Goba woreda government communication affairs office

Goba woreda government communication affairs office ይህ የጎባ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ(የፌስቡክ) ገጽ ነው።

‎የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ‎‎የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡‎‎ምር...
03/06/2026

‎የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ

‎የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

‎ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

‎ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

‎የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡

7ኛው አገራዊ ምርጫ የሕዝብ ድምፅና ፍላጎት ያለማንም ተጽዕኖ በነፃነት የተስተናገደበት ነው ፥ የጎባ ወረዳ የድሺ ከተማ ነዋሪዎች‎‎በካፋ ዞን በጎባ ወረዳ የድሺ ከተማ ነዋሪዎች ትላንትና በተ...
02/06/2026

7ኛው አገራዊ ምርጫ የሕዝብ ድምፅና ፍላጎት ያለማንም ተጽዕኖ በነፃነት የተስተናገደበት ነው ፥ የጎባ ወረዳ የድሺ ከተማ ነዋሪዎች

‎በካፋ ዞን በጎባ ወረዳ የድሺ ከተማ ነዋሪዎች ትላንትና በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ዙሪያ ያላቸውን አዎንታዊ አስተያየትና ዕይታ አጋርተዋል።

‎ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት፤ የምርጫው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ፣ ስልጡንና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።

‎የምርጫውን ሂደት አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎችና የምርጫው ተሳታፊዎች አቶ አበበ አለማየሁ፣ አቶ አካሉ አደቶ፣ ወ/ሮ ማሚቴ ማሮ እና ወ/ሮ አየለች በላይ እንደተናገሩት፤ ትናንት የተካሄደው ምርጫ የሕዝብ ድምፅና ፍላጎት ያለምንም ተፅዕኖ በነፃነት የተስተናገደበት ታሪካዊ መድረክ ነው።

‎ያለምንም የጸጥታ ሥጋት፣ ሁከትና ግርግር እያንዳንዱ መራጭ በራሱ ፈቃደኝነት ላይ ብቻ ተመስርቶ ሕገ-መንግሥታዊ መብቱን ሙሉ በሙሉ የተጠቀመበትና የዴሞክራሲ ብስለቱ የታየበት ወቅት ሆኖ ማለፉን በኩራት ገልጸዋል።

‎ነዋሪዎቹ በአስተያታቸው፤ ከምርጫው መጀመር አንሥቶ እስከ ማጠቃለያው ፍጻሜ ድረስ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የታየው የተረጋጋና የሰከነ መንፈስ ለየት ያለ እንደነበር ጠቁመዋል።

‎በተለይም የምርጫ አስፈጻሚዎች ያሳዩት ከፍተኛ ሙያዊ ብቃትና ገለልተኝነት፣ እንዲሁም የጸጥታ አካላት የነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበቃ ለትናንትናው ታሪካዊ ዕለት ስኬታማነት ትልቅና የማይተካ አስተዋጽዖ ማድረጉን በዝርዝር ተናግረዋል።

‎በመጨረሻም የድሺ ከተማ ነዋሪዎች፤ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ በመደረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ በቀጣይም ከምርጫው በሚገኘው ውጤት መሠረት የሚመጣው መንግሥት የአካባቢውን ሁለንተናዊ የልማትና የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች በትኩረት እንዲያሳካላቸው ያላቸውን ተስፋና ምኞት ገልጸዋል።

‎ኢትዮጵያ መርጣለች!

‎የጎባ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው
‎ለተሻለች ጎባ በጋራ እንሥራ!

7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በጎባ ወረዳ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ፥ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ታደሰ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ ‎‎ትናንት በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ የተካ...
02/06/2026

7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በጎባ ወረዳ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ፥ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ታደሰ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ

‎ትናንት በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ የተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በጎባ ወረዳ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ፥ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ታደሰ ለመላው የወረዳው ሕዝብ እና ለባለድርሻ አካላት በሙሉ ታላቅ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎ዋና አስተዳዳሪው ልዩና የላቀ ምስጋናቸውን ያቀረቡት፤ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ያለምንም የጸጥታ ሥጋት በስኬት እንዲጠናቀቅ ቀንና ሌሊት በቁርጠኝነት ሲንቀሳቀሱ ለነበሩት ለፖሊስ ሠራዊት፣ ለሚሊሻ አባላትና ለሕዝብ ጥበቃ መዋቅሮች (የፓትሮል ቅኝት አባላት) ነው።

