Beyeda Woreda ProsperityYouth League የበየዳ ወረዳ ብልፅግና ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • Beyeda Woreda ProsperityYouth League የበየዳ ወረዳ ብልፅግና ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት

Beyeda Woreda ProsperityYouth League  የበየዳ ወረዳ ብልፅግና ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት በጎ አመለካከት መልካም ስብዕናን ያጎናፅፋል

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ የውሳኔ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከበየዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አባላት ጋር ውይይት እያካሔደ ነው ።ጥር 24/2015 ዓ.ም ለኢትዮጵያ እ...
02/02/2023

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ የውሳኔ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከበየዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አባላት ጋር ውይይት እያካሔደ ነው ።

ጥር 24/2015 ዓ.ም

ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ብልጽግና የሚተጋ ወጣት እንፍጠር በሚል መሪ ቃል በበየዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አባላት በ1ኛው የወጣቶች ሊግ መደበኛ ጉባኤ የውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እያካሔደ ነው ።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የበየዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስማማው ሃብቴ እንደገለጹት ወጣቶች የሚያገኙትን እድል ወደ ድል በመቀየር ለሀገር ዘላቂ የሆነ እድገት፣ ሰላምና ብልጽግና እንዲመጣ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለው
የበቃ ወጣት እንዲፈጠር እና ጠንካራ የሆነ የሊግ መዋቅር እንዲኖረን ከተፈለገ በብዛትም በጥራትም እስከ ቀበሌና ድረስ አባላትን የማጠናከር ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የውይይቱን ሰነድ ያቀረበው የበየዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ የሆነው ወጣት ተስፋኢየሱስ ወርቄ ቅድመ ጉባኤና ድህረ ጉባኤው ላይ የወሰናቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በቀጣይነት ሊጉ ከጉባኤ እስከ ጉባኤ ወስኗል በዚህም:-
የጠንካራ መዋቅር ግንባታ፣ ለዘላቂ ሰላም እና ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር ሚናው የጎላ አደረጃጀት መሆን፣ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ላይ የጎላ ሚና መጫዎት የሚችል ተቋም መገንባት፣ የወጣቱን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል ተቋም መፍጠር፣ የኢትዮጵያን ሀገር መንግስት የሚያጎለብቱ፣ ህብረ
ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነትን የሚቀርጹ ተግባራትን መንደፍና እና የወጣቶችን አህጉራዊና አለም አቀፍ ተሳትፎና ሚና ማሳደግ የሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በዝርዝር አብራርተዋል።

ወጣት ተስፋኢየሱስ አያይዘውም በጉባኤ ውሳኔዎቻችን ላይ የተቀመጡ ውሳኔዎች አዳዲስ ፈጠራን በመጨመር መተግበርና ለመዋቅራችን መጠናከር ወሳኝ ነው ብለዋል ፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን 20ኛው የባህል ስፖርትና 16 ኛው የባህል ፌስቲቫል ውድድር ለተከታታይ 5 ቀናት ፍፁም ጨዋነት በተሞላበት መልኩ በሰላም ተጠናቋል። ለዚህ ስኬት ለበየዳ ወረዳ ማህበረሰብ ...
04/01/2023

የሰሜን ጎንደር ዞን 20ኛው የባህል ስፖርትና 16 ኛው የባህል ፌስቲቫል ውድድር ለተከታታይ 5 ቀናት ፍፁም ጨዋነት በተሞላበት መልኩ በሰላም ተጠናቋል። ለዚህ ስኬት ለበየዳ ወረዳ ማህበረሰብ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያለምንም ኮሽታ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ያልተበረዘውንና ያልተከለሰውን የአካቢቢያችን ባህል በማንፀባረቅ ላገዛችው ወጣቶች ፣ የፀጥታ መዋቅር ፣ የወረዳ አመራር ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ በወረዳችን ስር ላላችው በተለይ የገንዘብ ድጋፍ ላደረጋችው ቀበሌ መዋቅር ፣ የድልይብዛ ከተማ መዋቅር ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ተማሪወች ፣ መምህራን ፣ ነጋዴው ማህበረሰብ ፣ተቋማት እና በአጠቃላይ ማህበረሰቡ በወጣቶች እና እንዲሁም በተቋሙ ስም ትልቅ አክብሮትና ክብር አቀርባለው ።
የበየዳ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት
ታህሳስ 25/2015 ዓ/ም
በየዳ ድል-ይብዛ

የሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት በአዲሱ የፓርቲው የመረጃ አያያዝ እና አደረጃጀት ዙሪያ ለፓርቲ መዋቅር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።በሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት...
20/10/2022

የሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት በአዲሱ የፓርቲው የመረጃ አያያዝ እና አደረጃጀት ዙሪያ ለፓርቲ መዋቅር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።
በሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ስር ላሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ኃላፊዎችእና ባለሙያዎች በአዲሱ የፓርቲው የመረጃ አያያዝ እና አደረጃጀት ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በመድረኩ የሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ጌታቸዉ አማረ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸዉም ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ወቅቱ የሚጠይቀው አለም የደረሰችበት ቴክኖሎጂ በመሆኑ ብልጽግና ፓርቲም አዳዲስ አሰራሮችን በማፍለቅ ዘመናዊ የፓርቲ መረጃ አያያዝና አደረጃጀት እንዲኖር በማድረግ ላይ ያለ ፓርቲ ነው በማለት ገልጸዋል።አያይዘዉም የስልጠናዉ አላማው እንደ ብልፅግና ፓርቲ ወጥ በሆነ የአባላት የመረጃ ቋት መመራት በማስፈለጉ አጠቃላይ የብልፅግና ፓርቲ አባሉን በዳታቤዝ ስርዓት መያዝ ስልጠና ተሰጥቶ በአጭር ጊዜ የዞኑን አባላት መረጃ በብቃት እና በአጭር ጊዜ ማደራጀት ያስፈልጋል ብለዋል።
ስልጠናው ለተከታታይ 2 ቀን ከ ከፍ10-11/02/2015 ድረስ የሚሰጥ ይሆናል።

10/02/2015

ለመላው ኢትዮጵያዊ በሙሉ በሃገር ውስጥና በውጪ አለም ለምትኖሩ ሁሉ እንኳን ለ2015 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ  አዲሱ ዓመት ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮች ሁሉ ተወግደው ✋🙏 የአንድነት  💖 የ...
11/09/2022

ለመላው ኢትዮጵያዊ በሙሉ በሃገር ውስጥና በውጪ አለም ለምትኖሩ ሁሉ እንኳን ለ2015 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ አዲሱ ዓመት ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮች ሁሉ ተወግደው
✋🙏 የአንድነት
💖 የፍቅር
🙋 የሰላም
🏆 የብልፅግና ዘመን እንዲሆንልን እንመኛለን የበየዳ ወረዳ ብልፅግና ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት

"ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ብልጽግና የሚተጋ ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በወጣቶች ሊግ አባላት ጋር የሙህራን የቅድመ ጉባኤ ኮንፈረስ በር23/12/2014 ተካሄደ።በስሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ ...
29/08/2022

"ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ብልጽግና የሚተጋ ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በወጣቶች ሊግ አባላት ጋር የሙህራን የቅድመ ጉባኤ ኮንፈረስ በር23/12/2014 ተካሄደ።
በስሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ "ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ብልጽግና የሚተጋ ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በወጣቶች ሊግ አባላት ጋር የሙህራን የቅድመ ጉባኤ ኮንፈረስ ተካሄደ።
በውይይቱ የመተዳደሪያ ደንቦችህየሊጉ ፕሮግራምና በብልፅግና ወጣቶች ሊግ ከጉባኤ እስከ ጉባኤ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርትም ቀርቧል። እንዲሁም እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት በወረዳው ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ የቀረበ ሲሆን ከአባላቱ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል።

15/08/2022
የበየዳ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከራስ ደጀን አትሌቶች ክለብና ከአትሌት ወላጆች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ።በመድረኩ የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አይችሉትም አጥናፋ...
15/08/2022

