South west Ethiopian region children parliament

South west Ethiopian region children parliament የደቡብ ምዕራብ ህጻናት ድምፅ!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ በካፋ ዞን የአፍሪካ ህጻናት ቀን በአውራዳ ከተማ አስተዳደር ላላምባ አሶሴሽን ህጻናት ማቆያን በመጎብኘትና የህጻናት ፓርላማው ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በሰበሰበው...
13/06/2022

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ በካፋ ዞን የአፍሪካ ህጻናት ቀን በአውራዳ ከተማ አስተዳደር ላላምባ አሶሴሽን ህጻናት ማቆያን በመጎብኘትና የህጻናት ፓርላማው ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በሰበሰበው ወላጆቻቸውን ያጡና በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ ህጻናት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በደማቁ ተከብሮ ውሏል።

10/04/2022
09/04/2022

አቀፍ የህፃናት ፓርላማ ምስረታ

እንኳን በሰላም ገባችሁ
09/04/2022

እንኳን በሰላም ገባችሁ

ሀገር አቀፍ የህጻናት ፓርላማ ተመሠረተ።ክብርት ህጻን ሶስና ዘለቀ ከደቡብ ምዕራብ የፓርላማው ፀሀፊ ሆነው ተመረጡ።በአዲስ አበባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው የምርጫ ስነ ስርዓት የ...
30/03/2022

ሀገር አቀፍ የህጻናት ፓርላማ ተመሠረተ።

ክብርት ህጻን ሶስና ዘለቀ ከደቡብ ምዕራብ የፓርላማው ፀሀፊ ሆነው ተመረጡ።

በአዲስ አበባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው የምርጫ ስነ ስርዓት የተመሰረተው የኢትዮጲያ የህጻናት ፓርላማ 132 አባላትን የያዘ ሲሆን የተከበሩ ተማሪ ቅዱስ ሞላ ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ተማሪ እህተመድን አበባ ምክትል አፈ- ጉባኤ እና የተከበሩ ተማሪ ሶስና ዘለቀ ጸሀፊ ሆነው ተመርጠዋል።

በምስረታው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌድሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የኢትዮጲያ የህጻናት ፓርላማ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለህጻናት መብትና ደህንነት መጠበቅ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል።

በምስረታው ማብቂያ ላይም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህጻናት ፓርላማ በአፋርና አማራ ክልል ለተፈናቀሉ ህጻናት የሚሆን ያሰባሰቡትን የ አስር ሺህ ብር ድጋፍ ለሚኒስተር መስርያ ቤቱ አስረክበዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን በሲዝ ከተማ አስተዳደር በመዝገበ ምህረት አካዳሚ ህፃናት ፓርላማ  አባላት  አማካኝነት የሲዝ ከ/አ /ም ኃላፊ አቶ ዳሪዮስ ደበበ እና የደቡብ ምዕራ...
29/03/2022

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን በሲዝ ከተማ አስተዳደር በመዝገበ ምህረት አካዳሚ ህፃናት ፓርላማ አባላት አማካኝነት የሲዝ ከ/አ /ም ኃላፊ አቶ ዳሪዮስ ደበበ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህፃናት ፓርላማ ዋና ፀሐፊ የተከበሩ ኖዋን ካሣ በተገኙበት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ህፃናት እና አዛውንቶች የምገባ
ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን ለፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ መገባደድ የመ/ር ይታገሱ ጎሞሮ ተማሪዎች ትልቅ አስተዋፅኦ አደርገዋል ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የ2014 ዓ.ም አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በደማቁ ተከብሯል። በበዓሉም የደቡብ ምዕራብ ህጻናት ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ ህጻን ሳያት መስፍን ...
29/03/2022

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የ2014 ዓ.ም አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በደማቁ ተከብሯል። በበዓሉም የደቡብ ምዕራብ ህጻናት ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ ህጻን ሳያት መስፍን ተገኝተው በአፋርና አማራ ክልል ለተፈናቀሉ ህጻናት የሚሆን ሀብት በማሰባሰብ አክብረዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንች ሸኮ ዞን የ2014ዓ/ም መደበኛ ጉባኤ የተከበሩ የዞን ባለስልጣናት እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህፃናት ፓርላማ ዋና ፀሐፊ የተከበሩ ህፃን ኖዋን ካሣ በተገኙበ...
29/03/2022

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንች ሸኮ ዞን የ2014ዓ/ም መደበኛ ጉባኤ የተከበሩ የዞን ባለስልጣናት እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህፃናት ፓርላማ ዋና ፀሐፊ የተከበሩ ህፃን ኖዋን ካሣ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ክልል የህጻናት ፓርላማ ጥር 7/2014 ዓ.ም የክልሉ መቀመጫ በሆነችው ቦንጋ ከተማ የኢፌድሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ዴኤታ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ አ...
28/03/2022

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ክልል የህጻናት ፓርላማ ጥር 7/2014 ዓ.ም የክልሉ መቀመጫ በሆነችው ቦንጋ ከተማ የኢፌድሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ዴኤታ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ዑመድ እንዲሁም የተለያዪ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት በይፋ ተመሰረተ።

ምርጫውም ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ የተከናወነ ሲሆን ህጻናት ዴሞክራስያዊ ስርዓቱን እንዲለማመዱ ያስችላቸዋል።

በምርጫውም የተከበሩ ህጻን ሶስና ዘለቀ የክልሉ ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ህጻን ሳያት መስፍን ምክትል አፈ-ጉባኤ አንዲሁም የተከበሩ ህጻን ኖዋን ካሳ የክልሉ ጸሀፊ ሆነው ተመርጠዋል።

የፓርላማዉ መመስረትም ህጻናት በአለም አቀፍ ህጎች የተሰጣቸውን የተሳትፎ መብት እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል።

የተመረጡት ህጻናትም የመጀመርያ ተግባራቸው የሚሆነው በአፋርና አማራ ክልል ለተፈናቀሉት ህጻናት ወንድም እህቶቻቸው ሀብት ማሰባሰብ እንደሚሆን ገለፁ።

Address

Bonga

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South west Ethiopian region children parliament posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South west Ethiopian region children parliament:

Share