የምስራቅ ጉራጌ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ Misraq Gurage Zone SITD

  • Home
  • Ethiopia
  • Butajira
  • የምስራቅ ጉራጌ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ Misraq Gurage Zone SITD

የምስራቅ ጉራጌ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ Misraq Gurage Zone SITD ይህ በማዕከላዊ አትዮጵያ ክልል መንግስት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ይፋዊ የፌስቡክ ፔጅ ነው።

በእንሴኖ  ከተማ አስተዳደር  የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ወድድርና ኤግዚብሽን ተካሄደ ።ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)በእንሴኖ  ከተማ አስተዳደር  ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክ...
30/04/2026

በእንሴኖ ከተማ አስተዳደር የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ወድድርና ኤግዚብሽን ተካሄደ ።

ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)

በእንሴኖ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዩኒትና ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ዩኒት ጋር በመተባበር በትምህርት ቤቶች ፣ በኢንተርፕራይዞች እና በግል የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚብሽንና ውድድር ተካሂዷል።

በውድድሩ ላይ የተገኙት የ ከተማ አስተዳደሩ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ሃላፊ አቶ ፈቱ አሕመድ መንግስት ለሳይንስ ቴክኖሎጂና ለፈጠራ ስራዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የት/ት ዩኒት ሃላፊ አቶ ሹራላ ጀማል በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሳይንስ ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ውድድሩ ላይ የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮችን ሊፈቱ የሚችሉ የፈጠራ ስራዎች ማየት መቻላቸውን ተናግረዋል።

የታዩት የፈጠራ ስራዎች ወደ ማህበረሰቡ ጋር የሚደርሱበት ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ዛሬ በተካሄደው የፈጠራ ስራ ውድድር በርካታ አዳዲስ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች መቅረባቸውን ተናግረዋል።

የፈጠራ ስራዎች ከውድድር አልፈው የፈጠራ ባለቤቶችን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ እና ማህበረሰቡን ችግር መፍታት እንዲችሉ ያለባቸውን ችግሮች ለመቅረፍ በሁሉም መልኩ እገዛ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት የተሻለ ስራዎች ያቀረቡ አካላት በቀጣይ ለሚደረገው ዞናል ውድድር ጥሩ ውጤት ለማምጣት ጥረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል።

በመጨረሻም የተሻለ ስራ ያቀረቡ አካላት የእውቅና የምስክር ወረቀትና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በውድድሩ ላይ የፅ/ቤት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ የት/ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ ተማሪዎች ተገኝተዋል።

ዘገባው የእንሴኖ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዩኒት ነው።

ዲጂታል ቴክኖሎጂን ማበልፀግና በብቃት ማስተዳደር ለሀገር ብልፅግና ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገለፀ።ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ...
25/04/2026

ዲጂታል ቴክኖሎጂን ማበልፀግና በብቃት ማስተዳደር ለሀገር ብልፅግና ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገለፀ።

ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ሶፍትዌሮችን ማበልፀግ በሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ ዙሪያ ላይ ለዘርፉ ባለሞያዎች ስልጠና ሰጥቷል።

የቢሮው ምክትልና የዲጅታላይዜሽን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ እንደተናገሩት ዲጂታል ቴክኖሎጂን ማበልፀግና በብቃት ማስተዳደር ለሀገር ብልፅግና ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

አለም አንድ መንደር እየሆነች በመጣችበት በዚህ ዘመን ከቴክኖሎጂ ውጭ መሆን ስለማንችል ቴክኖሎጂዎችን በራስ ልጆችና በራስ አቅም ማበልፀግና በተገቢው ማስተዳደር ይገባናልም ብለዋል።

ስልጠናው (ASP. NET Core MVC) በሚባል አዲስ የሶፍትዌር ማበልጸጊያ ዘዴ ላይ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሞያዎች የተሰጠ መሆኑን የገለፁት አቶ ከበደ አገልግሎቶች ከወረቀት ንኪኪ ነፃ ዲጂታል እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

ሰልጣኞች ከስልጠናው ጎን ለጎን ሶፍትዌሮች እያበለፀጉ እንደነበር አስታውቀው በራስ አቅም በሁሉም መዋቅሮች ተደራሽ በማድረግ ዲጅታል ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ስልጠናው የባለሞያዎችን አቅም ከማጎልበት ባለፈ ክልሉን የቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ ለሚደረገው እንቅስቃሴም ወሳኝ ነው ብለዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የባለሞያዎችን አቅም መገንባት ተገቢ በመሆኑ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሀላፊው አስታውቀዋል።

