Amhara Innovation and Technology Bureau

Amhara Innovation and Technology Bureau “መረጃና ቴክኖሎጂ የዘመናችን ውድ ሐብት!”

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ፡፡===========================================ባህርዳር ግንቦት 19/2018 ዓ.ም...
29/05/2026

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ፡፡
===========================================
ባህርዳር ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (ኢቴቢ)፤ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የቢሮው ምክትል ሃላፊ፣የማኔጅመንት አባላት እና አፈፃፀሙን ለመገምገም ከክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር የመጡ አመራሮች በተገኙበት የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡
በግምገማው የቢሮው የቴክኖሎጂ ስራወች ማለትም እንደ ስማርት ሲቲ ግንባታ፣ ስታርታፕ ስራወች፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና የተለሙ ሲስተሞች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና እና የፋይዳ ሀገር አቀፍ ዲጂታል መታወቂያ አሰጣጥ እንዲሁም ሌሎች ስራወች ቀርበው ተገምግመዋል፡፡

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው እንደተናገሩት በ25 አመታት የአማራ ክልል ስራቴጂክ እቅድ ላይ ለቴክኖሎጂ ስራወች ልዩ ትኩረት መሰጠቱ የክልሉ መንግስት በሁሉም ልማቶች ላይ የሚያካሂደውን ስራ የተሳለጠና ውጤታማ እንዲሆን ቁርጠኝነቱን የሚሳይ ነው ብለዋል፡፡
የሌሎች ተቋማት በተዋቀሩበት ልክ ተቋሙ ወደ ታች ያልተዋቀረና ባልተሟላ የሰው ሀይል በመስራት አስደሳች ውጤት እየተገኘ ያለ መሆኑን አቶ የቻለ በማስረዳት በዚህ ተግባር ከዚህ በፊት ትኩረት ያልነበራቸው የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ትኩረት እያገኙ እና ክልሉ ወደ ዲጅታላይዜሽን አሰራር ሙሉ በሙሉ የሚገባበት ሁኔታ እየተፋጠነ ነው ብለዋል፡፡

ከክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር የመጡ አመራሮች አቶ ነጋ ይስማው እና አቶ አባይነው በበኩላቸው የቢሮው እቅድ አፈፃፀም በጥሩ ደረጃ የሚገኝ መሆኑን በማስረዳት ቀሪ ስራወችን ለመፈፀም በጥንካሬ መስራት ይገባል በማለት ግምገማው ተጠናቋል፡፡

የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ያዘጋጀውን የስታርታፕ ውድድርና ሽልማት ረቂቅ መመሪያ የግምገማ ወርክሾፕ አካሄደ፡:=================ባህርዳር ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (ኢቴ...
28/05/2026

የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ያዘጋጀውን የስታርታፕ ውድድርና ሽልማት ረቂቅ መመሪያ የግምገማ ወርክሾፕ አካሄደ፡:
=================
ባህርዳር ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (ኢቴቢ)፤ የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የቢሮው ሃላፊወችና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ያዘጋጀውን የስታርታፕ ውድድርና ሽልማት ረቂቅ መመሪያ የሚገመግም ወርክሾፕ አካሂዷል፡፡
በወርክሾፑ መክፈቻ ላይ የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው ቢሮው በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች መካከል የስታርታፕ ልማት ምህዳሩን መገንባት አንዱ መሆኑን እና ባለፉት አመታት ስታርታፖችን ለመደገፍ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከቴክኒክ ተቋማት፣ ከልማት አጋሮች እና ከግሉ ዘርፍ ተዋናዮች ጋር በመተባበር ሰፊ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ተግባራዊ አድርጓል ብለዋል። ከእነዚህም ውስጥ የስታርታፖች የኢኖቬሽን እና ዲዛይን፣ ፋይናንሽያል ማኔጅመንት፣ ማርኬቲንግ ስትራቴጂ እና የኮሙኒኬሽን ስልጠናዎች፣ የተማሪዎች ፈጠራ ቡት ካምፖች፣ የሳይበር እና ዲጂታል፣ የሮቦቲክስ እና የፈጠራ ስልጠናወች፣ የተግባር ፈጠራ ወርክ ሾፖች እና ኤግዚቢሽኖች ይገኙበታል ብለዋል። ረቂቅ መመሪያው ለስታርታፖች የሚሰጠው ማበረታቻ በህግ የተደገፈና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲከናወን የሚያስችል አሰራርን ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑን አቶ የቻለ ገልጸዋል፡፡
የፍትህ ቢሮ የህግ ምክር ማርቀቅና ማጠቃላል ዳይሬክቶሬት የክልል አቃቢ ህግ የሆኑት አቶ መስፍን መኮንን የረቂቅ ህጉን ሰነድ በመድረኩ ለተገኙት አካላት አቅርበው ሃሳብ እንዲሰጥ ያደረጉ ሲሆን በመጨረሻም ከረቂቅ መመሪያው መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ተስተካክለው መቅረብ እንዳለባቸው የፍትህ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ወንዳቸው ስራው አሳስበው ወርክሾፑ ተጠናቋል፡፡

