸውን የሚቀያይሩ አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን መከላከልና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል እንሚቻልም አቶ ነስሮ አንስተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ መህዲያ ቡሴር የፍትህና የዳኝነት ተቋማት እርስ በርሳቸውና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያላቸው ቅንጅት እውነተኛና ችግር ፈቺ መሆን እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡

በተግባር ሂደት ልዩ እገዛ ለሚፈልጉ አከባቢዎች በልዩነት መታገዝ እንዳለባቸው ያነሱት ወ/ሮ መህዲያ በዚህ ሂደት ከፍትህ ተቋማት ባሻገር በዞኑ መንግስትና በምክር ቤቶች በኩል ተገቢው ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡

በፍትህና የዳኝነት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት ከተፈለገ መፍታት እንደሚቻል ያስታወሱት ወ/ሮ መህዲያ ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

28/11/2024
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የወራቤ ማረሚያ ተቋም የክልሉ ማረሚያ ተቋማት አምባሳደር ሆነ።ህዳር 6/2017 ዓ/ም ወራቤየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፓሊስ ኮሚሽን የ...
15/11/2024

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የወራቤ ማረሚያ ተቋም የክልሉ ማረሚያ ተቋማት አምባሳደር ሆነ።

ህዳር 6/2017 ዓ/ም ወራቤ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፓሊስ ኮሚሽን የወራቤ ማረሚያ ተቋም በተለያዩ ግዜያት የተሻለ አፈፃፀም በማምጣቱ የፌዴራል ጉባዬ ተሳታፊ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በ2017 አንደኛ ሩብ ዓመት የላቀ የሥራ አፈፃፀም በማስመዝገቡ ለተቋሙ ኃላፊ የማበረታቻ ሽልማት ሰጥተዋል ።

በ2017 አንደኛ ሩብ ዓመት የላቀ የሥራ አፈፃፀም በማምጣት የክልሉ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አምባሳደር በመሆን የወራቤ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ኮማንደር አወል ሁሴን እዉቅና የተሰጣቸዉ ሲሆን ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።

የወራቤ ማረሚያ ተቋም ከሌሎች ተቋማት በተሻለ መልኩ ሥራዎችን በመስራት በአፋጣኝ ወደ ለዉጡ የመጣ ተቋም መሆኑን በክልሉ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስተዳደር ተገልጿል ።

ሌሎች ማረሚያ ተቋማትም የወራቤ ማረሚያ ተቋምን ተሞክሮ በመዉሰድ ወደ ለዉጥ መግባት እንዳለባቸዉ ኮሚሽኑ አክለዋል።

በመጨረሻም የወራቤ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ኮማንደር አወል ሁሴን እንደተናገሩት ለዚህ ውጤት መሳካት ከጎናችን ለነበራችሁ ለስልጤ ዞን ባለድርሻ አካላት ፣ የማናጅመንት አካላት መለዮ ለባሽና ሲቪል ሰርቫንት ሰራተኞች እንዲሁም በእርምት ላይ የምትገኙ የህግ ታራሚዎች ሽልማቱ የሁላችሁም በቅንጅት የመስራት ውጤት ነውና እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

03/11/2024
የወራቤ ማረሚያ ተቋም ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች፣ለህግ ታራሚዎችና ለህግ ታራሚ ቤተሰቦች እንኳን  ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ፍና ቴሌቨዠን የፌድራል ማረሚያ ...
20/04/2023

የወራቤ ማረሚያ ተቋም ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች፣ለህግ ታራሚዎችና ለህግ ታራሚ ቤተሰቦች እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ፍና ቴሌቨዠን የፌድራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በወራቤ ማረሚያ ተቋም ከህግ ታራሚዎች ጋር የሚደረግ የኢድ አል ፈጥር በዓል አከባበር በነጌው የበዓል ፕሮግራም በፍና የቴሌቭዥን ይጠብቁን

Address

Central
Dalocha
046

Telephone

+251925720401

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወራቤ ማረሚያ ተቋም Worabe Prison Institution posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ወራቤ ማረሚያ ተቋም Worabe Prison Institution:

Share