Ethiopia Daily News

Ethiopia Daily News Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopia Daily News, Public & Government Service, Wolaiyta, Boditi.

24/12/2024
26/11/2024
የወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ከዞን ጀምሮ እስከ መሠረታዊ ድርጅት ድረስ የሚገኙ የኮሚሽን አመራሮች በተገኙበት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ...
15/08/2024

የወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ከዞን ጀምሮ እስከ መሠረታዊ ድርጅት ድረስ የሚገኙ የኮሚሽን አመራሮች በተገኙበት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2017 የዕቅድ ኦረንቴሽን መድረክ ተካሄደ።

ነሐሴ 09/2016 ዓ.ም የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2017 የዕቅድ ኦረንቴሽን መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሄደ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የወላይታ ዞን ዋና አፈ-ጉባዔና የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ የፓርቲው የፖለቲካ ጤንነት እንዲጠበቅ ኮሚሽኑ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው በበጀት ዓመቱ በጥንካሬ የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራት ማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት በጥንካሬ የሚወሰድ እንደሆነ ያመላከቱት ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት በቀጣይ በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ፣ የጠንካራ ፓርቲ ግንባት እውን ለማድረግ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋልም፡፡

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ አበራ በኮሚሽኑ ቁልፍና ዐበይት ተግባራት እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች የኮሚሽኑን መጠናከር የሚያሳዩ በመሆኑ ኮሚሽኑ ለፓርቲው ጥንካሬ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት ስላለበት በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የተሰጡ የኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነቶች፤ እንዲሁም በፓርቲው አሥር ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ የተመላከቱ ጉዳዮች ውጤታማ በሆነ አግባብ መፈፀም እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ በፓርቲ በኩል የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የኮሚሽኑ ሚና እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ጠቁመው፣ የኮሚሽኑ የአሰራርና የአደረጃጀት መመሪያው ተግባራዊ እንዲሆን የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ሥራ መጠናከር እንዳለበት አመላክተዋል።

በ2016 በጀት ዓመት በኮሚሽኑ ቁልፍና ዐበይት ተግባራት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የኮሚሽኑ አደረጃጀቶች የእውቅና ሰርተፊኬት እንዲሁም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

በዚህም መሠረት በበጀት ዓመቱ ሶዶ ከተማ፣ አረካ ከተማ እና ጠበላ ከተማ አስተዳደር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች ከከተማ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች መካከል የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ የእውቅና ሰርተፊኬት የተሰጣቸው ሲሆን ሁምቦ፣ ቦ/ቦምቤ እና ኦፋ ደግሞ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ የእውቅና ሰርተፊኬት የተሰጣቸው የወረዳ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች ናቸው፡፡

በአጠቃላይ አፈፃፀም ከ23ቱ ወረዳና ከተማ አስተዳደር የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች ውስጥ ሶዶ ከተማ፣ አረካ ከተማ እና ሁምቦ ወረዳ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

ከዞን ማዕከል ፐብሊክ ሰርቫንት መሠረታዊ ድርጅት ኮሚሽኖች ውስጥ ማህበራዊ ቁጥር አንድ፣ አስተዳደራዊ ቁጥር ሁለት እና ኢኮኖሚያዊ ቁጥር ሁለት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅና ሰርተፊኬት የተበረከተላቸው ግንባርቀደም የኮሚሽን መሠረታዊ ድርጅቶች ናቸው፡፡

በመድረኩ የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ሰብሳሳቢ ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ፣ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ አበራ፣ የቅ/ጽ/ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ መቱሳል ቦሻ፣ የዞኑ ኮሚሽንና የመዋቅሮች ኮሚሽኖች ተገኝተዋል

እንደሀገር የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች ሴቶች ያበረከቱት ሚና የላቀ እንደነበረ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ገለጹሚያዚያ 15/2016 ...
23/04/2024

እንደሀገር የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች ሴቶች ያበረከቱት ሚና የላቀ እንደነበረ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ገለጹ

ሚያዚያ 15/2016 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ቅ/ጽ/ቤት በዞኑ ልማት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ዞናዊ የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን እንደሀገር የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የሴቶች ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ከውልደቱ ጀምሮ ሴቶችን በማሳተፍ ትላልቅ ሀገራዊ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉንም አስታውሰዋል።

እንደሀገር ያጋጠመውን የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ለተማሪዎች ግብዓት ማሟላት አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት ወ/ሮ ሰናይት ለዚህም እንደክልል የተጀመረው ለአንድ ተማሪ አንድ መጻፍ ሴቶች አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጠይቀዋል።

ልጆቻችን በክህሎት የበለጸጉ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ትውልድ እንዲሆኑ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መውጣት ይኖርብናል ነው ያሉት።

በክልሉ ያሉን የውስጥ ገቢ አቅምን አሟጦ በማሰባሰብ የህዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ሴቶች የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ሴቶች በገቢ ልማት ላይ አምባሳደር መሆን እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