የአማራ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እያለማ ያለውን የተቀናጀ የኦዲት አስተዳደር ሲስተም ገመገመ፤ባህርዳር ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (ኢቴቢ) የአማራ ክ...
22/05/2026

የአማራ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እያለማ ያለውን የተቀናጀ የኦዲት አስተዳደር ሲስተም ገመገመ፤ባህርዳር ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (ኢቴቢ) የአማራ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እያለማ ያለውን የተቀናጀ የኦዲት አስተዳደር ሲስተም የሁለቱ የመሥሪያ ቤቱ የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡የሲስተም ልማቱ የዲዛይንና የዶክመንት አስተዳደር የመጀመሪያ ስራው ቀርቦ በመድረክ በተገኙት አካላት የግምገማ ሃሳብ ተሰጦበታል፡፡ዲጅታል ኢትዮዽያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ የአማራ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በክልሉ ለሚገኙ የመንግስት ተቋማት በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት የተለያዩ ሲስተሞችን እያለማ ይገኛል፡፡

የ25 አመታት የአማራ ክልል የቴክኖሎጂ ዘርፍ ስትራቴጅክ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡=============ባህርዳር ግንቦት 7/2018 ዓ.ም (ኢቴቢ)፤ የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ...
15/05/2026

የ25 አመታት የአማራ ክልል የቴክኖሎጂ ዘርፍ ስትራቴጅክ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
=============
ባህርዳር ግንቦት 7/2018 ዓ.ም (ኢቴቢ)፤ የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የ25 አመታት የክልሉ የልማት እቅድ ውስጥ የተቀመጠውን የቴክኖሎጂ ዘርፍ ስትራቴጅክ እቅድ አስመልክቶ የቢሮው አመራሮችና የሚመለከታቸው ባለሙያወች በተገኙበት ውይይት አካሂዷል፡፡

የአማራ ክልልን የ25 ዓመት የቴክኖሎጂ ዘርፍ እቅድ ያቀረቡት ዶክተር ሰይድ በውይይቱ ለተገኙት እንደተናገሩት የኢኮኖሚ መሰረት የሆነውንና ካለንበት የኢኮኖሚ ችግር የሚያወጣን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ስራወች በእቅዱ ልዩ ትኩረት ተሰጧል፡፡

በ25 አመታት የልማት እቅድ ላይ የተቀመጠውን የቴክኖሎጂ ስራቴጅክ እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም በክልሉ የሚገኙ አካላት መረባረብ አለባቸው ሲሉ ዶክተር ሰይድ አሳስበዋል፡፡

ተወያዮቹ እቅዱን በሚመለከት የተለያዩ ሃሳቦችን አንስተው ውይይት ያደረጉ ሲሆን እቀዱን ለመፈጸምም ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

• በዋትሥአፕ = https://chat.whatsapp.com/CaMX3Rww8EZ2jc58gCIewk
• በፌስ ቡክ = https://web.facebook.com/profile.php?id=100067560995785
• በቲክቶክ = https://www.tiktok.com/tiktokstudio
• በቲውተር /X/ = https://x.com/AndAmhara13784?t=J9MYa70fJLC6B9WfzyqX9A&s=09
• በዩቱዩብ = https://youtube.com/...
• በኢንስታግራም = https://www.instagram.com/ait52543?igsh=MXV4Zzl6cXF6OGtjOQ==
ይከታተሉን፡፡

