Jiille Tumuga Culture,Tourism and sport office

Jiille Tumuga Culture,Tourism and sport office Manni kophe obsine gurgurtaa kophee dhalaa fi dhiira,kan magaala fi baadiya,akkasumas kophe

14/09/2026

🏋️ ላይፍ ጂም — ለጤናማ አካልና ለጠንካራ ሕይወት!

በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ላይፍ ጂም የስፖርት አገልግሎቱን በማስፋት አዳዲስ የጂም መስሪያ ማሽኖችንና የክብደት ብረቶችን አስገብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።

ስፖርት የአካልን ብቃት ከማሻሻል ባለፈ ጤናማ አኗኗርን፣ ትጋትንና የራስ መተማመንን የሚገነባ የሕይወት መርህ ነው። በመሆኑም የሰንበቴ ከተማ ነዋሪዎች ይህንን ዕድል በመጠቀም ለጤናቸውና ለአካላዊ ብቃታቸው ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።

ጤናማ አካል፣ ጠንካራ አእምሮ፣ የተሻለ ሕይወት! 💪

👉 ዛሬ ይጀምሩ፤ ስፖርትን የዕለት ተዕለት ልምድዎ ያድርጉ።
ላይፍ ጂም — ለጤናዎ ይንቀሳቀሱ!

አድራሻ :-ሰንበቴ ከተማ ወጣት ማእከል ግቢ
ኢንስትራክተር ሰይድ እንድሪስ
ስ.ቁ +251922616367

🏋️‍♂️  #ለሰንበቴ ከተማ ነዋሪዎች እና የስፖርት አፍቃሪዎች በሙሉ! 🏋️‍♀️ውድ የከተማችን ነዋሪዎች    የስፖርት ቤት ባለቤት ሰይድ እንድሪስ ዛሬ ልዩ የቡና ጠጡ ፕሮግራም በማዘጋጀት የ...
14/09/2026

🏋️‍♂️ #ለሰንበቴ ከተማ ነዋሪዎች እና የስፖርት አፍቃሪዎች በሙሉ! 🏋️‍♀️

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች የስፖርት ቤት ባለቤት ሰይድ እንድሪስ ዛሬ ልዩ የቡና ጠጡ ፕሮግራም በማዘጋጀት የተከበሩ እንግዶቹን ጋብዟል። በዚሁ ዕለትም ስፖርት ቤታችንን ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ አስደሳች ዜናዎች ተነግረዋል! ☕💪

ስፖርት ቤታችን ስፖርተኞችን በብቃት ለማስተናገድ የሚያስችሉ አዳዲስና ዘመናዊ የጂም እቃዎችን አስገብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጓል።
በቀጣይ 2 ወራት ውስጥ ከዚህም የላቁ እና ይበልጥ ዘመናዊ የሆኑ ተጨማሪ እቃዎች ወደ ስፖርት ቤታችን እንደሚገቡ ተገልጿል።

ስፖርት ለአካል ጤንነት ለአእምሮ ንቃት እና ለጠንካራ ሕይወት ያለውን ትልቅ ጠቀሜታ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ባለቤቱ ሰይድ እንድሪስ የሰንበቴ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ወደ ስፖርቱ በመቀላቀል ጤናቸውን እንዲጠብቁ እና አካላዊ ብቃታቸውን እንዲገነቡ አጥብቆ ጥሪውን አስተላልፏል።

አካል ብቃትዎን ለማሻሻል ክብደት ለመቀነስ ወይም ጡንቻ ለመገንባት ፈልገዋል? እንግዲያውስ 👇👇

​ አድራሻ ሰንበቴ ከተማ ወጣት ማዕከል
📞 ስልክ ቁጥር 0922616367

💪 ለጤናማ አካል እና ጠንካራ ሰውነት - Life Gym ሁልጊዜም ከአንተ ጋር!

11/09/2026
11/09/2026

Aweytu hot spring natural water found in oromo special zone,Jille Timuga woreda.



10/09/2026

09/09/2026

"ጳጉሜ 5 - የነገዋ ቀን

በነገው እለት ጳጉሜ 5 የነገዋ ቀን በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች በድምቀት ይከበራል።

የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር እና የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በጋራ በመሆንም የዚህን ታላቅ ቀን ትርጉም በተግባር ለመግለጽ የደም ልገሳ መርሃ ግብር በማካሄድ ያሳልፋል።

ደም መለገስ ሕይወትን ማዳን ነው። የምንለግሰው ደም በአስቸጋሪ ወቅት ላይ ላለ ወገናችን የሕይወት ተስፋ ሊሆን ይችላል።

ስለሆነም ሁላችሁም ደም መለገስ የምትችሉ ሁሉ ደም በመለገስ ህይወትን እንድታደጉ ጥሩ እናቀርባለን።

ነገን የምንገነባው ዛሬ በምንሠራው መልካም ተግባር ነው። እርስዎም የደም ልገሳውን በመቀላቀል አንድ ሕይወት ለማዳን የሚያስችል የመልካምነት አሻራዎን ያሳርፉ።

ደም እንለግስ፤ ሕይወት እናድን፤ መልካምነትን እናስፋፋ።

ጳጉሜ 5 የነገዋ ቀን ነው፤ የነገን ተስፋ ዛሬ እንገንባ!

03/09/2026
"የስፖርት ዘርፉን በባህላዊ አሠራር ብቻ መምራት አይቻልም" አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)የስፖርት ዘርፉን ከዚህ በፊት በነበረው ባህላዊ አስተሳሰብና አሠራር ብቻ መምራት የሚቻልበት ወቅት አለመሆኑን ...
03/09/2026

"የስፖርት ዘርፉን በባህላዊ አሠራር ብቻ መምራት አይቻልም" አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)

የስፖርት ዘርፉን ከዚህ በፊት በነበረው ባህላዊ አስተሳሰብና አሠራር ብቻ መምራት የሚቻልበት ወቅት አለመሆኑን የአማራ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶ/ር አብዱ ሁሴን ገለጹ።

ዶ/ር አብዱ ሁሴን ይህን የገለጹት 27ኛው የአማራ ክልል ስፖርት ምክር ቤት ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ ሲካሄድ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

ስፖርት ከጤናና ከዜጎች መሠረታዊ መብት ባሻገር ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መፍትሔ የሚያበረክት ዘርፍ መሆኑን ጠቁመው፣ በተለይም ወጣቶችን ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በየደረጃው ዘመናዊ አሠራር መዘርጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የክልሉን ስፖርተኞችና አሠልጣኞች ከስፖርቱ የሚገኘውን ዘመናዊ ጥቅም እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር፣ የክልሉን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለኢትዮጵያ የሚኖረውን አስተዋጽኦ ማሳደግ ከስፖርት አመራሩ የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑንም ገልጸዋል።

በተጨማሪም መንግሥት ለስፖርቱ ዘርፍ ልዩ ትኩረት እየሰጠ መሆኑን ጠቁመው፣ የስፖርት ልማትና አስተዳደር አዋጅ መጽደቅ፣ የስፖርት ፖሊሲ በአዲስ መልክ መዘጋጀትና የስፖርት መሠረተ ልማቶች መገንባት ለዘርፉ እድገት የሚያበረክቱ ተግባራት መሆናቸውን አንስተዋል።

በጉባኤው የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም፣ የ2019 ዓ.ም ዕቅድና የማስፈጸሚያ በጀት እንዲሁም የ2018 ዓ.ም የኦዲት ሪፖርት በጥልቀት እንደሚገመገም ተገልጿል።

Address

Bati

Telephone

+251920791673

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jiille Tumuga Culture,Tourism and sport office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share