‎በመቀጠልም ምስጋናቸውን ለጭሪ መደበኛ ክልል፣ ለጭሪ ልዩ እና ለጭሪ ልዩ ናኦ የምርጫ ክልል መራጮች ያቀረቡት አቶ ታረቀኝ፤ ሕዝቡ ሕገ-መንግሥታዊ የመምረጥና የመመረጥ መብቱን በሰለጠነ መንገድ ከመጠቀም ባሻገር፣ ለሀገራዊ የዴሞክራሲ ልምምድ ያበረከተው ታሪካዊ አስተዋጽኦና ያሳየው ወደር የሌለው ጨዋነት ለምርጫው ስኬት ቀዳሚውንና አንበሳውን ድርሻ መውሰዱን ገልጸዋል።

‎አስተዳዳሪው አያይዘውም፤ ምርጫውን በበሰለ የፖለቲካ አመራርና በተደራጀ አግባብ ሲያስተባብሩ ለነበሩት የወረዳው አስተባባሪዎች፣ የየደረጃው አመራሮችና አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች በእጩነት ቀርበውና የምርጫ ሥራዎችን በነቃ ተሳትፎ ሲያስተባብሩ ለነበሩት የብልጽግና ፓርቲ አባላት የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

‎በምርጫው ሜዳ ላይ በሰለጠነና በሰላማዊ መንገድ የተሳተፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር ግንባታና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዕድገት ያቀረቡት የተደራጀ ሐሳብና ያሳዩት ጨዋነት የተሞላበት ፉክክር የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው አመስግነዋል።

‎ለምርጫው ሰላማዊነት፣ ፍትሐዊነትና ዴሞክራሲያዊነት የበኩላቸውን ቀና እና ታሪካዊ አስተዋጽዖ ላበረከቱት ለተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ለወጣቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች፣ ለሃይማኖት አባቶችና ለታዛቢ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎በወረዳው ሥር በሚገኝ እያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊ፣ ሥልጡንና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ተጀምሮ በስኬት እንዲጠናቀቅ መላው ሕዝብ ያሳየው ጨዋነትና ከፍተኛ ንቃት የሚደነቅ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው በድጋሚ ገልጸዋል።

‎በመጨረሻም መራጮች በተባበረ ክንድ ሀገርን በጸና መሠረት ላይ ለማቆም ሲሉ፤ በተለያየ የሌሊት ጨለማና ብርድ፣ የቀን ፀሐይ ሀሩር፣ የዝናብና የጤና ሁኔታ ሳይበግራቸው ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመውረድ ድምፃቸውን በነፃነትና በደስታ ስሜት መስጠታቸውን የጠቆሙት አስተዳዳሪው፣ ለዚህ የሀገር ፍቅር ቁርጠኝነታቸው ላቅ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

‎ይህ የሕዝብ የበላይነትና አሸናፊነት የታየበት ታላቅ መድረክ መሆኑን በመግለጽ ፥"በዚህ ታሪካዊ ሂደት ኢትዮጵያ መርጣለች! ኢትዮጵያ አሸንፋለች!" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎ኢትዮጵያ መርጣለች! ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

02/06/2026

ውድ መራጮች በትላንትናው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በከፍተኛ ንቃትና ትዕግሥት ድምፃችሁን ስለሰጣችሁ እያመሰገንን፤ በምርጫ ሕጉ መሠረት ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስ በትዕግሥት እንድትጠባበቁ እና ከሌሎች ከማንኛውም ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን ከማሠራጨት እንድትቆጠቡ ቦርዱ ያሳውቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

ሕዝቡ ሕጋዊ ካልሆኑ ከማንኛውም ምንጮች ከሚወጡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በትላንትናው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በከፍ...
02/06/2026

ሕዝቡ ሕጋዊ ካልሆኑ ከማንኛውም ምንጮች ከሚወጡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በትላንትናው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በከፍተኛ ንቃት እና ትዕግሥት ድምፃቸውን ስለሰጡ አመስግኗል።

በምርጫ ሕጉ መሠረት ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስም በትዕግሥት እንዲጠብቁ እና ሌሎች አካላትም ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ፤ ሕዝቡም ከመሰል መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ቦርዱ አሳስቧል።

ኢትዮጵያ መርጣለች! #ኢትዮጵያመርጣለች
02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች!
#ኢትዮጵያመርጣለች

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት በፀጋ ለመቀበል ተዘጋጅተናል ፦ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት አስመልክቶ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ማብራሪያ ሰጥቷል ።የዘንድሮ ም...
02/06/2026

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት በፀጋ ለመቀበል ተዘጋጅተናል ፦ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት አስመልክቶ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ማብራሪያ ሰጥቷል ።