14/05/2026

AI የአማራ_ክልል_ኢኖቬሽንና_ቴክኖሎጂ_ቢሮ_የቴክኖሎጂ_ፈጠራ_ሃሳብ_ላላቸው_ተማሪወች_የፈጠራ_ውድድር_

ኢትዮ ኮደርስ ለፈጠራ ...ደብረ ብርሀን : ግንቦት 4/2018ዓ.ም.(አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ወጣቶችን ለተለያዩ ፈጠራዎች እያነሳሳ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር  ገለጸ...
12/05/2026

ኢትዮ ኮደርስ ለፈጠራ ...

ደብረ ብርሀን : ግንቦት 4/2018ዓ.ም.(አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ወጣቶችን ለተለያዩ ፈጠራዎች እያነሳሳ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ፡፡

በዞኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ሥልጠናውን እየወሰዱ መሆኑ ተገልጿል።

ከሥልጠናው በኋላ የራሳቸውን ሲስተም የፈጠሩ ሰልጣኞች መኖራቸውን የዞኑ አስተዳደር መምሪያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ደመላሽ በላይ ገልጸዋል፡፡

በዚህ በጀት ዓመት ሥልጠናውን እንዲወስዱ ከ37 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ የተሠራላቸው መሆኑን ቡድን መሪው ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሥልጠናውን ያጠናቀቁ ሲሆን ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በሥልጠና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠናን ከወሰዱት ውስጥ 90 የሚሆኑት በተለያዩ ተቋማት አሠራርን የሚያቀሉ የራሳቸውን የዲጂታል ሥርዓት መፍጠራቸውንም አቶ ደመላሽ በላይ ገልጸዋል፡፡

ይህም አሁን ካለው የቴክኖሎጂ ፍላጎት አንጻር የተቋማትን አገልግሎትና የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማሳደግ እንደ አንድ ትልቅ አቅም እንደሚወሰድ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮ ኮደርስ ተነሳሽነት በኢትዮጵያ ያለውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ለማሳደግና ዜጎችን ለወደፊቱ የሥራ ገበያ ለማዘጋጀት ያለመ መርሃ ግብር ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ቀዳሚ ግብ በሶፍትዌር ልማት፣ በዳታ ሳይንስ እና በሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እውቀት እንዲጨብጡ ማድረግ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ሰልጣኞች የቴክኖሎጂ እውቀቱን ካገኙ በኋላ በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ውስጥ ተቀጥረው እንዲሠሩ ወይም የራሳቸውን የፈጠራ ሥራዎች እንዲጀምሩ ማስቻልም ሌላው የፕሮጀክቱ ዓላማ ነው፡፡

አሚኮ

የማኅበረሰቡን ችግሮች የሚፈቱ ፈጠራዎችን ይዘው ብቅ ያሉት የባሕር ዳር ከተማ ተማሪዎች ባሕር ዳር: ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ታዳጊዎች የንድፈ-ሀሳብ ...
11/05/2026

የማኅበረሰቡን ችግሮች የሚፈቱ ፈጠራዎችን ይዘው ብቅ ያሉት የባሕር ዳር ከተማ ተማሪዎች

ባሕር ዳር: ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ታዳጊዎች የንድፈ-ሀሳብ ትምህርታቸውን ወደ ተግባር በመቀየር፣ የማኅበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የፈጠራ ሥራዎችን ይዘው ቀርበዋል።

የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ በባሕር ዳር ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል ባካሄደው የሳይንስ እና ፈጠራ ውድድር ላይ የተማሪዎቹ ውጤቶች የነገውን ተስፋ የሚያመላክቱ ኾነዋል።

በባሕር ዳር ብፁዕ ገብረ ሚካኤል ካቶሊክ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪ ቅዱስ አላምረው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የግብርና መፍትሔ በማቅረብ በፈጠራው ዘርፍ አዲስ ተስፋ ኾኖ ብቅ ብሏል።

