እምዬ ኢትዮጵያ

እምዬ ኢትዮጵያ " አንዲት እናት ሀገር ኢትዮጵያ ወይም ሞት!"
ጓድ ፕሬዚደንት መ?

"ፕ/ትራምፕ ሀገራቸውን ከኮቪድ-19 ከመታደግ ይልቅ በራሷ ጥረት ለማደግ ትግል ውስጥ በአለችው ኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል ገብተው እየፈተፈቱ ነው!" ባራክ ኦባማ*****************...
11/05/2020

"ፕ/ትራምፕ ሀገራቸውን ከኮቪድ-19 ከመታደግ ይልቅ በራሷ ጥረት ለማደግ ትግል ውስጥ በአለችው ኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል ገብተው እየፈተፈቱ ነው!" ባራክ ኦባማ
********************************

" አሜሪካን መታደግ የሚያስችል ብቁ የአመራርነት ሚና ባለመኖሩ ምክንያት ቫይረሱ ከህዝቦቿ አልፎ የነጩን ቤተመንግስት አባላት ላይ ጉዳት ማድረስ ጀምሯል።

ፕ/ትራምፕ ሀገራቸውን ከኮቪድ-19 ከመታደግ ይልቅ በራሷ ጥረት ለማደግ ትግል ውስጥ በአለችው ኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል ገብተው እየፈተፈቱ ነው!"

#እምዬኢትዮጵያ
በቴሌግራም መከታተል ለምትፈልጉ

እስኪ ይሄን ቅዱስ ልጅ አመስግኑት    እኛ  #ጆሲ የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅህ አልነው
11/05/2020

እስኪ ይሄን ቅዱስ ልጅ አመስግኑት
እኛ #ጆሲ የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅህ አልነው

 !!!ከሀዲዋ ወያኔ ከሀገሯ በላይ ለግብፅ ወገነች!************************************ህወሃት ከግብፅ ጋር በማበር የህዳሴ ግድቡን የውሃ ሙሌት ጊዜ ለማስተጓጎል የምታደር...
11/05/2020

!!!
ከሀዲዋ ወያኔ ከሀገሯ በላይ ለግብፅ ወገነች!
************************************
ህወሃት ከግብፅ ጋር በማበር የህዳሴ ግድቡን የውሃ ሙሌት ጊዜ ለማስተጓጎል የምታደርገው ሴራ ተጋልጠ!

ከራያ አማራ ተወልዶ ማንነቱን ክዶ ለህወሃት ተላላኪና አፈቀላጤ የሆነው ጌታቸው ረዳ በተደጋጋሚ በኬኒያ በኩል ወደ ግብጽ በመመላለስ ከግብጽ የደህንነት ሰዎች ጋር በመተባበር አባላትን መልምሎ ወደ መሀል ሀገር እየላከ ሁከት ለማስነሳት ሙከራዎች ቢያደርም አንድም ነገር አልተሳካለትም።

የህዳሴ ግድቡን ስራ ለማስተጓጎል እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሽመድመድ ጌታቸው እና ደቀ መዛሙርቶቹ ከግብጽ ጋር ተባብረው እየሰሩ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች እያፈተለኩ እየወጡ ነው። ለዚህም መሳካት ህወሀት ጌታቸውን ከፊት በማስቀደም ከግብጽ ጋር በመተባበር የፌደራል መንግስት የስልጣን ቦታ ለመቆንጠጥ ጥረት እያደረጉ ሲሆን ግብጽ ሀገር እንዲተራመስ እና ህወሀት የፌዴራል የስልጣን ቦታ እንዲቆናጠጡ ህዳሴ ግድቡን ግን በግብጽ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የተለያዩ ድጋፎች እያደረገች እንደምትገኝ ነው መረጃዎቹ አክለው የጠቆሙት ።

ስለሆነም ህወሀት ሀገራችን ለግብጽ ባርነት ሽጦ የፖለቲካ ፍላጎቱን ለማሳከት ወደኋላ የማይል ማፍያ፤የባንዳ ስብስብ እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማወቅ ይገበዋል! ኧረ ጎበዝ እንንቃ!

