Amhara National Regional Council Secretriat

Amhara National Regional Council Secretriat anrs council

06/09/2021

Our active face book page address is 'Amhara National Regional Council' Please, our viewer and follower follow the mentioned page. we are not using and posting currently 'Amhara National Regional Council Secretriat' page, please unfriend it and be friends with the 'Amhara National Regional Council'
ውድ የፌስቡክ ተከታይና ወዳጃችን ይህ ገጽ ችግር ስላለበት ትተነዋል፤ ነገር ግን መረጃው ሼር ሲደረግ ወደዚህ እየገባብን ነው፡ አሁን እየጠቀምን ያለነው 'Amhara National Regional Council' የሚለውን ገጽ ነው፡፡ እባካችሁ ጋጓደኝነታችሁን ከዚህ ገጽ ጋር አድርጋችሁ በዚህ ገጽ ተከታተሉን፡፡

16/06/2021

ውድ የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ወዳጆችና ተከታዮች ይህ ገጽ በአሁኑ ሰዓት እየተጠቀምንበት አይደለም፡፡ ወቅታዊ መረጃዎችን በ Amhara National Regional Council ይፋዊ የፌስቡክ ገጻችን ስለምንለቅ እንዲከታተሉን በትህትና እንገልጽላችኋለን፡፡
ምክር ቤቱ
June, 16/2021

15/02/2021

ውድ የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ወዳጆችና ተከታዮች ይህ ገጽ በአሁኑ ሰዓት እየተጠቀምንበት አይደለም፡፡ ወቅታዊ መረጃዎችን በ Amhara National Regional Council ይፋዊ የፌስቡክ ገጻችን ስለምንለቅ እንዲከታተሉን በትህትና እንገልጽላችኋለን፡፡
ምክር ቤቱ

02/09/2020

በኢትዮጵያ ስምንት ባህላዊ መድሃኒቶች ኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለማከም ፈዋሸነታቸው እየተገመገመ ነው።
በኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስን ለማከምና ለመከላከል የሚረዱ ስምንት ባህላዊ መድሃኒቶች ፈዋሽነታቸውን በሳይንሳዊ ዘዴ ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።
ከአማራ ብዙሀን ድርጅት ዘገባ እንዳገኘነው የአፍሪካ የባህል መድሃኒቶች ቀን በየዓመቱ ነሃሴ 25 ቀን ታስቦ የሚውል በመሆኑ 18ኛው አህጉር አቀፍ የባህል ህክምና ቀን እየተከበረ ነው።
በዓሉን በማስመልከት የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣንና የባህላዊ የህክምና አዋቂዎች ማኅበር ዛሬ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የምርት ደኅንነት ዳይሬክተር ወይዘሮ አስናቀች ዓለሙ እንዳሉት ኮሮናን ለመከላከልና ለማከም ”የባህላዊ መድሃኒቶች ጊዚያዊ ጋይዳንስ” ተዘጋጅቶ የሙከራ ጥያቄዎችን በማስተናገድ ላይ ናቸው።
በሂደቱ ስምንት የባህላዊ መድሃኒቶች ቀርበው በሰው ላይ ሙከራ እንዲደረጉ የሚያስችል የሰነድ ምርመራ እየተደረገባቸው ነውም ተብሏል።
የባህል ህክምና አዋቂዎች እነዚህ መድሃኒቶች በተለያዩ የሙከራ ዘዴዎች በማለፍ ውጤት አገኝተንበታል ብለው እውቅና እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ነሐሴ 26/2012 ዓ.ም

01/09/2020

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወደ ባንክ ማደጉ ተገለጸ
የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን የለውምወሰን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተቋሙ ወደ ባንክ መሸጋገሩን ተከትሎ ከ3 እስከ 6 ወር ባለ ጊዜ ውስጥ ስራ ለመጀመር ሰራተኞችን በቂ ስልጠና የመስጠትና ቢሮዎችን በማደራጀት ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ተቋሙ የባንክ አገልግሎቱን በ8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መነሻ ካፒታል የሚጀምር ሲሆን በ 53 ነባር የተቋሙ ቅርንጫፎች ተደራሽ እንደሚሆን አስረድተዋል ። ከዚህ በፊት ብድር ለወሰዱ ደንበኞች ሁለት አማራጭ መቀመጡን የተናገሩት ሃላፊው የመጀመሪያው በውሉ መሰረት መጨረስ ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ የወሰዱትን ብድር መልሰው በአዲስ መጠየቅ መሆኑንም ገልጸዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የሚስተዋሉ ችግሮችን በማረምና በማስተካከል የክልሉን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ይሰራልም ነው ያሉት።
የክልሉ መንግስት ድርሻ 98 በመቶ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ወደ ባንክ ሲያድግ ከ70 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት መመሪያው ሲለሚገድብ 30 በመቶው ለግል አክሲዮን እንደሚሸጥ መናገራቸውን ከአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ነሐሴ 26 /2012