የስልጠናው ተሳታፊ የክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የቴክኖሎጂ ዘርፍ ተጠሪ አቶ መንበረ ተስፋዬ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በማበልፀግ በራስ አቅም የተቋምን አገልግሎት ለማሻሻል የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

በስልጠና ሂደትም በቡድን የማዕከሉን አገልግሎት ቀልጣፋ የሚያደርጉ የሙከራ ሶፍትዌሮች ማበልፀጋቸውን ተናግረው በቀጣይ ለሚስፋፉ የመሶብ አንድ ማዕከላት ተደማሪ አቅም ፈጥሯል ብለዋል።

በክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የሶፍትዌር ባለሞያ አቶ ፍስሃ ጴጥሮስ በበኩላቸው ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እንደ ሀገር ለማምጣት ሶፍትዌሮችን ማበልፀግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ሶፍትዌሮችን አሁን ባለው ቴክኖሎጂ በራስ አቅም ማበልፀግ በቀጣይ ስራዎቹን ለማሻሻል ፣ለማሳደግ እና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የጎ ሚና እንዳላቸው ተናግው የክህሎት ስልጠናው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።

ዘገባው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።

የዲጅታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም መገንባት ወሳኝ ነው፡- አቶ እስጢፋኖስ ጡራሞየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለዞንና ለልዩ ወረዳ ...
25/04/2026

የዲጅታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም መገንባት ወሳኝ ነው፡- አቶ እስጢፋኖስ ጡራሞ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለዞንና ለልዩ ወረዳ ለተውጣጡ የኢኮቴ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ለአራት ተከታታይ ቀናት በወራቤ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)

የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በሶፍት ዌር ልማት፣ በኔትወርክ መሰረተ ልማት እንዲሁም በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከዞንና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ለአይሲቲ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የኢኮቴ ልማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ተወካይ አቶ እስጢፋኖስ ጡራሞ እንዳሉት ዓለም ወደ አንድ መንደር እየመጣ ባለበት በዚህ ዘመን ከቴክኖሎጂ ውጪ መሆን አይቻልም፡፡

በዚሁ መነሻ የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከተጣለበት ኃላፊነት በመነሳት ክልሉን የቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም በአዳዲስ የቴክኖሎጂ በመገንባትና በማብቃት ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በተለይ የዲጂታል ኢትዮጵያ ትልም 2030 እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቢሮው የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡ አቶ እስጢፋኖስ አክለውም በቀጣይም ይህን መሰለን ተከታታይነት ያለው ስልጠና በመስጠት ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት አስረድተዋል፡፡

ሰልጣኞች በአራት ቀን የወሰዱትን ስልጠና በየተቋማቸው ወደ ተግባር መቀየር ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም የእውቀት ሽግግር ማድረግ አለባቸው ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች ገንቢ የሚሏቸውን ሀሳብ አስታያየቶች ሰንዝረዋል ይህን መሰል የክህሎት ስልጠና መሰጠቱት የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት፣ እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዘርፉ ትርጉም ያለው ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ፋይዳው የጎላ ነው መሰረት ይጥላል ብለዋል፡፡

ዘገባው የስልጤ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በቡኢ ከተማ አስተዳደር  የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ወድድርና ኤግዚብሽን ተካሄደ ።ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)በቡኢ ከተማ አስተዳደር  ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/...
24/04/2026

በቡኢ ከተማ አስተዳደር የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ወድድርና ኤግዚብሽን ተካሄደ ።

ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)

በቡኢ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በትምህርት ቤቶች፣ በኮሌጅ፣ በኢንተርፕራይዞች እና በግል የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚብሽንና ውድድር ተካሂዷል።

በውድድሩ ላይ የተገኙት የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ መንግስት ለሳይንስ ቴክኖሎጂና ለፈጠራ ስራዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሳይንስ ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ውድድሩ ላይ የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮችን የሊፈቱ የሚችሉ የፈጠራ ስራዎች ማየት መቻላቸውን ተናግረዋል።