👉ፈጠራው እና ፋይዳው፦

"ዲጂታል ኢትዮጵያን" እውን ለማድረግ ግብርናው በቴክኖሎጂ መደገፍ አለበት ብሎ የሚያምነው ተማሪ ቅዱስ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) የሚሠራ ሲስተም አበልጽጓል። ይህ ቴክኖሎጂ ለአርሶ አደሮች ከሚሰጡት ወሳኝ ጥቅሞች መካከል፦

👉ተስማሚ ዝርያን መምረጥ፦

እንደ አፈሩ ዓይነት እና እንደ አየር ንብረቱ ሁኔታ ተስማሚ የኾኑ የሰብል ዝርያዎችን ይለያል።

👉የምርት ትንበያ፦

አርሶ አደሩ በሄክታር ምን ያህል ኩንታል ምርት ማግኘት እንደሚችል አስቀድሞ ይተነብያል።

👉የበሽታ መቆጣጠር፦

በሰብል ላይ የሚከሰቱ በሽታዎችን ከመከታተል ባለፈ በሽታው ሲከሰት አፋጣኝ ምላሽ እና መፍትሔ ለመስጠት ያስችላል።

👉ውጤት፦

ይህ ለአርሶ አደሮች የዕለት ተዕለት ችግር መፍትሔ የሚሰጥ የፈጠራ ሥራው በውድድር መድረኩ የአንደኛ ደረጃ ሽልማትን አስገኝቶለታል። ተማሪ ቅዱስ አላምረው በቴክኖሎጂ የታገዘ ግብርና ለሀገር ዕድገት ያለውን ወሳኝ ሚና በተግባር እያሳየ ይገኛል።

የጣና ሐይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ አብርሃም ዮሴፍ እና ጓደኞቹ ደግሞ የቤትን ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቅ ሲስተም ይዘው ቀርበዋል። ይህ "AEGIs Core Habitat" የተባለ የፈጠራ ሥራ፦

የጭስ እና የእሳት አደጋን ይከላከላል፤ የሙቀት መጠንን ይቆጣጠራል፤ እንዲሁም የስርቆት እና መሰል ወንጀሎችን ቀድሞ ለመለየት ያስችላል።

በአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ቢሮ የአቅም ግንባታ ዳይሬክተር ይመኑ ያዛቸው የፈጠራ ውድድሩ ተማሪዎች በሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ያላቸውን የፈጠራ ውጤት እንዲያሳድጉ ያለመ መኾኑን ጠቁመዋል።

በውድድሩ 19 የሚኾኑ የፈጠራ ውጤቶች የቀረቡ ሲኾን የላቀ ውጤት ላመጡ እና ከአንድ እስከ ሦሥተኛ ለወጡ ተማሪዎች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

አሚኮ

የ11ኛ ክፍል ተማሪው  የስማርት ሲስተም ፈጠራባሕር ዳር: ግንቦት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በትራፊክ መጨናነቅ ሰዓታትን ማሳለፍ፣ በመንገድ አደጋ ስጋት መኖር እና በወረቀት የታጀበው የትራ...
11/05/2026

የ11ኛ ክፍል ተማሪው የስማርት ሲስተም ፈጠራ

ባሕር ዳር: ግንቦት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በትራፊክ መጨናነቅ ሰዓታትን ማሳለፍ፣ በመንገድ አደጋ ስጋት መኖር እና በወረቀት የታጀበው የትራፊክ አሥተዳደር በኢትዮጵያ ከተሞች የሁልጊዜ ፈተናዎች ናቸው።

በባሕር ዳር ከተማ የብጹዕ ገብረ ሚካኤል ካቶሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የኾነው አብርሃም አበበ ለዚህ ችግር ዘመናዊ እና የተቀናጀ መፍትሔ ይዞ መጥቷል።

"ስማርት ትራፊክ ማኔጅመንት" የተሰኘው ይህ ዲጂታል ፕላትፎርም፣ ከመደበኛ አፕሊኬሽን ባለፈ የትራፊክ አዛዦችን፣ ኦፊሰሮችን፣ ታክሲዎችን እና አሽከርካሪዎችን በአንድ መስመር ውስጥ የሚያገናኝ ዘመናዊ ሲስተም ነው።

👉 የአብርሃም ፈጠራ ምን ለውጥ ያመጣ ይኾን?

