Kaffa Zone Prosperity Party Branch Office የካፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Bonga
  • Kaffa Zone Prosperity Party Branch Office የካፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

Kaffa Zone Prosperity Party Branch Office የካፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት Kafa Zone Pp

የቀጣይ ድጋፍ አቅጣጫን ለመለየት ትኩረት ያደረገ የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች ጉብኝትየተለያዩ የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች በደቡብ ምዕራብ ኢ...
03/02/2026

የቀጣይ ድጋፍ አቅጣጫን ለመለየት ትኩረት ያደረገ የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች ጉብኝት

የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) መሪነት፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)፣ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO)፣ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO)፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ (OCHA) እና የሕፃናትን መብት፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ንጹህ ውሃ እና መከላከያ ለማሻሻል በዓለም አቀፍ የሚሰራው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UNICEF) የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ በካፋ ዞን እየተተገበሩ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጉብኝት አድርገዋል።

የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የሚገኘው የአባይነሽ ፋርም የእንስሳት እርባታ እንዲሁም በዞኑ ዴቻ ወረዳ በሃ ላንድ የቡና እርሻ ልማት የሥራ እንቅስቃሴን ተመልክቷል።

እንዲሁም በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ የተቋቋመው የዲንቻ የመንግስት ሻይ ችግኝ ብዜት ጣቢያ ሌላኛዉ የጉብኝቱ አካል ነው።

የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች የልማት ሥራዎች ጉብኝቱ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን በተግባር በመመልከት የቀጣይ ድጋፍ አቅጣጫን ለመለየት ዓላማ ያደረገ ነዉ።

በነገው ዕለትም የተባበሩት መንግስታት የልማት አጋር ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች ከክልሉ መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ የቀጣይ ድጋፍ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

“የአፍሪካ ቀንድ እንዳይቀደድ የተሰፋ፤ እንዳይጣመር የተቀፈደደ አከባቢ ነው፡፡ እንዳንለያይ አንዳይነት ዘር፣ አንድ አይነት ቋንቋ፣ አንድ አይነት ባህል አለን፤ እንዳንጣመርና አብረን እንዳንሰ...
03/02/2026

“የአፍሪካ ቀንድ እንዳይቀደድ የተሰፋ፤ እንዳይጣመር የተቀፈደደ አከባቢ ነው፡፡ እንዳንለያይ አንዳይነት ዘር፣ አንድ አይነት ቋንቋ፣ አንድ አይነት ባህል አለን፤ እንዳንጣመርና አብረን እንዳንሰራ ደግሞ ብዙዎቻችን ብሄራዊ ጥቅማችን ላይ አይደለም እየሰራን ያለነው፡፡ ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት ከፍተኛ ፉክክር ያለበት አከባቢ ነው፡፡”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ቦንጋ ከተማ ገቡየተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ቦንጋ ከተማ ገ...
03/02/2026

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ቦንጋ ከተማ ገቡ

የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ቦንጋ ከተማ ገብተዋል።

ወደ ክልሉ ከገቡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች መካከል የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)፣ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO)፣ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO)፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ (OCHA) እና ሌሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ይገኙበታል።

የተባበሩት መንግስታት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ወደ ቦንጋ ከተማ ሲደርሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ መንግስት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የልማት አጋሮቹ በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ከመጎብኘት ባሻገር በንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን በጤና እና ትምህርት ዘርፍ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋም ግብርና ሥርዓት በመዘርጋት ዙሪያ ከክልሉ መንግሥትጋርውይይት የሚያደርጉና የቀጣይ ድጋፍ አቅጣጫ ይለያሉ ሲል የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል ።

“ብዙ ባንዳዎች ኢትዮጵያን አቁስለዋል ነገር ግን ማጥፋት አልቻሉም” የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
03/02/2026