የታዩት የፈጠራ ስራዎች ወደ ማህበረሰቡ ጋር የሚደርሱበት ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ከበደ ዛሬ በተካሄደው የፈጠራ ስራ ውድድር በርካታ አዳዲስ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች መቅረባቸውን ተናግረዋል።

እንደከተማ አስተዳደር ባለፈው ዓመት እስከ ፌድራል ደረጃ የደረሱ የፈጠራ ስራዎች እንደነበሩ ያነሱት አቶ ቴዎድሮስ በዚህ ዓመትም የተሻለ ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎች ያሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የፈጠራ ስራዎች ከውድድር አልፈው የፈጠራ ባለቤቶችን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ እና ማህበረሰቡን ችግር መፍታት እንዲችሉ ያለባቸውን ችግሮች ለመቅረፍ በሁሉም መልኩ እገዛ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት የተሻለ ስራዎች ያቀረቡ አካላት በቀጣይ ለሚደረገው ዞናል ውድድር ጥሩ ውጤት ለማምጣት ጥረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል።

በመጨረሻም የተሻለ ስራ ያቀረቡ አካላት የእውቅና የምስክር ወረቀትና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በውድድሩ ላይ የቡኢ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ አዳነ ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ መምህራን እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።

ዘገባው የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

ለአዳዲስ ሀሳቦች እውቅና በመስጠት ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎች በማበረታታት ለትውልድ ተስፋን መመገብ እንደሚያሻ ተገለጸ። ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)የምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ...
24/04/2026

ለአዳዲስ ሀሳቦች እውቅና በመስጠት ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎች በማበረታታት ለትውልድ ተስፋን መመገብ እንደሚያሻ ተገለጸ።

ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)

የምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለአዳዲስ ሀሳቦች እውቅና በመስጠት ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎች በማበረታታት ለትውልድ ተስፋን መመገብ እንደሚያሻ ተገልጿል።

የሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ በቴ እንደገለጹት የሳይንስና የፈጠራ ውጤቶች ለሀገር የቀጣይ ዕድገት መሰረት መሆኑና የተማሪዎች የፈጣራ ስራዎችን ለማዳበር ሳይንስና ቴክኖሎጂ አይነተኛ መሳሪያ መሆኑ አንስተዋል።

ዓመታዊ የፈጣራ ስራ ስኬታማ ጥረትን የታከለበትና የተለፍበት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየተሻሻለ መምጣቱና ማህበረሰቡ ዘንድ በቀጥታ ደርሰው አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ፈጠራዎች የታየበት ሁኔታን መኖሩንና የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ መሆኑ አንስተዋል።

ፍቱን መፍትሔ የሆኑ የፈጠራ ስራ አቅራቢ ተማሪዎችና ለውጤቱ የደከሙ መምህራን አመስግነው ቀጣይ ላይ ይበልጥ ለመስራት መተጋገዝ ይገባልም ብለዋል።

የሶዶ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ብርሃኔ በመርሐግብሩ የተገኙ አካላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ፈጠራ ችግርን መፍታት ብቻ ሳይሆን አዲስ ነገር መፍጠር ጭምር እንደሆና ሀገር ልትሻገር ተወዳዳሪ ልትሆን የምትችለው በፈጣን የፈጠራ ስልት ብቻ መሆኑ ገልፀዋል ።

ሀገራችን የመፍጠንና የመፍጠር ህሳቤን በዜጎች ላይ በማስረጽ በሁሉም ዘርፍ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊው፣ በፖለቲው ዘርፎች በፈጠራ እንዲመራ የሚያመጣው ለውጥ የላቀ ነው ብለው የብልጽግና ጉዞን ማሳካት እንደማቻል እና ሁሉም አካል የራሱን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

በወረዳው ትምህርት ጽሕፈት ቤት እና በወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽሕፈት ቤት በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዓላማውም ተማሪዎች በትምህርታቸው የቀሰሙትን እውቀት ወደ ተግባራዊ የፈጠራ ስራ በመለወጥ ለሀገር ግንባታ የጎላ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ዕድል መፍጠር መሆኑ በመግለፅ በአሁኑ ሰዐት የሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበዜ ተሰማ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ዘገባው የሶዶ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

"ፈጠራ ችግርን መፍታት ብቻ ሳይሆን አዲስ ነገር መፍጠር"ነው በሚል መሪ ቃል የሶዶ ወረዳ  የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚቢሽን ባማረና በደመቀ መልኩ እየተካሄደ  ይገኛል።...
24/04/2026