የዘንድሮ ምርጫ ሠላማዊ፣ታዓማኒ፣ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንደሆነ የካፋ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ናትናኤል በድሩ ተናግረዋል።

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አንድ ፓርቲ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ምርጫ መሆኑን ገልጸዋል ።

7ኛው ጠቅላላው ምርጫ ለአለም ተምሳሌት የምሆን ምርጫ መሆኑን የተናገሩት አቶ ናትናኤል በድሩ ለቀጣይ ትውልድ ደሞክራሲ ማላመድ ነው ብለዋል ።

የምርጫ ውጤት መላው ህዝብና የፖለቲካ ፓርቲዎች በፀጋ መቀበል እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

ኢትዮጵያ ብሐራዊ አንድነት ፓርቲ ዋና ስራ-አስፈፃሚና የደ/ም/ኢ/ክ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ አባል ወ/ሪት መቅደስ መኮንን በበኩላቸው መላው ህዝብ ይበጀኛል ያለውን ፓርቲ በነፃነት የመረጡት ምርጫ እንደሆነ አስረድተዋል ።

የምርጫ ውጤት ምንም ሆነ ምን በፀጋ እንደሚቀበሉ ገልጸው ለቀጣይ ምርጫ ከዚህ ልምድ በመውሰድ እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገርቱ ዴሞክራሲ ልምምድ የተደረገ አበረታች ምርጫ እንደሆነም ተናግረዋል ።

ምርጫው ከመነሻ ጀምሮ እስከ ምርጫ ዕለት ድረስ በሠላማዊ መንገድ የተካሄደ መሆኑን ከሠላም ለኢትዮጵያ ጥምረት ፓርቲ አቶ ክፍለ መሸሻ ገልጸዋል ።

ሠላም ለኢትዮጵያ ጥምረት ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች የምርጫ ውጤቱን ለመቀበል መዘጋጀት እንዳለባቸው አስረድተዋል።

ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ከማድረግ አልፎ የመደበለ ፓርቲ ስርዓት ለማጎልበት የተሰሩ ስራዎች አስደናቂ ናቸውም ብለዋል።

በመጨረሻም አቶ ክፍለ መሸሻ ከምርጫ በኋላ ያሸነፈው ፓርቲም ሆነ የተሸነፉ ፓርቲዎች ለሀገር ሠላምና ዕድገት በጋራ መስራት እንደሚገባቸው ምክራቸውን ለግሰዋል።

የዘገበው የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው ።

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የተሰጠ  የምስጋና መግለጫትናንት በመላው ሀገራችን የተካሄደውና እጅግ ወሳኝ የሆነው ጠቅላላ ምርጫ በክልላችን በስኬት ተጠናቋል። የክልላችን ...
02/06/2026

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የተሰጠ የምስጋና መግለጫ

ትናንት በመላው ሀገራችን የተካሄደውና እጅግ ወሳኝ የሆነው ጠቅላላ ምርጫ በክልላችን በስኬት ተጠናቋል። የክልላችን ህዝብ ከጠዋቱ ጀምሮ በነቂስ በመውጣት፣ ዲሞክራሲያዊ መብቱን በመጠቀምና የነገ እጣ ፈንታውን በራሱ እጅ ለመወሰን ያሳየው ከፍተኛ ተነሳሽነትና ብስለት ታሪካዊና አርአያነት ያለው ነው።

በክልላችን በሚገኙ 1,780 የምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ ምርጫው ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ፣ ነጻና ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ታላቅ ሚና ለተጫወቱት፡ለተከበረውና ሰላም ወዳዱ የክልላችን ህዝብ ለዳበረው የዲሞክራሲ ባህሉ እና ለነቃ ተሳትፎው፣ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላሳዩት ሰላማዊና ህጋዊ የፉክክር መንፈስ፣የምርጫ አስፈጻሚዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካለት ላሳያችሁት ቁርጠኝነትና የስራ ተነሳሽነት ፣በየደረጃው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት ሌሊት ከቀን በመትጋት አስተማማኝ ሰላም በመፍጠራቸው፣ክልላችን መንግስት ያለውን ላቅ ያለ ክብርና ልባዊ ምስጋና ያቀርባል።

ይህበሰላም የተጠናቀቀው ምርጫ የሀገራችንና የክልላችንን አንድነት፣ ልማትና ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ይበልጥ የሚያጠናክር ትልቅ ድል ነው።
የክልል ኮሙኒኬሽን ዘግቧል

ኢትዮጵያ መርጣለች !