ከተዝረከረከ የወረቀት አሠራር ወደ ዲጂታል፦

የትራፊክ ቅጣት፣ የአደጋ ሪፖርት እና የታክሲ ፌርማታ አሥተዳደር ሙሉ በሙሉ በዲጂታል በመኾኑ የወረቀት ሥራን ያስቀራል፤ ግልጽነትን በመፍጠር ሙስናን ይከላከላል።

👉 ብልህ የትራፊክ ፍሰት

ስማርት ካሜራዎችን በመጠቀም የመንገድ መጨናነቅን ይለያል፤ ፍሰቱን ያስተካክላል፤ አደጋዎች ሲከሰቱ አፋጣኝ ጥቆማ ይሰጣል። ካሜራ በሌለባቸው ቦታዎችም በኦፊሰሮች እና በተጠቃሚዎች መረጃ ሥራውን በብቃት ያከናውናል።

ታክሲዎች እና የግል ተሽከርካሪዎች መጨናነቅ የሌለበትን እና ፈጣኑን መንገድ እንዲመርጡ (Route Planner) በማገዝ ነዳጅ እና ጊዜን ይቆጥባል።

ይህ ፕሮጀክት የአንድ ታዳጊ የፈጠራ ውጤት ብቻ ሳይኾን፣ "ዲጂታል ኢትዮጵያን" (Digital Ethiopia) እውን ለማድረግ እና የመንገድ ደኅንነትን ለማረጋገጥ የሚረዳ ትልቅ መፍትሔ ነው። በፈጠራ ሥራው በአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ቢሮ ተሸላሚ የኾነው አብርሃም በትምህርት ገበታ ላይ ኾኖ የማኅበረሰቡን ትልቅ ሕመም የሚፈውስ ቴክኖሎጂ በማቅረቡ ለተከታዮቹ አርዓያ ኾኗል።

በአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ቢሮ የሥልጠና ሙያተኛው ሃብታሙ ላቀ ለተማሪዎች በመካኒካል እና ሶፍት ዌር ዘርፎች በቴክኖሎጅ ፈጠራ ሥልጠና ሲሰጥ መቆየቱን አንስተዋል።

የሥልጠናው ዓላማ ተማሪዎች ከታችኛው የክፍል ደረጃ ጀምሮ የፈጠራ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ እና ለወደፊቱም በሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዘርፉ የፈጠራ ባለቤት እንዲኾኑ ለማስቻል ነው ብለዋል።

አሚኮ

የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ተማሪዎች ባዘጋጀው የፈጠራ ውድድር አሸናፊወችን በመለየት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ፡፡======================...
11/05/2026

የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ተማሪዎች ባዘጋጀው የፈጠራ ውድድር አሸናፊወችን በመለየት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ፡፡
=========================================
ባህር ዳር ግንቦት 2/2018 ዓ.ም (ኢቴቢ)፤ የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ተማሪዎች ከሚያዚያ 30 እስከ ግንቦት 02/2018 ዓ.ም ለ3 ቀናት ባዘጋጀው የፈጠራ ውድድር በተሰየሙ ዳኞች ውድድሩ የተገመገመ ሲሆን ከ1 እስከ 3 የወጡት ትምህርት ቤቶችና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤት የሆኑት ተማሪወች ተለይተው ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ 7 ትምህርት ቤቶች የሳይንስና ፈጠራ ክበባት ተመልምለው የመጡ 19 የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውና ለውድድር እጩ የሆኑ ተማሪወች በተጨማሪም እነኝህን ተወዳዳሪወች ይዘው ለመጡ የሳይንስና ፈጠራ ክበባት ተጠሪ መምህራን ባለፉት 2 ቀናት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ግንቦት 2/2018 ዓ.ም ተማሪወች ፕሮጀክቶቻቸውን አቅርበው በመወዳደር ከ1 እስከ 3 የወጡት በዳኞች ተለይተዋል፡፡

