Southwest Ethiopia Police Commission

Southwest Ethiopia Police Commission “በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!!”
(2)

ከታሪፍ በላይ ያስከፈለ አሽከርካሪ ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ መነሻውን ከቦንጋ ወደ ጠሎ ያደረገው  ኮድ ሶስት ደ/ም 00661 የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በህግ ከተቀመጠዉ ታሪፍ በላይ በማ...
30/05/2026

ከታሪፍ በላይ ያስከፈለ አሽከርካሪ ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ

መነሻውን ከቦንጋ ወደ ጠሎ ያደረገው ኮድ ሶስት ደ/ም 00661 የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በህግ ከተቀመጠዉ ታሪፍ በላይ በማስከፈሉ እርምጃ መወሰዱን የጠሎ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የትራፊክ ስራ ሂደት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉጌታ በዛብህ ተናግረዋል።

ተሽከርካሪው ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓም ከቦንጋ-ጠሎ ህጋዊ ታሪፍ 170 ብር ሲሆን ያለአግባብ 400 ብር ማስከፈሉን ነው ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉጌታ ያብራሩት።

በዚህም በተደረገው ክትትል 29 ሰዎችን ከጫነው ተሽከርካሪ ለእያንዳንዳቸው 2 መቶ 30 ብር ተመላሽ የተደረገ ሲሆን በተመሳሳይ በሰራዉ ህገወጥ ተግባር 1 ሺህ 500 ብር መቀጣቱን ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን በመጠቆም የተለመደውን ትብብር ማድረግ እንዳለበት የጠቆሙት ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉጌታ የተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ከህገወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ቤንዚል በቁጥጥር ስር ማዋሉን የየኪ ወረዳ ፖሊስ ገለፀ ።ኮድ 3 አ.አ የሰሌዳ ቁጥሩ 14896 የሆነ አይሱዙ በህገወጥ መንገድ 5 ሺህ ሊትር ቤንዚን ጭኖ...
29/05/2026

በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ቤንዚል በቁጥጥር ስር ማዋሉን የየኪ ወረዳ ፖሊስ ገለፀ ።

ኮድ 3 አ.አ የሰሌዳ ቁጥሩ 14896 የሆነ አይሱዙ በህገወጥ መንገድ 5 ሺህ ሊትር ቤንዚን ጭኖ የኪ ወረዳ አላሞ ቀበሌ ልዩ ስፍራ አሻዋ ተብሎ በሚጠራበት ስፍራ ሲደረስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል ።

ሁለት ተጠርጣሪዎችን ከህገወጥ ቤንዚን ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉንም የሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግኑኝነትና ገጽታ ግንባታ መረጃ ያሳያል።

በተያያዘ ዜና የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ በባለ ሁለት ሊትር ሃይላንድ ቤንዚን በመሙላት በማዳባሪያ በመቋጠር በየኪ ወረዳ ፍዴ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቆላ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ከተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል ፖሊስ ምርመራ መጀመሩም ተገልጿል ።

ህገወጥ የቤንዚን ዝውውርና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር እየተሰራ ስሆን ህብረተሰቡ የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ እንዲያስቀጥልም የሸካ ዞን ፖሊስ ጥሪ ማስተላለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግኑኝነትና ገጽታ ግንባታ ጠቅሶ የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ዘግቧል ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የፖሊስ የደንብ ልብስ ለማቅረብ የውል ስምምነት ተፈራረመየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለ2018 በጀት ዓመት የፖሊስ ሠራዊት የደንብ ልብስ፣ ካለፉ...
29/05/2026

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የፖሊስ የደንብ ልብስ ለማቅረብ የውል ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለ2018 በጀት ዓመት የፖሊስ ሠራዊት የደንብ ልብስ፣ ካለፉት ዓመታት በተሻለ ጥራት እና በሀገራችን ለተለያዩ የአየር ንብረት ሁኔታዎች ተስማሚ በሆነ መልኩ እንዲዘጋጅ የሚያስችል የውል ስምምነት ከሮንግ ሸንግ ቴክስታይል ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር ተፈራርሟል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በውል ስምምነቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር የፖሊስ ሠራዊቱ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለግዳጅ ሲሰማራ፣ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመፈጸም እንዲያስችለው የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ አልባሳት እንዲቀርቡ በአጽዕኖት ተናግረዋል።

ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የሮንግ ሸንግ ቴክስታይል ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በውሉ መሠረት አልባሳቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ፣ በጥራትና በፍጥነት እንዲያስረክብም አሳስበዋል።

የሮንግ ሸንግ ቴክስታይል ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተወካዮች በበኩላቸው፤ በውሉ መሠረት አልባሳቱን በከፍተኛ የጥራት ደረጃ አምርተው በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንደሚያስረክቡ አረጋግጠዋል። መረጃዉ የኢፌፖሚ