"ፈጠራ ችግርን መፍታት ብቻ ሳይሆን አዲስ ነገር መፍጠር"ነው በሚል መሪ ቃል የሶዶ ወረዳ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚቢሽን ባማረና በደመቀ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል።

ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ቀጣይ ላይ የሀገር ተረካቢ ተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ለማጎልበት፣ ለማሳደግና ለማበረታታት የታሰበ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድር ኤግዚቢሽን በአማረና በደመቀ መልኩ መካሄድ ጀምሯል።

በኤግዚቢሽኑ ላይ የቀረቡት ስራዎች በተለይም የግብርናውን ዘርፍ የሚያዘምኑ፣ ስራን የሚያቀሉ ጊዜንና ጉልበትን የሚቆጥቡ በቴክኖሎጂ የታገዙ የአርሶ አደሩን የዕለት ተዕለት ኑሮን የሚያቀልሉ ውጤቶች በተመልካቾች ዘንድ ትልቆ አድናቆትና ማበረታታትን አትርፈዋል።

ዘመኑ ከወረቀት ስራ ወደ ዲጂታላይዝድ ቴክኖሎጂ መሸጋገሯን የሚያሳዩ በርካታ የፈጠራ ስራዎች በሰፊው ለማየት ተችሏል።

በፕሮግራሙ ላይ የምስራቅ ጉራጌ ዞን የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ልኬለሽ ከበደ፣ የሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ በቴ፣ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸጋ ሀብቴ፣ የሶዶ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ የብልፅግና ፓርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ደርጫ ፣ የወረዳው ጠቅላላ አመራሮች ርዕሳነ መምህራን፣ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች የፈጠራ ስራ አቅራቢ ተማሪዎች ተገኝተዋል።

ዝርዝር መረጃ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

ዘገባው የሶዶ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

በኢኮቴ መሰረት ልማት ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመጣ የባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ክህሎት ማጎልበት ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለፀ፡፡ሚያዚያ 15/2018 ዓ...
23/04/2026

በኢኮቴ መሰረት ልማት ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመጣ የባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ክህሎት ማጎልበት ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለፀ፡፡

ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከዞንና ለልዩ ወረዳ ለተውጣጡ የኢኮቴ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት በወራቤ ከተማ እየሰጠ ያለው ስልጠና ዛሬም እንደቀጠለ ነው…

የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የኢኮቴ ልማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ተወካይ አቶ እስጢፋኖስ ጡራሞ የአቅም ግንባታ ስልጠናው በኢኮቴ መሰረተ ልማት ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመጣ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
ቢሮው ከተጣለበት ኃላፊነት በመነሳት መጠነ ሰፊ ርብርብ እያደረገ ይገኛል ያሉት አቶ እስጢፋኖስ የዘርፉን ባለሙያዎች ክህሎት መገንባት ተቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በተለይ በበጀት ዓመቱ ተከታታይነት ያላቸው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሲሰጡ መቆየቱን ጠቅሰው ለክልሉ ዜጎች የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዘመኑን የዋጀ በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በዕቅድ ተይዞ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡

በዚህም በክልሉ የተቋማት አገልግሎቶች በኢኮቴ መሰረት ልማት እንዲታገዙ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል፡፡

በዘርፉ እየተመዘገቡ ያሉ ውጤታማ ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የዘርፉን ባለሙያና ባለድርሻ አካላት አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት በህዋዌ ኦፕሬትንግ ኔትወርኪንግ ርዕሰ ላይ ያተኮረ ስልጠና በITSC ካምፓኒ ከፍተኛ የኔትወርክ ባለሙያ አቶ ሐብታሙ አሳይቶ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

ዛሬም ልክ እንደትናንቱ በተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያነጣጠረ የክህሎት ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ዘገባው የስልጤ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

የደቡብ ሶዶ ወረዳ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚቢሽን በድምቀት መካሄድ ጀመረ።ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)በምስራቅ ጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ የወደፊት የሀገር...
23/04/2026

የደቡብ ሶዶ ወረዳ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚቢሽን በድምቀት መካሄድ ጀመረ።

ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም (ቡታጅራ)

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ የወደፊት የሀገር ተረካቢ ተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ለማሳደግና ለማበረታታት የታለመ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድር ኤግዚቢሽን መካሄድ ጀምሯል።

