የሕግ ጉዳይ

የሕግ ጉዳይ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሕግ ጉዳይ, Bahir Dar.

11/04/2026
11/04/2026
11/04/2026
11/04/2026

እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ሚያዚያ 03/2018 ዓ.ም (አብክመ ሥ.ፀ.ሙ.ኮ) የትንሳኤ በዓል የሰው ልጅ ከፍቃድ ወጥቶ ካጠፈው ጥፋት ይመለስ ዘንድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እውነት እና ስለ ሰው ፍቅር ሲል በእለተ ዓርብ እራሱን አሳልፎ ለሞት የሰጠበት እና በሶስተኛውም ቀን መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል በእለተ እሁድ ሞትን ድል አድርጐ በመነሳት የሰውን ልጅ የታደገበት ታላቅ መንፈሳዊ በዓል ነው። ኮሚሽናችን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ይላል፡፡

ፈጣሪ ለሰው ልጅ ክብር እና ፍቅር ሲል የከፈለው ከፍተኛ ዋጋ ታላቅ አስተምህሮ እንዳለው ሁሉ እኛም በዓሉን ስናከብር ሀገርንና ህዝብን ለከፍተኛ ችግር ከሚዳርጉ የሌብነትና ብልሹ አሰራር ወንጀሉች እራሳችንን በማጽዳት ፣ ሃይማኖታዊ አስተምህሮውን በማሰብ፣ ይህን አስከፊ የሥነ ምግባር ጥሰትና ሌብነት ተገቢ አለመሆኑን በመረዳት መላው የክልላችን ህዝብ በሚችለው መንገድ ሁሉ ትግል እንዲያደርግ ኮሚሽናችን መልዕክቱን ያስተላልፋል።

መልካም የትንሳኤ በዓል!!!

"ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በህብረት እንታገል !"

//ተጨማሪ የኮሚሽኑን መረጃ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ//
👉ፌስቡክ_https://www.facebook.com/anrseac
👉ቴሌግራም_ https://t.me/Anrs_Ethics_Anti_Corruption_comm
👉ዋትስ አፕ_ https://chat.whatsapp.com/Bo9Co45id7XKF8E5WsuI5h
👉ዩትዩብ_ https://www.youtube.com/
👉ቲክቶክ_https://vm.tiktok.com/ZMrQ9aESA/

11/04/2026

"ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ" ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው

ባህርዳር ፣ ሚያዚያ 03/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው፣ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በየደረጃው ባሉ የክልላችን ፍርድ ቤቶች የምትሰሩ የክርስትና እምነት ተከታይ ዳኞች፣ ተሿሚዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ ባለጉዳዮች እና ባለድርሻ አካላት፣ እንኳን ለ 2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ያሉት ክቡር ፕሬዝዳንቱ፣ ለመላው ኢትዮጵያዊያን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።

የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ሀይማኖታዊ ትርጓሜ የሚሰጠው ታላቅ መንፈሳዊ በዓል ነው ያሉት ክቡር ፕሬዘዳንቱ፣ በዓሉን ስናከብር እርዳታችን ለሚያስፈልጋቸው የሰው ልጆች በሙሉ አቅማችን የፈቀደውን በማድረግ፣ በአብሮነት፣ በመቻቻል፣ በወንድማማችነት እና በአንድነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በዓሉ ክርስቶስ ትህትናን ለሰው ልጆች ያስተማረበት፤ ጥፋትን፣ ክፋትን፣ ጠላትነትን፣ ድል የነሳበት እና ከሰው ልጆች ጋር እርቅ የፈጸመበት ቀን ነው ያሉት ክቡር ፕሬዝዳንቱ፣ እኛም በዓሉን ስናከብር በይቅርታ፣ አንዳችን ላንዳችን ያለንን አጋርነት በማሳየት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ክቡር ፕሬዝዳንቱ በመልእክታቸው፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤታችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ወጭ ቆጣቢ እና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት ፍትሕን ለማረጋገጥ በትጋት እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የዳኝነት አገልግሎት እንዲሁም በባህል ፍርድ ቤቶች እና በሌሎች አማራጭ የዳኝነት አገልግሎት መስጫ ዘዴዎች በመታገዝ የሚሰጠውን ተደራሽና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ከበዓሉ ማግስትም የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለውን ቁርጠኝነት አንስተዋል።

በመጨረሻም፣ በዓሉ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የሰላም፣ የአንድነት፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ፣ የጤና እና የደስታ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

መልካም የትንሳኤ በዓል!

11/04/2026
11/04/2026
09/04/2026

ኢትዮጵያዊቷ የሕግ ባለሙያ ሜሮን አራጋው በአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ ተባለች

| ​ናይጄሪያ መቀመጫውን ያደረገውና በመላው አፍሪካ ያሉ ከፍተኛ የህግ ባለሙያዎች ስብስብ የሆነው "ኮርትሩም ሜይል 100" (Courtroom Mail 100) ለ2026 የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ 100 አፍሪካውያን ሴት የህግ ባለሙያዎችን ይፋ ሲያደርግ፣ ከኢትዮጵያ ሜሮን አራጋው በብቸኝነት ተመርጣለች።

​ሜሮን አራጋው ለምን ተመረጠች?

​የላቀ ሙያዊ ብቃት፦
በስርዓተ-ፆታ፣ በወጣቶችና በማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአለምአቀፍ ድርጅት ከፍተኛ አማካሪ ሆና በመስራት ላይ ትገኛለች።

​ታሪካዊ አመራር፦
የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር (EWLA) ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር በመሆን የብዙዎችን መብት በማስከበር ረገድ ትልቅ አሻራ አሳርፋለች።

​የመንግስት አገልግሎት፦
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ምክትል ኃላፊ በመሆን የፖሊሲ ለውጦች እንዲመጡ ሰርታለች።

​አርአያነት፦
ከዚህ ቀደም ይህንን እውቅና ካገኘችው ከታዋቂዋ የህግ ባለሙያ ብርቱካን ሚደቅሳ በመቀጠል፣ ኢትዮጵያን በአፍሪካ መድረክ ያስጠራች ብርቱ ሴት ሆናለች።

​ለሀገራችን የፍትህ ስርዓት መጠናከርና ለሴቶች መብት መከበር የምትተጋው ሜሮን አራጋው እንኳን ደስ አለሽ!

​ #ሜሮንአራጋው #የህግባለሙያ #ኢትዮጵያ #እውቅና #ጌጡተመስገን

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሕግ ጉዳይ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የሕግ ጉዳይ:

Share