ምንጫችን ይህ ሊንክ ነው👎
https://www.facebook.com/382164759007734/posts/649526578938216/

በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ረገብ ብሎ የሰነበተው የሕዳሴው ግድብ የውሀ ሙሌትና አለቃቀቅ ድርድር ወደ ውስብስብ የዲፕሎማሲ ጥልፍልፍ ውስጥ እየገባ ነው። --------------------------...
11/05/2020

በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ረገብ ብሎ የሰነበተው የሕዳሴው ግድብ የውሀ ሙሌትና አለቃቀቅ ድርድር ወደ ውስብስብ የዲፕሎማሲ ጥልፍልፍ ውስጥ እየገባ ነው።
------------------------------------------------------
ግብፅና ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን የመደራደሪያ ምክር ሀሳብ አንቀበልም በማለት ውድቅ አድርገውታል።

ግብፅ የዲፕሎማሲ ጥረቷን የበለጠ በማጠናከር ጉዳዩ ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የወሰደች ሲሆን አሜሪካ ድርድሩን በአስቸኳይ አስቀጥላ ኢትዮጵያ በአሜሪካ የቀረበውን ሰነድ እንድታስፈርም ጠይቃለች።

ግብፅ አንደምትለው ኢትዮጵያ ስምምነቱ ሳይፈረም የግድቡን ውሀ መሙላት ብትጀመር በቀጠናው የከፋ አለመረጋጋት ይከሰታል።

ይህ ጉዳይ ያሳሰባቸው የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ስልክ ደውለው የመንግስታቱ ድርጅት ለጉዳዩ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግለት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው በጉዳዩ ላይ ስምምነት ሳይፈረም የግድቡ የውሀ ሙሌት እንዳይጀመርና ባለድርሻዎቹ ሀገራት በቶሎ ወደ ድርድር እንዲመለሱ ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ በኩል የተዘጋጀው የድርድር ምክረ ሀሳብም

ሰነዱ 9 ገጾች ያሉት ሰሆን በመጀመርያው ላይ ጠቅላላ ጉዳዮችን አንስቶ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብን እንዴት እንደምትሞላ ያብራራል።

የመጀመርያው ደረጃ ሙሌት በሁለት አመት የሚከናወን ሲሆን በመጀመርያው አመት 4.9 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ ይይዛል ይላል።

በቀጣይ አመት ደግሞ 13.5 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ በጥቅሉ 18.4 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀን ግድቡ ይይዛል ይላል። ይህም የውሀውን ደረጃ ከግድቡ 595 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ያደርሰዋልም ሲል ሰነዱ ይገልጻል።

ይህ በተደጋጋሚ ሲገለጽ የነበረው ቁጥር ችግር ባይኖረውም ቀጥሎ የተቀመጠው ዐርፍተ ነገር ግን ችግር ያለበትና አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም።

ይህም ግድቡ በመጀመርያ ደረጃ ሙሌቱ የመጀመርያው አመት ላይ 4.9 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ ከያዘ በሁዋላ በሁለተኛው አመት ወደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደርሰው ውሀ በዝናብ እጥረት ወይንም በድርቅ ምክንያት ከ31 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ በታች ከሆነ ሙሌቱ አይከናወንም የሚል ነው።

ድርቅን ሲገልጽ በኢትዮጵያ የሚከሰተውን ድርቅ ብሎ መጥቀሱ ከዚህ ቀደም ከነበሩ አቋሞች መሻሻልን አሳይቷል ።

የሁለተኛ ደረጃው ሙሌት ግን የኢትዮጵያን ጥቅም በፍጹም የሚጎዳ ሆኖ አግኝተነዋል። የሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሀ ሙሌት ግድቡ የሚይዘውን ውሀ 49.3 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ እንደሚያደርሰው የውሀ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ በተደጋጋሚ ሲያብራሩ ነበር።

የተያዘው ውሀ 49.3 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ እንዲደርስ ወይንም የግድብን ከባህር ጠለል በላይ 625 ሜትር ላይ እንዲደርስ በመጀመርያ ሙሌት ላይ ከወሰደው ሁለት አመት በተጨማሪ ከሁለት እስከ አምስት አመት ይወስዳልም ይላል።

