ቦሌ ወረዳ 1/Bole woreda 01 Communication

ቦሌ ወረዳ 1/Bole woreda 01 Communication ይህ የቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 01 የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ትክክለኛ የፌስ ቡክ ገፅ ሲሆን በዚ ገፅ ማህበራዊ; ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መረጃዎች ለማህበረሰቡ ተደራሽ የምናረግበት የወረዳ አስተዳደሩ ፔጅ ነው
(1)

በሁሉም  ፈጣሪ አምላክ ረድቶን 7ኛውን ዙር ምርጫ ባጠናቀቅንበት ማግስት   ዛሬ 8ኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ክፍት አድርገናል። ለህዝባችን በገባነው ቃ...
04/06/2026

በሁሉም ፈጣሪ አምላክ ረድቶን 7ኛውን ዙር ምርጫ ባጠናቀቅንበት ማግስት ዛሬ 8ኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ክፍት አድርገናል።

ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ዛሬ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ባለ 7 ወለል ህንፃ ገንብተን በቴክኖሎጂ ተደራጅቶ 96 ተገልጋዮችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግዱ መስኮቶች ያሉት፣ በ22 ተቋማትና በ114 አገልግሎቶች ስራ አስጀምረናል።

ማዕከሉ ከፍ ባለ ጥራት እጅግ ውብ፣ ፅዱ፣ አካታች የሆነ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ፣ የህፃናት ማቆያ ያለው፣ ለሰራተኞችም ለተገልጋዮችም ምቹ ሆኖ የተገነባ ነው።

በቀጣይም በርካታ አገልግሎቶችን ወደ መሶብ ማዕከል በማስገባት ነዋሪዎች ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲያገኙ እናደርጋለን።

የከተማችን ነዋሪዋች መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አግልግሎት ለዘመናት አስልቺ ከነበረውና ውጣ ውረድ ከበዛበት እና በእጅ መንሻ ከተማረራችሁበት ቢሮክራሲ የሚያላቅቃችሁ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ! በማዕከላቱ በቦታ ሳትገደቡ በሚቀርባችሁ በየትኛውም ማዕከል በመገኘት ተገልገሉ።

ይህ ማዕከል ተጠናቆ ስራ እንዲጀምር ያስተባበራችሁትን በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት - ግንቦት 27፣ 2018 ዓ.ም
04/06/2026

የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት - ግንቦት 27፣ 2018 ዓ.ም

03/06/2026
03/06/2026
የወርሀ ሚያዝያ እና ግንቦት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት
03/06/2026

የወርሀ ሚያዝያ እና ግንቦት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁየአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡ምርጫውን አ...
03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡

02/06/2026
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል። አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲ...
02/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የድምፅ መስጫ ሂደቱ እስከ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ሲከናወን ቆይቷል። በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ግንቦት 24 ቀንም ሆነ ሌሊት ምንም አይነት ወንጀል አለመፈጸሙ ተገልጿል።

ድምጽ የመስጠት ስርዓቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ መራጩ ህዝብ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዕጩዎች እና ታዛቢዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለተወጡ መላው የጸጥታ አካላት ኮማንድ ፖስቱ ምስጋናውን አቅርቧል።

ድምጽ ቆጠራው ቀጥሏል።

ድህረ ምርጫ ያለው ሂደት በተመሳሳይ በስኬት እንዲከናወን ባለ ድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት ጥሪውን አቅርቧል።

01/06/2026
ኢትዮዽያ እየመረጠች ነው !እኔም መርጫለሁ!!ከንቲባ አዳነች አቤቤ
01/06/2026

ኢትዮዽያ እየመረጠች ነው !
እኔም መርጫለሁ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Address

Ring Rode
Bole

Telephone

+251936305947

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቦሌ ወረዳ 1/Bole woreda 01 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share