Amhara Health Bureau - አብክመ ጤና ቢሮ

Amhara Health Bureau - አብክመ ጤና ቢሮ This page is an official page of the Amhara Regional Health Bureau.

29/05/2026
በጤናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ የተቋማት የሪፎርምና የግንባታ ስራዎችን የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተው ተመልክተዋል።አመራሮቹ በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በደብረታቦ...
28/05/2026

በጤናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ የተቋማት የሪፎርምና የግንባታ ስራዎችን የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተው ተመልክተዋል።

አመራሮቹ በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በደብረታቦር ጤና ጣቢያንና በደብረታቦር ሆስፒታል የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎችንና ግንባታዎችን ተመልክተዋል።

በደብረታቦር ጤና ጣቢያ የተሰሩ የተቋማት ሪፎረም ስራዎች በተለይም የተቋሙን ገጽታ ለማሻሻል ምቹና ሳቢ የተገልጋይ እና የስራ ከባቢ ለመፍጠር የተሰሩ የገጽታ ማሻሻል ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸው ተመላክቷል።በተቋሙ የተፈቱና ያልተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንም አመራሮች የተመለከቱ ሲሆን የላብራቶሪ ክፍሎችን የማዘመን ስራ፣የኦፕሬሽን ሩም ለማስጀመር እንዲሁ የእናቶችና ህጻናት ህክምና ላይ የተሰሩ ስራዎች ለሌሎች ሞዴል የሚሆኑ እንደሆነም ነው የተመለከቱት።

በደብረታቦር ሆስፒታል በክልሉ ጤና ቢሮ ድጋፍና በተቋሙ በቅንጅት እየሰተሩ ያሉት የህጻ ማሻሻልና የማስፋፋት ስራዎች በሆስፒታሉ አገልግሎቶችን ለማላቅ አቅም እንደሚሆን ተገልጿል።የህክምና አገልግሎትን በተመለከተ ታካሚዎችን እየተዘዋወሩ በመጠየቅ ያለውን የአገልግሎት ሁኔታ ተመልክተዋል።

በመጨረሻም ከሆስፒታሉ አካላት ጋር ስለ አገልግሎት አሰጣጥ፣የገጽታ ማሻሻል ግንባታዎችና ማስፋፊያ ስራዎች በተመለከተ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታና በሚያጋጥሙ ክፍተቶች ውይይት ተደርጎ በተቋሙ፣በከተማ አስተዳደሩ እና በክልሉ በኩል ሊፈቱ የሚገቡት ተለይተው በባለድርሻ አካላት በኩል እንዲፈቱ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የአብክመ መሬት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ፣ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን፣የአብክመ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አማካሪ አቶ ባየ አለባቸው፣የርዕሰ መስተዳደሩ የመሰረተ ልማት አማካሪ አቶ ደሴ አሰሜ፣የአብክመ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አገኘሁ ካሳው ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት በምልከታው ተገኝተዋል።ከአብክመ ኮምንኬሽን የተወሰደ)
#አብክመጤናቢሮ

ኢድ የደስታ፣ የእዝነትና የርህራሄ የመተሳሰብ፣ ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የሚያሳልፈው ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናክር በዓል ነው ሲሉ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አብዱል...
26/05/2026

ኢድ የደስታ፣ የእዝነትና የርህራሄ የመተሳሰብ፣ ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የሚያሳልፈው ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናክር በዓል ነው ሲሉ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ ገለጹ፡፡

‎የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የዒድ አል አድሃ፣ አረፋ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
‎******
‎በቅድሚያ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሐ( አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ማለት እወዳለሁ።

‎ዒድ አል አድሃ፣አረፋ የእስልምና እምነት ተከታዮች በታላቅ ክብር እና ፍቅር የሚያከብሩት፣ መስዋዕትነትን የሚዘክር በዓል ነው፡፡

‎ህዝበ ሙስሊሙ ታላቁን የአረፋ በዓል ሲያከብር አቅመ ደካማ ወገኖቹን በመጠየቅ የተራቡትን በማብላትና የታረዙትን ማልበስ የተለመደ ተግባር እንደሆነ ይታወቃል።

‎ኢድ የደስታ፣ የእዝነትና የርህራሄ የመተሳሰብ፣ ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የሚያሳልፈው ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናክር በዓል ነው፡፡