በሰነዱ መሰረት ሁለተኛ ደረጃ ሙሌት ላይ ግድቡ የሚይዘው ውሀ 49.3 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ እንዲደርስ ተጨማሪ 30.9 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ መያዝ ነው የሚጠበቅበት።

ለ30.9 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ ተጨማሪ ከሁለት እስከ አምስት አመት ካስፈለገ ግድቡ በሁለተኛው የሙሌት ደረጃ በአማካይ በየአመቱ 6 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ ነው የሚይዘው ማለት ነው።

ዘገባው #የአሚማ ነው

"በወያኔ ዘመን እኔ ሰባት ጊዜ የሚሆን ታስሬ ነበር። አንድም የሰብአዊ መብት ጥሰት አልተፈፀመብኝም ሲፈፀምም አላየሁም።አሁን "ተኮላሸሁ፣ እንዲህ ሆንኩ፣ እንዲህ ተፈፀመብኝ" ወዘተ የሚሉ ሁሉ...
11/05/2020

"በወያኔ ዘመን እኔ ሰባት ጊዜ የሚሆን ታስሬ ነበር። አንድም የሰብአዊ መብት ጥሰት አልተፈፀመብኝም ሲፈፀምም አላየሁም።አሁን "ተኮላሸሁ፣ እንዲህ ሆንኩ፣ እንዲህ ተፈፀመብኝ" ወዘተ የሚሉ ሁሉም #ውሸት ነው።

ሌላ በወያኔ ዘመን አንድም በቢሄሩ ምክንያት በደል የተፈፀመበት ሰው የለም። ይህም አንድ አንድ ሰዎች በብሄራቸው ምክንያት በደል እንደተፈፀመባቸው የሚያወሩት ትልቅ ቅጥፈት ነው።

እኔ ኦሮሞ ነኝ ። በኦሮሞነቴ የተፈፀመብኝ ችግር የለም። አሁን ግን ሰው በብሄሩ ምክንያት እየተንቋሸሸ ነው። እየተዋረደ ነው። በደል እየተፈፀመበት ነው። ለምሳሌ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የብልጽግና ሚዲያዎች እየተፈፀመ ያለው በደል ለማንም ግልጽ ነው ብለዋል።"
ኦቦ በቀለ ገርባ
Source : Tigray Daily

" ለአንድ መንግስት ዲሞክራት መሆን ሊከብደው ይችላል፤ አምባገነን መሆን ግን ቀላል ነው"*************************    የህዝቦች መልካምነት ለመልካም መንግስት ይበልጥ መልካም ...
10/05/2020

" ለአንድ መንግስት ዲሞክራት መሆን ሊከብደው ይችላል፤ አምባገነን መሆን ግን ቀላል ነው"
*************************
የህዝቦች መልካምነት ለመልካም መንግስት ይበልጥ መልካም ሊያደርገው ይችላል። ዲሞክራሲያዊ የሆነን መንግስት አምባገነን የሚያደርጉት ግን ብዙ ጊዜ እራሱ የመረጠው ህዝብ ነው።

አብዛኛው ያሰለጠነ(ያልተማረ) ማህበረሰብ ብዙ ነጻነቶችን ሲያገኝ የማንአለብኝነት ና የስርአተአልበኝነት ባህርያትን ያሳያል። ዴሞክራሲያዊው መንግስት በመጀመርያ ማስተማርን፣ መምከርን ና ማስመከርን መርህ ያደርግ ያደርግና ለውጥ ሲያጣበት ተስፋ ይቆርጥና አምባገነን ሆኖ ያርፈዋል። ማሰር እና የሰብአዊ መብት መጣስ ይጀምራል። ህዝቡም ጩኸት ይጀምራል።

በኢትዮጵያም አሁን እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ መንግስትን ከለዘብተኛነት፣ ከትእግስት ና ከነገ ዛሬ ለውጥ አያለሁ ከሚለው ተስፋ አዘል ምኞቱ ወደ አምባገነናዊ አስተዳደር የሚገፋ ነው።

https://t.me/Emeyeetopia/

በቴሌ ግራም ቤተሰብ መሆን ለሚፈልጉ ሁሉ           ይህ የቴሌግራም ቻናላችን ነውየቤተሰቦችን ቁጥር ለመጨመር             እንዲያደርጉልን በታላቅ ትህትና ይጠየቃሉ
10/05/2020