7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫው  ሰላማዊ  ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሙሉ ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ዶክተር ካሳ መጪው 7ኛ...
29/05/2026

7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሙሉ ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ዶክተር ካሳ መጪው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በስድስቱም ዞኖች፣ ወረዳዎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ቀበሌዎች የምርጫው ሂደት ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተሰርቶ ወደስራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች መደበኛ ፖሊስ እና ሚሊሻ ኃይል በቋሚነት ጥበቃ መመደባቸውን ያመለከቱት ኮምሽነር ዶክተር ካሳ የምርጫ ቁሳቁሶች በየምርጫ ጣቢያ የእጀባ ስራዎች እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

ኮምሽነሩ አክለውም በምርጫው ዕለት መራጩ ህዝብ ያለስጋት እንዲመርጥ ፀጥታውን ለማስከበር የክልሉ አድማ ብተና ሻለቃ እና የከፍተኛ ባለስልጣናት ጥበቃ (የቪ አይ ፒ) ሻለቃዎች በተሸከርካሪ የታገዘ ተንቀሳቃሽ ጥበቃ እንዲያደርጉ መመደባቸውን አስረድተዋል፡፡

በኮሚሽኑ የክልሉ አድማ ብተና ሻለቃ አዛዥ ኢንስፔክተር አየለ አረጋ በበኩላቸው ሰራዊቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን የመጠበቅ፣ ሁከትና ረብሻዎችን አስቀድሞ የመከላከል እንዲሁም የሕዝብን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮውን ለመወጣት በአካልና በስነ-ልቦና መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ለአድማ ብተና አባላት ከምርጫ ሕጉና ከስነ-ምግባር መመሪያው በመነሳት ጥብቅ ኦረንቴሽን መሰጠቱን የገለጹት ኢንስፔክተር አየለ አረጋ እያንዳንዱ አባል በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ ለሕዝብና ለአስመራጮች ከፍተኛ አክብሮት በማሳየት፣ ሕግን የማስከበር ስራውን ብቻ በገለልተኝነት እንዲወጣ ይደረጋል ብለዋል።

ከሕዝብ ጎን በመቆም ሕግን የማስከበርና ሰላምን የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለፁት በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የከፍተኛ ባለስልጣናት ጥበቃ ሻለቃ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ዉለታው ቆጭቶ 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ አስተማማኝ ለማድረግም ከአካባቢው መደበኛ ፖሊስ፣ ከዞን የፀጥታ አካላት ጋር ቅንጅት መፈጠሩን ጠቁመዋል።

አክለውም ዜጎች በምርጫው ዕለት ያለምንም ስጋትና ፍርሃት ወጥተው ድምጻቸውን መስጠት እንዲችሉ ቀጣይነት ያለው የፓትሮል ስራ እንደሚሰራም ጠቅሰዉ የፀጥታ አካል የሕዝብ አገልጋይ መሆኑንና ለትኛውንም ወገን ሳይወግን በገለልተኝነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ ለመላው የክልሉ ህዝቦች፤የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩ ተወዳዳሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው ለህግ የበላይነት እንዲገዙ እና ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንዲሰሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡፡

ፎቶ ግራፍ፦ፎቶ ኪቤ ቦንጋ እና የቤንች ሸኮ ኮሙኒኬሽን ነዉ

የፖሊስ አባላት የንግድ ሱቅና የመኖሪያ ቤት እድሳት አደረጉ።‎‎የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና የሚዛን አማን ከተማ  አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አመራሮችና አባላት ለአብሮነትና ለወገን...
28/05/2026

የፖሊስ አባላት የንግድ ሱቅና የመኖሪያ ቤት እድሳት አደረጉ።

‎የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አመራሮችና አባላት ለአብሮነትና ለወገን ደራሽነት ያላቸውን አጋርነት በተግባር አሳይተዋል።

‎የፖሊስ አመራርና አባላት ለ11 ዓመታት በፖሊስነት ሕዝብንና አገሩን በታማኝነት አገልግሎ በድንገተኛ ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ለቀድሞው ባልደረባቸው ዋና ሳጅን ጥላሁን ዳይመራ ቤተሰቦች ታላቅ የበጎ አድራጎት ሥራ አከናውነዋል።

‎ለቤተሰቡ ዘላቂ የገቢ ምንጭ የሚሆን የ3 በ 3 ሜትር ስፋት ያለው ሱቅ በመስራት እና ሸቀጣ ሸቀጦችን በማሟላት ለልጆቹ እናት ስራ እድል ተፈጥሮ የኩሽና እና የአንድ ሰርቪስ ቤት የማደስ ሥራ ተከናውኗል።