‎አረፋ፣ የሰው ልጅ ለፈጣሪው እና ለእምነቱ ሲል፣ መከራ ለመቀበል፣ ካስፈለገም ለመስዋዕት ያለውን ፈቃደኛነት የምናስታውስበት፣ የምናከብርበት፣ የምንዘክርበት ልዩ ቀን ነው፡፡

‎ኢድ የደስታ፣ የእዝነትና የርህራሄ የመተሳሰብ፣ ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የሚያሳልፈው ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናክር በዓል ነው፡፡

‎በዓሉ የደስታና የመረዳዳት በዓል በመሆኑ የእምነቱ ተከታይ ወንድሞችና እህቶች በዓሉን ስናከብር አቅመ ደካማ ወገኖቹን በመጠየቅ የተራቡትን በማብላትና የታረዙትን ማልበስ የተለመደ ተግባር እንደሆነ ይታወቃል።

‎የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና ሃይማኖታዊ ስርዓቱንም በተከተለ መልኩ ሊሆን ይገባዋል፡፡

‎በመጨረሻም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ ሌት ተቀን ህዝብን ለማገልገል ቆርጣችሁ ለተነሳችሁ የጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያዊያን በድጋሚ እንኳን ለ1ሺ 447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሠላም፣ የጤና የመተሳሰብና የአንድነት በዓል እንዲሆንላችሁ ምኞቴን እገልፃለሁ ።

‎አብዱልከሪም መንግስቱ
‎የአብክመ ጤና ቢሮ ሃላፊ
‎ግንቦት/2018 ዓ/ም


#አብክመጤናቢሮ

25/05/2026

በእርግዝና ወቅት ደም መፍሰስ

23/05/2026
የጤና ሚንስቴር ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር  አለም አቀፍ ከወሊድ በኃላ የሚፈጠር ፊስቱላን የማጥፋት ቀን በባህር ዳር ከተማ አከበረ።በዓሉ በዓለም ለ 14ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ13...
23/05/2026

የጤና ሚንስቴር ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር አለም አቀፍ ከወሊድ በኃላ የሚፈጠር ፊስቱላን የማጥፋት ቀን በባህር ዳር ከተማ አከበረ።

በዓሉ በዓለም ለ 14ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ13ኛ ጊዜ "ጤናዋ መብቷ:- ለፊስቱላና በወሊድ ወቅት ለሚከሰቱ ጉዳዩች ትኩረት እንስጥ" (Her health is a right :Invest in fistula and child birth injuries) በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የፌደራል፣የክልልና የአጋር አካላት የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት ተከብሯል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የእናቶች፣ህጻናት፣ወጣቶችና ስርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መልሰው ጫንያለው እንደገለጱት በጤና ተቋማት ነፍሰ ጡር እናቶች በቅድመ ወሊድ፣ወሊድና ድህረ ወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ በተሰራው ስራ የእናቶችና ህጻናት ጤና ማሻሻል ተችሏል ብለዋል።

ሴቶች ከማርገዛቸው በፊት የቅድመ እርግዝና ምርመራ በጤና ተቋም እንዲያገኙ አዲስ አገልግሎት በ3መቶ 72 ተቋማት መጀመሩን አሳውቀዋል።

ከርቀት አካባቢ የሚመጡ ነፍሰጡር እናቶችን በእናቶች ማቆያ ክፍል ቆይተው ክትትል በማድረግ በሰለጠነ ባለሙያ እንዲወልዱ መደረጉን ገልጸዋል ።
በክልሉ በሚገኙ ከ6መቶ በላይ የእናቶች ማቆያ ክፍሎች በላፉት 9 ወራት ከ18ሽህ በላይ እናቶች አገልግሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት ከ600 በላይ ፊስቱላ እና ከ3ሽህ 6 መቶ በላይ የማህጸን መውጣት ችግር የተጋለጡ ወገኖች ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።

ተጎጅዎችን ለይቶ በመላክ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ አስተዋጾ ላደረጉ የጤና ባለሙያዎች፣ታክመው የዳኑ አምባሳደሮችና አጋር ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል።

በጤና ሚንስቴር የእናቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች መሪ ስራ አስፈጻሚ ተወካይ ሲ/ር ዘምዘም መሀመድ እንዳሉት መንግስት የእናቶችና ህጻናት ጤና ለማሻሻል በሰራቸው ስራዎች አበረታች ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል።

64 በመቶ ነፍሰጡር እናቶች በጤና ተቋም ክትትል አድርገው በሰለጠነ ባለሙያ መውለዳቸውን አሳውቀዋል::

ለእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት የሚሰጡ የጤና መሰረተ ልማት እንዲስፋፉ፣ በግብዓት፣ በህክምና መሳሪያና በሰለጠነ ሰው ሀይል እንዲደራጁ አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በወሊድ ምክንያት የሚከሰተውን ፊስቱላ ተጠቂዎች ለይቶ ህክምና በጤና ተቋም እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ሁሉም አካል የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በጤና ሚንስቴር የፕሮግራም ዘርፍ አማካሪ አቶ ዩናስ ዞላ የፊስቱላ ተጎጅዎች ከሚገጥሟቸው የጤና ችግሮች በተጨማሪ ለስነ ልቦና፣ ለማህበራዊና ኢኮኖሚ ችግሮች ይጋለጣሉ ብለዋል።

ህሙማን ህክምናውን ካገኙ በኃላ ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ በገቢ ማስገኛ ስራዎች እንዲቋቋሙ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የፊስቱላ በሽተኞችን ለይቶ በማፈላለግ ህክምና እንዲያገኙ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመድረኩ የተለያዩ የውይይት መነሻ ጽሁፎች ቀርበው የፓናል ውይይት ተካሄዷል።
#አብክመጤናቢሮ


ግንቦት 14/2018 ዓ.ም

የአማራ ክልል ማህበራዊ ክላስተር ሴት የመንግስት ሰራተኞች በወቅታዊ ጉዳይ በጋራ ተወያዩ።በውይይቱ የተለያዩ ጥያቄዎችና አሰተያየቶች ተነስተው ማደማደሚያ የተሰጠ ሲሆን ሴት የመንግስት ሰራተኞች...
22/05/2026

የአማራ ክልል ማህበራዊ ክላስተር ሴት የመንግስት ሰራተኞች በወቅታዊ ጉዳይ በጋራ ተወያዩ።

በውይይቱ የተለያዩ ጥያቄዎችና አሰተያየቶች ተነስተው ማደማደሚያ የተሰጠ ሲሆን ሴት የመንግስት ሰራተኞች በተሰማሩበት የስራ መስክ እያበረከቱት ያለውን አስተዋጾ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠይቋል።

ሴቷች ሰላም እንዲሰፍን፤ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫም በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
#አብክመጤናቢሮ


ግንቦት 14/2018ዓ.ም

22/05/2026

የደም ግፊት Hypertension (HTN)
________

👉የደም ግፊት (Hypertension) ምንድን ነው?

የደም ግፊት (Hypertension) ማለት ደም በደም ሥሮች ግድግዳ ላይ የሚፈጥረው ግፊት ለረጅም ጊዜ ከመደበኛው በላይ ሆኖ ሲቆይ ነው።

በዓለም ላይ ከ3 አዋቂዎች 1ዱ የደም ግፊት አለበት፤ ብዙዎች እንዳለባቸው እንኳን አያውቁም።

👉ለደም ግፊት አጋላጭ ሁኔታዎች

▪ከመጠን በላይ ጨው መመገብ
▪የፍራፍሬና አትክልት አመጋገብ ዝቅተኛ መሆን
▪የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማነስ
▪ከመጠን ያለፈ ውፍረት

ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ተጋላጭ ሲሆኑ ወንድ ዕድሜ ከ55 በላይ፣ ሴት ዕድሜ ከ65 በከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው።

👉የደም ግፊት ምልክቶች

ብዙ ሰዎች በመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶችን ላያስተውሉ ይችላሉ። ስለዚህ “ዝምተኛ ገዳይ” ተብሎ ይጠራል።

▪የተለመዱ ምልክቶች፦ ራስ ምታት፣ ማዞር፣ የዓይን ብዥታ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም፣ የልብ ምት መጨመር፣ ድካም፣ አንዳንድ ጊዜ ከአፍንጫ ደም መፍሰስ፤

▪ከፍተኛ የደም ግፊት ምልክቶች፦ ከባድ ራስ ምታት፣ ግራ መጋባት፣ ለመተንፈስ መቸገር፣ ከባድ የደረት ህመም፤

👉የደም ግፊት ምርመራ

የደም ግፊት በዋናነት ምርመራ የሚደረገው የደም ግፊት በመለካት ነው።
▪መደበኛ፦ ከ120/80 mmHg በታች
▪ከፍ ያለ፦ 120–139 / 80-89
▪ደረጃ 1 የደም ግፊት፦ 140–159 / 90–99
▪ደረጃ 2 የደም ግፊት፦>160/>100 mmHg
▪ሌሎች ምርመራዎች፦ የደም ምርመራ፣ የሽንት ምርመራ፣ ECG/EKG፣ የኩላሊት ሥራ ምርመራ፣ የዓይን ምርመራ፤