በቴሌ ግራም ቤተሰብ መሆን ለሚፈልጉ ሁሉ
ይህ የቴሌግራም ቻናላችን ነው
የቤተሰቦችን ቁጥር ለመጨመር
እንዲያደርጉልን በታላቅ ትህትና ይጠየቃሉ

የቴሌግራም ቻናላችንን በማድረግ ድጋፍ ያደርጉልን ዘንድ በታላቅ ትህትና ይጠየቃሉ! እምዬ ኢትዮጵያ /Emye Ethiopia/ አንዲት እናት ሀገር ወይም ሞት! https://t.me/Emeyeetopia

ሰበር መረጃየብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማጭበርበር እና ዘረፋ ወንጀል አከሸፈ።************ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት...
10/05/2020

ሰበር መረጃ

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማጭበርበር እና ዘረፋ ወንጀል አከሸፈ።
************
ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ረጅም ጊዜ በመውሰድ በተለያየ መንገድ ክትትል ሲያደርግበት የነበረው እና በጉዳዩም ላይ በቂ መረጃ ሲያሰባስብበት የቆየው ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓትን በመጠቀም 110 ሚልዮን ዶላር የማጭበርበር እና የዘረፋ የወንጀል ሙከራ በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርጓል።

ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጉዳዩን አስመልክቶ በላከው መግለጫ ተጠርጣሪዎቹ ነዋሪነቱ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በሆነው ኒል ቻርለስ የተባለ ግለስብ ስም በባንክ የተቀመጠ 110 ሚልዮን ዶላርን የባንክ ሒሳብ ባለቤቱ እንዳዘዘ አስመስለው አዲስ አበባ ከተማ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ተብሎ ከሚታወቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማውጣት የተለያዩ የማጭበርበር ስልቶችን ሲያቀናጁ እንደነበር አስታውቋል።

ይሁንና ሕገ ወጥ የገንዘብ ማዘዋወር እና ዘረፋ ወንጀሉ በብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ክትትል ስር የነበረ በመሆኑ፣ ግንቦት 1 ቀን 2012 ዓ.ም በመጀመሪያ ዙር 60,990,939ብር ከተጠቀሰው ባንክ አውጥተው በማዳበሪያ ጭነው ባዘጋጁት ተሽከርካሪ ሊወስዱ ሲሉ ቀድሞም በጥብቅ ክትትል ስር ስለነበሩ እዚያው ባንክ ውስጥ እያሉ በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ብሏል። ወንጀሉን በማቀነባበር ከሚታወቁት መካከል አድይሚ አድርሚ አብዱልራፊ የተባለ ናይጄሪያዊ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ሸገር እንግዳ ማረፊያ በቀን 450 ብር እየከፈለ ከአንድ ዓመት በላይ በመቀመጥ ተልእኮውን ለማስፈጽም ሲንቀሳቀስ እንደነበር ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሲያካሂድ በነበረው ክትትል አረጋግጧል።

በትግራይ ክልል ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!የትግራይ ጤና ምርምር ኢኒስቲትዩት በይፋዊ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ መሰረት 86 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች ...
10/05/2020

በትግራይ ክልል ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

የትግራይ ጤና ምርምር ኢኒስቲትዩት በይፋዊ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ መሰረት 86 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን አሳውቋል።

በትግራይ ክልል ደረጃ እስካሁን 694 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ስድስት (6) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው በተረጋገጠው ታማሚዎች ዙሪያ የክልሉን የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎዶፋይን አነጋግረን ተጨማሪ መረጃዎችን እንሰጣችኃለን።

የኤርትራ ጦር አዛዥ በኢትዮጵያ ውስጥ ነው***********************************08 ግንቦት 2020 - (ኢ.ኢ.ሲ) ጄኔራል ፊሊጶስ የኤርትራ የጦር ሰራዊት ዋና አዛዥ ና የደ...
10/05/2020

