13/06/2026
ከኢፌዲሪ ባህልና ስፓርት ሚኒስቴር የተውጣጡ የክትትልና ድጋፍ ቡድን በጊምቦ ወረዳ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ምልከታ አደረጉ።
የክትትልና ድጋፍ ቡድኑ በጊምቦ ወረዳ የስፖርት ጂም ቤት፣ዘመናዊ ኮፊ ሐውስ እና በጋሪ ያሆ ባህል መንደር ውስጥ የተለያዩ የቅርስ እቃዎችን ጨምሮ በፕሮጀክት ደረጃ ተይዘው እየተሰሩ ያሉ የወተት ላም፣የቦንጋ በግ እርባታ፣የእንቁላል ጣይ ዶሮ፣የንብ ማነብ እና ሌሎችም የልማት ስራዎች ናቸው የተጎበኙት።
የጊምቦ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝ ማሞ እንዳሉት ጽህፈት ቤቱ በባህል አማካሪ ም/ቤት በኩል በወረዳ ደረጃ የሚሰሩ ሥራዎች በግንባር ቀደምትነት እየተስፋፋ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ተገኝ አክለው በወረዳው መንግስት መልካም ፍቃድ ለህዝብ አገልግሎት ለሚውሉ ሥራዎች በጀት መድቦ የተለያዩ ተግባራትን ከባህል አማካሪ ም/ቤቱ ጋር በጋራ በመሆን እየሰራ እንደሆነ አብራርተዋል።
በባህል ማዕከል ውስጥ ያሉ የተለያዩ ታሪክ ያዘሉ ቅርሶችንና በጀግንነት ታሪክ የሰሩትን በተመለከተ በሙዝየሙ ሥራ አስኪያጅ በጊምቤራሻ መለሰ መሸሻ በኩል ለክትትልና ድጋፍ ቡድኑ ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
የክትትልና ድጋፍ ቡድኑ በወረዳው በተመለከቱት የልማት እንቅስቃሴ መደሰታቸውንም አስታውቀዋል።
እስከ ስፍራው ተገኝተው ተግባራትን ለተመለከቱ የክትትልና ድጋፍ ቡድኑ የወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ተገኝ ማሞ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በእለቱም የስፖርት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አበባ አማሬን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል እንግዶች ከወረዳው ባለድርሻ አካላቶች ጋር በመሆን ነው ምልከታ ያደረጉት::