👉የደም ግፊት የሚያስከትለው ጉዳት

በጊዜ ያልታከመ የደም ግፊት ብዙ የሰውነት አካላትን ሊጎዳና ውስብስብ የጤና እክሎችን ያስከትላል።
የልብ ችግር፣ የልብ ድካም፣ የልብ ድንገተኛ ህመም፣ የልብ መጠን መጨመር፣ የአንጎል ችግሮች፣ ስትሮክ፣ የኩላሊት ሥራ መቋረጥ፣ የእይታ ችግር፣ አኑሪዝም (Aneurysm)።

👉መከላከያ መንገድ

▪የጨው መጠን መቀነስ
▪መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ
▪ጤናማ ክብደት መጠበቅ
▪ሲጋራ ማቆም፣ አልኮል መቀነስ
▪ውጥረት/ጭንቀት መቀነስ
▪መድሀኒቶችን በሐኪም ትዕዛዝ መሠረት ብቻ መውሰድ

👉ከመድሀኒት ወጪ መቆጣጠሪያ መንገዶች

1. አመጋገብ (Diet)
ጤናማ አመጋገብ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ይረዳል።
የሚመከሩ ምግቦች፦

▪ፍራፍሬና አትክልቶች (ሙዝ፣ ፖም፣ ብርቱካን፣ ማንጎ)
▪ያልተፈተጉ እህሎች (Whole grains)
▪ለውዝ፣ ዝቅተኛ ስብ ያላቸው የወተት ተዋጽኦዎች፣ ዓሳና ዶሮ
▪ጤናማ ዘይቶች (የወይራ ዘይት፣ የአኩሪ አተር ዘይት፣ የበቆሎ ዘይት፣ የሱፍ አበባ ዘይት) በትንሽ መጠን (በቀን ከ2 ማንኪያ በታች)

2. በፖታስየም የበለፀገ ምግብ
ፖታስየም ያላቸው ምግቦች የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳሉ። ፖታስየም የጨው (sodium) ተጽእኖን ይቀንሳል።
ፖታስየም ያላቸው ምግቦች፦ ሙዝ፣ አቮካዶ፣ ስፒናች፣ ባቄላ፣ ብርቱካን፣ ድንች

3. ውጥረት/ጭንቀት መቀነስ (Stress Reduction)
ረጅም ጊዜ የሚቆይ ውጥረት/ጭንቀት መቆጣጠር የደም ግፊትን ለመቀነስ ያግዛል፣ እንዲሁም ጤናማ የአኗኗር ለውጦችንና መድሀኒቶችን በትክክል መከተልን ያነሳሳል።

ውጥረትን/ጭንቀትን ለመቀነስ የሚረዱ መንገዶች፦
በቂ እንቅልፍ ማግኘት (በሌሊት 7–9 ሰዓት)፣ ራስን ማረጋጋት፤

እነዚህ የአኗኗር ለውጦች እንደ ስትሮክ፣ የልብ ድካም፣ የኩላሊት በሽታ እና የዓይን ችግሮች ያሉ ውስብስቦችን ለመከላከል ጠቃሚ ናቸው።

‎ጤና ተቋማትን ጽዱ ፣ ውብ ፣ ሳቢና ማራኪ በማድረግ በተገኘው ስኬት የብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ‎‎በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የማህበረሰብ ተሳትፎና የመጀመርያ ደረጃ ጤ...
22/05/2026

‎ጤና ተቋማትን ጽዱ ፣ ውብ ፣ ሳቢና ማራኪ በማድረግ በተገኘው ስኬት የብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ

‎በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የማህበረሰብ ተሳትፎና የመጀመርያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ዳይሪክቶሬት የ2018ዓ/ም የ9 ወር በዋን ዋሽ ፕሮግራም የሃይጅንና አካባቢ ጤና አጠባበቅን ዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ በባህርዳር ከተማ እያካሄደ ነው፦