የኤርትራ ጦር አዛዥ በኢትዮጵያ ውስጥ ነው
***********************************
08 ግንቦት 2020 - (ኢ.ኢ.ሲ) ጄኔራል ፊሊጶስ የኤርትራ የጦር ሰራዊት ዋና አዛዥ ና የደህንነት ኃላፊ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በጠበቀ የጋራ ጉዳይ ዙሪያ ለመተባበር አዲስ አበባጉብኝት አደረጉ ፡፡

ጉብኝቱ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ በዚህ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በጋራ የሚነጋገሯቸውን “ኣካባቢያዊ ጉዳዮች” በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል ፡፡

ከነፃነት ትግሉ ወዲህ በኤርትራ ጦር ኃይል ውስጥ ካሉ ታላላቅ ጄኔራሎች ውስጥ ጄኔራል ፊሊጶስ አንዱ ናቸው ፡፡

ኤርትራ የመከላከያ ሚኒስትር የላትም ፣ ጄኔራሉም እጅግ ከፍተኛ መኮንንና የኃይሉ ሃላፊ ነው ፡፡

ጉብኝቱን የሚስብ እና የሚስብ ነገር ቢኖር ከሀገራቸው ውጭ የኤርትራዊ ጦር ጄኔራል የስራ ጉብኝት የመጀመሪያ መሆኑ ነው ፡፡

መለስ ስትፈልግ ገደል ግባ ብሎ ያባረረው ስዬ አብረሃ ዛሬ ገግሞ ጦርነቱ ሙሉ ጦርነት ነዉ የሚሆነው እያለ ነዉ!*******************************************"ዶር አብይ...
10/05/2020

መለስ ስትፈልግ ገደል ግባ ብሎ ያባረረው ስዬ አብረሃ ዛሬ ገግሞ ጦርነቱ ሙሉ ጦርነት ነዉ የሚሆነው እያለ ነዉ!
*******************************************
"ዶር አብይ ሌላ ቦታ እንዳደረገው ትግራይ ወስጥ ለመግባት ባይሞክር ይሻለዋል፣ ትግራይን ከነካ total war / ሙሉ ጦርነት ነው የሚሆነው፤ እኛ ብዙ ጦርነትን አይተናል፣ ጦርነትን የሚያውቅ ይፈራል፣ አይተነኩስም፣ ስለዚህ እኛ ጦርነት እንፈራለን፣ አንፈልግም።"

"ጦርነት ሲመጣብን ደሞ እንዴት እንደምናሸንፍ እናውቅበታለን፤ ጉራ አይደለም ደጋግመን ያደረግነው ነው። ኮሮችን ደምስሰን ኮሮችን ገንብተናል፣ መካናይዝድ ሐይል ደምስሰን መካናይዝድ ገንብተናል፣ ወታደራዊ መንግስት አፍርሰን፣ ህዝባዊ መንግስት ገንብተናል።"

ህውሐት 20 ሚሊዮን ዶላር ቁማር ተበላች! በፖለቲካም ነጥብ ጣለች!**********     #ጠቅላይ ሚኒስተር ኣቢይ ኣህመድና የ ኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ህወሃትን ቁማር በልዋት!...
10/05/2020

ህውሐት 20 ሚሊዮን ዶላር ቁማር ተበላች! በፖለቲካም ነጥብ ጣለች!
**********


#ጠቅላይ ሚኒስተር ኣቢይ ኣህመድና የ ኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ህወሃትን ቁማር በልዋት!

ነገሩ እንዲህ ነው የተቀናጀው የሁለቱ ኣገራት የድህንነት ተቋም ፤ህወሃት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ኣፎርቂን ለማስገደል ፍላጎት እንዳላት ይደርሱበታል ፡፡ ከዛም ራስዋ በማሰችው ጉድጓድ ሊከትዋት ሃሳብ ተቀየሰ ።

ህወሃት ወያኔ ወደ መሃል ኣገር ወደ 4 ኪሎ ስልጣን ላይ መምጣት እንደማትችል የተረዳችው ወያኔ 'የኤርትራ ህዝብ ይቅር ይለኛል እንቅፋቱ ፈጣሪዬ ኢሳያስ ነው' ብላስለምታስብ ኤርትራ ላይ እንደመዥገር ለመጣበቅ ስታልም እንደከረመች የኣደባባይ ሚስጥር ነው ። እናም እንቅፋት ነው ብላ ምታስበውን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለማስገደል 20 ሚልዮን የ ኣሜሪካን ዶላር መድባ ነበር እንቅስቃሴ የጀመረችው ፡፡