የበየዳ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከራስ ደጀን አትሌቶች ክለብና ከአትሌት ወላጆች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አይችሉትም አጥናፋ እንደገለጹት በውይይቱ የታዩ ክፉተቶችና ና ጥንካሬዎችን በመገምገም ቀጣይ የአትሌቶችን ውጤት ለማሻሻል በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መወያየት መቻሉን
ገልጸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የራሱን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት የጋራ መግባባት መደረሱን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በዕለቱ ለ22 አትሌቶች የመሮጫ ማሊያና ጫማ ጽ/ቤቱ በስጦታ መልክ እንዳበረከተ ገልጸዋል።
ይህ በእዲህ እንዳለ በአመቱ የተሻለ እንቅስቃሴ ላሳዩ አራት አትሌቶች የማበረታቻ ሽልማት የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ ውድድሮች የተሻለ ውጤት በማምጣት ወላጆችና ጽ/ቤቱ ለመሸለም አትሌቶች የተሻለ ውጤት አምጥተው ለመሸለም ቃል የተገባ ሲሆን በመጨረሻም ለተግባሩ አጋዥ የሆኑ ውል
መዋዋል መቻሉን አብራርተዋል።

ነሃሴ 9/2014ዓ/ም

የበየዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሌግ ጽ/ቤት

07/02/2021

ተግባብቶ ለአንድ አላማ ወይም ለጋራ ብልጽግና መስራት፣
ለሁሉን አቀፍ ለውጥ በጋራ መንቀሳቀስ፣ህብረ ብሔራዊነትን
ሊያጎሉ የሚችሉ መተሳሰቦችን፣ከሚለያዩን ጉዳዮች ይልቅ
ሊያቀራርቡን በሚችሉ መሰረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መሰባሰብና
መግባባት፣አንድነታችንን ለኢትዮጵያችን ህልውና መሰረት እንደሆነ
አልመን መስራት ተገቢነት አለው፡፡
ሀገር የጋራችን ናት ስለሆነም በሀገር ጉዳይ ላይ እንደ ውጭ ዜጋ
ከሩቅ ሆኖ ሃሳብ መሰንዘር ወይንም በምናገባኝ ስሜት ባይተዋር
መሆን ኢትዮጵያዊ ዜግነትን አያመላክትም፤እርግጥ ነው ብዙ
የሚያስከፉን አሊያም ተስፋ የሚያስቆርጡን ነገሮች ሊኖሩ
ይችላሉ፡፡ወጣም ወረደም ግን ከሀገራችን ውጭ ሌላ ሀገር
የለንም ፡፡ሀገራችን አንድ ናት እሷም ኢትዮጵያ፡፡
ስለ ሀገራችን ሰላም፣ልማት፣ህብረ ብሔራዊነት
መጎልበት፣የጎለበተ ዴሞክራሲ መፈጠር እንዲሁም ለዜጎች
ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማደግ የእያንዳንዳችን ድርሻ በእጅጉ የጎላ
ነው፡፡
ሀገር ከድህነት ቀንበር ወጥታ ልማቷ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ
እስኪደርስ እና የዜጎች ተጠቃሚነት እስኪረጋገጥ ድረስ
የምንተኛበት ምክንያት አይኖርም ፡፡ለሀገር ብልጽግና ከብልጽግና
ሆኖ ሌት ተቀን መልፋትና መስራት ይጠይቃል፡፡

05/02/2021

በ24/05/2013 የምክንያታዊ ወጣቶች መድረክ
በበየዳ ወረዳ ወ12 ሴ 35 ድ 147 ወጣቶች በተገኙበት ተየካሄደ ሲሆን የውይይቱ አላማ ወጣቶች ሃገር ተረካቢ እንደመሆናቸው መጠን የተሳሳተ አስተሳሰቦችን በማረምና ብሄር መንግስን ና ሃገረ መንግስትን የመገንባት ሂደትን ማስቀጠል በሚል መነሻ ፁሑፍ የተወያየን ሲሆን ወጣቶቹም ያለፈውን አሰራር በማውገዝ ቂምና ቁርሾን በመተው እርቀ ሰላም በማውረድ ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ ና ሰላምን በማስፈን የሃገርን ብልፅግና ለማረጋገጥናበቀጣይ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል የወጣቱ ድርሻ የጎላ ስለሆነ ውይይቱም መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል ።

22/06/2020

Address

Bahir Dar

Telephone

+251918392919

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Beyeda Woreda ProsperityYouth League የበየዳ ወረዳ ብልፅግና ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Beyeda Woreda ProsperityYouth League የበየዳ ወረዳ ብልፅግና ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት:

Share