Amhara National Regional State Environment & Forest Protection Authority

Amhara National Regional State Environment & Forest Protection Authority The Authority strives to ensure the right of citizens to live in clean and unpolluted environment.

04/06/2026
የደቡብ ወሎ ዞን አካ/ደ/ጥ/ተ/ጽ/ቤት ከወሎ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለዞን እና ለወረዳ የደን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።የደ/ወሎ ዞን አካ/ደ/ጥ/ተ/ጽ/ቤት በወረዳ የደን ባለሙያዎች ያለባቸ...
04/06/2026

የደቡብ ወሎ ዞን አካ/ደ/ጥ/ተ/ጽ/ቤት ከወሎ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለዞን እና ለወረዳ የደን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

የደ/ወሎ ዞን አካ/ደ/ጥ/ተ/ጽ/ቤት በወረዳ የደን ባለሙያዎች ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት በመለየት ለወሎ ዩንቨርስቲ ፕሮፓዛል በማዘጋጀት የአቅም ግንባታ ስራ እንዲሰጠን በጠየቅነው መሠረት ዩንቨርስቲው ጥያቄያችንን በመቀበል 405,671ብር (አራት መቶ አምስት ሽህ ስድስት መቶ ሰባ አንድ ብር) መድቦልናል።

በዚህም መሠረት በForest Resource Assessment and Mapping for Sustainable Forest Managnment (የደን ሐብት መረጃ አሰባሰብ እና ካርታ አዘገጃጀት ለዘላቂ ደን አስተዳደር) በሚል ዋና ርዕስ እና ተሳትፏዊ የደን አስተዳደር፣ የደን ቆጠራ፣ የደን አስተዳደር ዕቅድ ዝግጅት፣ GIS እና የአረንጓዴ አሻራ እና የተጋጋጡ መሬቶች ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ዝርዝር ርዕስ የያዘ የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ስልጠና ከግንቦት10 እስከ 14/2018 ዓ.ም ለ5(አምስት) ቀናት መስጠት እንደተቻለ በመግለፅ በሥልጠናው ወንድ 29 ሴት 4 ድ 33 ባለሙያዎች መሳተፍ እንደተቻለ የዞኑ የአካ/ደ/ጥ/ተ/ጽ/ቤት አሳውቋል።

04/06/2026
የአለም አካባቢ ቀን ክብረ በዓል በምዕራብ ጎጃም ዞን( የቡሬ ዙሪያ ወረዳ)“የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን እንታደግ” በሚል መሪ ቃል የወረዳው አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ...
04/06/2026

የአለም አካባቢ ቀን ክብረ በዓል
በምዕራብ ጎጃም ዞን( የቡሬ ዙሪያ ወረዳ)

“የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን እንታደግ” በሚል መሪ ቃል የወረዳው አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የአለም አካባቢ ቀንን እያከበረ ይገኛል።

በአሉን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሻገር አያና የአየር ንብረት ለውጥ በምድራችን ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ለአካባቢ ጥበቃ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን በአግባቡ ከማከናወን ጀምሮ የደን ልማትን በማሳደግና አካባቢን ደህንነት በማስጠበቅ ለአካባቢ ጥበቃ በትኩረት መሠራት እንዳለበት ጠቁመዋል።

በሬ ዙሪያ ወረዳ አካ/ጥ/ጽ/ቤት

04/06/2026

የዓለም የአካባቢ ቀን በሀገራችን ግንቦት 28/2018 በተለያዩ ኩነቶች ይከበራል።
ግንቦት 27/2018
አዲስ አበባ
============
የዓለም የአካባቢ ቀን በየዓመቱ ግንቦት 28 ይከበራል፡፡ የዘንድሮ የዓለም አካባቢ ቀን “Climate Action’’ በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ53ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይከበራል።

የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ሁኔታ እና የበአሉ አስፈላጊነትን በተመለከተም ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት የምታበረክተው አስተዋጽኦ ከ 0.5% በታች ቢሆንም፣ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለሚከሰቱት ተደጋጋሚ ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት፣ የደን መመናመንና የመሬት መራቆት በእጅጉ ተጋላጭ ናት። እነዚህ ተግዳሮቶች በዝናብ ጥገኛ በሆነው ግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በውሃ ሀብታችን እና በገጠሩ ማኅበረሰብ የኑሮ ሁኔታ ላይ ቀጥተኛ ስጋት ደቅነዋል። በመሆኑም “Climate Action’’የሚለው መሪ ቃል ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም ያለው። የአገራችን አየር ንብረት ለውጥ ምላሽ በሚከተሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትክረት በማድረግ እየተሰሩ ይገኛሉ፦
የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር፦ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋኑን ወደ 23.6% አሳድጋለች።

የ2018 ዓ.ም ትኩረታችን የችግኞችን የመጽደቅ መጠን ማሻሻል፣ ዘላቂ የተፋሰስ ልማት እና የረጅም ጊዜ ሥነ-ምህዳራዊ ጥቅሞችን ማረጋገጥ ላይ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ግብርና እና የውሃ ልማት፦ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወደ አፈር ጥበቃ፣ መስኖ ማስፋፋት እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም (climate-smart) አሠራሮች መሸጋገር።
ወደ አረንጓዴ ኢነርጂ/የሐይል ምንጭ ሽግግር፦ ከ95% በላይ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ስኬታችንን መሰረት በማድረግ፣ ንጹህ ኃይልን ወደ ትራንስፖርት እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማስፋፋት።
የከተሞች ጽዳትና ውበት፦ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እና የከተማ አረንጓዴ መሠረተ-ልማትን ማጠናከር እና ከከተሞች የሚወጣውን የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት በመቀነስ።

ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ ፋይናንስ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለእውቀት ማሳደግ አጋርነትን ማጠናከር።
የዘንድሮ የዓለም አካባቢ ቀን ሲከበርም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም መላው የህብረተሰብ ክፍል የሚከተሉትን ተግባራት ከግምት ውስጥ በማስገባት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ችግኞችን መትከል እና መንከባከብ።
ዘላቂ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ሥርዓትን መከተል።
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን ላይ በንቃት መሳተፍ።
ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ እና የሚበሰብሱ የእቃ መያዣዎችን በመጠቀም፡፡
ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ ፋይናንስ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለእውቀት ማሳደግ አጋርነትን ማጠናከር።
የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ግንዛቤዎችን ማስፋፋት፡፡
በወንዝ ዳርቻ ልማት እና በኮሪዶር ማስፋፊያ ስራዎች የተገኙ ውጠየቶችን ለመጠበቅ እና ለማስፋት በሚደረግ ርብርብ ጠንካራ ተሳትፎ ማድረግ፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ጽዱ ኢትዮጵያ ባህል እናደርግ

04/06/2026
"  #የአየር  #ንብረት  #ተፅዕኖን  #መግታት" (   ) በሚል መሪቃል በባህርዳር  ጣና ክፍለከተማ ተከበረግንቦት 28 ቀን ዓለም አቀፍ አካባቢ ቀን!!በባሕርዳር ከተማ የጣና ክ/ከተማ በሃ...
04/06/2026

" #የአየር #ንብረት #ተፅዕኖን #መግታት" ( ) በሚል መሪቃል በባህርዳር ጣና ክፍለከተማ ተከበረ
ግንቦት 28 ቀን ዓለም አቀፍ አካባቢ ቀን!!

በባሕርዳር ከተማ የጣና ክ/ከተማ በሃገራችን ለ33ኛ ጊዜ በክልላችን ለ29ኛ ጊዜ የሚከበረውን አለማቀፍ የአካባቢ ቀን በማስመልከት የመጤ አረምና ተስፋፊ ተክሎችን ማስወገድ ዘመቻ ተካሄደ።
" #የአየር #ንብረት #ተፅዕኖን #መግታት" ( )

‎«የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ መታደግ»በሰሜን ሸዋ ዞን(መንዝጌራ)‎‎በሰ/ሸዋ ዞን የአሳግርት ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ተ/ጽ/ቤት "የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ መታደግ" በሚል መሪ ሀሳ...
04/06/2026

‎«የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ መታደግ»
በሰሜን ሸዋ ዞን(መንዝጌራ)

‎በሰ/ሸዋ ዞን የአሳግርት ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ተ/ጽ/ቤት "የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ መታደግ" በሚል መሪ ሀሳብ የአለም የአካባቢ ቀንን በጽዳት ዘመቻ አክብሯል።

‎የከተማን ጽዳት ለመጠበቅ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት የተገለፀ ሲሆን ከተማችንንና አካባቢያችንን ከቆሻሻ ብክለት ነጻ በማድረግ ምቹ ውብና ማራኪ አካባቢን መፍጠር እንደሚገባም ተጠቁሟል።

የአሳግርት ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ተ/ጽ/ቤት‎ ማህበረሰቡ ጽዳትን የሁልጊዜም ተግባር በማድረግ መተግበር እንዳለበትም አሳስቧል።

የአለም የአካባቢ ቀን በአለም ለ53ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ33ኛ በክልልላችን ለ29ኛ ጊዜ በጽዳት ዘመቻ የሚከበር ሲሆን ‎በዛሬው ዕለትም የወረዳው አመራሮች በተገኙበት አካባቢን የማጽዳት ተግባር ተከናውኗል።

👉የአለም አካባቢ ቀን ፅዳት ዘመቻ በደብረ ማርቆስ ከተማ       =========///==========✍️,ግንቦት 27/2018ዓ ም  በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በደጅ አዝማች ተድላ ጓሉ...
04/06/2026

👉የአለም አካባቢ ቀን ፅዳት ዘመቻ በደብረ ማርቆስ ከተማ
=========///==========
✍️,ግንቦት 27/2018ዓ ም በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በደጅ አዝማች ተድላ ጓሉ ክፍለ ከተማ የአለም አካባቢ ቀን አከባበርን ምክንያት በማድረግ "የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን እንግታ" በሚል መሪ ሃሳብ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በፅዳት ዘመቻ ተከብሯል።

በፅዳት ዘመቻው የተገኙት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፅዳትና ውበት አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ቸርነት አለማየሁ የዘንድሮውን የአለም አካባቢ ቀን ስናከብር አሁን ላይ እየገጠመን ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ በመረዳት ችግሩን ሊቀለብስ የሚችል የተለያዩ ተግባራትን በመፈፀም ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በፅዳት ዘመቻው የመምሪያ፣ የክፍለ ከተማና የቀበሌ አመራሮች፣ ባለሙያዎች ፣ በጎ ፈቃደኞ ወጣቶች እንዲሁም የደረቅ ቆሻሻ አንሽ ማህበራትና የምግብ ዋስትና ሰሪ ሀይሎች ተሳትፈዋል።

01/06/2026

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara National Regional State Environment & Forest Protection Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share