ለዚህ ፕሮግራም ከፍተኛ ስትራቴጂ በቀየሰችው በህወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የቀድሞው የደህንነት መሪ ወንጀለኛው ጌታቸው ኣሰፋ ይህንን ሚሽን እንደሚወጣው ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል ።

ህወሃት ይህንን በወሰነችበት ቀን የጌታቸው ኣሰፋን ቡድን ሲደቁስ የኖረው የ ኤርትራው የደህንነት ሹም ስምኦን በኩረ ድንግል ይህንን መረጃ በቢሮቸው ይከታተሉ ነበር ። እናም መረጃውን እና መፍትሄ ያሉትን ለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ኣሳውቀው ምላሽ ይጠባበቃሉ ።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ኣፎርቂ ቀጥታ ወደ ዶክተር ኣቢይ ኣህመድ ደወለው ተነጋገሩ። ከዛም እንዲህ ሆነ የህወሃቱ ደም መጣጭ ኣቶ ጌታቸው ኣሰፋ ኣስመራ ውስጥ የ ኣቶ ኢሳያስ የቅርብ ሰው ይህንን ሚሽን ሊወጣ እንደሚችል ለሕወሃት ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ኣሳወቀ ።

ሚሽኑን ከሚያስፈጽመው ሰው ጋር ቅድመ ክፍያ 10 ሚልዮን ዶላር መክፈል እንዳለባቸው ተነጋግረው ተስማሙ ።
በዚህም ከ ኤፈርት ካዝና ለፕሬዝዳንቱ መግደያ 10 ሚልዮን ዶላር ቅድመ ክፍያ ተፈጸመ ። ሚሽኑም ቀጠለ።

በሚሽኑ መሰረት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በኢመርጀንሲ ወደ ሳውዲ እንደተጓዙ እና የተሳካ ግድያ እንደተፈጸመባቸው የኤርትራ ሚሸን ፈጻሚው ቡድን መረጃውን ለጌታቸው ኣሰፋ ኣቀበለ ። እንደተባለውም ኢሳያስ ኣልተመለሱም ።

የሆስፒታሉ መረጃ ቋትም ፕሬዝዳንቱ ኮማ ላይ መሆናቸውን እና በ ኣይምሮኣቸው የፈሰሰው ደም ወደሙታን ኣለም ሚሸኝ እንደ ሆነ ኣስረግጦ ያስነብባል። በዚህ ግዜ ኣስመራ ላይ ለየት ያለ የሰራዊት እንቅስቃሴዎች በዝተዋል ።

ኣንዲት የ ሳውዲ ኣየርኧ ሃይል የጦር ኣውሮፕላን በለሊት ኣስመራ ኣውሮፕላን ማረፍያ ደረሰች በከፍተኛ የወታደሮች እንቅስቃሴ የታጀበው ከዚህች ኣውሮፕላን የወረደ ሚስጥ ነበር ።

ይህ ሚስጥር ምን እንደሆነ በቅርበት ሚያውቁት የጌታቸው ኣሰፋ የኤርትራው ሚሸን ፈጻሚዎችም መረጃውን ወደ ህወሃት ዋና ጽህፈት ቤት ሃወልቲ መረጃውን ያቀብሉ ነበር ፡፡ በዚህ መሃል የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስተር እና የቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚንስተር ወርቅነህ ገበየሁ ቻርተር ኣውሮፕላን ኣስነስተው ወደ ኤርትራ በረሩ ።

የተቀበልዋቸው ግን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ሳይሆኑ ኤታማዦር ሹሙ ጀነራል ፊሊጶስ ወልደዮሃንስ እና የደህንነት ሹሙ ኮረኔል ስምኦን በኩረ ድንግል እና የፕሬዛድንቱ ኣማካሪ ኣቶ የማነ ገብረኣብ ነበሩ ።