በጤናው ዘርፍ ሴቶች ተገቢውን ግንዛቤ በማግኘት ጤናቸውን እንዲጠበቁ እንዲመረመሩ እኛ ግንባር ቀደሚ መሆን አለብን ነው ያሉት።

የወላይታ ዞን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም ደገፉ እኛ ሴቶች የለውጥ መንግስት የሰጠውን ዕድል በአግባቡ ተጠቅመን በሁሉም ዘርፍ የራሳችንን አደረጃጀቶችን በማጠናከር ዘርፈብዙ ተግባራትን ማከናወን ችለናል ብለዋል።

ያለሴቶች ተሳትፎ የትኛውም ዕቅድ ማሳካት አንችል ያሉት ወ/ሮ መስከረም ሴቶች በተሰማሩበት በስራ መስኮች የሚጠበቅብንን ኃላፊነት በትጋትና በታማኝነት እንዲወጡ አሳስበዋል።

እንደሀገር ተያይዘው የመጣውንና አሁን ያጋጠመውን የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ለተማሪዎች የትምህርት ግብዓት ማሟላት ሁነኛ መፍትሔ እንደሆነ የጠቆሙት ወ/ሮ መስከረም ለዚህም ለአንድ ተማሪ አንድ መፅሐፍ ንቅናቄ የተጀመረ ሲሆን እኛ ሴቶች የላቀ ተሳትፎን ማበርከት ይኖርብናል ብለዋል።

ገቢ ለአንድ ሀገር እድገት ወሳኝ መሆኑ የገለጹት ወ/ሮ መስከረም ሴቶች በየትኛውም የግብይት ሂደት ላይ ደረሰኝ ሳይወስዱ ግብይት እንዳይፈፅሙ ባህል እንዲያደርጉ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ለመስራት ከእኛ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመውጣት ቁርጠኛ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

ሴቶች ጤናቸው እንዲጠበቁ ለማስቻል ከልብ የመነጨ ሁሉአቀፍ ድርሻችን መውጣት እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል፡፡

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ድርሻዬ በለጠ በበኩላቸው መድረኩ በዋናነት በዞኑ መሠረታዊና አንገብጋቢ ከሆኑ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ሴቶች ግንባር ቀደም ሚናቸውን እንዲጫወቱ ለማስቻል ነው ብለዋል።

በመድረኩ የዞኑ ከፍተኛ ሴት አመራሮች፣ የወረዳና ከተማ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በወላይታ ዞን ለፍትህ ዘርፍ ሪፎርም የሚሆን ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ነውሚያዝያ 11/2016 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከወላይታ ዞን ምክር ...
19/04/2024

በወላይታ ዞን ለፍትህ ዘርፍ ሪፎርም የሚሆን ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው

ሚያዝያ 11/2016 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከወላይታ ዞን ምክር ቤት ጋር በጋራ ለፍትህ ማሻሻያ /ሪፎርም/ ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዱጼ ታምሩ ከተለዋዋጭ አለማዊ እና አገራዊ ሁኔታ ጋር እያደገ የመጣውን የህዝብ የመልካም አስተዳደር እና ፍትህ የማግኘት ፍላጎት ለማረጋገጥ ከህዝቡ ጋር በመወያየት ጊዜው የሚጠይቀውን የፍትህ አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።

በፍትህ አሰጣጥ ያሉ ጉድለቶችን ለይቶ በማውጣት ለፍትህ ማሻሻያ የመፍትሔ ሀሳብ የሚቀመጥበት እንደሆነ ያነሱት አቶ ዱጼ በቀጣይነት ባሉ የህዝብ ውይይት መድረኮች ግብዓቶች እንደሚሰበሰቡ ተናግረዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ለተሳታፊዎች ባሰሙት ንግግራቸው መልካም አስተዳደር ለማስፈን የህግ የበላይነት መከበር ወሳኝ እንደሆነ በመግለጽ ዜጎች ፍትህ የማግኘት ጉዳይ ሪፎርም የሚያስፈልገው እንደሆነ አስረድተዋል።

በፍትህ ተቋማት የሚስተዋለው የአገልጋይነት ስሜት መጓደል ፍትህን በገንዘብ የመስጠትና የማግኘት ሁኔታ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት አሠራር መጓደል የተገልጋይ እርካታና አመኔታ ማጣት በመሠረታዊነት ለመቀየር ሪፎርም ማስፈለጉን በማስረዳት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በየአካባቢው የሚነሱ የፍትህ አሠጣጥ ችግሮችን በማንሳት ውይይት እንዲደረግበት እና ግብዓት እንዲያቀርቡ አሳስበዋል።

የመድረኩ ዓላማ የፍትህ ተቋማት ገለልተኛና ነፃ እንዲሆኑ ማድረግን ግቡ ያደረገ መድረክ እንደሆነ በመግለጽ እየተሸረሸረ የመጣውን የህዝብ አመኔታ ለመፍጠር የሚካሄድ መድረክ ነው ብለዋል።

የወላይታ ዞን ምክር በት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ በበኩላቸው ህዝባችን በየመድረኮቹ ለሚያነሷቸው የፍትህ እና መልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሔ የሚሆን ግብዓት የሚገኝበት መድረክ እንደሆነ በማንሳት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በየአካባቢው የሚነሱ ከፍትህ አሰጣጥ ጋር የተያያዙ የህዝብ ጥያቄዎችን በኃላፊነት እንዲያቀርቡ አስገንዝበዋል።

Address

Wolaiyta
Boditi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Daily News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share