‎የፖሊስ አባላት አቅማቸው የፈቀደውን በማዋጣት ወደ 100 ሺህ ብር የሚጠጋ ገንዘብ እጅ በእጅ በመሰብሰብ ለሥራው አውለዋል።

‎ይህ የፖሊስ አባላት ተግባር የአንድነት፣ የሙያዊ አጋርነትና የወገንተኝነት ታላቅ ማሳያ ከመሆኑም በላይ ለሁሉም አርአያ የሚሆን ተግባር ነው።

የዳውሮ ዞን ፍትህ መምሪያ 7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ተዓማኒ እንዲሆን ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ገለጸምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የ...
28/05/2026

የዳውሮ ዞን ፍትህ መምሪያ 7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ተዓማኒ እንዲሆን ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ገለጸ

ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፍትህ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን በተገቢው እንዲወጡም ተጠይቋል።

የዳውሮ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ የሺ አሰፋ ቀሪዎቹ የምርጫ ቀናት እስከ ድህረ-ምርጫ ድረስ ያሉ ሂደቶችን በንቃት መምራት እንደሚገባ በመግለጽ ምርጫው ፍትሃዊ፣ ተዓማኒና ወቅቱን የጠበቀ የፍትህ ስርዓት እንዲሰፍን በየደረጃው የሚገኙ የፍትህ አካላት በትጋት መስራት እንደሚኖርባቸውም አሳስበዋል።

በተጨማሪም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከወትሮ በተለየ መልኩ በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን መራጩን ህዝብ ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ውይይቱ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣ የድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራና የውጤት አሰጣጥ እና አገላለፅ ሂደት እንዲሁም የምርጫ ቅስቀሳ ስነ-ምግባር መመሪያዎች ዙሪያ በዘርፉ ባለሙያዎች ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት ከምርጫ ጋር ተያይዘው ለሚፈጸሙ ወንጀሎች በሁሉም አካባቢዎች ተመሳሳይ ትርጓሜና ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል መድረክ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆንና የፍትህ ስርዓቱ እንዲጠናከር ልዩ ችሎቶች ተቋቁሞ ወደ ስራ መገባት አለበትም ብለዋል።

የዳውሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ብርሃኑ ከዞኑ ፖሊስ አባላት በምርጫ ሂደቱ የህግ የበላይነትን ለማስከበር ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ብለዋል።

በተጨማሪም በምርጫ ነክ ወንጄሎች ዙሪያ በየደረጃው በፈጣን የፍትህ አሰጣጥ ሂደት ላይ የሚታዩ መዘግየቶች ከወዲሁ ታርመው እንደምሄዱም አስገንዝበዋል።

በመድረኩ ከዞን፣ ከወረዳ እና ከከተማ አስተዳደር የፍትህ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በጨታና ጠሎ አዋሳኝ ደንበር አካባቢ የጋራ ውይይት መድረክ ተካሄደ።በጨታ ወረዳ ሾና ያለና በጠሎ ወረዳ በኩል ገራ ቀበሌዎች አዋሳኝ ደንበር አካባቢ ወንጀልን ለመከላከል እና ሰላምን ለማፅናት ...
28/05/2026

በጨታና ጠሎ አዋሳኝ ደንበር አካባቢ የጋራ ውይይት መድረክ ተካሄደ።

በጨታ ወረዳ ሾና ያለና በጠሎ ወረዳ በኩል ገራ ቀበሌዎች አዋሳኝ ደንበር አካባቢ ወንጀልን ለመከላከል እና ሰላምን ለማፅናት የሚያስችል ዉይይት ተደርጓል።

በየደረጃው ህዝባዊ የሰላም ውይይት መድረኮች በመፍጠር የህዝብን አንድነት ወደ ነበረበት ሰላም መመለስና ወደ ልማት መግባት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በመድረኩ የሁለቱ ወረዳዎች ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎችና የፀጥታ መዋቅሮች ተገኝተዋል ሲል የጨታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የደካ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤጽ አስታወቀ፡፡የደካ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለ...
28/05/2026

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የደካ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤጽ አስታወቀ፡፡

የደካ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን መንግሥቱ እንደገለፁት፤በደካ ከተማውን ሰላምና ፀጥታን አስተማማኝ እንዳደረግነው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከፖሊስ ጋር በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አክለውም በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ 6ቱ የምርጫ ጣቢያዎች፣ ዜጎች ያለምንም ስጋት ድምፃቸውን እንዲሰጡ እና የምርጫ ሂደቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ፤ ከህብረተሰቡ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ውይይት መደረጉን አመልክተው በከተማው ውስጥ ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ሶስት ተፎካካሪ ፓርቲዎች በምርጫው እየተሳተፉ መሆናቸውን አቶ ሰለሞን አስረድተዋል።