ጠ/ሚ አብይ ሁለት ቀን በኣስመራ ቆይታ ኣደረጉ ፡፡ በኤርትራ የጌታቸው ኣሰፋ ክንፍም ዶክተር ኣቢይ የ ቀብር ኣስፈጻሚ መሆናቸውን እና ቀጣዩ የ ኤርትራ ጊዝያዊ መሪም ለህወሃት ቅርብ ናቸው የተባሉት ኣቶ ወልደንኪኤል ኣብርሃ እንደሆኑ ኃሳብ ኣቀረቡ ፡፡ ጠቅላይ ሚንስተር ኣቢይ እና የፕሬዝዳንቱ ኣማካሪ ኣቶ ይማነየ ደግሞ የኢሳያስ ልጅ ኣብርሃም ኢሳያስን ቀጣዩ መሪ ለማድረግ ያደረጉት ሙከራ እነ የኤርትራ ኢታማጆር ሹሙ ጀነራል ፊሊጶስ እና መከላከያው እንዳልተቀበሉት እና የጠቅላዩ ሙከራ እንደ ከሸፈ የኤርትራ የግምጃ ቤት ሃላፊ ኣቶ ሃጎስ ገብረሂወት ( ሃጎስ ኪሻ ) እና የ ፕሬዝዳንቱ ልጅ ኣብርሃም ኢሳያስ የቁም እስረኞች እንደተደረጉ መረጃ ወደ መቀሌ ይደርሳል ።

ቀሪውንም 10 ሚልዮን ዶላር ለሚሽን ፈጻሚው ቡድን ክፍያው እንዲፈጸም ይደረጋል ። ህወሃትም በቢሮዋ ኮሮናን ሳትፈራ ትልቅ ዳንኪራ ኣካሄደች ። ( ዲጅታል ወያኔ ብላ ) ለሰየመቻቸው የህወሃት ጡረተኞችዋም ይህንን ታላቅ የምስራች ሹክ ኣለቻቸው ። ይህ በመቐለ ከተማ ዋና መቀመጫውን ያደረገው ዲጅታል የፕሮፖጋንዳ ተቀላቢ በትግራይ ተወላጆች እና በ ኤርትራውያን ብዙ ተከታይ ኣለው ተብሎ በሚታመን ነው። ብርሃነ ሃጎስ ( ልፍዓተይ ተስፋ ) በሚባለው ብሎገራቸው ኣድርገው ለፌስቡኩ ኣለም መረጃውን ይፋ ኣደረጉት ፡፡

ዲጅታል ወያነ የተባለው ስብስብም በቅጽበት ይህንን መረጃ በሚልዮኖች ኣባዝቶ በሚድያ ተቀባበለው ። በኤርትራ ወገን ይህንን ማስተባበል የቻለ ኣንድም ኣካል ኣለነበረም ። ሌላው ይቅር ጠቅላዩ ኤርትራ እንደቆዩ የጠ/ሚኒስትሩ ሴክረታርያት ጽሕፈት ቤት እንኳን ኣላስተባበለም ። እውነትም 'የኤርትራው የነጻነት ዋርካ ሳይወድቁ ኣይቀርም!' ተባለ ።

የምእራባውያን ዲፕሎማቶችም ኣባሎቻቸውን ከኤርትራ ምድር ማስወጣታቸውን በይፋዊ ድረ ገጾቻቸው ገልጸዋል ። ኤርትራ ከፕሬዝዳንቱ በኋላ የጦርነት ኣውድማ ትሆናለች ሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ጥላውን ኣጥልቷል። የህወሃት ሜድያዎችም ስለ ኤርትራ ቀጣይ እጣ ፈንታ ይወያዩ ገቡ ፡፡

በኣሜሪካን ኣገር በሚገኘው ሌላው ትግራይ ሜድያ ሃውስ በተባለው ሜድያቸውም ሰፊ ሽፋን እንዲሰጠው እና የኤርትራውያን የዳያስፖራ ማህበረሰብ እንዲያውቀው ለማድረግ ተሞከረ። ይህንን መልካም ኣጋጣሚም የትግራይ መንግስት በጥብቅ እየተከታተለው መሆኑን ደጋግመው ገለጹ ፡፡