መርሐግብሩ በወረዳው ትምህርት ጽሕፈት ቤት እና በወረዳው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽሕፈት ቤት በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዓላማውም ተማሪዎች በትምህርታቸው የቀሰሙትን እውቀት ወደ ተግባራዊ የፈጠራ ስራ በመለወጥ ለሀገር ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ዕድል መፍጠር ነው።

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ሶዶ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳለ ቡልቡላ እንደተናገሩት፣ ተማሪዎች የቴክኖሎጂን አስፈላጊነት በሚገባ ተረድተው አዳዲስ ነገሮችን እንዲፈጥሩ ምቹ መድረኮችን ማመቻቸት የወቅቱ ወሳኝ ተግባር ነው ብለዋል።

ዛሬ ላይ የታዩት ሞዴል የፈጠራ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል የአርሶ አደሩን የሥራ ጫና የሚቀንሱ፣ የከተማውን ነዋሪ ኑሮ የሚያቀልሉና በአጠቃላይ የማህበረሰቡን ችግሮች የሚፈቱ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ኃላፊው አክለውም "መፍጠር ካልቻልን ተወዳዳሪ መሆን አንችልም" በሚል መርህ ትምህርት ቤቶች ለፈጠራ ስራዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩና ተማሪዎችን እንዲያበረታቱ ጥሪ አቅርበዋል።

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌራ አሰና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት፣ የአሁኑ ዘመን በእውቀት ምርምርና በፈጠራ የታጀበ መሆኑን ገልጸዋል።

ማንኛውንም ችግር በሳይንሳዊ መንገድ መፍታት እንደሚቻል የገለጹት ኃላፊው፣ የወረዳው ታዳጊዎች በዕለቱ ያቀረቧቸው የፈጠራ ውጤቶች ማህበረሰቡን ወደ ተሻለ እድገት ለማሸጋገር ትልቅ ተስፋ የሚታይባቸው መሆናቸውን አስረድተዋል።

በኤግዚቢሽኑ ላይ የቀረቡት ስራዎች በተለይም የግብርናውን ዘርፍ የሚያዘምኑና የዕለት ተዕለት ኑሮን የሚያቀልሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በተመልካቾች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፈዋል።

በኤግዚቢሽኑ ላይ የተሳተፉ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ለውድድር ያቀረቧቸውን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ከሰፊ ማብራሪያ ጋር ለእንግዶች ያስመለከቱ ሲሆን፣ ስራዎቹን የተመለከቱ የፕሮግራሙ ተካፋዮችም ታዳጊዎቹ ያላቸውን ጥልቅ የፈጠራ አቅም በማድነቅ "ለብልጽግና የምንመኛት ኢትዮጵያ በእንዲህ ያሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሻራዎች ትገነባለች" ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

በመድረኩ ስነ-ስርዓት ላይ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳለ ቡልቡላ፣ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር ጌታቸው ጋሹ ፣ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ የብልፅግና ፓርት ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ተሾመ ሞላ ፣ የቡኢ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን አቶ ታሪኩ የማነህ የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌራ አሰና ፣ የኮሌጁ ምክትል ዲን አቶ ተረፈ ኩራዜ የደቡብ ሶዶ ወረዳ መምህራን ማህበር ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ግዛው፣ የወረዳው አመራሮች፣ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ እና ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የተወከሉ ባለሙያዎች፣ ርዕሳነ መምህራን መምህራን እና የፈጠራ ስራ አቅራቢ ተማሪዎች ተገኝተዋል።

በአሁኑ ሰዓት የፓናል ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

ዝርዝር ማጠቃለያ ይን እንመለሳለን ።

ዘገባው የደቡብ ሶዶ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን የዳበረ ትውልድን በመቅረጽ የተሻለች ሃገርን መፍጠር የሚችል ዜጋን ልንገነባ ይገባል! የተከበሩ አቶ መሃመድ ውልጫፎ========በመስቃን ወረዳ የሳይንስ እና ፈጠራ ስራ...
08/04/2026

በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን የዳበረ ትውልድን በመቅረጽ የተሻለች ሃገርን መፍጠር የሚችል ዜጋን ልንገነባ ይገባል! የተከበሩ አቶ መሃመድ ውልጫፎ
========
በመስቃን ወረዳ የሳይንስ እና ፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚብሽን በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ።