 #የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የምስጋና መልዕክትየካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ 7ኛው  ሀገራዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን አስመልክቶ መላውን የዞን ህዝብ  አመስግነዋል::"ኢትዮ...
02/06/2026

#የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የምስጋና መልዕክት
የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን አስመልክቶ መላውን የዞን ህዝብ አመስግነዋል::

"ኢትዮጵያ መርጣለች አሸንፋለችም!" ያሉት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ይህም የመላው ህዝባችን ያላሰለሰ ጥረት ታክሎበት ነው በማለት ለዚህም ለህዝቡ ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆት ገልፀዋል::

የዞኑ አስተዳዳሪ እንደተናገሩት በመላው ሀገራችን የተካሄደውና ታሪካዊው 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ በካፋ ዞን ደረጃ በድል መጠናቀቁን አመላክተዋል። መላው የዞኑ ህዝብ ብርድና ውርጭ ሳይበግረው ከጠዋቱ 11:00 ጀምሮ በነቂስ ወጥቶ ወረፋ በመያዝ እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ድረስ የተሰጠውን ዴሞክራሲያዊ መብት ተጠቅሞ የሀገሪቱን የነገ እጣ ፈንታ በራሱ እጅ ለመወሰን ያሳየው ከፍተኛ ቁርጠኝነትና የሀገር ፍቅር ታሪክ የማይረሳው ነው።

በዞናችን ስር በሚገኙ 603 የምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ ምርጫው ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ ፣ ፍትሃዊና ነጻ እንዲሁም ያለምንም ጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከፍተኛውን ድርሻ ለተወጡት ባለድርሻ አካላት፣ ለተወደደው እና ለተከበረው ሰላም ወዳዱ የካፋ ህዝብ ላሳየው ተባባሪነት እና የነቃ ተሳትፎ በእጅጉ አመስግኗል::

የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ላሳዩት ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር ፣የምርጫ አስፈጻሚዎች ታዛቢዎችና ወኪሎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካለት ላሳያችሁት የሀገርና የህዝብ ውግንና በዞኑ አስተዳደርና በመላው ህዝብ ሥም ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው::

በየደረጃው የሚገኙ መላው የጸጥታ አካላት፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች ሳይበግራችሁ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ በማድረጋችሁ የዞኑ መንግስት ያለውን ክብርና አድናቆት ያቀርባል።

በመጨረሻም ይሄው በስኬት የተጠናቀቀው ምርጫ የሀገራችን፣ የክልላችንና የዞናችን ህዝቦች አንድነት፣ ልማትና ዴሞክራሲያዊ ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ብሏል ዋና አስተዳዳሪው በመግለጫቸው ::

ኢትዮጵያ መርጣለች አሸንፋለች!
አቶ እንዳሻው ከበደ
የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ግንቦት 25/2018 ዓ/ም
ቦንጋ

ኢትዮጵያ መርጣለች፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችም መርጠናል:-  ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)መላው የክልላችን  መራጭ ሕዝቦች በዕለተ ሰኞ ከጧቱ  12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ  እኩለ ...
02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችም መርጠናል:- ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

መላው የክልላችን መራጭ ሕዝቦች በዕለተ ሰኞ ከጧቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት ድምፃቸውን በነፃነት በመስጠት መንግሥትን ለመመሥረት ያደረጉት ፅናት: የሀገር ፍቅርና ለመንግሥት አስተዳደር አስፈላጊነት ያላቸው ቦታ የሚደነቅ ነው::

ሀገሬ ይህች ናት:: በማንኛውም ወጀብና ማስፈራሪያ የማትበገር ፅኑ መሠረትና አርቆ አስተዋይ ህዝብ ያላት': የራሷን ዕጣ ፈንታ በራሷ የመወሰን አቅም ያላት ክንዴ ብርቱ ሀገር መሆኗን ዛሬም በፅናት አረጋግጣለች::

በክልላችን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የፖለቲካ ፖርቲዎች በምርጫ ሂደት ያሳዩት መልካም ሥነምግባርና ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ያበረከቱት አስተዋፅኦ በጣም ከፍ ያለ ነው::

በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተሳተፋችሁ የክልላችን መራጮች: ዕጩዎች: የምርጫ አስፈፃሚዎችና ታዛቢዎች ለሀገር መንግሥት ግንባታ: ለዴሞክራሲ ባህል መጎልበትና የሀገርና ትውልድ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ ላሳዩችሁት በጎ ሚና በክልሉ መንግሥትና ሕዝብ ስም ላቅ ያለ ምሥጋና ለማቅረብ እወዳለሁ::

ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር
ግንቦት 25/2018 ዓ.ም

Address

Goba Wereda
Bonga
1988

Telephone

+251924416207

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goba woreda government communication affairs office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share