ታላቁ ጌታቸው ኣሰፋ የመሩት ሚሽን በድል ተጠናቆ የፕሬዝዳንቱ ይፋዊ ሞት እና የቀብር ስነስርኣት ይጠበቅ ጀመር ይህ የህወሃት እና የጌታቸው ኣሰፋ የሚሽን ጉዳይ ዝርዝር ሂደት ነው ፡፡

በስውር የጌታቸው ኣሰፋን ሚሽን ፈጻሚ ቡድን ይመሩት የነበረው የጌታቸው ኣሰፋን መርዝ መማምከን የተካኑት የኤርትራው የደህንነት ሹም ኮረኔል ስምኦን ናቸው ። በዚህም ቅድመ ክፍያ ብለው 10 ሚልዮን ዶላር ተቀበሉ ።

ከፕሬዝዳንቱ እና ከ ጠቅላዩ ጋ በተደረሰው ስምምነት መሰረትም ፕሬዝዳንቱ በኣስመራ ገደም ወደ ሚገኘው የ መከላከያ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ከዛም ወደ ሳውዲ እንዲገቡ ተደረገ ። በዚ ግዜ በህወሃት ቤት የህልም ደስታ ይጠበቅ ነበር ።

ለዚህ ሚሽን የ ሳውዲ ደህንነት ቢሮ ተባባሪ እንደነበር ልብ ይበሉ ። ይህ በጥብቅ የሚያዘው የሳውዲ ሆስፒታል መረጃም በህወሃት ኣይን እና ጆሮ ሆን ተብሎ እንዲደርስ ተደረገ ።

ዶክተር ኣቢይም ድንገት የመከላከያውን ሹም ኣደም እና ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ብቻ ይዘው በለሊት ኣስመራ ገብተዋል ፡፡ ያለ ይፋዊ ጉዞ ሁለት ቀናትን ኣድርገዋል ። የተቀብልዋቸውም ጀነራሎች እና የደህንነት ሹሞች ናቸው ፡፡

ኣሁን የኤርትራን ከነጻነት የትግል ኣጋማሽ ጀምሮ እስከዚች ቀን ሲመርዋት የነበሩት ታጋዩ እና ቆፍጣናው ፕሬዝዳንት ኣርፈዋል ። ለዚህም መቀሌ ላይ ዳንኬራ ኣስመራ ላይ ደሞ ሃዘን ኣጥቷል ፡፡

ህወሃትም በደስታ ብዛት ቀሪውን ክፍያ ለመፈጸም ኣላቅማማችም ። ኢትዮጵያም ድርሻዋን 10 ሚልዮን ዶላር በኤርትራው ደህንነት ሹም ደህንነት በኩል ኣገኘች ።

ከዛም በጎርጎርዮሳውያን ቀመር የቀን ኣቆጣጠር ግንቦት 3 - 2020 ፡ ግን ለ ህወሃት ኣስከፊ መርዶ ደረሰው! ሟቹ ፕሬዝዳንት ከሙታን መካከል ተነስተው ፡ ኣዲስ ኣበባ ተከሰቱ የህወሐት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይህንን ማመን ኣልቻሉም ።

ኣቶ ጌታቸው ኣሰፋም በድንጋጤና በንዴት ለጊዜው ኣይደር ሆስፒታል ገብተው ነበር ፡፡ ዶክተር ኣቢይ እና ኢሳያስ ኣፎርቂም ፡ ኣንድም ክላሽ ሳይተኩሱ ፡ ህወሃት ቀድሞ ከሰረቀው ገንዘብ 20 ሚልዮን ዶላር ውስጥ ኣስር ኣስር ሚልዮን በሚገርም የድህንነት ጥበብ ወያኔን ቁማር በልዋት የደስ ደስም የቀሞውን ጠቅላይ ሃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የምሳ ግብዣ በፕሬዝዳንትዋ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ተደገሰ ። ወዲ ኣፌና ኣቢቹ እየተጎራረሱ ህወሃት ብቴሌቪዥን መስኮት ተመለከተች ፡፡ ድንቅ ጥበብ ፡፡

ምንጭ - ሕዝባዊ ሻዕቢያ ።
በቴሌግራም መከታተል ለምትፈልጉ

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እምዬ ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category