መጋቢት 30ቀን 2018 ዓ.ም(የመስቃን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት)

የመስቃን ወረዳ ሳንይስና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት እንዲሁም የመስቃን ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር የሳይንስ የፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚብሽን ፕሮግራም ተካሄደ።

በፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚቢሽን ፕሮግራሙ ላይ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሃመድ ውልጫፎ እንዲሁም የወረዳው አመራርና ከወረዳ የተውጣጡ 17 ክላስተር ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የፈጠራ ባለሙያዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እና ተጋባዥ እንግዶች በመገኘት ፕሮግራሙን ታድመዋል።

የፈጠራ ስራዎች ዉድድርና እና ኤግዚብሽን ትምህርት ቤቶች ዓመቱን በሙሉ ከተማሪዎቻቸው የሃሳብና የዕውቀት መጠን ዝግጅት ሲያደረጉ ቆይተው በዛሬው ዕለትም በዋናነት በየአካባቢያቸው በሚስተዋሉ የማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮውን መነሻ በማድረግ የአርሶ አደሩን ጉልበትን ጊዜን የሚቆጥቡ ሃብትን ከብክነት የሚያድኑ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን በየአካባቢያቸው በቀላሉ ሊገኙ በሚችሉ የወዳደቁ ቁሳቁሶችን በመስራት ለፈጠራ ስራዎች ለውድድርና ለኤግዚቢሽን አቅርበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሃመድ ውልጫፎ እንደገለጹት የፈጠራ ስራዎችና ክህሎቶቻቸውን ሊያወጡ ሊያሳድጉ የሚችሉበት ዕድል ከተፈጠረላቸው በሀገር ደረጃ የሚጠቅሙና ዕውቅ በርካታ የፈጠራ ስራዎች የሚችሉ ተማሪዎች ማፍራት እንደሚቻል በመግለፅ ለዚህ ደግሞ ትምህርት ቤቶች መነሻ በመሆናቸው በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የመስቃን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ሃላፊ አቶ ከድር ሁሴን አያይዘው እንደገለጹት ለውድድርና ለኤግዚቢሽን ምልከታው ተማሪዎች ፈጠራ ስራቸው የአካባቢውን ማህበረሰቡ ችግር በመረዳት ሊያግዙና ሊደግፉ የሚችሉ ስራዎች በተሻለ መልኩ ለመስራት መሞከራቸውን ገልፀው ይህንን የተጀመረው የፈጠራ ስራዎች ስልጠናና በበጀት በመደገፍ የማጎልበትና ስራዎች ተፎካካሪና ወደ ተግባር የመቀየር ስራዎች መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለዚህም ትምህርት ቤቶች ሌሎችም ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የመስቃን ወረዳ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ አይሻ ከድር
እንደገለፁት በ2016ዓ.ም በወረዳ ደረጃ አስራ አንድ የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ለዞን ውድድር በማቅረብ ሁለቱን በፌደራል የአዕምሮ ንብረት ጥበቃ ተመዝግቦ ለሽግግር በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ እንደዚህ አይነት የፈጠራ ስራዎችን በበቂ ሁኔታ ቢደገፉ ሽግግር አድርገው ለማህበረሰባችን ችግር ፈቺ ሊሆኑ እንደሚችሉ አመላክተዋል።

በዚህም መሰረት የተሻለ ሰርተው ለተገኙ የፈጠራ ስራ ባለቤት ለሆኑ ተማሪዎችና መምህራን የዋንጫና የተለያዩ ሽልማቶች የተበረከቱ ሲሆን ይህም ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ያደርጋል ተብሏል።
=================
ዘገባው የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ነው

በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ሣይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤቶች በመተባበር በተዘጋጀው የሣይንስና የሂሳብ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚብሺን እና ውድድር በፈጠራ ስራቸው የተሻለ ውጤት...
08/04/2026

በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ሣይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤቶች በመተባበር በተዘጋጀው የሣይንስና የሂሳብ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚብሺን እና ውድድር በፈጠራ ስራቸው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ መምህራን፣ ተማሪዎች እና የግል ተወዳዳሪዎች እውቅና እና የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል።

መጋቢት 30/2018

Address

Butajira

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የምስራቅ ጉራጌ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ Misraq Gurage Zone SITD posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የምስራቅ ጉራጌ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ Misraq Gurage Zone SITD:

Share