ተወዳዳሪወች በውድድሩ ያቀረቧቸው እና የተወዳደሩባቸው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ፕሮጀክቶቻቸው ለማሳያ የተዘጋጁ እና ወደፊት በተግባር የሚሰሩ ሲሆኑ የክልሉን ህብረተሰብ ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ እንደ ሰብል ማጨጃና መሰብሰቢያ ማሽን፣ እሳትና ከፍተኛ ጭስ በቤት ውስጥ ሲከሰቱ እንዲሁም ሌባ በርና መስኮቶችን ሰብሮ እንዳይገባ ምልክት የሚሰጡና አስፈላጊ ሲሆን ለአካባቢው ህበረተሰብ በድምፅ ጥሪ የሚያሰሙ፣ ተሸከርካሪወች በጉዞ ላይ ከሌላ መኪና ጋር ሊጋጩ ሲሉ ቀድሞ በማወቅ ድምጽ አሰምተው ሹፌሩን የሚያነቁና የመኪናወችን አቅጣጫ በራሳቸው ከግጭቱ በተቃራኒ እንዲዞሩ የሚያደርጉ ቴክኖሎጂወች፣ የቡና መፈልፈያ ማሽን፣ በቤት ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ሰወችን እንደሰው የሚታዘዙና የሚረዱ እንዲሁም ሌሎች በርካታ አስደናቂ ፈጠራወች ናቸው፡፡

በቢሮው የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይመኑ ያዛቸው በሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርአቱ እንደተናገሩት ተማሪወችና ትምህርት ቤቶች ለውድድር የተገመገሙበት መስፈርት የፈጠራ ቴክኖሎጂወቻቸው ለክልሉ ማህበረሰብ ኑሮ መሻሻል ከማምጣት አንፃር፣ በሃገራችን ዲጅታል ትራንስፎርሜሽንን ለማሳካት ከሚደረገው ርብርብ እንዲሁም ከጊዜና ከወጭ አንፃር ታይቶ የተወዳደሩ መሆኑን በዝግጅቱ ለነበሩ ታዳሚወች አስረድተዋል፡፡
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተማሪወች የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ጌታነህ አያሌው ሽልማታቸውን የሰጡ ሲሆን 1ኛ የወጣው ቅዱስ አላምራው የተባለ የጣና ሃይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪና በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ የግብርና ስራን ሊያግዝ የሚችል ፈጠራ በመፍጠር የ 18 ሺህ ብር ሽልማት፣ 2ኛ የወጣው አብርሃም ዮሴፍ የተባለ የካቶሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ በቤት ውስጥ አደጋ ሊከሰት ሲል ምልክት በመስጠት ችግሩን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል የቴክኖሎጂ ፈጠራ በመፍጠር 13 ሺህ ብር ሽልማት፣እንዲሁም 3ኛ ደረጃ የወጣው አብርሃም አበበ የተባለ የአቡነ ጎርጎሪዮስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪና በከተሞች የትራፊክ ሁኔታን መቆጣጠርና መከታተል የሚያስችል ቴክኖሎጂ በመፍጠር 8 ሺህ ብር ተሸላሚ ሁነዋል፡፡

የቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ ሰላማዊት ደሴ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ትምህርት ቤቶች ተወካዮቻቸው ሽልማቱን የሰጡ ሲሆን 1ኛ ለወጣው ጣና ሃይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 30 ሺህ፣ 2ኛ የወጣው ካቶሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 20 ሺህ ብር እንዲሁም 3ኛ የወጣው አቡነ ጎርጎሪዮስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 15 ሺ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የአማራ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በክልሉ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ግለሰቦች መደገፍና ማበረታታት ዋና ሃላፊነትና ተግባሩ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የትምህርት ቤቶች የቴክኖሎጂ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ተማሪወች ለማበረታታትና ለመደገፍ በየአመቱ ሽልማት የሚያሰጥ ውድድር በማካሄድ ለአሸናፊወች የገንዘብ ሽልማት ያበረክታል፡፡