“ብዙ ባንዳዎች ኢትዮጵያን አቁስለዋል ነገር ግን ማጥፋት አልቻሉም” የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የወልቃይት አካባቢ የተፈናቃዮች ጉዳይየወልቃይት አከባቢ ነዋሪዎች በሰላማዊ መንገድ የመኖር መብት አላቸው። ይህን የፌደራል መንግስት በጽኑ የሚያምነው ጉዳይ ነው። ነገር ግን የአማራና የትግራይ...
03/02/2026

የወልቃይት አካባቢ የተፈናቃዮች ጉዳይ

የወልቃይት አከባቢ ነዋሪዎች በሰላማዊ መንገድ የመኖር መብት አላቸው። ይህን የፌደራል መንግስት በጽኑ የሚያምነው ጉዳይ ነው። ነገር ግን የአማራና የትግራይ ክልሎች በወልቃይት ጉዳይ ለረዥም ጊዜ የይገባኛል ጥያቄ ሲያነሱ ቆይተዋል። ሆኖም የፌደራል መንግስት እያለ ያለው ሰው አይፈናቀል ባለበት ይመለስ፤ ራሱን ያስተዳደር፤ ራሱ ጥያቄውን ይመልስ ነው። ማንም ከውጭ ሆኖ ሊወስንለት አይገባም።

#የጠሚሩምላሾች

የዘንድሮውን ምርጫ በሚመለከትየዘንድሮው ምርጫ ሰላማዊ፣ፍትሃዊና አካታች እንዲሁም ካለፈው ምርጫ የተሻለ እንዲሆን መንግስት አበክሮ እየሰራ ነው። ምርጫውን በሚመለከት ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለኝ መ...
03/02/2026

የዘንድሮውን ምርጫ በሚመለከት

የዘንድሮው ምርጫ ሰላማዊ፣ፍትሃዊና አካታች እንዲሁም ካለፈው ምርጫ የተሻለ እንዲሆን መንግስት አበክሮ እየሰራ ነው። ምርጫውን በሚመለከት ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለኝ መልስ በውጤት እንየው ነው። በእርግጠኝነት መናገር የምፈልገው ጉዳይ ይህ ፓርላማ በብዙ መልኩ በርካታ ድምጾች የሚሰሙበት ይሆናል። ምርጫው በሰላም ይከናወናል፤ በምርጫ የሚሳተፉ ሃይሎችም ተጠቃሚ ይሆናሉ።

#የጠሚሩምላሾች

 #የሰላም ጉዳይ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም እጦት እንድንኖር ካደረጉን እና ካልተላቀቅንባቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው ከጥንት የተጠባነው ልዩነቶችን በሃይል ብቻ  የመፍታት ልምምድ ነው። ሁለ...
03/02/2026

#የሰላም ጉዳይ

ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም እጦት እንድንኖር ካደረጉን እና ካልተላቀቅንባቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው ከጥንት የተጠባነው ልዩነቶችን በሃይል ብቻ የመፍታት ልምምድ ነው። ሁለተኛው ደግሞ አሁንም ከጥንት የመጣ የባንዳነት ልምምድ ሲሆን ሶስተኛው የጠላቶቻችን ኢትዮጵያ ካደገች የሚል ያልተቋረጠ ስጋት ነው።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ማብራሪያ:-⨳ የስራ ዕድ...
03/02/2026

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ማብራሪያ:-

⨳ የስራ ዕድልን በሚመለከት ባለፉት 6 ወራት 2.6 ሚሊዮን ሰው ስራ አግኝቷል።

⨳ ባለፉት 6 ወራት ከ350ሺ ሰው በላይ የውጭ የስራ ዕድል ተመቻችቶላቸው እየሰሩ ነው።

⨳ ባለፉት 6 ወራት ከ20,000 ሰው በላይ ሀገር ውስጥ ሆኖ ቨርቿል ስራዎችን እንዲሰሩ ተደርጓል።

⨳ የቤት ልማት ፖሊሲ በቅርቡ ፀድቋል በዚህም 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመስራት አቅደናል።

ኢትዮጵያ በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ አንድም ብር ብድር ብድር አልወሰደችም ! #ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ👉ኮመርሻል ሎን ሳንወስድ የቀደመውን ስሁት የብድር ስርዓት ለማሻሻል ለመቀ...
03/02/2026

ኢትዮጵያ በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ አንድም ብር ብድር ብድር አልወሰደችም !

#ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ

👉ኮመርሻል ሎን ሳንወስድ የቀደመውን ስሁት የብድር ስርዓት ለማሻሻል ለመቀየር ከዓለም ጋር ስንደራደር ስራዎቻችን ግን ከምን ላይ ነበሩ የተባለ እንደሆነ ክቡራንና ክቡራት ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካለአንድ ብር እርዳታ ፣ ካለአንድ ብር ብድር ያሳካ መንግስት እና ህዝብ ፕሮጀክት አይሰራምማ አይባልም ግፍ ነው፡፡

👉ኢትዮጵያ በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ አንድም ብር ብድር ብድር አልወሰደችም። በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ አቋም በሀገር ውስጥም በሀገር ውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን ቁርጠኝነት ጨክነው በጋራ ቁመው ስለሰሩ የተከወነ ፕሮጀክት ነው።

ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ከሰጡት ማብራሪያ

በኢትዮጵያ በከተሜነት ለውጥና በገጠር ኮሪደር እየመጣ ያለው ለውጥ እጅግ የሚገርም ነው ከቢሮ የጀመርነው ለውጥ ዛሬ በኢትዮጵያ ትልቅ አብዮት ፈጥሮ በርከት ያሉ ከተሞችን መፍጠር ጀምሯል። #ጠ...
03/02/2026

በኢትዮጵያ በከተሜነት ለውጥና በገጠር ኮሪደር እየመጣ ያለው ለውጥ እጅግ የሚገርም ነው ከቢሮ የጀመርነው ለውጥ ዛሬ በኢትዮጵያ ትልቅ አብዮት ፈጥሮ በርከት ያሉ ከተሞችን መፍጠር ጀምሯል።

#ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶ/ር አብይ አህመድ

የበጀት ዓመቱ ሲጀመር መንግስት 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ የያዘ ሲሆን፤ ባለፉስ ስድስት ወራት ብቻ 709 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕ...
03/02/2026

የበጀት ዓመቱ ሲጀመር መንግስት 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ የያዘ ሲሆን፤ ባለፉስ ስድስት ወራት ብቻ 709 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ማብራሪያ:-⨳ በግብርናው...
03/02/2026

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ማብራሪያ:-

⨳ በግብርናው 999 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ ችለናል።

⨳ ኦርጋኒክ ማዳበሪያዎችን የማምረት ስራው እየተለመዱ መምጣታቸው ለውጡን የሚደግፍ ነው።

⨳ በሀገር ውስጥ ማዳበሪያዎችን ማምረት ብቻ በቂ ስላልሆነ እያንዳንዱን መሬት ፈትሸን መሬቱ እንደሚፈልገው ልክ ለማቅረብ ጥናት ጀምረናል ይህን ማሳካት ከቻልን ከ7.3 በመቶ በላይ ዘርፉን ማሳደግ እንችላለን።

⨳ በዚህ 6 ወር የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች የሀይል አቅርቦት 16 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

⨳ ከሶላር ኤክስፖርት ብቻ 900 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እናገኛለን

⨳ 30 በመቶ በማዕድን ዘርፉ ዕድገት ተመዝግቧል።

⨳ ኢትዮጵያ ከካሽ ወደ ሞባይል ዋሌት ማደጓ ትልቅ ለውጥ እና የሚታይ ዝላይ ነው።

⨳ የቱሪስት ፍሰቱ ጨምሯል አለም አቀፍ ስብሰባዎችን እያከናውንን ነው 10.2 በመቶ እድገት እናመጣለን፤ ጠንክረን ከሰራን ከዚህም በላይ እናስመዘግባለን።

Address

Bonga

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kaffa Zone Prosperity Party Branch Office የካፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share