‎በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማህበረሰብ ተሳትፎና የመጀመርያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ዳይረክቶሬት ዳይሪክተር አቶ ወንድሜነህ ልየው እንደተናገሩት በአማራ ክልል የንፁህ ውሃ፣ ሳኒቴሽን እና ሃይጂን አገልግሎቶችን ለማሻሻል በተለያዩ ወረዳዎች ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

‎ ፕሮግራሙ በተለይ በገጠር አካባቢዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሳደግ፣ የመጸዳጃ ቤት አገልግሎትን ለማሻሻል እና የህዝብ የጤና ግንዛቤን ለማጠናከር ተግባራዊ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

‎በፕሮግራሙ ከተሰሩ ዋና ስራዎች መካከል የውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ የውሃ መስመር ዝርጋታ፣ በትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማት የመጸዳጃ ቤት እና እጅ መታጠቢያ ተቋማት ግንባታ፣ እንዲሁም ለማህበረሰቡ የንፅህና ግንዛቤ ስልጠናዎች ይገኙበታል ብለዋል።

‎በዚህም ምክንያት ብዙ ዜጎች የንፁህ ውሃ ተጠቃሚ ሆነዋል ብለው ከውሃ ጋር የተያያዙ በሽታዎች መቀነሳቸውንና የትምህርት ቤቶች የንፅህና ሁኔታም መሻሻሉን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

‎በተጨማሪም ሴቶችና ህፃናት ውሃ ለማምጣት የሚያጠፉትን ጊዜ በእጅጉ መቀነሳቸውንና፤ አንዳንድ አካባቢዎችም ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ዘላቂ በሆነ መንገድ ነፃ (SODF) ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለህብረተሰቡ ጤናና ለአካባቢ ንፅህና ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን አብራርተዋል።

‎ሆኖም ፕሮግራሙ በተግባር ሲፈፀም የፀጥታ ችግሮች፣ የፋይናንስ እጥረት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ግዜ አለመጠናቀቅ እና የግንባታ ማቴርያል የዎጋ መናር በጥቂት ወረዳዎች ለፕሮግራሙ ተገቢውን የአመራርና የባለሙያ ትኩረት ሰጦ የመምራት እና የሚመለከታቸው ሴክተሮች የቅንጅት ጉድለት ተግዳሮት መሆኑን አቶ ወንድሜነህ ልየው ገልፀዋል።

‎ሆኖም እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ በቀሪ ጊዜት የመንግስት፣ የአጋር ድርጅቶችና የማህበረሰቡ የተቀናጀ ትብብር እና የአመራሩና የባለሙያውን ጥብቅ ክትትል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎በግምገማ መድረኩ ችግሮች ተለይተው የጋራ የመፍትሄ ሀሳብ የሚቀመጥበት ፣ተሞክሮዎች ላይ የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት እና በቀሪ ወራት የጋራ እርብርብ በሚደረግባቸው በተለዩ የሀይጅ እና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ስራዎች ላይ በቂ ውይይትና መግባባት የሚደረግበት መድረክ ይሆናል ሲሉም ገልጸዎል።

‎የቢሮው የዋን ዋሽ አስተባባሪ አቶ ዘውዱ ዘገዬ በበኩላቸው በክልሉ በ 90 ወረዳዎች በ18 አነስተኛ ከተሞች የሚሰራ እንደሆነና 184 (በአንድ መቶ ሰማኒያ አራት) የጤና ተቋማት ለባለሙያ ለታማሚና አስታማሚ ሚቹና ጽዱ የማድረግ ስራ እየተሰራ ያለ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎የተለያዩ ሪፓርቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

‎ከጤና ቢሮ የሚመለከታቸው ባለሙያዎችና ከየዞኑ የመጡ የዋን ዋሽ ባለሙያዎች ፣ አካውንታቶችና ፎካሎች ተሳታፊ ናቸው።

‎ #አብክመጤናቢሮ


‎ግንቦት 14/2018 ዓ.ም

በተጠሪ ተቋማት የተከናወኑ የጤና መሰረተ ልማት የአዲስ ፣የእድሳትና መልሶ ግንባታ ስራዎች #አብክመጤናቢሮ     ግንቦት 14/2018 ዓ.ም
22/05/2026

በተጠሪ ተቋማት የተከናወኑ የጤና መሰረተ ልማት የአዲስ ፣የእድሳትና መልሶ ግንባታ ስራዎች
#አብክመጤናቢሮ


ግንቦት 14/2018 ዓ.ም

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Health Bureau - አብክመ ጤና ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Health Bureau - አብክመ ጤና ቢሮ:

Share