የደካ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጂን አገኘሁ አባተ በበኩላቸው ምርጫዉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፖሊስ አመራሮችና አባላት ጋር ዉይይት ተደርጎ ስምሪት መሰጠቱን ተናግረዋል።

አክለዉም ዋና ሳጂን አገኘሁ አባተ ዋሪዎች የምርጫ ሂደቱ ፍትሃዊ እና ሰላማዊ እንዲሆን የድርሻቸውን እንዲወጡና ለፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል ፡፡

27/05/2026
በሚዛን አማን ከተማ በተከናወነ የተቀናጀ ኦፕሬሽን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ንብረቶች ከተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ግንቦት 16 ቀን 20...
27/05/2026

በሚዛን አማን ከተማ በተከናወነ የተቀናጀ ኦፕሬሽን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ንብረቶች ከተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በተከናወነ የተቀናጀና ስኬታማ የኦፕሬሽን ስራ፣ የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ከተለያዩ የቴክኖሎጂ ንብረቶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።

በጥብቅ ክትትል ከተያዙት ንብረቶች መካከል ሶስት ዘመናዊ ስማርት ቲቪዎች (Smart TVs) እና አንድ ስማርት ስልክ ይገኙበታል።

ፖሊስ እንደገለጸው፣ ይህ መጠነ-ሰፊ ኦፕሬሽን ሊከናወን የቻለው ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥራት ያለው ጥቆማ እና የወንጀል መከላከል ክፍሉ ባደረገው ተከታታይ ጥብቅ ክትትል ነው። የሌባ ቡድን አባላት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ግለሰቦች፣ ማህበረሰቡን በማስመረር በተለያዩ መኖሪያ ቤቶችና ግለሰቦች ላይ የሰረቋቸውን እነዚህን ውድ የኤሌክትሮኒክስ ንብረቶች ለመሸጥ በድርድር ላይ እያሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ምናሉ ታደሰ በበኩላቸው በወቅታዊው የጸጥታ ሁኔታና በህዝብ ተሳትፎ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ጥሪ አስተላልፈዋል።

ኮማንደሩ እንዳሉት የከተማችንን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ማስጠበቅ የሚቻለው በፖሊስና በህብረተሰቡ መካከል ጠንካራና የማይበገረ የጋራ ትብብር ሲኖር ብቻ ነው። ዛሬ የተመዘገበው ስኬት የዚሁ ህዝባዊ አጋርነት ማሳያ ነው። ወንጀልን ለመከላከልና የህዝባችንን የሀብትና የንብረት ዋስትና ለማረጋገጥ ሌሊትና ቀን እየሰራን እንገኛለን።

ህብረተሰቡ በየአካባቢው የሚያያቸውን ማናቸውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች፣ እንግዳ የሆኑ ሰዎችንና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ወዲያውኑ ለፖሊስ በመጠቆም እያደረገ ያለውን አኩሪ ተሳትፎ ይበልጥ ሊያጠናክር ይገባልም ብለዋል።"*

ኮማንደር ምናሉ አክለውም፣ ፖሊስ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ምንም ዓይነት ምህረት እንደማያደርግና ህግ የማስከበር ስራው ወደኋላ እንደማይል አስምረውበታል።

የሚ/አ/ከ/አ/ፖ/ማ/አ/ወ/መ/ማስተባበሪያ ኃላፊ ዋና ሳጅን ማርቆስ አለማዬው በጉዳዩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ አስተማማኝ ለማድረግና የህዝብን ንብረት ከሌቦች ለመጠበቅ የተጀመረው ይኸው የተቀናጀ የኦፕሬሽን ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ወንጀለኞች በማንኛውም ሰዓትና ቦታ ተደብቀው ሊሰሩ እንደማይችሉና ፖሊስ ስምሪቱን ይበልጥ እያሰፋ እንደሚሄድም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር በዋሉት ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ ጥልቅ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝና የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀት በቀጣይም ጉዳያቸው በህግ አግባብ ታይቶ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ከፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተሽከርካሪ አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።ከቦንጋ ታርጫ ይጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በካፋ ዞን ጠሎ ወረዳ ዋሻ ቀበሌ የመገልበጥ አደጋ ደርሶ በአራት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳ...
27/05/2026

በተሽከርካሪ አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።

ከቦንጋ ታርጫ ይጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በካፋ ዞን ጠሎ ወረዳ ዋሻ ቀበሌ የመገልበጥ አደጋ ደርሶ በአራት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የአደጋዉ መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ያመለከተዉ ፖሊስ አሽከርካሪዎች መንገዱ አስቸጋሪ በመሆፍጥነታቸዉን ቀንሰዉ እንዲያሽከረክሩ የጠሎ ወረዳ ፖሊስ የትራፊክ ስራ ሂደት ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉጌታ በዛብህ ገልፀዋል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Address

ሸታ
Bonga

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Southwest Ethiopia Police Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category