• በዋትሥአፕ = https://chat.whatsapp.com/CaMX3Rww8EZ2jc58gCIewk
• በፌስ ቡክ = https://web.facebook.com/profile.php?id=100067560995785
• በቲክቶክ = https://www.tiktok.com/tiktokstudio
• በቲውተር /X/ = https://x.com/AndAmhara13784?t=J9MYa70fJLC6B9WfzyqX9A&s=09
• በዩቱዩብ = https://youtube.com/...
• በኢንስታግራም = https://www.instagram.com/ait52543?igsh=MXV4Zzl6cXF6OGtjOQ==
ይከታተሉን፡፡

የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ተማሪወች የፈጠራ ውድድር እና ስልጠና እያካሄደ ነው፡፡=====================================ባህር ...
08/05/2026

የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ተማሪወች የፈጠራ ውድድር እና ስልጠና እያካሄደ ነው፡፡
=====================================
ባህር ዳር ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም (ኢቴቢ)፤ የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከሚያዚያ 30 እስከ ግንቦት 02/2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ 7 ትምህርት ቤቶች የሳይንስና ፈጠራ ክበባት ተመልምለው ለመጡ 19 ተማሪወች እና ለ7 ትምህርት ቤቶች የሳይንስና የፈጠራ ክበባት ተጠሪ መምህራን የተዘጋጀ የፈጠራ ውድድር እና ስልጠና እያካሄደ ነው፡፡

በመክፈቻ ንግግሩ እንደተገለፀው በመጀመሪያወቹ 2 ቀናት በፈጠራና በቴክኖሎጂ ዙሪያ የተወዳዳሪወችን አቅም መገንባት የሚያስችል ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን ስልጠናውም በፈጠራ ሃሳብ፣ቢዝነስና የፕሮጀክት ሃሳብ እንዴት ይመነጫል? በሚል እንዲሁም በፈጠራና ዲዛይን ላይ የሚያተኩር ነው፡፡

የአማራ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በክልሉ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ግለሰቦች መደገፍና ማበረታታት ዋና ሃላፊነትና ተግባሩ ሲሆን የትምህርት ቤቶች የቴክኖሎጂ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ተማሪወችን ለማበረታታትና ለመደገፍ በየአመቱ ሽልማት የሚያሰጥ ውድድር በማካሄድ ለአሸናፊወች የገንዘብ ሽልማት ያበረክታል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ሃላፊ የሆኑት አቶ የቻለ ይግዛው የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ፕሮግራሙን ያስጀመሩ ሲሆን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ብቁ ዜጎችን ማውጣት የቢሮው ዋነኛ ሃላፊነት ነው በማለት ይህ መርሃ ግብር ለትምህርት ቤቶች ድጋፍና ክትትል የምናደርግበት ነው ብለዋል፡፡ የፈጠራ ውድድር ፕሮግራሙ እውቅና የሚሰጠው ሃሳብና ፈጠራን ነው፡፡ ስለዚህ ተማሪወች ለፈጠራ ልዩ ትኩረት በማድረግ መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን አቶ የቻለ አሳስበዋል፡፡

ክልሉን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ዋናው ችግር በፈጠራ ሰዎች፣ እነሱን በሚደግፉ አካላትና ፈጠራውን ወደ ተጠቃሚወች በተጨባጭ ለማድረስ በብዛት ወደ ምርት በሚያስገቡ ባለሃብቶች መካከል ትስስር አለመኖር መሆኑን በመጠቆም ሁሉም አካላት በዚህ ዙሪያ በትብብርና በቅንጅት መስራት አለባቸው ሲሉ ምክትል ቢሮ ሃላፊው አስገንዝበዋል፡፡
የቢሮው የአቅም ግንባታ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይመኑ ያዛቸው በበኩላቸው በመክፈቻ መድረኩ ባደረጉት ንግግር የተማሪወች የፈጠራ ውድድር ከዚህ በፊት ተሞክሮ ለውጥ ያመጣ ነው፤ የዚህ ፈጠራ ውድድር ምሰሶወችም የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ተማሪወች መሆናቸውን እና ተወዳዳሪወች የፕሮጀክት መነሻቸውን አስፍተው ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

Address

Unison
Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Innovation and Technology Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share