የአማራ ክልል ህዝብ ዝክረ-ታሪክ ማዕከል
Amhara people Historical memoirs Center
ነባሩ ስያሜ የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት ጽ/ቤት የሚለው በውስጡ ከ1973-1983 ድረስ የአስር ዓመት ሰማዕታት መታሰቢያ ብቻ ይዞ ስለነበር ስያሜውና የውስጥ ይዘቱ አይገናኙም ነበር፡፡
አዲሱ የተቋሙ ስያሜ በይዘት ደረጃ በቀጠናው ያለውን ማህበረሰብ፤ ከፍታ ላይ የደረሰ ታሪክ የነበረን (ላልይበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያን፤ የሾንኬ መንደር፤ ጎንደር ቤተ-መንግስት፤ አንኮበር ቤተ-መንግስት፤ ንጉስ ተክለሃይማኖት ቤተ-መንግስት፤ ንጉስ ሚካኤል ቤተ-መንግስትና ሌሎችንም ይዘክራል፡፡
ክልሉ የተፈጥረ ጸጋ
ባለቤት፤ (ጣና ሃይቅ፡ አባይ ወንዝ፡ ሰሜን ተራሮች ፓርክ፤ አላጣሽ ፓርክ፡ ልዩ ልዩ ፋፋቴዎች)፤ ከየክፍለ ዘመኑ ትውልድ ተሸጋሪ የሆኑ ሰራዎች ማስተማርና ስነ-ልቦናን ለተሻጋሪ ስራ ማዘጋጀት፤ ለአሸናፊነት ስነ-ልቦና መዘጋጀት የሚያነሳሱ፤ ታታሪነትና ጥበብ (ዊዝደም) ያለው ማህበረሰብ መገንባት፤ በራስ ማንነት ቋንቋ ፣ ባህል የሚሰራ ትውልድ ማነጽ፤ ለውጭ ወራሪ የማይበገር ማህበረሰብ መሆኑን ማስተላለፍና ድክመቶች ላይ አለማተኮርን ይይዛል፡፡
ስያሜውና ይዘቱ እንዲጣጣም ባለን ውስን ሙዚየም የክልላችን ህዝብ ታሪክ በጥንታዊ፡ በመካከለኛውና በዘመናዊዉ ታሪክ በማደራጀት በየዘመናቱ የታሪክ አሻራ ጥለው ያለፉት ላይ እንዲያተኩር ይደረጋል፡፡
የሥዕል ጋላሪውም በተፈጥሮ መስዕብ፤ በባህልና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች የሚደራጅ ይሆናል፡፡
በአጠቃላይ የአማራ ክልል ህዝብ ዝክረ-ታሪክ ማዕከል /Amhara Regional People Memoirs Cenetr/ ከበሩ ጀምሮ የክልላችን ህዝብ ታሪክ ግቢው እንዲናገር ተደርጎ ይደራጃል፡፡
ስያሜውንና ይዘቱን ለማስረጽ በኪነ-ቅርጽ፤ በመልዕክቶች፤ በንባብ ቤቶች፤ በኢንተርኔት ቴክኖሎጅ፤ በአንፊ ቲያትር፤ በስዕል ጋላሪ፤ በጋርደኖች፤ በመዝናኛ ቤቶች ማህበረሰብ መገንባትና የቱሪስት መዳረሻ ማድረግ ላይ አተኩረን እንሰራለን!
አሻራቸው ለትውልድ የሚያስተላልፉ ተመርጠው በሚሰሩ ኪነ-ቅርሶች (Sculptures) ለአብነት (ንጉስ ላልይበላ፣ አጼ ፋሲለደስ፣ የአጼ ቴዎድሮሰ፣ የአጼ ሚኒሊክ፣ እቴጌ ጣይቱ፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት፣ ንጉስ ሚካኤል፣ ደጅአዝማች በላይ ዘለቀ፣ የዘመኑን ተጋድሎ የሚያስታውስ) ሌሎቹ በሙዚየምና በስዕል ጋላሪ ክፍሉ ይካተታሉ፡፡
የሚሰጡንን አስተያየት እንደ አስፈላጊነቱ እንጠቀምበታለን፡፡
058218 0448
058 218 458
058 2180378
0913614454
ባህር ዳር
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Amhara people History memoirs Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.