06/08/2026
ከበዴሳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለተገልጋዮች የተላለፈ መልዕክት ፦
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 6/2016 አንቀጽ 59(2) መሰረት ከነሃሴ 01 ቀን እስከ መስከረም 30 ቀን ድረስ በከፊል ዝግ ሆኖ የሚቆዩ መሆኑንና በዚህ ጊዜ የክልሉ ፍርድ ቤቶች ዳኞች የእረፍት ጊዜ እንድሆን በክልሉ የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁ 7/2016 አንቀጽ 39/1/ የተደነገገ በመሆኑ በእነዚህ ጊዜያት ፍርድ ቤቱ በከፊል ዝግ ሆነው የተመረጡና ጊዜ የማይሰጡ አስቸኳይ ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎት የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡
በዚህም መሠረት የበዴሳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከነሃሴ 1/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ወራት በከፊል ዝግ ሆኖ የሚቆይ መሆኑን ባለጉዳዮቻችንን እናሳስባለን።
ፍርድ ቤቱ በከፊል ዝግ በሚሆንበት ጊዜ የዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብት እንዳይጣስና ጊዜ የማይሰጣቸው አስቸኳይ የሕግ ጉዳዮችን ማየት አስፈላጊ በመሆኑ በከፊል ዝግ ወቅት የሚታዩ ጉዳዮች የሚከተሉት ብቻ ናቸዉ።
-->👉 ፦
✅ የዋስትና ክርክር፤
✅የጊዜ ቀጠሮ፤
✅የብርበራ ትዕዛዝ፤
✅የመያዣ ትዕዛዝ፤
✅አካል ነፃ ማውጣት ጥያቄ፤
✅አመክሮ፤
✅ቅጣት ይደመርልኝ ጥያቄ
✅እጅ ከፍንጅ ወንጀሎች
✅በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃትን የሚመለከቱ ወንጀሎች፤
--> ፦
✅የቀለብ ክርክር፤
✅የሥራ ክርክርና የደመወዝ ጥያቄ፤
✅በተከራካሪ ወገኖች ስምምነት የተሰጡ ፍርዶች አፈፃፀም በሚመለከት
✅የዕግድ ትዕዛዝ የሚመለከቱ ጉዳዮች
✅ተከራካሪ ወገኞች ስምምነት መሠረት ፍርድ እንዲሰጥ ወይም እንዲመዘገብ የሚቀርብ አቤቱታ ሆኖ ሌሎች አፈፃፀም ጉዳዮች ታግዶ የሚቆዩ ሲሆን በፍትሐብሄርም ሆነ ወንጀል ጉዳዮች ፋይል መክፈት የሚሰራ ይሆናል።
ማሳሰቢያ:-ሌሎች እንደ ጉዳዪ አግባብ እየታዬ አስቸኳይነቱ በፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ፣ በመስማትና መወሰን ዋና ሥራ ሂደት ወይም በችሎቱ ሲታመን በተረኛ ችሎት ሊታዪ ይችላሉ።
አስተዳደር _መጀመሪያ_ደረጃ_ፍርድ_ቤት
ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም
በዴሳ