28/08/2020

ማስክ ሣያደርጉ መንቀሳቀስን ማቆም ይገባል ተባለ

በአለማችን፣ በሃገራችን ብሎም በክልላችን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ ለመከላከል ሲባል ከክልል ጀምሮ እስክ ቀበሌ ድረስ ያሉ ም/ቤቶች ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመናበብና በመተባበር በሽታውን ለመከላከል የገንዘብና የቁሣቁስ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ የሚደረገው ድጋፍ አቅም ለሌላቸው አካላት ለማስክ አቅርቦት የሚውል ገንዘብ በተቋም ደረጃ ከመደገፍ፣ የማስክ፣ የሳሙና፣ የሶፍትና የሳኒታይዘር ግዥዎችን በመፈጸም ለሁሉም ም/ቤቶች እንዲሰራጭ ከማድረግ ጀምሮ የምክር ቤት አባላትና አፈጉባዔዎች የግል ቤታቸውን ከኪራይ ነጻ እስከማድረግ ድረስ የሚገለጽ ነው፡፡ በግንዛቤ ፈጠራም የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ በሌላ በኩል የኮረና ቫይረስ አሣሣቢነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በአንፃሩ በየደረጃው ከተሰራው የግንዛቤ ፈጠራ አንጻር የመጣው ለውጥ ከሚጠበቀው በታች ነው፡፡ ማስክ የማይለብሰው ህዝብ ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ከህዝቡ አልፎ የተሻለ ግንዛቤ አላቸው ተብለው የሚታሰቡት በተለያየ ደረጃ በገጠርም በከተማም የሚገኙ አመራሮችና የመንግስት ሠራተኞች ሣይቀር በስፋት ተጠቂ ሁነዋል፡፡ የመመርመር/ ያለመመርመር ካልሆነ በስተቀር ጉዳዩ ከዛም በላይ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡
በመሆኑም ይህን በመከላከል ግንባር ቀደም አርአያ መሆን ከሁሉም ም/ቤቶች የሚጠበቅ ሲሆን አንድም የክልል፣ የብሄረሰብ፣ የወረዳና የቀበሌ ም/ቤት አመራርና አባል እንዲሁም የተቋሙ ሰራተኞች ማስክ ሣያደርጉ እንዳይንቀሣቀሱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ ያሳሰቡ ሲሆን በተዋረድ ያሉ ምክር ቤቶችም የሚከታተሏቸውን ተቋማት በዚህ ደረጃ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መደገፍ ይገባቸል ብለዋል፡፡
ነሀሴ 22/2012 ዓ.ም.
የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባዔ

26/08/2020

የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብሱን ሊቀይር ነው
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫን አስመልክቶ ለሁለት ቀናት ግምገማ አድርጓል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ እንደሚቀየርና ጉዳዩን አስመልክቶ በመጪው ቅዳሜ ሰፊ ማብራሪያ በኮሚሽኑ እንደሚሰጥ በዚሁ ወቅት ለኢዜአ ገልጸዋል።
ለደንብ ልብሱ መቀየር አሁን ያለው የደንብ ልብስ በቀላሉ የሚገኝ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነ ምግባር ችግር የተባበሩ ፖሊሶች ልብሱን ለብሰው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።
በዚህም የደንብ ልብሱን በመልበስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችና ዝርፊያዎች መበራከታቸውን ነው ያስታወቁት።
በሌላ በኩል በ2013 ዓ.ም አዳዲስ የፖሊስ ዘርፎች በሙከራ ደረጃ ወደ ሥራ ሊገቡ እንደሆነ ኮሚሽነር እንዳሻው አያይዘው ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲ፣ የቱሪዝምና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ፖሊስ በሚሉ ዘርፎች ወደ ሥራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በሙከራው የሚገኙ ልምዶችን በመውሰድ የፖሊስ ዘርፎቹ ወደፊት በዘላቂነት ሊሰራባቸው የሚችልበት ሁኔታ እንደሚኖርም አመልክተዋል ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ነሀሴ 20/2012 ዓ.ም.

26/08/2020

የአማራ ክልል የካቢኒ አባላት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ
የአማራ ክልል የካቢኒ አባላት ለገበታ ለሐገር ፕሮጀክት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት መወሰናቸውን
የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የገበታ ለሐገር ፕሮጀክት በአማራ፣ ደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማት የታቀደ ነው።
ለዚህም 3 ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ መታቀዱ ይታወሳል።
ይህን ለመደገፍም የአማራ ክልል የካቢኒ አባላት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት መወሰናቸውን የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ገልጸዌል።
በአማራ ክልል ጎርጎራ ላይ የታሰበው ፕሮጀክት የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃትና ገጽታን ለመገንባት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋልም ብለዋል።
ለፕሮጀክቱ እውን መሆን መላውን ሕዝብ የሚያሳትፍ የገቢ ማሰባሰብ መርሐ ግብር እንደሚዘጋጅም ተናግረዋል።
የዘገባ ምንጫችን የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ነው፡፡
ነሀሴ 20/2012 ዓ.ም.

25/08/2020
14/08/2020

ኢትዮጵያ በዓለም የጤና ድርጅት የተጀመረውን የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛን የሚያስተዋውቅ ዘመቻ ተቀላቀለች
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ በዓለም የጤና ድርጅት የተጀመረውን የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛን የሚያስተዋውቀውን ዘመቻ መቀላቀሏን አስታወቁ፡፡
ዘመቻውን “ማስክ ኢትዮጵያ” በሚል መቀላቀሏን አስታውቀዋል፡፡
በዚህ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ዘመቻ የሁላችንም ተሳትፎ ጨምሮ፣ እውቀታችን አድጎ፣ ባህሪያችንም ተለውጦ፣ ወረርሽኙን በተሻለ አቅም መከላከል እንችላለን ብዬ አምናለሁ ብለዋል ፕሬዚዳንቷ፡፡
እንዲሁም ሁላችንም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛን በብዛት በማምረት፣ በትክክል በመጠቀም፣ ራሳችንንም፣ ወገኖቻችንንም ከበሽታ እንጠብቅ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አንድም ሰው በበሽታ እንዲያዝ ፣ የማይተካ ሕይወት እንዲያልፍ ፣ የሃገራችን እድገት እንዲስተጓጎል ምክንያት አንሁን፣ የሁላችንም ያልተቋረጠና የተባበረ ጥረት ወረርሽኙን ለማሸነፍ ይሁን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ነሐሴ 8፣ 2012
ምንጭ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

Address

Bahir Dar
1324

Telephone

0582221440

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara National Regional Council Secretriat posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share